No summary available.
ኀዲር 16 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ሒጏስ ወልደ ተሻገር ገ/ስላሴ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካቾች፡-
ጉዲዩ የቀረበው አመልካቾች የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልትና የሰበር ችልት ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት ስላመለከቱ ነው። ክርክሩ የአፈፃፀም ክርክር ነው። ጉዲዩ በመጀመሪያ የታየው በወልመራ ወረዲ ፍርድ ቤት ነው። በወረዲው ፍርድ ቤት አመልካቾች የፍርድ ባለእዲዎች (የአፈፃፀም ተከሳሾች) አንደኛ ተጠሪ የፍርድ ባለመብት (የአፈፃፀም) ከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል። ሁለተኛ ተጠሪ የወረዲው ፍርድ ቤት ባወጣው የሀራጅ ማስታወቂያ መሰረት በጨረታ በመካፈል በብር 32,000 (ሰላሣ ሁለት ሺ ብር) አሸናፉ በመሆን ቤት ገዝቷል።
የወረዲው ፍርድ ቤት ከቤቱ ሽያጭ ዋጋ የአንደኛ ተጠሪ ድርሻ 16,100(አስራ ስድስት ሺህ አንድ መቶ ብር) መሆኑንና አንደኛ ተጠሪ ድርሻዋን እንዱከፍላት አድርጓል። ቀሪው ብር 16,100(አስራ ስድስት ሺህ አንድ መቶ ብር) የአመልካቾች ድርሻ መሆኑንና አመልካቾች ድርሻቸውን ለመውሰድ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው በሞዳል 85 ተይዞ እንዱቆይና በጠየቁ ጊዜ እንዱሰጣቸው ትእዛዝ ሰጥቶ የአፈፃፀም መዝገቡን ዘግቷል። በዚህ የአፈፃፀም ትእዛዝ ቅር በመሰኘት አመልካቾች ይግባኝ ለከፍተኛው ፍርድ ቤት አቅርበዋል። የከፍተኛው ፍርድ ቤት ከሐራጅ ሸያጩ በፉት ቤቱ ብር 40,000 መገመቱን አንደኛ ተጠሪ በእርቅ ብር 20,000 ለመውሰድ ተስማምታ እያለ በእርቅ ስምምነቱ መሰረት እንዱፈጸመላት የአፈፃፀም ክስ ስታቀርብ ቤቱ በብር 28,047.50(ሃያ ስምንት ሺ አርባ ሰባት ብር ከሃምሣ ሣንቲም) ግምት መነሻ ለጨረታ እንዱቀርብና በብር 32,200 እንዱሸጥ ማድረጉ ስህተት ነው በማለት የወረዲው ፍርድ ቤት የሰጠውን የአፈፃፀም ትእዛዝ ሽሮታል።
በዚህ ትእዛዝ ቅር በመሰኘት የቤቱ የጋራ ባለሐብት የሆነችው አንደኛ ተጠሪና ቤቱን በሐራጅ ተጫርቶ የገዛውና የቤቱን ሙለ ዋጋ ለወረዲው ፍርድ ቤት ገቢ ያደረገው ሁለተኛው ተጠሪ ይግባኝ ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አቅርበዋል። የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ የፍርድ ባለእዲዎች የአፈፃፀም ክሱና መጥሪያው ደርሷቸው በመጀመሪያው ቀነ ቀጠሮ ባለመቅረባቸው ቤቱ በሃራጅ እንዱሸጥ የወሰነ መሆኑን በመግለጽ ቤቱ በሐራጅ እንዱሸጥ የወረዲው ፍርድ ቤት ትእዛዝ የሰጠው በእርቅ ውሣኔው መሰረት የማይፈጽሙበትን ምክንያት በቀነ ቀጠሮው ቀርበው ባለማስረዲታቸውና በላለበት የተሰጠውን ትእዛዝ በፍታብሓር ሥነ ሥርአት ሕግ ቁጥር 78 ሣያስነሱ አዱስ ክርክር በይግባኝ ለከፍተኛው ፍርድ ቤት ማቅረባቸው የሕግ ድጋፍ የላለው መሆኑን በመዘርዘር የከፍተኛው ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ በመሻር የወረዲው ፍርድ ቤት የሰጠውን የአፈፃፀም ትእዛዝ አጽንቶታል። አመልካቾች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት የሰበር አቤቱታ ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቅርበዋል። የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት የአመልካቾችን የሰበር አቤቱታ አልተቀበለውም። አመልካቾች መጋቢት 10 ቀን 2002 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ አንደኛ ተጠሪና ሟች አባታችን የጋራ ንብረት የሆነውን ቤት እንድናካፍላት አንደኛ ተጠሪ ክስ አቅርባ ቤቱ በብር 40,000 /አርባ ሺህ ብር/ ተገምቶ ብር 20,000 (ሃያ ሺ ብር) ልንከፍላት በሽማግላ ታርቀን እርቁ በፍርድ ቤት ተመዝግቧል። ከዚህ በኋላ አንደኛ ተጠሪ ያቀረበችው የአፈፃፀም ክስና መጥሪያ ሣይደርሰን በብር 28,047.50 ለሐራጅ ቀርቦ በብር 32,200 መሸጡ ተገቢነት የላለውና መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው። ሐራጅ በሚከናወንበት ወቅት ቤቱን ለማስቀረት ጠይቀን በወረዲው ፍርድ ቤት ተከልክለናል። ስለሆነም የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሐራጅ ሽያጩ የፍትሐብሕር የሥነ ሥርአት ሕግ ድንጋጌዎችን ያልተከተለ መሆኑን በማረጋገጥ የወረዲውን ፍርድ ቤት ትእዛዝ በመሻር የሰጠውን ውሣኔ በክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልትና ሰበር ችልት መሻሩ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልን በማለት አመልክተዋል። አንደኛ ተጠሪ መጥሪያው በፍርድ ቤት ግቢ ተለጥፍ ባለመቅረባቸው ክርክሩ በላለበት እንዱቀጥል ትእዛዝ ተሰጥቷል። ሁለተኛው ተጠሪ ሰኔ 11 ቀን 2002 ዓ.ም ባቀረበው መልስ አመልካቾች ለወረዲው ፍርድ ቤት በፍርድ ቤት በፀደቀው የእርቅ ስምምነት መሰረት የማይፈጽሙበትን ምክንያት እንዱያስረደ በተሰጠው ቀነ ቀጠሮ ቀርበው ባለማስረዲታቸውና በሂደቱም ሐራጁን ለማስቆም ወይም ለማሳገድ ያደረጉት እንቅስቃሴ ሣይኖር በሕጉ መሰረት ተጫርቼ ከገዛሁና ሙለ ዋጋውን ከከፈልኩ በኋላ በሥር ፍርድ ቤት ያላቀረቡትን ክርክር በማንሣት ሐራጁ እንዱሰረዝ የሚያቀርቡት ክርክር የሕግ ድጋፍና መሰረት የለውም ስለሆነም የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልትና የሰበር ችልት የሰጡት ውሣኔ የሕግ ስህተት የለበትም በማለት ተከራክሯል።
No topics extracted.
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር ግራ ቀኙ በጽሐፍ ያቀረቡት ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን የፍትሐብሕር ሥነ ሥርአት ሕግ ቁጥር 78 ለአፈፃፀም ክርክር ተፈፃሚነት እንዲለው በመቁጠር የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጠው የሕግ ትርጉም ተገቢ ነው ወይስ አይደለም? የሚለውን ጭብጥ ለማጣራት ጉዲዩ ለሰበር የቀረበ መሆኑን በመገንዘብና የወረዲው ፍርድ ቤት የሰጠው የአፈፃፀም ትእዛዝ የሚሻርበት ህጋዊ ምክንያት አለ? ወይስ የለም? የሚለውን ጭብጥ በመመሥረት ጉዲዩን መርምረናል።
ጉዲዩን እንደመረመርነው አመልካቾችና አንደኛ ተጠሪ በመጀመሪያ በፍርድ ቤት የተከራከሩበት በኋላም የእርቅ ስምምነት አድርገውና በፍርድ ቤት አጸድቀው የጨረሱት መሰረታዊ ጉዲይ የአመልካቾች ወላጅ አባትና የአንደኛ ተጠሪ የጋራ ሐብት የሆነውና በሃራጅ የተሸጠው ቤት ነው። አንደኛ ተጠሪ አመልካቾች በገቡትና በፍርድ ቤት በፀደቀው የእርቅ ስምምነት መሰረት ብር 20,000(ሃያ ሺህ ብር) እንዱከፍሎት የአፈፃፀም ክስ አቅርበዋል። አንደኛ ተጠሪ ያቀረቡት የአፈፃፀም ክስና መጥሪያ አልደረሰንም በማለት አመልካቾች በሰበር አቤቱታቸው የገለፁ ቢሆንም የአፈፃፀም ክስና መጥሪያው ደርሷቸው በቀነ ቀጠሮው በፍርድ ቤት በፀደቀው የእርቅ ስምምነት መሰረት የማይፈጽሙበትን ምክንያት ባለማስረዲታቸው የወረዲው ፍርድ ቤት የአመልካቾች አባትና አንደኛ ተጠሪ የጋራ ሐብት የሆነው ቤት በሐራጅ እንዱሸጥ ትእዛዝ ሰጥቷል።
አመልካቾች የፍርድ ቤቱ መጥሪያና አንደኛ ተጠሪ ያቀረቡት የአፈፃፀም ክስ የደረሳቸው መሆኑ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የተረጋገጠና በውሣኔውም በግልጽ ያሰፈረው በመሆኑ አመልካቾች የአፈፃፀም ክስና መጥሪያው አልደረሰንም በማለት ለዚህ ችልት ያቀረቡት አቤቱታ ተገቢና ተቀባይነት ያለው ሆኖ አላገኘነውም። የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አመልካቾች መጥሪያ ደርሷቸው ባለመቅረባቸው ቤቱ በሐራጅ እንዱሸጥ የወረዲው ፍርድ ቤት የሰጠውን ትእዛዝ በፍታብሓር ሥነ ሥርአት ሕግ ቁጥር 78 መሰረት ማስነሳት ነበረባቸው የሚል ትችት በውሣኔው ውስጥ አስፍሯል። የአፈፃፀም ክስና መጥሪያው ደርሶት የፍርድ ባለእዲው ሣይቀርብ በሚቀርበት ጊዜ ፍርድ ቤቶች የሚከተለት ሥርአት የፍትሐብሕር ሥነ ሥርአት ሕግ ቁጥር 70/ሀ/ ድንጋጌን መሰረት የሚያደርግ አይደለም። ስለሆነም የፍርድ ባለእዲው ባለመቅረቡ አፈፃፀሙን የያዘው ፍርድ ቤት የሰጠውን የአፈፃፀም ትእዛዝ በፍትሐብሕር ሥነ-ሥርአት ሕግ ቁጥር 78 መሰረት ለማስነሣት የሚቻልበት ሁኔታ የላለ በመሆኑ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ለፍታብሓር ሥነ-ሥርአት ሕግ ቁጥር 78 በአፈፃፀም ክርክር የፍርድ ባለእዲው በላለበት የተሰጠውን ትእዛዝ ለማስነሣት እንደሚያገለግል በመቁጠር የሰጠው የሕግ ትርጉም ተገቢ ሆኖ አላገኘነውም። ከዚህ አንፃር የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 78ን አላግባብ የጠቀሰና የተረጏመ መሆኑን ተገንዝበናል። የአፈፃፀም ክርክር ስለሚመራበት ሥርአት የተደነገጉ ድንጋጌዎችን ስንመለከት የአፈፃፀም ክስ ማመልከቻውና የፍርድ ቤቱ መጥሪያ የደረሰው የአፈፃፀም ተከሳሽ ወይም የፍርድ ባለእዲ ፍርድ ቤቱ በሰጠው ቀነ ቀጠሮ በመቅረብ ፍርደን ፈጽሞ ከሆነ ፍርደን መፈፀሙን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ ወይም ፍርደን የማይፈጽምበት ምክንያት ካለው ይህንኑ ምክንያቱን ለፍርድ ቤቱ የማስረዲት ግዳታና ኃላፉነት አለበት። የፍርድ ባለእዲው ፍርድ ቤቱ በሰጠው ቀነ ቀጠሮ ቀርቦ ከላይ በተገለፀው መንገድ ካላስረዲ አፈፃፀሙን የያዘው ፍርድ ቤት ፍርደን ለማስፈፀም አስፈላጊ መስል የታየውን ትእዛዝ መስጠት እንዲለበት የፍትሐብሕር ሥነሥርአት ሕግ ቁጥር 386/2/ በግልጽ ይደነግጋል። በያዝነው ጉዲይ አንደኛ ተጠሪ ያቀረቡት የአፈፃፀም ክስና መጥሪያ ከደረሳቸው በኋላ አመልካቾች ፍርድ ቤቱ በያዘው ቀነ ቀጠሮ ያልቀረቡ በመሆኑ የወረዲው ፍርድ ቤት የአመልካቾች አባትና የአንደኛ ተጠሪ የጋራ ሐብት የሆነው ቤት በሐራጅ ተሰጦ አንደኛ ተጠሪ ድሻዋን እንድትወስድ የሰጠው ትእዛዝ የፍትሐብሕር ሥነ-ሥርአት ሕግ ቁጥር 386/2/ ንመሰረት ያደረገና ጉድለት የላለበት ሆኖ አግኝተነዋል። ስለሆነም የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልትና ሰበር ችልት ለፍትሐብሕር ሥነ-ሥርአት ሕግ ቁጥር 78 የተሣሣተ ትርጉም የሰጡ ቢሆንም ስህተቱ በውጤት ደረጃ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልትና ሰበር ችልት የደረሱበትን መደምደሚያ ውሣኔ ሉያስለውጥ የሚችል መሰረታዊ የሕግ ስህተት አይደለም።
አመልካቾች የቤቱ በሐራጅ መሸጥ የቤት ግምትና ላልች ነጥቦችን በማንሣት የወረዲው ፍርድ ቤት የአፈፃፀም ትእዛዝ ከመሰጠቱ በፉት በመቅረብ አልተከራከሩም። አመልካቾች ከአንደኛ ተጠሪ ጋር ባደረጉት የእርቅ ስምምነት መሰረት የማይፈጽሙበትን ምክንያት በቀነ ቀጠሮው ቀርበው አላስረደም የወረዲው ፍርድ ቤት ቤቱ በባለሙያ ተገምቶ ለጨረታ እንዱቀርብ ማድረጉ የፍትሐብሕር ሥነ-ሥርአት ሕግ ቁጥር 423ና ተከታይ ድንጋጌዎችን መሰረት ያደረገ ሆኖ አግኝተነዋል። አመልካቾች የጨረታው ሑደት በፍትሐብሕር ሥነ-ሥርአት ሕግ ቁጥር 445 የተደነገጉ ተግባራት የተፈፀሙ መሆኑን ያላስረደ በመሆኑ የእርቅ ስምምነት ያደረግንበት የቤት ዋጋ ቤቱ በሐራጅ ለሁለተኛ ተጠሪ ከተሸጠበት የበለጠ ነበር የሚል ምክንያት በማቅረብ የሐራጅ ሽያጩ እንዱፈርስ ያቀረቡት ጥያቄ የሕግ ድጋፍ ያለው ሆኖ አላገኘነውም። ስለሆነም የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የከፍተኛው ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ በመሻር የወረዲው ፍርድ ቤት የሰጠውን የአፈፃፀም ትእዛዝ በማጽናት የሰጠውን ውሣኔ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት ማጽደቁ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለበትም በማለት ወስነናል።
የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልትና ሰበር ችልት የሰጡት ውሣኔ ጸንቷል።
በዚህ ፍርድ ቤት መጋቢት 14 ቀን 2002 ዓ.ም የተሰጠው የእግድ ትእዛዝ ተነስቷል።
ይፃፍ።