No summary available.
ጥቅምት 3 ቀን 2003 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሒጏስ ወልደ ዓልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ሱልጣን አባተማም አመልካች፡- ጉና ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ - ጠበቃ ጥላዬ ተገኝ ቀረበ።
ተጠሪዎች፡-
ቡሬ ባጉና የማዕድን ውሃ ፊብሪካ
ሞሃ ለስላሳ መጠጦች ኢንደስትሪ አ/ማ - ጠበቃ ተፈራ ደንበል - ቀረበ።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ - ታምራት አባተ - ቀረበ።
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ለሰበር አቤቱታው መነሻ የሆነው ጉዲይ በአፈፃፀም ሂደት የተነሳውን ክርክር የሚመለከት ነው። ክርክሩ የተጀመረው በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን፣ የአፈፃፀም መዝገቡ የተከፈተው የአሁኑ አመልካች በ1ኛ ተጠሪ ላይ የሰጠውን ውሳኔ ለማስፈፀም ነው። 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች ክርክሩ ውስጥ የገቡት የአፈጻጸም ሂደቱ የእኛን መብት ነክቶአል በማለት ነው። ከመዝገቡ እንዲየነው አመልካች በፍርድ ባለመብትነቱ በ1ኛ ተጠሪ ፊብሪካ ላይ የአፈጻጸም ትዕዛዝ አሰጥቶ ነበር። በልላ በኩል ደግሞ ፊብሪካው የምዕራብ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የአገር ውስጥ ገቢ ባለሥልጣን በ1ኛ ተጠሪ ላይ ላሰጠው ውሳኔ ማስፈጸሚያነትይውል ዘንድ በፊብሪካው ላይ የሐራጅ ማስታወቂያ አስቀድሞ አውጥቶ እንደነበር እና በዚህ ጨረታም 3ኛ ተጠሪ ተወዲድሮ በማሸነፍ ፊብሪካውን እንደገዛ፣ በመቀጠልም 3ኛ ተጠሪ ፊብሪካውን ለ2ኛ ተጠሪ እንደሸጠው፣ 2ኛ ተጠሪም ዋጋውን ከመክፈለም በላይ፣ ፊብሪካውን በስሙ አስመዝግቦ ባለቤት እንደሆነ ከመዝገቡ ተመልክተናል።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤትም እነዚህን ሁኔታዎች በተጨባጭ ካረጋገጠ በኋላ፣ አመልካች የ1ኛ ተጠሪ ፊብሪካ ነው በማለት አሰጥቶት የነበረውን የአፈጻጸም ትዕዛዝ እንዱቋረጥ ወስኖአል። ይህን ውሳኔ በመቃወም ይግባኝ የቀረበለት የፋዳራል ጠ/ፍ/ቤትም ውሣኔው ጉድለት የለበትም በማለት ይግባኙን ሰርዞአል። የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚህ ላይ ነው።
አመልካች ነሐሴ 5 ቀን 2001 ዓ.ም. በጻፈው ማመልከቻ የሥር ፍ/ቤቶች የሰጡት ውሳኔ/ትዕዛዝ/ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው የሚልበትን ምክንያት በመግለጽ ስህተቱ ይታረምለት ዘንድ አቤቱታ አቅርቦአል። በበኩላችንም አቤቱታውን መሰረት በማድረግ ክርክሩን ሰምተናል። በተደረገላቸው ጥሪ መሰረት የቀረቡት 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች ሲሆኑ፣ 1ኛ ተጠሪ በጥሪው መሰረት ባለመቅረቡ ክርክሩ የተሰማው በላለበት ነው። አቤቱታው በሰበር ችልት እንዱታይ የተደረገው ለወደፉቱ የሚሰጥ ፍርድን ማስፈጸም ይቻል ዘንድ ለዋስትና ሲባል የተከበረ ንብረት በልላ እዲ ምክንያት በተሸጠ ጊዜ ቀደም ሲል ንብረቱን ያስከበረው ወገን የሚኖረው መብት ምንድን ነው?
የሚለውን ጥያቄ አግባብነት ካለው ሕግ አኳያ ለመመርመር ሲባል ነው። በዚህ መሰረትም ግራቀኝ ወገኖች በዚህ ረገድ ያሰሙትን ክርክር አቤቱታ ከቀረበበት ውሳኔ /ትዕዛዝ/ እና ከሕጉ ጋር አገናዝበን መርምረናል።
ከላይ እንደተመለከተው ፊብሪካው የተሸጠው ፍ/ቤት በሰጠው የአፈፃፀም ትዕዛዝ መሰረት ነው። በወቅቱ የፍርድ ባለመብት የነበረው ግብር አስገቢ የሆነው የአገር ውስጥ ገቢ ባለሥልጣን ወይም መሥሪያ ቤት ነው። አመልካች ንብረቱን አስከብሬ /በፍ/ቤት የእግድ ትዕዛዝ አሰጥቼ/ ነበር የሚለው ፊብሪካው ከመሸጡ በፉት ነው። ሆኖም ከፊብሪካው ይፈለግ የነበረው የግብር ዕዲ በመሆኑ እና የአገር ውስጥ ገቢ ባለሥልጣን ከማናቸውም ላልች ባለዕዲዎች የቀድምትነት መብት እንዲለው በገቢ ግብር አዋጅ ቁ. 286/1994 አንቀጽ 80/1/ በመደንገጉ ፊብሪካው የግብር ዕዲውን ለመክፈል ሲባል መሸጡ ተገቢ ነው። አመልካችም በዚህ ጊዜ የነበረው መብት ከሺያጩ ገንዘብ ላይ ተራፉ ካለ መብቱን አስረድቶ መውሰድ ነው። ከዚህ ውጭ ፊብሪካውን የመከተል ወይም ከገዛው ወገን ላይ ወስድ ማሸጥ የሚችልበት አግባብ የለም። የአሁኑ 2ኛ ተጠሪ ፊብሪካውን የገዛው ከ3ኛ ተጠሪ ላይ ነው። 3ኛ ተጠሪ ደግሞ በግብር ዕዲው ምክንያት በወጣው ጨረታ ተወዲድሮ በማሸነፍ ፊብሪካውን ገዝቶአል። በዚህም የፊብሪካው ባለቤት ሆኖ ነበር። በዚህ መልክ ያገኘውን የባለቤትነት መብት መሰረት በማድረግም ነው ፊብሪካውን ለ2ኛ ተጠሪ የሸጠው። በመሆኑም አመልካች በ3ኛ ተጠሪ ላይ ያልነበረውን መብት በ2ኛ ተጠሪ ላይ ሉኖረው አይችልም። ሲጠቃለል የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የአመልካችን ጥያቄ ውድቅ ማድረጉ በአግባቡ ነው ከሚባል በስተቀር በዚህ ረገድ የተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለም።
ው ሣ ኔ
የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ.51946 ጥቅምት 25 ቀን 2001 ዓ.ም. የሰጠው ትዕዛዝ እና የፋዳራል ጠ/ፍ/ቤት በፍ/ብ/ይ/መ.ቁ.45060 ግንቦት 21 ቀን 2001 ዓ.ም. የሰጠው ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ-ሥ ሕግ ቁ. 348/1/ መሰረት ፀንተዋል።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተቀባይነት የለውም ብለናል።
ግራቀኝ ወገኖች ወጪና ኪራቸውን ይቻቻለ።
No topics extracted.