No summary available.
ሐምል 9 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ታፈሰ ይርጋ ፀጋዩ አስማማው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- አቶ ብርሃኑ ፈይሳ - ቀረቡ ተጠሪ፡-
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የአማራ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ በመዝገብ ጥቅምት 12 ቀን 2000 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔና የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 5984 መጋቢት 11 ቀን 2000 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት በማመልከታቸው ነው።
ክርክሩ በመጀመሪያ የታየው በከፍተኛው ፍርድ ቤት ነው። በከፍተኛው ፍርድ ቤት አመልካች ንበረትነቱ የአንደኛው ተጠሪ የሆነ ሱዙኪ ቪታራ መኪና በሁለተኛው ተጠሪ በማሽከርከር ላይ እያለ የካቲት 6 ቀን 1996 ዓ.ም ከቀኑ በግምት ስድስት ሰዓት ሲሆን በአንጏለላናጠራ ወረዲ መኪ ከተማ ከትምህርት ቤት ፉት ለፉት መንገደን በመሳት የአስራአንድ ዓመት ታዲጊ ወጣት የሆነውን ልጄን ዮሐንስ ብርሃኑን በመግጨት የሞት አደጋ አድርሶበታል። በልጄ መሞት ከፍተኛ ጉዲት የደረሰብኝ ሲሆን ልጄ አስራ ስምንት ዓመት ከሞላው በኋላ ለእኔ ሉያደርግልኝ የነበረ ድጋፍ እንክብካቤና የገንዘብ እርዲታ ቀርቶብኛል። ስለዚህ ታዲጊ ወጣት ብርሃኑ ፈይሳ ቢኖር ኖሮ እድሜው አካለ መጠን ሲደርስ ሉያደርግልኝ የሚችለው ድጋፍ እንክብካቤና የገንዘብ ድጋፍ የቀረብኝ በመሆኑ አንደኛ ተከሳሽ /ተጠሪ/ የመኪናው ባለቤት በመሆኑ ሁለተኛው ተጠሪ /ተከሳሽ/ ጥፊት በሆነ ቸልተኝነት ዩሐንስ ብርሃኑን ለሞት የዲረገ በመሆኑ ብር 76,800 /ሰባ ስድስት ሺ ስምንት መቶ ብር/ ካሣ እንዱከፍለኝ በማለት ክስ አቅርበዋል።
ተጠሪዎች በሥር ፍርድ ቤት በተከሳሽነት ቀርበው በተናጠል የመከላከያ መልስ አቅርበዋል።
ተጠሪዎች በህፃኑ መሞት ምክንያት አመልካች በክሱ የገለፁትን ያህል ወደፉት የሚገኝ ጥቅም የቀረባቸው መሆኑን በማረጋገጥ አላቀረቡም። ሟች ህፃን ብርሃኑ ፈይሳ ራሱን በመርዲት ለአባቱ እገዛ ማድረግ የሚችል ስለመሆኑ ማረጋገጫ የለም። ስለዚህ ከሳሽ /አመልካች/ ለደረሰባቸው የህሉና ጉዲት የሞራል ካሣ ከሚጠይቁ በስተቀር የቀረባቸው ጥቅም ስለመኖሩ ማስረጃ ያላቀረቡ በመሆኑ ጥያቄአቸው ተቀባይነት የለውም በማለት ተከራክረዋል። የሥር ፍርድ ቤት ህፃን ብርሃኑ ፈይሳ ላይ ለደረሰው የሞት አደጋ አንደኛና ሁለተኛ ተጠሪ በአንድነትና በነጠላ አላፉነት አለባቸው በማለት ኃላፉነቱን በሚመለከት ውሣኔ ሰጥቷል። የካሣውን መጠን በተመለከተ ከሳሽ /አመልካች/ በልጃቸው መሞት ምክንያት የቀረባቸው ጥቅም ያለ መሆኑንና ለወደፉቱም የሚቀርባቸው ጥቅም ስለመኖሩ ያላረጋገጡ ስለሆነ ጥያቄአቸው ተቀባይነት የለውም። በአደጋው ምክንያት ልጃቸው በመሞቱ ለደረስባቸው የህሉና ጉዲት ካሣ ብር 800 /ስምንት መቶ ብር/ አንደኛ ተከሳሽ /አንደኛ ተጠሪ/ ይክፈል በማለት ውሣኔ ሰጥቷል። አመልካች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቅርበው የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኛቸውን ሰርዞታል።
አመልካች ሐምል 21 ቀን 2000 ዓ.ም አሻሽል ባቀረበው የሰበር አቤቱታ ልጄ ብርሃኑ ፈይሳ በደረሰበት የመኪና አደጋ በመሞቱ ልጁን ለማሳደግና ለማስተማር ያወጣሁት ወጭ ፍሬ አልባ ከመሆኑ በተጨማሪ ከትምህርት ቤት መልስ ያደርግልኝ የነበረው እገዛና ይሰጠኝ የነበረው ግልጋልት ተቋርጦብኛል። እኔ ሟች ታዲጊ ወጣት ብርሃኑ ፈይሳ ከትምህርት ቤት መልስ ከብቶችን በመንከባከብና በላልች የእርሻ ሥራዎች የሚያደርግልኝን እገዛ ከላላ ሰው ለማግኘት በቀን አስር ብር /10 ብር/ እከፍላለሁ። ልጄ በህይወት ቢኖር ኖሮ በእውቀቱና በጉልበቱ ሰርቶ ሉያገኝ የሚችለው ገቢ እየጨመረ እንደሚሄድና ላላ የላለኝ በመሆኑ በእሱ መሞት ምክንያት ከፍተኛ ችግርና ኪሣራ እንደሚገጥመኝ የታወቀ ነው። በአዋጅ ቁጥር 559/2000 ተሽከርካሪ በሶስተኛ ወገን ላይ ለሚያደርሰው ጉዲት የሚገባው የመድን ዋስትና መነሻው ብር 40,000 /አርባ ሺህ ብር/ እንደሆነ ተደንግጓል። የሥር ፍርድ ቤትና የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይህንን መነሻ በማድረግ አለመወሰናቸውና በህፃን ብርሃኑ ፈይሳ መሞት ምክንያት የደረሰብህና ለወደፉትም የሚደርስብህ ጉዲት የለም በማለት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ይታረምልኝ በማለት አመልክቷል።
አንደኛ ተጠሪ የፍርድ ቤቱ መጥሪያ ደርሶት ባለመቅረቡ ሁለተኛ ተጠሪ መጥሪያው በፍርድ ቤት ቅጥር ጊቢ ተለጥፍ ያልቀረበ በመሆኑ ጉዲዩ ተጠሪዎች በላለበት እንደሚታይ ችልቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል። አመልካች ህፃን ብርሃኑ ፈይሳ በመሞቱ የደረሰባቸው እርግጠኛ ጉዲት ያለ መሆኑንና ህፃን ብርሃኑ ፈይሳ ለላላ ሰው የሚከፍለትን በቀን የአስር ብር ወጭ ይሸፍንላቸው እንደነበር ወደፉትም ያለጧሪ መቅረታቸው ራሱን የቻለ ጉዲት እንደሆነ በቃል ክርክር አስረድተዋል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና አመልካች በጽሁፍና በቃል ያቀረቡት ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም ጉዲዩን መርምረናል። ጉዲዩን እንደመረመርነው አመልካች እድሜው አስራ አንድ የሆነው ልጃቸው የሞት አደጋ ስለደረሰበት የደረሰባቸው እርግጠኛ ጉዲትና የቀረባቸው ጥቅም አለ ወይስ የለም? አመልካች በህፃኑ መሞት ምክንያት ወደፉት ሉያገኙ ይችለ የነበሩት ጥቅም ቀርቶባቸዋል ወይስ አልቀረባቸውም? የሚለት ነጥቦች የክርክሩ መሰረታዊ ጭብጥ ሆኖ አግኝተነዋል።
የመጀመሪያውን ነጥብ በተመለከተ አመልካች በእርሻ ሥራ የሚተዲደሩ አርሶ አደር መሆናቸውን ከመዝገቡ ውስጥ ያለት ፍሬ ጉዲዮች ያሳያለ። በእርሻ ሥራ ውስጥ ሟች የሚያደርግላቸው እገዛና የሚሰጣቸው ግልጋልት እንደነበር ተጠሪዎች በግልጽ ክደው አልተከራከሩም። ይኸም ተጠሪዎች በፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 234/1/ ሰ መሰረት በአመልካች በኩል የተነሱትን ነጥቦች እንዲመኑ የሚያስቆጥር ነው። ሟች ለአመልካች ከትምህርት ቤት ሲመለስና በእረፍት ቀናት የተለያዩ አገልግልቶች እገዛ ያደርግላቸው የነበረ መሆኑ ከተረጋገጠ በሟች መሞት ምክንያት የደረሰበት ጉዲት የለም ብል ለመደምደም አይቻልም። ከዚህ በተጨማሪ አመልካች የአስራ አንድ አመት ልጃቸው በደረሰበት የመኪና አደጋ በመሞቱ ልጃቸው ወደፉት የሚሰጣቸው የጉልበትና ላልች እገዛዎች የተቋረጠ መሆኑን ለመገንዘብ ይቻላል። በአጠቃላይ አመልካች የአስራ አንድ ዓመት ልጃቸው በደረሰበት የመኪና አደጋ በመሞቱና ከልጃቸው ያገኙት የነበሩት የእርሻ ሥራ ድጋፍና እገዛ ተቋርጦባቸዋል። አመልካች ይህንን እገዛ ወደፉት ሉያገኙ የሚችለ የነበረ ቢሆንም ወደፉት ከልጃቸው ሉያገኙት የሚችለት እገዛና ድጋፍ ተቋርጦባቸዋል።
ስለዚህ አመልካች የካሣ ጥያቄ በፍታብሓር ህግ ቁጥር 2090 እና በፍታብሐር ሕግ ቁጥር 2091 የሚሸፈን ሆኖ አግኝተነዋል።
የካሣው መጠንም መወሰን ያለበት አመልካች ልጃቸው ቢኖር ሉያገኙት የሚችለትን ጥቅም መሰረት በማድረግ ሳይሆን በፍታብሓር ሕግ ቁጥር 2095 ንዐስ አንቀጽ 2ን መሰረት በማድረግ ላሆን ይገባዋል። ከዚህ አንፃር ስንመለከተው አመልካች የደረሰባቸውንና ወደፉት ሉደርስባቸው የሚችለውን እርግጠኛ የጉዲት መጠን ለማረጋገጥ ባይቻልም እንደዚህ አይነት ሁኔታ ሲያጋጥማቸው ዳኞች ፍትህንና ርትዕን መሰረት በመድረግ እንደሚወስኑ የፍታብሓር ሕግ ቁጥር 2092/1/ የሚደነግግ በመሆኑ የሥር ፍርድ ቤቶች በዚህ ድንጋጌ መሰረት የአመልካችን ጥያቄ ተቀብለው ውሣኔ አለመስጠታቸው መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል። ስለሆነም የሥር ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚው ችልት አመልካች የሞራል ካሣ ብር 800 /ስምንት መቶ ብር/ ብቻ ይከፈላቸው በማለት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት አለበት በማለት ወስነናል።
የካሣውን መጠን በተመለከተ ርትዕና ፍትህን መሰረት በማድረግ እንዱወስኑ ጉዲዩ ለሥር ፍርድ ቤት ቢመለስ የሚያስከተለውን ወጭና በአመልካች ላይ የሚደርሰውን መጉላላት ታሳቢ በማድረግ ተጠሪዎች በአንድነትና በነጠላ ለአመልካች ብር 12,000 /አስራ ሁለት ሺህ ብር/ እንዱከፍለ በማለት በፍታብሓር ሕግ ቁጥር 2092/2/ መሰረት ውሣኔ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ
የከፍተኛው ፍርድ ቤት እና የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰጡት ውሣኔ ተሻሽሎል።
ተጠዎች የሥር ፍርድ ቤት የወሰነውን የሞራል ካሣ 800 እና በዚህ ፍርድ ቤት የተወሰነውን ብር 12,000 /አስራ ሁለት ሺህ/ በድምሩ 12,800 /አስራ ሁለት ሺህ ስምንት መቶ ብር/ በአንድነትና በነጠላ ለአመልካች ይክፈለ ብለናል። ይፃፍ። ይህ ፍርድ በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሙለ ድምጽ ተሰጠ።
No topics extracted.