No summary available.
የካቲት 14 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጎስ ወልድ ዲኜ መላኩ ተሻገር ገ/ሥላሴ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- የመንግሥት ቤቶች ኤጀንሲ - ከበደ ዓለሙ - ቀረበ ተጠሪዎች፡-
በዚህ መዝገብ በሰበር ችልቱ እንዱወሰን የተያዘው ጭብጥ የቤት ኪራይ ውልን መነሻ ባደረገው ክስ የተጠየቀው የገንዘብ ክፍያ በፍ/ብ/ሕግ ቁ. 2ዐ24/መ/ የተመለከተውን ድንጋጌ በመጥቀስ እንደተከፈለ ይቆጠራል በማለት በሥር ፍ/ቤቶች የሰጠው ውሣኔ በሕጉ አግባብ ነው ወይ? የሚል ነው።ከመዝገቡ እንደሚታየው ክርክሩ በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲጀመር ከሣሽ የነበረው የአሁኑ አመልካች ሲሆን፣ ተጠሪዎችን የከሰሰው በሕግ አግባብ እና በኤጀንሲው የኪራይ መመሪያ መሰረት የኪራይ ውል ሣይኖራቸው በቤቱ የተገለገለ በመሆናቸው ያለአግባብ በበለፀጉበት መጠን ክስ የቀረበበትን ገንዘብ ሉከፍለኝ ይገባል በማለት ነው። ተጠሪዎችም ለክሱ በሰጡት መልስ በእነሱ እና በአመልካች መካከል የኪራይ ውል ወይም ግንኙነት እንደላለ በመግለጽ የመክሰስ መብት የለውም እንደዚሁም ገንዘቡ የተጠየቀው በሕጉ በተወሰነው ጊዜ ስላልሆነ ክሱ ሉስተናገድ አይገባም በማለት መቃወሚያ አቅርበዋል። የክሱን ሥረ ነገር በሚመለከትም ቤቱን የያዝነው ከቀድሞው ተከራይ የንግድ መደብሩን በመግዛት ነው። ቤቱ በአሁኑ ጊዜ ፈርሶአል የሚለትን የመከራከሪያ ነጥቦች በማንሣት ክሱ ውድቅ ይደረግላቸው ዘንድ ጠይቀዋል። ክሱን የሰማው ፍ/ቤት ክርክሩን የመረመረ ሲሆን፣ በመቀጠልም የክፍያ ጥያቄው በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ ያልቀረበ በመሆኑ በፍ/ብ/ሕግ ቁ.
2ዐ24/መ/ መሰረት እንደተከፈለ ይቆጠራል የሚል ምክንያት በመስጠት ክሱን ሙለ በሙለ ውድቅ አድርጎል። በልላ በኩል ደግሞ አመልካች ውሣኔውን በመቃወም ለፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ አቅርቦ የነበረ ሲሆን ፍ/ቤቱም ይግባኝ የተባለበት ውሣኔ ጉድለት የለበትም በማለት ይግባኙን ሰርዞአል። የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚህ ላይ ነው።
እኛም አመልካች መጋቢት 16 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም በፃፈው ማመልከቻ ያቀረበውን አቤቱታ መሰረት በማድረግ ተጠሪዎችን አስቀርበን ክርክሩን ሰምተናል። ክርክሩ የተሰማው የሥር ፍ/ቤቶች የተጠየቀው ገንዘብ እንደተከፈለ ይቆጠራል በማለት የህሉና ግምት የወሰደት ሕጉን በአግባቡ በመተርጎም ነው ወይ? በሚለው ጭብጥ ላይ ነው። በመሆኑም ግራ ቀኝ ወገኖች ጭብጡን መሰረት በማድረግ ያሰሙትን ክርክር አቤቱታ ከቀረበበት ውሣኔ እና ከሕጉ ጋር አገናዝበን መርምረናል።
የአመልካች እና የተጠሪዎች ግንኙነት በኪራይ ውል ላይ የተመሰረተ ላለመሆኑ አላከራከረም። አመልካች ተጠሪዎችን የከሰሰው የውል ግዳታ አልተወጡም ወይም በገቡት የኪራይ ውል መሰረት ኪራይ አልከፈለም በማለት እንዲልሆነም ከመዝገቡ ለመገንዘብ ችለናል። አመልካች ክስ የመሰረተው ተጠሪዎች ቤቴን ያለአግባብ ይዘው ከህግ ውጪ በልጽገዋል በማለት ነው።
በእርግጥ የጠየቀውን ገንዘብ ያሰላው ቤቱን በማከራየት አገኝ ነበር ባለው መጠን ነው። ተጠሪዎችም በቤቱ አልተገለገልንም የሚል ክርክር አላነሱም። ይልቁንም ከአመልካች ጋር የውል ግንኙነት የለንም በማለት ገንዘቡን መክፈል የለባቸውም እንዱባልላቸው የተከራከሩት በመሆኑም እነዚህን ፍሬ ነገሮች ደምረን ጉዲዩን ስንመለከተው ክርክሩ ከኪራይ ክፍያ ጋር የሚያያዝበት ምክንያት የለም።
የሥር ፍ/ቤቶች ለክርክሩ አወሳሰን ተገቢነት አለው በማለት የጠቀሱት የፍ/ብ/ሕግ ቁ. 2ዐ24 የሚገኘው ‛ ስለውልች በጠቅላላው ‛ በሚል በተደነገገው በፍትሐብሕር ሕጉ በአንቀጽ 12፣ በምዕራፍ 7 በክፍል 3 ሥር ሲሆን፣ ክስ የቀረበበት ገንዘብ በሁለት ዓመት እንደተከፈለ የሚያስቆጥር የህሉና ግምት የሚወሰድባቸውን አግባቦችም በዝርዝር ያመለክታል። የህሉና ግምት ከሚወሰድባቸው የክፍያ ጥያቄዎች አንደ የቤት ኪራይ እንደሆነም በንኡስ ቁጥር /መ/ ተመልክቶአል። በያዝነው ጉዲይ ለክርክሩ መነሻ የሆነው ገንዘብ የኪራይ ገንዘብ እንደሆነ ከላይ በዝርዝር ተመልክተናል።
በመሆኑም የፍ/ብ/ሕግ ቁ. 2ዐ24 ለክርክሩ አወሳሰን የሚጠቀስ ወይም አግባብነት ያለው አይደለም።
ቀደም ሲል እንዲመለከትነው በአመልካች እና በተጠሪዎች መካከል በውል ላይ የተመሰረተ ግንኙነት የለም። ይህም ሆኖ ግን አመልካች በተጠሪዎች ላይ ክስ ለመመሥረት የሚያስችል ምክንያት አለው። ቤቱን ያለዋጋ ሲጠቀሙ ቆይተዋል። ይህን የመሰለ ግንኙነት የሚገዛው ከውል ውጪ ስለሚደርስ ኃላፉነት እና ያለአግባብ ስለመበልፀግ በሚል በተደነገገው በፍትሐብሕር ሕጉ በአንቀጽ 13 በምዕራፍ 2 ሥር ባለት ድንጋጌዎች ነው። የላላ ሰው ሐብት በሆነ ነገር በመገልገል በቂ ባልሆነ ምክንያት ጥቅም ያገኘ ሰው አለአግባብ ጥቅም ባገኘበት መጠን ለባለሐብቱ ኪሣራ መክፍል እንዲለበት ከፍ ሲል በተጠቀሰው በምዕራፍ 2 ሥር በሚገኘው በፍ/ብ/ሕግ ቁ. 2162 ተመልክቶአል። ተደጋግሞ እንደተገለፀው ተጠሪዎች የአመልካች ንብረት በሆነው ቤት አልተገለገልንም የሚል ክርክር የላቸውም። አመልካች አስልቶ ባቀረበው የገንዘብ መጠንም ተቃውሞ አላነሱም የገንዘብ መጠኑ የተሰላው የንግድ ሥራ የሚካሄድባቸው ቤቶች ለላላ ሰው በንግድ ሽያጭ ውል ሲተላለፈ ኪራይ ለመተመን በኤጀንሲው በወጣው መመሪያ መሰረት ነው። ይህም ማለት ቤቱ በተጠሪዎች በመያዙ ምክንያት አመልካች የወለን ገቢ ነው የጠየቀው ማለት ነው። በመሆኑም ተጠሪዎች በቤቱ መገልገላቸው እስከተረጋገጠ ድረስ አመልካች ቤቱን ባለው መመሪያ መሰረት አከራይቶ ሉያገኝ ይችል የነበረውን ገንዘብ ያክል የመክፈል ኃላፉነት አለባቸው። የሥር ፍ/ቤቶች እነዚህን ሁኔታዎች ሣያገናዝቡ ሕጉን ተከትለው ጉዲዩን ሣይመረምሩ በመወሰናቸው የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ሆኖ ተገኝቶአል። ስለዚህም ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ.ቁ. 13ዐ183 ሐምል 24 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ እና የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ. 84627 ጥር 18 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም የሰጠው ትእዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 348/1/ መሰረት ተሽረዋል።
ተጠሪዎች ክስ የቀረበበትን ገንዘብ ብር 138,122.19 /አንድ መቶ ሰላሣ ስምንት ሺህ አንድ መቶ ሃያ ሁለት ብር ከአሥራ ዘጠኝ ሣንቲም/ ለአመልካች በአንድነትና በነጠላ ይክፈለ ብለናል።
በዚህ ሰበር ችልት በተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሣራ በተመለከተ ግራ ቀኝ ወገኖች ይቻቻለ።
No topics extracted.