No summary available.
ጥር 25 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ዲኜ መላኩ ተሻገር ገ/ሥላሴ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- አቶ አብራር ሳቢር - ጠበቃ ቸርነት ወርድፊ - ቀረቡ ተጠሪ፡-
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የጉዲት ካሳ ይከፈለኝ ጥያቄን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኗ 1ኛ ተጠሪ በአሁኑ አመልካች ላይ በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው። የክሱ ይዘትም ባጭሩ የሰላዲ ቁጥር 2- 37663 ሀይለክስ ቶዮታ መኪና፣ ንብረትነቱ የአሁኑ አመልካች የሆነች ባለቤታቸውን (አቶ አብርሃም አክሉልን) በአቶ ዘነበ ብርሃኑ ጥቅምት 25 ቀን 1996 ዓ.ም በመነዲት ላይ እያለች ሸረራ በተባለ ቀበላ ገበሬ ማህበር ክልል ውስጥ ስትደርስ መንገደን በመልቀቅ ሮጣ ከእንጨት ላይ በመጋጨት በአቶ አብርሃም ላይ ጉዲት በማድረሷ አቶ አብርሃም በሕክምና ሲረደ ቆይተው ታህሳስ 03 ቀን 1996 ዓ.ም ከዚህ አለም በሞት መለየታቸውን፣ በሕይወት እያለም የፍራፍሬ ንግድ ስራ ሰርተው ገቢ ያስገኙ እንደነበር፣ ሟች እድሜአቸው 32 ዓመት እንደነበር፣ በሚያገኙት ገቢም ተጠሪን ያስተዲድሯቸው እንደነበርና የገቢ መጠኑንም ጭምር በመግለጽ በጉዲቱ ምክንያት ብር 134,400.00(አንድ መቶ ሰላሳ አራት ሺህ አራት መቶ ብር) ገቢ የተቋረጠባቸው መሆኑን፣ ለህክምናና ለቀብር ወጪ ማውጣታቸውን የሕሉና ጉዲትም የደረሰባቸው መሆኑን ጠቅሰው በጠቅላላው ብር 138,400(አንድ መቶ ሰላሳ ስምንት ሺህ አራት መቶ ብር) በክሱ ምክንያት ካወጡት ወጪና ኪሳራዎች ጋር አመልካች እንዱከፍለ ይወሰንላቸው ዘንድ ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። የአሁኑ አመልካች ለክሱ በሰጡት መከላከያ መልስም የመኪናዋ ባለንብረት ቢሆኑም መኪናዋን ለአሁኑ 2ኛ ተጠሪ በኯንትራት ሰጥተው በነበሩበት ወቅት ጉዲቱ መድረሱን ገልጸው ኃላፉነት የለብኝም በማለት የተከራከሩ ሲሆን የአሁኑ 2ኛ ተጠሪም ወደ ክሱ እንዱገባ ጥያቄ አቅርበዋል። የስር ፍርድ ቤትም የአሁኑ 2ኛ ተጠሪ ወደ ክሱ እንዱገባ ትእዛዝ ሰጥቶ ተጠሪም ቀርቦ ለጉዲቱ ኃላፉነት የለብኝም በማለት ተከራክሯል። ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የአርሲ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ በመመርመር የአሁኑን አመልካች በመኪናው ባለንብረትነቱ ለጉዲቱ ኃላፉ ሲያደርግ 2ኛ ተጠሪን ግን ከክሱ ነጻ አድርጎታል። የጉዲት መጠኑን በተመለከተም በርትዕ ብር 40,000.00(አርባ ሺህ) ላሆን ይገባል ሲል ወስኗል። በዚህ ውሳኔ አመልካች ባለመስማማት ይግባኛቸውን ለኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ የስር ፍርድ ቤት አመልካችን ለጉዲቱ ኃላፉ፣ 2ኛ ተጠሪን ደግሞ ነፃ በማድረግ የሰጠውን የውሳኔ ክፍል በማፅናት የጉዲት መጠኑን ብቻ ብር 25,000.00(ሃያ አምስት ሺህ ብር) እንዱሆን በማሻሻል ወስኗል። ከዚህም በኋላ አመልካች ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ቢያቀርቡም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 337 መሰረት ተሰርዞባቸዋል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
የአመልካች ጠበቃ ሚያዝያ 18 ቀን 2002 ዓ.ም በፃፈት ሶስት ገፅ የሰበር አቤቱታ በበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ላይ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈፅሟል የሚለበትን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም ባጭሩ አመልካች ለጉዲቱ ኃላፉ ተብለው መወሰኑም ሆነ ለ1ኛ ተጠሪ ካሳ ይከፈል ተብል መወሰኑ ከፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2095፣ 2082፣ 2089 እና 2102 ድንጋጌዎች ውጪ ነው የሚለባቸውን ምክንያቶችን በመዘርዘር መከራከራቸውን የሚያሳይ ነው። አቤቱታቸው ተመርምሮም ኃላፉነትን በተመለከተ የተሰጠውን ውሳኔ ሕጋዊነት ለመመርመር ሲባል ለሰበር ችልቱ እንዱቀርብ ተደርጓል። በዚህም መሰረት ለተጠሪዎች ጥሪ ተደርጎላቸው 2ኛ ተጠሪ ቀርቦ በጠበቃው አማካኝነት ጥቅምት 11 ቀን 2003 ዓ.ም በተጻፈ ሁለት ገፅ ማመልከቻ መልሱን የሰጠ ሲሆን 1ኛ ተጠሪ ግን በጋዜጣ ጥሪ ተደርጎላቸው ባለመቅረባቸው ጉዲዩ በላለበት እንዱታይ ተደርጓል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታ መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩ ለሰበር ችልት ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንጻር በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። ጉዲዩ ለሰበር ችልት ሲቀርብ የተያዘው ጭብጥ አመልካች ለጉዲቱ ኃላፉ ተብል መወሰኑ ባግባቡ ነው ወይስ አይደለም የሚለውን ነጥብ ከፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2082(2) እና 2089 ድንጋጌዎች አንፃር ለይቶ ለመወሰን ሲባል ነው።
No topics extracted.
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው የ1ኛ ተጠሪ ባለቤት የሆኑት አብርሃም አክሉል ንብረትነቱ የአመልካች በሆነች ሃይለክስ ቶዮታ መኪና ተሳፍረው ሲሄደ በደረሰው አደጋ ምክንያት ከዚህ አለም በሞት የተለዩ መሆኑን፣ መኪናው ጉዲቱን ባደረሰበት እለት በ2ኛ ተጠሪ እጅ የነበረ መሆኑ፣ መኪናው ወደ ሁለተኛ ተጠሪ እጅ ሉገባ የቻለውም በኪራይ ስለመሆኑ ነው። የስር ፍርድ ቤቶች 2ኛ ተጠሪን ለጉዲቱ ኃላፉነት የለበትም በማለት ሉወስኑ የቻለት 2ኛ ተጠሪ ሲገለገልበት አልነበረም በሚል ምክንያት ሳይሆን መኪናው ጉዲቱን ባደረሰበት ጊዜ ይሽከረከር የነበረው በአመልካች በተቀጠረ ሹፋር በመሆኑና መኪናውን የመቆጣጠር ኃላፉነት የሹፋሩ ነው በሚል ምክንያት ነው።
በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2081(1) መሰረት የአንድ መኪና ወይም ባለሞተር ተሽከርካሪ ባለቤት የሆነ ሰው ንብረቱ ተሰርቆ በነበረበት ጊዜ ለደረሰው አደጋ ከተጠያቂነት ነፃ ከሚሆን በስተቀር መኪናውን ወይም ባለሞተር ተሽከርካሪውን ለመንዲት ባልተፈቀደለት ሰው እንኳን ተነድቶ ጉዲት አድርሶ ቢገኝ የመኪናው ወይም የባለሞተር ተሽከርካሪው ባለቤት ለደረሰው ጉዲት ኃላፉ እንደሚሆን ተመልክቷል። የአንድ መኪና ወይም ባለሞተር ተሽከርካሪ ባለቤት ከውል ውጭ በሚደርሱ ኃላፉነቶች ውስጥ በፍትሐብሕር ሕጉ አጥፉ ሳይሆን አላፉ ከሚባለት ምድቦች ውስጥ የሚመደብ በመሆኑ መኪናው ወይም ባለሞተር ተሽከርካሪው ላደረሰው ጉዲት ባለቤቱ ኃላፉ ነው። ይህ ማለት ግን ስሙ በባለቤትነት ያልተመዘገበ መኪናውን ወይም ባለሞተር ተሽከርካሪውን ለግል ጥቅሙ ሲገለገልበትና ሲጠቀምበት የነበረው ሰው መኪናው ወይም ባለሞተር ተሽከርካሪው በእጁ በነበረበት ጊዜ ለደረሰው ጉዲት ከተጠያቂነት ነጻ ይሆናል ማለት አለመሆኑን ከፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2082(1) መረዲት ይቻላል። በዚህ መነሻነት በአንድ መኪና ወይም ባለሞተር ተሽከርካሪ ጉዲት የደረሰበት ሰው የመኪናውን ወይም የባለሞተር ተሽከርካሪውን ባለቤት ወይም በንብረቱ ተገልጋይ የነበረውን ማንኛውም ሰው በአንድነትም ሆነ በተናጠል ከሶ ለደረሰበት ጉዲት ካሣ ለመጠየቅ በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2081(1) እና 2082(1) መሰረት መብት ያለውን ያህል የመኪናው ወይም የባለሞተር ተሽከርካሪው ባለቤት ተብል የሚታወቀው ሰው የንብረቱ ባለቤት በመሆኑ ብቻ ተበዲይን ተገድ ከካሰ በኋላ መኪናውን በእጁ አድርጏ ሲገለገል የነበረውን ማንኛውም ሰው የከፈለውን ገንዘብ እንዱከፍለው የመጠየቅ መብት ያለው መሆኑ በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2083(1) ተመልክቷል።
ወደተያዘው ጉዲይ ስንመለስ አመልካች በስር ፍርድ ቤቶች የተከሰሱት የመኪናው ባለንብረት በመሆናቸው ሲሆን 2ኛ ተጠሪ ወደ ክሱ እንዱገቡ የተደረገውም መኪናውን ጉዲቱ በደረሰበት ጊዜ ሲገለገልበት ነበር በሚል ምክንያት ሁኖ ይኸው ስለመሆኑም በሚገባ ተረጋግጧል። 2ኛ ተጠሪ መኪናውን ሲገለገልበት የነበረ መሆኑ ከታወቀ የመኪናውን አሽከርካሪ ባለንብረቱ መቅጠሩ መታወቁ መኪናውን ሲገለገልበት የነበረን ሰው ከኃላፉነት ነጻ ሉያደርገው የሚችል ሕጋዊ ምክንያት ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2082 ድንጋጌ በመስፈርትነት ያላስቀመጠው ነጥብ ነው። በመሆኑም ጉዲቱን ያደረሰውን መኪና ሲገለገልበት የነበረው 2ኛ ተጠሪ መሆኑ ከተረጋገጠ የመጨረሻ ኃላፉነቱን (ultimate liability) ሉወስድ የሚገባው ይኸው ተጠሪ ነው። በመሆኑም የበታች ፍርድ ቤቶች አመልካችን ለክሱ ኃላፉ፣ 2ኛ ተጠሪን ከክሱ ነጻ በማድረግ ውሳኔ መስጠታቸው ከፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2081፣ 2082(1) እና 2083 ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ ውጪ በመሆኑ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ሁኖ አግኝተናል።
ሟች በፍራፍሬ ንግድ ስራ ላይ የነበሩ መሆኑና ሲያገኙ የነበሩት የገቢ መጠን ፍሬ ነገርን ለማጣራትና ማስረጃን ለመመዘን ስልጣን ባላቸው የስር ፍርድ ቤቶች የተረጋገጠ ጉዲይ ነው።
አመልካችም ሆነ ጣልቃ ገብ የነበረው 2ኛ ተጠሪ በዚህ ረገድ 1ኛ ተጠሪ ያቀረቡትን ማስረጃ የሚያፈርስ የመከላከያ ማስረጃ አለማቅረባቸው በስር ፍርድ ቤቶች የተረጋገጠ ጉዲይ ነው። የስር ፍርድ ቤቶች በጉዲቱ ምክንያት በ1ኛ ተጠሪ ላይ የቀረባቸውን ጥቅም በተጠሪ ማስረጃ መረጋገጡን መሰረት በማድረግ ተጠሪዋ የሚገባቸውን የካሳ መጠን በርትዕ በመለየት ወስነዋል።
ካሳ የሚከፈለው ጉዲት መኖሩ ሲረጋገጥ ሲሆን የካሳ አተማመን፣ መጠንና አከፊፈልን በተመለከተ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2090፣ 2091፣ 2092፣ 2095 እና 2102 ድንጋጌዎች የተቀመጠ ሁኖ ከእነዚህ ድንጋጌዎች መገንዘብ የሚቻለውም ካሳው በተቻለ መጠን ከጉዲቱ ጋር መመጣጠን ያለበት መሆኑን ነው። የበታች ፍ/ቤቶች በሚሰጡት የካሣ መጠን ላይ ይግባኝ የላለው መሆኑ በመርህ ደረጃ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 2152 ስር የተመለከተ ሲሆን ይግባኙ በልዩ ሁኔታ የሚፈቀድባቸው ሁኔታዎች ደግሞ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2153 ስር ተገልጸዋል። በመሆኑም ለ1ኛ ተጠሪ ይከፈል የተባለው ካሳ መጠን ብር 25,000.00(ሃያ አምስት ሺህ ብር) የሚነቀፍበት የሕግ ምክንያት አላገኘንም። በአጠቃላይ በጉዲዩ ላይ በተሰጠው ውሳኔ አመልካችን ኃላፉ በማድረግ ረገድ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ሲሆን በካሳ መጠኑ ግን ሉነቀፍ የሚችል ባለመሆኑ ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በበታች ፍርድ ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁጥር 348(1) መሰረት ተሻሽሎል።
2ኛ ተጠሪ ጉዲቱን ያደረሰውን መኪና ሲገለገልበት የነበረ መሆኑ የተረጋገጠ በመሆኑ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2082(1) መሰረት ለጉዲቱ ኃላፉ ነው ብለናል።
ለ1ኛ ተጠሪ ብር 25,000.00 (ሃያ አምስት ሺህ) የጉዲት ካሳ ሉከፍላቸው የሚገባው አመልካች ሳይሆኑ 2ኛ ተጠሪ (ጥበብ ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግል ማህበር) ነው ብለናል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።