No summary available.
ሐምል 29 ቀን 2000 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ዓብደልቃድር መሐመድ ሐጎስ ወልደ መስፍን ዕቁበዮናስ ታፈሰ ይርጋ አመልካች፡- ወ/ሮ አስናቀች ወ/ማርያም - ጠበቃ ኪሩቤል ኃ/ማርያም - ቀረቡ።
ተጠሪ፡- አቶ አለማየሁ አህመድ - ቀረቡ።
ፍ ር ድ፣ ለሰበር አቤቱታው ምክንያት የሆነው ጉዲይ የተጀመረው በፋ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት ነው።
አመልካች በሥር ፍ/ቤት ባቀረቡት ክስ፣ የስር 3ኛ ተከሣሽ የነበሩት የሰ/ቁ 3-ዐ3657 የሆነ መኪና ሲያሽከረክሩ ምናሴ ከበደ የተባለውን ልጃቸውን ገጭተው በመግደላቸው በወንጀል ተከሰው ተፈርድባቸዋል። መኪናውን የሥር 2ኛ ተከሣሽ ገዝተው የባለቤትነት ስሙ በስማቸው ባይተላለፍም በይዞታቸው ሥር ነበር፤ የአሁኑ ተጠሪም የመኪናው የባለቤትነት ስም በስማቸው በመሆኑ የመኪናው ባለቤት ናቸው። በመሆኑም ሶስቱም ተከሣሾች ለደረሰው አደጋ ኃላፉነት ስላለባቸው የጉዲት ካሣ ይክፈለኝ በማለት ጠይቀዋል።
ፍ/ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር ሰምቶ የአሁኑ ተጠሪ መኪናውን ለሥር 2ኛ ተከሣሽ ሸጠው ኃላፉነቱ ለ2ኛ ተከሣሽ የተላለፈ በመሆኑ ሉጠየቁ አይገባም በማለት የሥር 2ኛ እና 3ኛ ተከሣሾች ብቻ ለደረሰው ጉዲት ሃላፉ በመሆናቸው የጉዲት ካሣውን ይክፈለ ሲል ወስኗል። አመልካችም ተጠሪ ሃላፉ ሉሆኑ አይገባም በማለት በተሰጠው ውሣኔ ላይ የይግባኝ ቅሬታ ለፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት አቅርበው ቅሬታቸው ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቷል።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሣኔ ላይ ነው። ይህ የሰበር ችልትም ጉዲት ያደረሰው መኪና የባለቤትነት ስም በተጠሪው ስም በመሆኑ ተጠሪው በሃላፉነት ሉጠየቁ ይገባል ወይስ አይገባም? የሚለውን ለመመርመር አቤቱታው ለሰበር ችልት እንዱቀርብ አድርጓል። ግራ ቀኙም ክርክራቸውን በፁሁፍ አቅርበዋል። ይህ ችልትም መዝገቡን እንደሚከተለው መርምሯል።
በዚህ ጉዲይ መልስ ማግኘት ያለበት ጭብጥ የአንድ መኪና ወይም ባለሞተር ተሽከርካሪ ባለሃብትነት ወደ ላላ ሰው ተላለፈ የሚባለው መቼ ነው? መኪኖች እና ባለሞተር ተሽከርካሪዎች ከውል ውጭ ባለ ግንኙነቶች ለሚያደርሱት ጉዲት በኃላፉነት የሚጠየቀው ማነው? የሚለው ይሆናል። ለተያዘው ጭብጥ መልስ ለመስጠት የተንቀሳቃሽ ንብረት ባለሃብትነት የሚተላለፍበትን መንገድ የሚመለከቱትን የህጉ ድንጋጌዎች መመልከቱ ጠቃሚ ነው። በተለይ በዚህ ጉዲይ ክርክር የተነሣበት ሃብት መኪና በመሆኑ ግዙፍነት ያላቸው ተንቀሳቃሽ ንብረቶች ልዩ ከሆኑ አንዲንድ የሚንቀሣቀሱ ንብረቶችን በሚመለከት የተደነገጉትን የህግ ድንጋጌዎች መመልከቱ ተገቢነት ይኖረዋል።
በፍትሐብሄር ሕግ ቁጥር 1186 ‛ግዙፍነት ያላቸው ተንቀሣቃሽ ንብረቶች ባለሀብትነት ንብረቱን በመግዛት ወይም በልላ አኳኋን ያገኘው ወይም በኑዛዜ የተሰጠው ሰው ንብረቱን እጁ ባደረገ ጊዜ የተላለፈለት ይሆናል“ በማለት ይደነግጋል። በዚህ የህግ ድንጋጌ መሰረትም የአንድ የሚንቀሣቀስ ንብረት ባለሃብት ለመሆን ላላ ተጨማሪ ሁኔታ ማሟላት ሣያስፈልግ ንብረቱን በመግዛት ወይም በልላ አኳኋን ንብረቱን አግኝቶ በእጅ በማድረግ ብቻ ባለሀብት ላሆን የሚቻል መሆኑን መረዲት ይቻላል።
ሆኖም ይህ ድንጋጌ ልዩ የሆኑ አንዲንድ ተንቀሳቃሽ ንብረቶችን ባለሀብትነት ለማስተላለፍ በተለይ የተመለከቱትን የሕግ ድንጋጌዎች የማያጠቃልል መሆኑን በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1186(2) ላይ በግልጽ ተመልክቷል። በዚህ መሰረት የምዝገባና የባለሀብትነት ማስተላለፉያ ስርዐትን በመከተል ብቻ ባለሀብትነት ከሚተላለፍባቸው ግዙፍነት ካላቸው ተንቀሳቃሽ ንብረቶች መካከል መኪና እና ባለሞተር ተሽከርካሪዎች ዋንኞቹ ስለመሆናቸው በመንገድች ላይ ጉዞንና ማመላለሻን ለመቆጣጠርና ለመወሰን የወጣውን አዋጅ ቁጥር 256/196ዐ ተከትል የወጣውን እና የተለያዩ ክፍልቹ በየጊዜው የተሻሻለትንና እንደአግባብነቱ ተፈጻሚነት ያለውን የሕግ ክፍል ማስታወቂያ ቁጥር 36ዐ/1961ን መመርመሩ አስፈላጊ ነው።
በቅድሚያ የፍጥነት ወሰኑ በሰዓት ከ2ዐ ኪል ሜትር የማይበልጥ ልዩ ተሽከርካሪ መሣሪያዎች በስተቀር ማናቸውንም ባለሞተር ተሽከርካሪ የማስመዝገብ ግዳታ በአስገዲጅነት በሕጉ የተጣለ መሆኑን አዋጅ ቁጥር 256/196ዐ አንቀጽ 6 ‛ን“ እንደአግባብነቱ ካሻሻለው እና የሚኒስቴሩን መ/ቤት በአዱስ ካቋቋመው አዋጅ ቁጥር 468/1997 አንቀጽ 21 መረዲት ይቻላል።
ባለሞተር ተሽከርካሪን ከማስመዝገብ ግዳታ ጋር ተያይዞ ማንም ሰው በደንብ ቁጥር 36ዐ/1961 አንቀጽ 6 መሰረት የባለንብረትነት መታወቂያ ደብተር አያስፈልጋቸውም ተብለው ከተመለከቱት ተሽከርካሪዎች ውጭ ያለ ተሽከርካሪዎችን ለአገልግልት ከተላለፈበት ጊዜ ጀምሮ በ3ዐ ቀናት ውስጥ የባለንብረትነት መታወቂያ ደብተር እንዱሰጠው ለአዋጅ አስፈጻሚ መ/ቤት ማመልከቻውን ማቅረብ የሚገባው መሆኑን በደንቡ ቁጥር 7 ላይ ተመልክቷል። በማንኛውም መንገድ ተሽከርካሪው ለአገልግልት የተላለፈለት ሰው በስሙ የባለንብረትነት መታወቂያ ደብተር እንዱሰጠው ከሚያቀርበው ማመልከቻ ጋርም የንብረቱን ባለሀብትነት ያገኘበትን አግባብ የሚያረጋግጡ ሰነድችን ማቅረብ የሚገባው መሆኑ ተመልክቷል። በዚህ መሰረት የተሽከርካሪው ባለሀብትነት የተገኘው ከቀድሞው ባለቤት ላይ ከሆነ የቀድሞውን ባለቤት የባለንብረትነት መታወቂያ ደብተር፣ ወይም ማመልከቻው የሚመለከተው ከዚህ በፉት በውጭ አገር የተመዘገበን ተሽከርካሪ እንደሆነ በተባለው አገር የተሰጠ የባለንብረት መታወቂያ ሰነድ ወይም የተሽከርካሪውን ባለንብረትነት ለማወቅ ለሚኒስቴሩ መ/ቤት አስፈላጊ ናቸው የሚባለትን ማናቸውንም ሰነድችና መረጃዎችን አያይዞ ማቅረብ የሚገባ መሆኑን በደንቡ ቁጥር 7 (1) እና (3) ላይ ተደንግጓል። ይህ የደንቡ ክፍል በአዱስ የተገዙትን፣ በውጭ አገር አገልግልት ሰጥተው ወደ አገር ውስጥ የሚገቡትን እና በአገር ውስጥ ያገለገለ ተሽከርካሪዎች ከአንደ ወደ ላላው በተለያየ ምክንያት ሲተላለፈ ተሽከርካሪው ለአገልግልት የተላለፈለት ሰው የባለንብረትነት መታወቂያ ደብተር እንዱሰጠው ከማመልከቻው ጋር በማያያዝ ሉያቀርብ የሚገባቸው ሰነድች የትኞቹ እንደሆኑ የሚያመለክቱ ናቸው። ከዚህ በተጨማሪ በአገር ውስጥ የሰራ ተሽከርካሪ ለአገልግልት ከአንደ ወደ ላላው ሲተላለፍ የተላለፈለት ሰው የአስተላለፈውን የባለንብረትነት መታወቂያ ደብተር እንዱረከብና ሁለቱ ወገኖች በደብተሩ ውስጥ የሚገኘውን የባለንብረትነት መታወቂያ ገጽ በሚገባ ሞልተው እና ፈርመው ማቅረብ የሚገባቸው መሆኑን በደንቡ ቁጥር 8 እና 11(1) ላይ ተመልክቷል። በመጨረሻም የሚኒስቴሩ መ/ቤት ማመልከቻው እውነተኛና ትክክለኛ መሆኑን ካረጋገጠ ማመልከቻ አቅራቢው የተሸከርካሪው ባለቤት ነው እንዱባል አንድ የባለንብረት መታወቂያ ደብተር የሚሰጠው መሆኑን በቁጥር 9 ላይ ተመልክቷል።
ከፍ ብለው ከተመለከቱት የደንቡ ድንጋጌዎች መረዲት የሚቻለው ነገር ቢኖር፣ የፍጥነት ወሰናቸው በደንቡ ላይ የተመለከቱት ተሽከርካሪዎች ከአንደ ወደ ላላ በሽያጭ፣በስጦታ ወይም በላልች መንገድች ተላልፈው ሲገኙ እንደ አብዛኛዎቹ ግዙፍነት ያላቸው ተንቀሳቃሽ ንብረቶች ዋጋ ሰጥቶ ንብረቱን በእጅ በማድረግ ብቻ የባለሀብትነት መብት የማይተላለፍ መሆኑን፤ ይልቁንም ልዩ የሆኑትን እነዚህን ግዙፍነት ያላቸውን ተንቀሳቃሽ ንብረቶች ባለሀብት ሆኖ ለመገኘት ሻጭ እና ገዥ ወይም ስጦታ አድራጊና ስጦታ ተቀባይ ከሚያደርጉዋቸው የተሳኩ የውል ስምምነቶች ባሻገር ከፍ ብለው በደንቡ በተመለከተው እንኳን የተሽከርካሪውን ባለሀብትነት ከአስተላላፉው ወደ ተላለፈለት ሰው የሚዘዋወርበት ስርዓት በሚኒስቴሩ መ/ቤት መጠናቀቅ የግድ መሆኑን ነው። ላላው ቀርቶ ባለንብረትነቱ የታወቀለት ሰው ተሽከርካሪው ከጥቅም ውጭ ሆኖ በወላለቀና ጨርሶ በወደመ ጊዜ እንኳን ይህንኑ ሁኔታ በ3ዐ ቀናት ውስጥ ለሚኒስቴሩ መ/ቤት አሳውቆ በስሙ የተመዘገበው የባለቤትነት ደብተር እንዱሰረዝና ከመዝገብ እንዱፊቅ ካላስደረገ በቀር ባለሃብቱ ስሙ በመታወቂያ ደብተሩ ላይ የተመዘገበው ሰው ሆኖ እንደሚቀጥል ከደንቡ ቁጥር 42 እስከ 45 እና በቁጥር 11(2) የተመለከቱትን ድንጋጌዎች በመመርመር መረዲት ይቻላል።
ባለሞተር ተሽከርካሪዎች በሰው ልጆች ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት ውስጥ የሚኖራቸው ጠቀሜታ ከፍተኛ የመሆኑን ያህል እነዚህ ማሽኖችና ተሳቢዎች በጏዲናዎች ላይ በሚሽከረከሩበት ጊዜ በሰውና በንብረት ላይ ሉያደርሱ የሚችለት የጉዲት መጠን የዛኑ ያህል ከፍተኛ በመሆኑ እነዚህ ልዩ ተንቀሳቃሽ ንብረቶች ወደ አገር ውስጥ ሲገቡም ሆነ በቴክኒክ ረገድ ብቃት ኖራቸው በጏዲናዎች ላይ ሲሽከረከሩ፤ እንዱሁም በተለያዩ ሁኔታዎች ንብረቶቹ ከአንደ ወደ ላላው ሲተላለፈም ሆነ ከአገልግልት ውጭ ሆነው ጨርሶ ሲወድሙ ልዩ የምዝገባና የቁጥጥር ሥርዐት እንዱደረግባቸው ማድረጉ ማህበራዊ ደህንነትን ከመጠበቅ አኳያ ጠቀሜታው ከፍተኛ በመሆኑ ኢትዮጵያን ጨምሮ በርካታ አገሮች ባለሞተር ተሽከርካሪዎች እና ተሳቢዎቻቸውን ከሞላ ጏደል ተመሣሣይነት ባላቸው ልዩ ደንቦች እንዱመሩ የሚያደርጉ መሆኑን የተለያዩ አገሮችን ልምድ በመዲሰስ ለመረዲት ተችሎል።
የመኪና እና ባለሞተር ተሽከርካሪ ባለሀብትነት የሚገኘው ከፍ ብለን በገለጽነው ሥርዐት ብቻ መሆኑ ከታወቀ በመቀጠል ሉነሳ የሚገባው ጭብጥ የባለሀብትነት ዝውውር ሥርዐቱ ደንቡ በሚጠይቀው አኳኋን ሳይከናወን አንድ መኪና ወይም ባለሞተር ተሽከርካሪ ከሻጭ ወደ ገዥ ወይም ከስጦታ አድራጊ ወደ ስጦታ ተቀባይ ይዞታው ተላልፍ በነበረበት ጊዜ መኪናው ወይም ባለሞተር ተሽከርካሪው በሰውም ሆነ በንብረት ላይ ጉዲት አድርሶ ቢገኝ ኃላፉው ንብረቱ በስሙ የሚገኘው ሰው ነው? ወይስ ንብረቱን በእጁ አድርጎ ሲገለገልበት የነበረው ሰው? የሚለው ይሆናል። እነዚህን ጭብጦች ለመመለስ እንድንችል መዝገቡን አሁን ከተያዘው ጉዲይ ጋር መመርመሩ ተገቢነት ይኖረዋል።
ወደያዝነው ጉዲይ ስንመለስ የአሁኑ አመልካች ክሳቸውን ሲመሰርቱ የስር 3ተኛ ተከሳሽ የነበረው ሾፋር የሰ/ቁ. 3-03657 የሆነውን መኪና እያሽከረከሩ ጉዲት በማድረሳቸው ለደረሰው ጉዲት ኃላፉ እንዱባለ፤ የስር 2ተኛ ተከሳሽ ጉዲት ያደረሰውን መኪና ገዝተው በይዞታቸው ሥር እያለ ጉዲት በማድረሱ 2ኛ ተከሳሽም ኃላፉ እንዱባለ፣ የመኪናው የባለቤትነት ስም ደግሞ በስር 1ኛ ተከሳሽ በነበሩት በአሁኑ ተጠሪ ስም በመሆኑ ተጠሪው የመኪናው ባለቤት በመሆናቸው ለደረሰው ጉዲት ኃላፉ እንዱሆኑ ጠይቀዋል። ከመዝገቡም የስር 3ተኛ ተከሳሽ በቸልተኝነት ሰው መግደል ወንጀል ጥፊተኛ የተባለ መሆኑን፣ ጉዲት ያደረሰውን መኪና የሥር 2ተኛ ተከሳሽ ገዝተው የተረከቡ መሆኑን ነገር ግን የባለንብረትነት መታወቂያ ደብተሩ በአሁኑ ተጠሪ ስም መሆኑን መረዲት ተችሎል።
በዚህ መሰረት ለጭብጦቹ ምላሽ ለማግኘት በቅድሚያ በፍትሐብሕር ሕጉ ውስጥ የሚገኙትን ከውል ውጭ ስለሚደርስ ኃላፉነት የተደነገኑትን ድንጋጌዎች መፈተሹ አግባብነት ይኖረዋል።
በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2ዐ81(1) መሰረት የአንድ መኪና ወይም ባለሞተር ተሽከርካሪ ባለቤት የሆነ ሰው ንብረቱ ተሰርቆ በነበረበት ጊዜ ለደረሰው አደጋ ከተጠያቂነት ነጻ ከሚሆን በስተቀር መኪናውን ወይም ባለሞተር ተሽከርካሪውን ለመንዲት ባልተፈቀደለት ሰው እንኳን ተነድቶ ጉዲት አድርሶ ቢገኝ የመኪናው ወይም የባለሞተር ተሽከርካሪው ባለቤት ለደረሰው ጉዲት ኃላፉ እንደሚሆን ተመልክቷል። የአንድ መኪና ወይም ባለሞተር ተሽከርካሪ ባለቤት ከውል ውጭ በሚደርሱ ኃላፉነቶች ውስጥ በፍትሐብሕር ሕጉ አጥፉ ሳይሆን አላፉ ከሚባለት ምድቦች ውስጥ የሚመደብ በመሆኑ መኪናው ወይም ባለሞተር ተሽከርካሪው ላደረሰው ጉዲት ባለቤቱ ኃላፉ ነው። ይህ ማለት ግን ስሙ በባለቤትነት ያልተመዘገበ መኪናውን ወይም ባለሞተር ተሽከርካሪውን ለግል ጥቅሙ ሲገለገልበትና ሲጠቀምበት የነበረው ሰው መኪናው ወይም ባለሞተር ተሽከርካሪው በእጁ በነበረበት ጊዜ ለደረሰው ጉዲት ከተጠያቂነት ነጻ ይሆናል ማለት አለመሆኑን ከፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2ዐ82(1) መረዲት ይቻላል። በዚህ መነሻነት በአንድ መኪና ወይም ባለሞተር ተሽከርካሪ ጉዲት የደረሰበት ሰው የመኪናውን ወይም የባለሞተር ተሽከርካሪውን ባለቤት ወይም በንብረቱ ተገልጋይ የነበረውን ማንኛውም ሰው በአንድነትም ሆነ በተናጥል ከሶ ለደረሰበት ጉዲት ካሣ ለመጠየቅ በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2ዐ81(1) እና 2ዐ82 (1) መሰረት መብት ያለውን ያህል የመኪናው ወይም የባለሞተር ተሽከርካሪው ባለቤት ተብል የሚታወቀው ሰው የንብረቱ ባለቤት በመሆኑ ብቻ ተበዲይን ተገድ ከካሰ በኋላ መኪናውን በእጁ አድርጏ ሲገለገል የነበረውን ማንኛውም ሰው የከፈለውን ገንዘብ እንዱከፍለው የመጠየቅ መብት ያለው መሆኑ በፍትሐብሕር ሕግ ቁ. 2ዐ83 (1) ተመልክቷል።
ከዚህ ድንጋጌ መረዲት የሚቻለው ነገር ደንቡ የሚጠይቀውን የመኪና ወይም የባለሞተር ተሽከርካሪ የባለቤትነትን የማስተላለፍ ሥርዐት ባልተከናወነበት ጊዜ ሁለ በመኪናው ወይም በባለሞተር ተሽከርካሪው ለሚደርስ አደጋ ስሙ በባለቤትነት የሚታወቀው ሰው የንብረቱ ባለቤት በመሆኑ ብቻ የሚጠየቅ መሆኑን እና ንብረቱን በማናቸውም መንገድ በእጁ አድርጏ ለግል ጥቅሙ ሲገለገልበት የነበረ ሰው ለደረሰው ጉዲት ምንግዜም የመጨረሻው ኃላፉነት የማይቀርለት መሆኑን ነው ። ከዚህ ላላ ስለባለቤቱ ወይም ስለላላ ሰው ሆኖ በአንድ መኪና ወይም ባለሞተር ተሽከርካሪ ላይ ይሰራ የነበረ ታዛዥ መኪናው ወይም ባለሞተር ተሽከርካሪው ጉዲት አድርሶ የተገኘው በራሱ ጥፊት ምክንያት ካልሆነ በቀር እንደ ባለቤቱ ወይም እንደ ንብረቱ ተገልጋይ ሰው ለደረሰው ጉዲት ኃላፉ እንደማይሆን የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2082(2) ይደነግጋል። በዚህ ጉዲይ ግን የሥር 3ተኛ ተከሳሽ የነበረው ሾፋር በወንጀል ክስ ቀርቦበት ጥፊተኛ ሆኖ በመገኘቱ በፍትሐብሄር ሕግ ቁ.
2082(2) መሰረት ለጉዲቱ ኃላፉ ነው መባለ ተገቢ ነው።
ባጠቃላይ የአሁኑ ተጠሪ ጉዲት ያደረሰውን ተሽከርካሪ በሽያጭ ለስር 2ተኛ ተከሳሽ ለነበሩት ሰው በማስተላለፊቸው ብቻ በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2324(1) በተመለከተው አኳኋን የጉዲት ኃላፉነቱ ሙለ በሙለ ወደ ገዢው ብቻ ተላልፎል ለማለት አይቻልም። መኪና ወይም ባለሞተር ተሸከርካሪ ልዩ የምዝገባና የባለሃብትነት ስም ዝውውር የሚሻ ንብረት በመሆኑ እንደአብዛኛዎቹ ግዙፍነት ያላቸው ተንቀሳቃሽ ንብረቶች ዋጋ ሰጥቶ ንብረቱን በእጅ በማድረግ ብቻ ባለሃብትነት የሚተላለፍ አይደለም። በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2267(2) በተደነገገው መሰረት አንዲንድ ግዙፍነት ያላቸው ተንቀሳቃሽ ንብረቶችን የሚመለከቱ ልዩ ሕጎች ውስጥ የሚገኙ ድንጋጌዎች በፍትሐብሕር ሕጉ ውስጥ ስለሽያጭ በተጻፈ ደንቦች አይነኩም በማለት የተደነገገውም የህንኑ የሚያጠናክር ነው።
በመሆኑም የተሸከርካሪው የባለሃብትነት ስም ዝውውር ደንቡ በሚጠይቀው አግባብ ባልተጠናቀቀበት ሁኔታ የሥር ፍርድ ቤቶች የአሁኑ ተጠሪ ተሸከርካሪውን ለሥር 2ተኛ ተከሳሽ በሽያጭ አስተላልፎል በሚል ብቻ ተጠሪ ኃላፉ ሉሆኑ አይገባም ብለው መወሰናቸው መሰረታዊ የሕግ ሥህተት ሆኖ አግኝተነዋል።
ው ሣ ኔ
የመኪናው ባለኃብትነት በስሙ የሚታወቀው በስር 1ኛ ተከሳሽ የነበረው የአሁኑ ተጠሪ በንብረቱ አማካኝነት ለደረሰው የሞት አደጋ ንብረቱን ለግል ጥቅሙ ሲገለገልበት ከነበረው ከሥር 2ተኛ ተከሳሽ እና ስለ 2ተኛ ተከሳሽ ሆኖ በመኪናው ይሰራበት ከነበረው እና በጥፊቱ ኃላፉ ከተባለው ከሥር 3ኛ ተከሳሽ ጋር በአንድነት ኃላፉ ናቸው ብለናል።
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የአሁኑ አመልካች በልጃቸው ሞት ምክንያት እንዱከፈላቸው የተወሰነውን ብር 71‚887.50 /ሰባ አንድ ሺህ ስምንት መቶ ሰማኒያ ሰባት ብር ከሃምሳ ሳንቲም/ ከስር 2ኛ እና 3ኛ ተከሳሾች በተጨማሪ የአሁኑ ተጠሪ በአንድነትና በነጠላ ለአመልካች እንዱከፍለ ተወስኗል። ተጠሪ የከፈለትን የጉዲት ካሣ ከሥር 2ኛ እና 3ኛ ተከሳሾች ለመጠየቅ ይችላለ።
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በ5/8/97 በመ/ቁ ዐ3696 በሰጠው ፍርድ እና የፋ/ከ/ፍ/ቤት የካቲት 8 ቀን 1998 በቁጥር 4ዐ41ዐ በሰጠው ትዕዛዝ ላይ የአሁኑ ተጠሪ ከተጠያቂነት ነጻ ናቸው በማለት የሰጡት የውሳኔ ክፍል ብቻ በፍ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 348(1) መሰረት ተሽሯል።
የዚህን ፍ/ቤት ወጭና ኪሳራ ግራ ቀኙ ይቻቻለ።
መዝገቡ ያለቀለት ስለሆነ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.