No summary available.
ሐምል 25 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ሒጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- አቶ በቀለ ወልቻም - ጠበቃ አቶ አለሙ ገ/ህይወት ተጠሪ፡- አቶ ጥበቡ ጦና - ጠበቃ አቶ ታደሰ ሲሳይ - ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የሀዋሣ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የደቡብ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልትና የሰበር ችልት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት ያቀረቡትን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው። ክርክሩ በመጀመሪያ የታየው በሀዋሣ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው።
በስር ፍርድ ቤት ተጠሪ ከሣሽ አመልካች ተከሣሽ በመሆን ተከራክረዋል። የክርክሩ መነሻ ተጠሪ ንብረትነቱ የአመልካች በሆነና የሰላዲ ቁጥሩ 3-03593 /ደ.ህ/ በሆነ የህዝብ ማመላለሻ መኪና በመሳፈር ነሐሴ 6 ቀን 2001 ዓ.ም እየተጓዘ እያለ የአመልካችን መኪና ያሽከረክር የነበረው አቶ ወንድወሰን ሽታ ከተፈቀደለት የፍጥነት ወሰን በማለፍ በማሽከርከሩ መኪናው ተገልብጦ የቀኝ እግሬ ተቆርጧል። የተከሣሽ /አመልካች/ ሹፋር የነበረው አቶ ወንድወሰን በሀዋሣ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በወንጀል ተከስሶ ጥፊተኛ ሆኖ በመገኘቱ በሶስት ወር እስራት እንዱቀጣ ተወስኖበታል።
የደረሰበኝ ጉዲት 60% /ስልሳ ፏርሰንት/ የመሥራት አቅሜ እንደቀነሰ በጥቁር አንበሳ የሀኪሞች ቦርድ ተረጋግጧል። አደጋው ከመድረሱ በፉት ብር 658 /ስድስት መቶ ሃምሣ ስምንት ብር/ በየወሩ ተቀጥሬ ስሰራበት ከነበረው ሚዛን ተፈሪ ሆስፑታል ይከፈለኝ ነበር። በአደጋው ምክንያት ለህክምና ያወጣሁትን ወጭና ላልች ወጭዎች ተከሣሽ መተካት ያለበት ሲሆን የተቋረጠ ጥቅምና ገቢዬን የመክፈል ሀላፉነት ያለበት ስለሆነ ብር 348,247.22 /ሶስት መቶ አርባ ስምንት ሺህ ሁለት መቶ አርባ ሰባት ብር ከሀያ ሁለት ሣንቲም/ ካሣ እንዱከፍል ይወሰንልኝ በማለት ክስ አቅርቧል።
አመልካች በተከሣሽነት ቀርቦ ከሣሽ የሰላሣ አምስት ዓመት ደመወዝ ያለምንም ቅንስናሽ እንዱከፈለው ያቀረበው ጥያቄ ተገቢ አይደለም። የደመወዝ ጭማሪ አገኝ ነበር በማለትና የጡረታ ገንዘብ በማለት ያቀረበው ጥያቄም የህግ መሰረት የለውም። እስከ 8ዐ ዓመት እኖራለሁ ብል አስልቶ የጠየቀው የካሣ ገንዘብ ተገቢ አይደለም። የህክምና ማስረጃ የአካል ጉዲት እንደደረሰበት እንጅ 6ዐ% የከሣሽ የመስራት አቅም እንደቀነሰ አያረጋግጥም። የስር ፍርድ ቤት በከሣሽ ላይ ለደረሰው ጉዲት ተከሣሹ ሀላፉ ነው ወይስ አይደለም? ተከሣሽ ጉዲቱን የመካስ ሀላፉነት አለ ቢባል ሉከፈል የሚገባው ካሣ ምን ያህል ነው? የሚለትን ጭብጦች መስርቷል። የመጀመሪያውን ጭብጥ በተመለከተ ተከሣሽ /አመልካች/ በከሣሽ ላይ ለደረሰው ጉዲት ሀላፉነት የለብኝም የሚል ክርክር አላቀረቡም። ተከሣሽ ለጉዲቱ ሀላፉ የሚሆነው በንግድ ህግ ቁጥር 599 በተደነገገው መሰረት መሆን አለበት በማለት ወስኗል። የካሣውን መጠን በተመለከተ ከሣሽ አደጋው ሲደርስ እድሜው ሰላሣ ዓመቱ ነው። ወደፉት ጡረታ እስኪወጣ ሰላሣ ዓመት ይቀረዋል። የከሣሽ ደመወዝ በወር ብር 658 ሲሆን የገቢ ግብር ብር 51.20 ሲቀነስለት የተጠሪ ገቢ 606.80 ነው። የዚህ ስልሣ ፏርሰንት ገቢ እንደቀረበት ተደርጏ የካሣው መጠን መሰላት ይገባዋል በማለት ተከሣሽ /አመልካች/ ብር 131,068.80 /አንድ መቶ ሰላሣ አንድ ሺ ስልሣ ስምንት ብር ከሰማኒያ ሣንቲም/ የተቋረጠ ጥቅም ስለሆነ ሉከፍል ይገባል። ከዚህ በተጨማሪ ለህክምናና ላልች ወጭዎች የወጣ ብር 7604.34 /ሰባት ሺ ስድስት መቶ አራት ብር ከሰላሣ አራት ሣንቲም/ እና የህሉና ጉዲት ብር 1000 /አንድ ሺ ብር/ ተከሣሽ /አመልካች/ ለከሣሽ /ተጠሪ/ ይክፈል በማለት ውሣኔ ሰጥቷል።
አመልካች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቅርበዋል።
የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ የስር ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ አጽንቶታል። አመልካች የሰበር አቤቱታ ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት አቅርበው የሰበር ችልቱ የስር ፍርድ ቤት እና ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ አጽንቷል።
አመልካች ሚያዝያ 2ዐ ቀን 2003 ዓ.ም በተጻፈ የሰበር አቤቱታ ተጠሪ ጉዲት የደረሰበት መኪናው በድንገት በመገልበጡ ነው። ስለሆነም አመልካች አጓዥ በመሆኑ ለተጠሪ ልከፍለው የሚገባው የካሣ መጠን የንግድ ህግ ቁጥር 597ን መሰረት በማድረግ ሉወሰን ሲገባው የንግድ ህግ ቁጥር 599 መሰረት ተደርጏ መወሰኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት አለበት። ተጠሪ የሰላሣ ዓመት ገቢ እንደተቋረጠበት ተደርጏ ካሣው መሰላቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው። ተጠሪ ጉዲት የደረሰበት እግሩ ላይ በመሆኑ ላላ ስራ ሰርቶ ገቢ ማግኘቱን የሚከለክለው አይደለም። ስለዚህ ጉዲዩ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት አመልክቷል።
ተጠሪ ሰኔ 3 ቀን 2003 ዓ.ም በተጻፈ መልስ በንግድ ህግ አንቀጽ 597 የተደነገገው የካሣ መጠን አጓዙ በተጓዡ ላይ ለሚደርሰው ጉዲት እስከ ምን ድረስ ካሣ የመክፈል ግዳታ እንዲለበት የሚደነግግ መሰረታዊ መርህ ሲሆን የንግድ ህግ ቁጥር 599 በመርህ ከተደነገገው በላይ አጓዡ ለተጓዡ ካሣ እንዱከፍል የሚገድቡትን ልዩ ሁኔታን የሚደነግግ ድንጋጌ ነው። በያዝነው ጉዲይ የአመልካችን መኪና ሲያሽከረክር የነበረው የአመልካች ሰራተኛ ከተፈቀደለት በላይ በፍጥነት በማሽከርከሩ አደጋው የደረሰ መሆኑ ተረጋግጦ በወንጀል ጥፊተኛ ተብል በወንጀል የተቀጣ በመሆኑ የስር ፍርድ ቤት የንግድ ህግ አንቀጽ 599 መሰረት በማድረግ መወሰኑ ተገቢ ነው። የካሣውም መጠን ቢሆን በማስረጃ በማጣራት የተሰጠ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ የህግ መሰረት የለውም የሚል መልስ አቅርቧል። አመልካች የመልስ መልስ አቅርቧል።
አመልካች ሰኔ 27 ቀን 2003 ዓ.ም የተጻፈ የመልስ መልስ አቅርበዋል።
ከስር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የቀረበው ክርክር ከላይ የተገለጸው ሲሆን እኛም የስር ፍርድ ቤትና የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልትና የሰበር ችልት አመልካች ለተጠሪ የሚከፍለውን የካሣ መጠን የንግድ ህግ አንቀጽ 599 መሰረት በማድረግ ማስላታቸው ተገቢ ነው ወይስ አይደለም? የሚለውን ጭብጥ በመያዝ ጉዲዩን መርምረናል። ከላይ የተያዘውን ጭብጥ ለመወሰን ለጉዲዩ አግባብነት ያላቸው የህግ ድንጋጌዎችን ይዘትና ትርጉም እንደዚሁም ድንጋጌዎቹ ተፈጻሚ የሚሆኑበትን ሁኔታ መመርመር ያስፈልጋል።
የንግድ ህግ አንቀጽ 595 አጓዡ መንገደኛው በጉዞ ጊዜ በሚሣፈርበትና በሚወርድበት ጊዜ በአደጋ ምክንያት ለሚደርስበት መቁሰል ወይም የአካል መጉደል ወይም ህይወት ማለፍ አጓዡ በሀላፉነት የሚጠየቅ መሆኑን በመሰረታዊ መርህነት የሚደነግግ ሲሆን ፣ አጓዡ ከሀላፉነት ነጻ የሚሆንባቸዉን ልዩ ሁኔታዎች የሀላፉነቱን መጠንና አጓዡ በህግ ከተደነገገው መጠን በላይ በሀላፉነት ሉጠይቅ የሚችልባቸውን ሁኔታዎች የሚደነግጉ ልዩ ድንጋጌዎች በንግድ ህጉ ተካተዋል።
ሆኖም በንግድ ህግ አንቀጽ 597 የተደነገገው የሀላፉነት መጠን አጓዡ በንግድ ህግ አንቀጽ 596 የተደነገጉትና ከሀላፉነት ነጻ የሚያደርጉት ሁኔታዎች መኖራቸውን ለማስረዲት ባልቻለበት ሁኔታና መንገደኛው በንግድ ህግ አንቀጽ 599 በሚደነግገው መሰረት አጓዡ አደጋ ሉያደርስ የሚችል መሆኑን እያወቀ በፈጸመው ተግባር ወይም ጉድለት ምክንያት አደጋው የደረሰ መሆኑን ለማስረዲት ባልቻለበት ጊዜ ተፈጻሚ የሚሆን ድንጋጌ ነው። በያዝነው ጉዲይ የአመልካች ንብረት የሆነውን የትራንስፕርት መኪና ያሽከረክር የነበረው የአመልካች ሰራተኛ የመኪናው ሹፋር ከተፈቀደለት ፍጥነት በላይ በማሽከርከሩ መኪናው የተገለበጠና ተጠሪ ላይ ጉዲት የደረሰ መሆኑ የአመልካችን መኪና ያሽከረክር የነበረው ሹፋር በሀዋሣ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በወንጀል መዝገብ በወንጀል ተከስሶ የካቲት 1ዐ ቀን 2002 ዓ.ም በፍርድ ጥፊተኛ መሆኑ ተረጋግጦ በሶስት ወር እስራት የተቀጣ መሆኑን በማረጋገጥ የስር ፍርድ ቤት ውሣኔ ተሰጥቷል። በንግድ ህግ ቁጥር 588 በሚደነግገው መሰረት የመንገደኛውን መልካም ይዞታ ደህንነትና ምቾች በመጠበቅ መንገደኛውን የማጓጓዝ ሀላፉነቱን አጓዡ የሚወጣው አጓዡ ራሱ የመኪናው አሽከርካሪ ከሆነ አጓዡ፣ ረዲቱና ላልች ሰራተኞች አማካኝነት ሲሆን አጓዡ የመኪናው አሽከርካሪ ካልሆነ መኪናውን በሀላፉነት ይዞ በሚያሽከረክረው ሹፋር ፣ ረዲቱና ላልች ሰራተኞች በኩል መሆኑን ለመገንዘብ ይቻላል።
በተመሣሣይ ሁኔታ በንግድ ህግ ቁጥር 599 በተደነገገው መሰረት አደጋ ሉያደርስ ወይም ሉፈጥር የሚችል መሆኑን እያወቀ አጓዡ በፈጸመው ተግባር ወይም ጉድለት ምክንያት አደጋው የደረሰ መሆኑን መንገደኛው የሚያስረዲው አጓዡ የመኪናው አሽከርካሪ ከሆነ እሱ ራሱ መኪናውን ሲያሽከረክር ወይም ረዲቱና ላልች ሰራተኞች በፈጸሙት ተግባር ወይም ጉድለት ምክንያት አደጋው የደረሰ መሆኑን በማስረዲት ነው። አጓዡ መንገደኛው የተሣፈረበትን መኪና የማያሽከረክር በሆነ ጊዜ መኪናውን አጓዡ በሀላፉነት ተረክቦ ሲያሽከረክር የነበረው ሰው ፣ ረዲቱ ወይም ላላ የአጓዡ ሰራተኛ አደጋ ሉያደርስ ወይም ሉፈጥር የሚችል መሆኑን እያወቀ በፈጸመው ተግባር ወይም ጉድለት ምክንያት አደጋው የደረሰ መሆኑን በማስረዲት ነው።
በንግድ ህግ አንቀጽ 599 ‛አጓዡ የተፈጸመው ተግባር ወይም ጉድለት“ የሚለው ሀረግ አጓዡ በግለ የፈጸመውን ተግባር ወይም ጉድለት የሚመለከት ሣይሆን የአጓዡ ሰራተኞች አደጋ ሉያደርስ ወይም ሉፈጠር እንደሚችል እያወቁ የፈጸሙትን ተግባር ወይም ጉድለት የሚያካትት ነው። የንግድ ህግ አንቀጽ 599 ድንጋጌ ይዘት ህግ አውጭው ከውል ውጭ ስለሚደርስ ሀላፉነት ‛አንድ ሰራተኛ ስራውን በሚሰራበት ጊዜ ሀላፉነትን የሚያስከትል ጥፊት የሰራ እንደሆነ በፍታብሓር በሀላፉነት የሚጠየቀው አሰሪው ነው“ በማለት በፍታብሓር ህግ ቁጥር 2130 የደነገገውን መሰረታዊ መርህ በሚያካትት ሁኔታ መተርጏምና የህጉ ድንጋጌ ተግባራዊ እንዱሆን ካልተተረጏመ የንግድ ህግ አንቀጽ 599 ህግ አውጭው የሰጠውን ግብ የሚያሣካ አይሆንም።
ከዚህ አንጻር ስንመለከተው አደጋው የደረሰው የአመልካችን መኪና ሲያሽከረክር የነበረው ሹፋር ከተፈቀደለት ፍጥነት በላይ ማሽከርከሩ አደጋ ሉያደርስ ወይም ሉፈጥር የሚችል መሆኑ በቂ የሙያ ዕውቀትና ክህልት እያለው ከተፈቀደለት ፍጥነት በላይ በማሽከርከሩ መሆኑን ተጠሪ ስላስረዲ የበታች ፍርድ ቤቶች የንግድ ህግ አንቀጽ 599 ለጉዲዩ ተፈጻሚ ማድረጋቸው ተገቢ ሆኖ አግኝተነዋል።
በተጠሪ አካል ላይ ጉድለት ያደረሰው አደጋ የተከሰተው የአመልካች ሰራተኛ የሆነውና መኪናውን ያሽከረክረው የነበረው ሹፋር የትራፉክ ደንብና ስርዓት በመጣስ መኪናውን ከተፈቀደለት ፍጥነት በላይ በማሽከርከር በፈጸመው ተግባር መኪናው የተገለበጠ መሆኑን ተጠሪ በበቂ ማስረጃ እንዲስረዲ ፍሬ ጉዲይ የማጣራትና ማስረጃ የመመዘን ስልጣን ባላቸው የስር ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚው ችልት ተረጋግጧል። ስለሆነም አመልካች በተጠሪ ላይ ለደረሰው ጉዲት በንግድ ህግ አንቀጽ 597 ከተደነገገው በላይ ካሣ የመክፈል ሀላፉነት የለብኝም በማለት ያቀረቡት ክርክር የህግ መሰረት ያለው ሆኖ አላገኘነውም። የበታች ፍርድ ቤቶች አመልካች በንግድ ህግ አንቀጽ 599 መሰረት በንግድ ህግ አንቀጽ 597 ከተደነገገው የሀላፉነት መጠን በላይ ለተጠሪ ካሣ የመክፈል ሀላፉነት አለበት በማለት የሰጡት የህግ ትርጉምና ውሣኔ ተገቢና የህግ ስህተት ያላለበት በመሆኑ በዚህ በኩል አመልካች ያቀረቡትን የሰበር አቤቱታ አልተቀበልነውም።
በግንድ ህግ ቁጥር 599 ድንጋጌ መሰረት ለመንገደኛው ካሣ የመክፈል ሀላፉነት ያለበት አጓዡ ለመንገደኛው የሚከፍለው የካሣ መጠን ለመወሰን በፍታብሓር ህግ ቁጥር 2091 እና በፍታብሓር ህግ ቁጥር 2092 የተደነገጉት የካሣ አከፊፈል መርሆች አግባብነት ያላቸው ናቸዉ።
ከዚህ አንጻር ስንመለከተው የስር ፍርድ ቤት አመልካች ለተጠሪ ሉከፍል የሚገባውን የካሣ መጠን የወሰነው ከላይ የጠቀስናቸውን መሰረታዊ የካሣ አከፊፈል ድንጋጌዎች መሰረት በማድረግ ሆኖ አግኝተነዋል። የስር ፍርድ ቤት አመልካች ተጠሪ በአደጋው ምክንያት የደረሰበትን ጉዲት ለመታከም ያወጣውን ወጭና ላልች አስፈላጊ ወጭዎች በማስረጃ በማረጋገጥ ለተጠሪ እንዱከፈል የንግድ ህግ አንቀጽ 599ን ከፍታብሓር ህግ ቁጥር 2091 ጋር አጣምሮ በመተርጏም የወሰነ መሆኑን ተገንዝበናል። ከዚህ በተጨማሪ የስር ፍርድ ቤት አመልካች አደጋው ሲደርስበት ያገኝ ከነበረው የወር ደመወዝ ለገቢ ግብር የሚከፍለውን በመቀነስ ፣ ተጠሪ ከሚያገኘው የወር ደመወዝ ስልሣ ፏርሰንቱን ብቻ አመልካች እንዱከፍል ወስኗል። የስር ፍርድ ቤት ተጠሪ የጡረታ መገለያ እድሜው እስኪደርስ ያገኝ የነበረው የተጣራ ገቢ ስልሣ ፏርሰንቱን ብቻ አመልካች እንዱከፍል የንግድ ህግ አንቀጽ 599ን ከፍታብሓር ህግ ቁጥር 2092 ጋር አጣምሮ በመተርጏም የካሣውን መጠን የወሰነ እንደሆነ ተገንዝበናል። የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልትና የሰበር ችልት የስር ፍርድ ቤት የንግድ ህግ አንቀጽ 599 አግባብነት ካላቸው የፍታብሓር ህግ ድንጋጌዎች ጋር በማጣመር ተግባራዊ ያደረጉ መሆኑን በማረጋገጥ የስር ፍርድ ቤት ውሣኔ ማጽናታቸው ተገቢና የህግ ስህተት ያላለበት በመሆኑ በዚህ በኩል አመልካች ያቀረበውን የሰበር አቤቱታ አልተቀበልነውም።
በአጠቃላይ አመልካች በተጠሪ ላይ ለደረሰው የአካል መጉደል ካሣ የሚከፍለው በንግድ ህግ አንቀጽ 597 ድንጋጌዎች መሰረት ሣይሆን በንግድ ህግ አንቀጽ 599 መሰረት ነው በማለት የካሣውን መጠን የፍታብሓር ህግ ቁጥር 2091 እና የፍታብሓር ህግ ቁጥር 2092 መሰረታዊ መርሆች በመጠቀም መወሰናቸው ተገቢና መሰረታዊ የህግ ስህተት ያላለበት ነው በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የደቡብ ብሓር ብሓረሰቦች ህዝቦች ክልል የሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት፣ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልትና ሰበር ችልት የሰጡት ውሣኔ ጸንቷል።
በዚህ ፍርድ ቤት ሚያዝያ 21 ቀን 2003 ዓ.ም የተሰጠው የዕግድ ትዕዛዝ ተነስቷል፤ ይጻፍ።
በዚህ ፍርድ ቤት የወጣውን ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ ለየራሳቸው ይቻለ። መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.