No summary available.
ሚያዝያ 18 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጏስ ወልደ አልማው ወሉ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሤ አመልካች፡- ሜሪስቶኘስ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ - ጠበቃቸው አቶ ኃይልዬ ሳህለ ተጠሪ፡- ወ/ት ሰናይት ዓለማየሁ - ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
በሰበር ተጠሪ ከሳሽነት ለሥር ከፍተኛ ፍ/ቤት የቀረበው ክስ ፍሬ ቃለ በተከሳሽ ድርጅት /በሰበር አመልካች/ ምርመራ ተደርጏልኝ “ኖርኘላንት“ የተባለ የወሉድ መከላከያ መደኃኒት በክንድ እንዱቀበር ከተደረገ በኃላ መድኃኒቱ ህመም ስላስከተለብኝ ተከሳሽ በራሱ የህክምና ባለሙያዎች መድኃኒቱ እንዱወጣ ሲያደርግ በባለሙያዎቹ ተገቢ የሆነ ጥንቃቄ ባለመደረጉ የተነሣ መድኃኒቱ የተቀበረበት እጄን ለማያቋርጥ ህመምና ስቃይ የዲረገኝ ከመሆኑ ላላ በጡትና በጀርባዬ ላይ ባስከተለው የመሸማቀቅ ህመም የተነሣ የጀርባ ህመም፣ የፉት ማበጥ እና የልብ ህመም አስከትልብኛል። ህመሙም በመወሳሰቡ የደም ዝውውር ስርዓት ላይ ችግር በማስከተል የደም ቱቦ በመዘጋቱ እጄ እየመነመነ በመምጣት ሥራዬን መሥራት እንዲልችል በማድረጉ ህክምናውን በውጪ ሀገር እንድከታተል ላልች የህክምና ተቋማት ያረጋገጡልኝ ስለሆነ ተከሳሽ ላደረሰብኝ ጉዲት ሀላፉ ነው ተብል እንዱወሰንበትና ታይላንድ ሀገር ሄጂ ለመታከም፡ለህክምና ወጪ ብቻ ብር 192‚881 ለደም ሥርዓት ማስተካከያ ቀድ ጥገና ብር 114‚699 ለደም ምርመራ ኤክስሬይ /x-ray/ እና ላቦራቶሪ ምርመራ ብር 22‚100 ኤም.አር ምርመራ ብር 13‚377 ታይላንድ ደርሶ መልስ የአውሮኘላን ትኬት ብር 14‚000 የ10 ቀን የሆቴል ወጪ ብር 6‚500 ለ10 ቀን የሆስፑታል አልጋ ወጪ ብር 159‚949 ለህክምና ተጨማሪ ወጪ መጠባበቂያ ብር 100‚000 ታይላንድ ባንኮክ የታክሲ፣ የፕስፕርት እና ላላ ወጪ ብር 13‚400 ለአስታማሚ ትራንስፕርት ሆቴል፣ የጉዞ ሰነድ ወጪ ብር 34‚780 በጉዲቱ ምክንያት ሥራ በማቆሜ ያጣሁትን ብር 632 ክስ እስከቀረበበት ሐምል 2001 ታስቦ ብር 22‚752 የሞራል ካሣ ብር 1‚000 በድምሩ 694‚918 ብር /ስድስት መቶ ዘጠና አራት ሺህ ዘጠኝ መቶ አሥራ ስምንት/ ተከሳሽ እንዱከፍለኝ እንዱወሰንበት የሚል ነው።
የሥር ተከሳሽም በሰጠው መልስ አንድ ሀኪም ብልም ሆስፑታል በሙለ ሀላፉነት የሚጠየቀው የሞያ ደንብ ተጥሶ ሲገኝ ሲሆን ይኸው ደንብ ተጥሶ በመሰራቱ ምክንያት በከሳሽ ላይ ጉዲት ስለመድረሱ አላስረዲችም፣ ከሳሽ በውጪ ሀገር ለመታከም የሚያስችላትን ሰርትፍኬት ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በማስረጃነት አላቀረበችም በውጪ ሀገር ህክምና ያስፈልጋታል ቢባል እንኳን የዚህ ዓይነት ህክምና በቅርብ በኬኒያ ወይም ህንድ ሀገር የሚሰጥ በመሆኑ ታይላንድ ሀገር ለመታከም የጠየቀችው ያለአግባብ ነው። ከሣሽ ለህክምና የጠየቀችው ብር 192‚881 በማስረጃ ያልተረጋገጠ ከመሆኑ ላላ ለምርመራ በማለት ልዩ ልዩ ወጪዎችን መጠየቋ ተገቢነት የለውም፣ በሆስፑታል ለ10 ቀናት እንደምትቆይ በመጥቀስ የጠየቀችው ገንዘብም ቢሆን ከ2 ቀን በላይ በሆስፑታለ ስለማትቆይ በጣም የተጋነነ ነው ለአስታማሚ በሚል የጠየቀችውን ገንዘብ ተከሣሽ መክፈል አይገባውም ፣ የደረሰባት ጉዲት የግል ሥራዋን የሚከለክላት ስለመሆኑም ማስረጃ አላቀረበችም፣ የሞራል ካሣም ቢሆን ተከሳሽ ለከሳሽ መከፈል የለብኝም ሲል ተከራክሯል።
ጉዲዩን የመረመረው የሥር ከፍተኛ ፍ/ቤትም የከሳሽ የህክምና ወጪዎች በትክክል ለማወቅ የሚያስቸግር ናቸው በማለት በርትዕ ተከሳሽ ለከሳሽ ብር 300‚000 ሉከፍል ይገባል ብሎል።
በዚህ በሥር ከፍተኛ ፍ/ቤት የግራ ቀኙ ተከራካሪዎች ይግባኝ ለፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ያቀረቡ ሲሆን የሥር ተከሣሽ ይግባኝ በፍትሀብሄር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 337 መሰረት ሲዘጋ በከሳሽ የይግባኝ መዝገብ ላይ ክርክር ተካሂድ የሥር ከፍተኛ ፍ/ቤት ውሣኔን በማሻሻል መልስ ሰጪ /ተከሳሽ/ ለይግባኝ ባይ በሥር ፍ/ቤት ቀደም ሲል የተወሰነላትን ብር 300‚000 /ሶስት መቶ ሺህ/ የተቀበለች ስለሆነ ይኸው የተቀበለችው ገንዘብ የሚታሰብ ሆኖ ብር 694‚918 /ስድስት መቶ ዘጠና አራት ሺህ ዘጠኝ መቶ አሥራ ስምንት/ እንዱከፍላት በሚል ወስኗል።
በዚህ በጠቅላይ ፍ/ቤት ውሳኔ ላይ አመልካች ቅር በመሰኘት የሰበር አቤቱታ ለዚህ ችልት ያቀረበ ሲሆን በዋናነት የዘረዘራቸው ነጥቦችም፡- በተጠሪ ላይ ለደረሰው ጉዲት /ሉከፈላት የሚገባው የካሣ መጠን/ ሉታወቅ የሚችል ስለሆነ የሥር ፍ/ቤቶች የካሣ መጠኑን በርትዕ መወሰን አይገባቸውም፣ በርትዕት የሚወሰን የካሣ መጠን አነስተኛ መሆን ይገባዋል፣ ለተጨማሪ የካሣ ክፍያ የብር ተመን መውረድን የጠቅላይ ፍ/ቤቱ ይግባኝ ሰሚው ችልት እንደምክንያት መውሰደ ተገቢነት የለውም የሚለ ናቸው።
No topics extracted.
ለስበር አቤቱታ ተጠሪዋ በሰጠች መልስ አመልካች ለደረሰብኝ ጉዲት በሥር ፍ/ቤቶች ሀላፉነት እንዲለበት ተወስኖ እስከ ሰበር ድረስ በመ/ቁ. 58041 ቅሬታውን አቅርቦ ጉዲዩን የመረመረው የፋ/ሰበር ሰሚ ችልትም በሥር ፍ/ቤቶች ውሳኔ ላይ መሰረታዊ የህግ ስህተት አልተፈፀመም በሚል አቤቱታውን ውድቅ ያደረገበት ስለሆነ የካሣን መጠን በሚመለከት ያቀረበውን ክርክር የሰበር ሰሚ ችልት ሥልጣን ባለመሆኑ ቅሬታው ተቀባይነት የለውም በማለት ተከራክሯለች።
አመልካችም ለተጠሪዋ መልስ የመልስ መልስ በማቅረብ ክርክሩን በማጠናከር አቅርቧል።
የግራ ቀኙ ክርክር ከዚህ ከላይ በተገለፀው አኳኋን የቀረበ ሲሆን እኛም የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በሰጠው የካሳ ውሳኔ ላይ መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈጽሟል ወይስ አልተፈጸመም? የሚለውን ጭብጥ ይዘን እንደሚከተለው መርምረናል።
በሥር ፍ/ቤቶች በተደረገው ክርክር የአመልካች የህክምና ድርጅት ለተጠሪ ህክምና ባደረገላት ወቅት በተፈጠረው ችግር የተጠሪዋ ጤና ላይ ጉዲት የደረሰ በመሆኑ ይህም የደረሰባት ጉዲት በሀገር ውስጥ በህክምና ለማዲን የሚቻል ባለመሆኑ ታይላንድ ሀገር ሄዲ እንድትታከም ተወስኗል። ነገር ግን ለዚህ ቅሬታ ዋና መነሻ የሆነው ለህክምናና ለተለያዩ ወጪዎች ጠቅላይ ፍ/ቤቱ አመልካች ለተጠሪዋ የህክምናና ልዩ ልዩ ወጪዎች በርትዕ ከፍ አድርጏ መወሰኑ ነው።
በእርግጥ በመርህ ደረጃ በጉዲቱ ምክንያት ተበዲዩ የሚካሰው ለጉዲቱ ተመዛዛኝ የሆነ ኪሣራ በመክፈል መሆኑን የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2090 የሚደነግግ ሲሆን ለጉዲቱ ሀላፉ የተደረገው ሰውም ሀላፉነቱ ያመጣውን ጉዲት በተበዲዩ ላይ ከደረሰው ጉዲት ጋር እኩል ሆኖ ተመዛዝኖ መክፈል ይኖርበታል።
በዚህ በተያዘው ጉዲይ ግን የጠ/ፍ/ቤቱ ይግባኝ ሰሚው ችልት ለደረሰው ጉዲት ካሣ ለማስክፈል እንደ አማራጭ የወሰደው ርትዕን ነው። ለዚህም በምክንያትነት ከተጠቀሱት ነጥቦች ዋና ዋናዎቹ ተጠሪዋ ያቀረበቻቸው ለህክምናው ወጪ ያስፈልጋለ የተባለት ማስረጃዎች እንደሚያሳዩት የህክምናው ወጪ ከፍተኛ ነው፣ ለተጠሪዋም አስታማሚ የሚያስፈልጋት ሲሆን ወጪውም ምን ያህል እንደሆነ ከወዱሁ ለማወቅ የሚያስቸግር ነው፣ በመላው ዓለም እየታየ ያለውም የዋጋ ንረት ለተጠሪዋ ህክምና ወጪ የራሱ የሆነ ሚና ይኖረዋል፣ የብር ምንዛሪ መውረደ ተጠሪዋ ለህክምና ያስፈልገኛል በማለት በጠየቀችው የገንዘብ መጠን ላይ መዋዥቅን ያስከትላል የሚለ ናቸው።
በፍትሃብሄር ህጉ አንቀጽ 2102 ዳኞች ስለደረሰው ጉዲት ኪሣራን በርትዕ እንዱወሰኑ መብት የተሰጠውም በግልጽና በትክክል የኪሣራውን መጠን ለመወሰን አስቸጋሪ በሆነ ጊዜ ነው። ከዚሁ አንፃር የጠቅላይ ፍ/ቤቱ ይግባኝ ሰሚው ችልትም በክሱ የተጠቀሰውን ገንዘብ በርትዕ ከዚሁ አንፃር የጠቅላይ ፍ/ቤቱ ይግባኝ ሰሚው ችልትም በክሱ የተጠቀሰውን ገንዘብ በርትዕ ለማስከፈል የጠቀሳቸው ምክንያቶች የቀረቡትን ማስረጃዎች እና በአሁኑ ጊዜ በዓለም እየታየ ያለውን የዋጋ ንረት ያገናዘቡ በመሆናቸው ይህ ችልትም የሚቀበለው ነው። ከዚህ ጋር ተያይዞ መነሣት ያለበት አመልካች ዳኞች የጉዲት ካሣን በርትዕ ሉወሰኑ የሚችለት ልዩ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙ ነው በማለት የተከራከረው በአግባቡ ቢሆንም ርትዕን መሰረት አድርገው ዳኞች ካሣ ሉወሰኑ የሚችለት የካሣ መጠን ለመቀነሥ እንጂ ከፍ ለማድረግ አይደለም ሲል የተከራከረው ግን ህጋዊ መሰረት ያለው አይደለም። ስለሆነም በዚህ ረገድ ያቀረበው ክርክር ተቀባይነት የለውም።
ፍ/ቤቱ በርትዕ ሲወስንም ሉገመቱ የሚገባቸውን የነገሩን አጋጣሚ ሁኔታ ያለአግባብ ስለመያዙ ወይም ሉገመቱ የሚገባቸውን ትክክለኛውን መንገድ በመተው ያለአግባብ የሆነውን የአገማመት መንገድ ስለመያዙ አመላካች ነገር የለም። የተወሰነውም የካሣ ልክ በግልጽ ከአእምሮ ግምት ውጪ ሆኖ አልተገኘም።
ስለሆነም ከዚህ በላይ በተገለጹት የህግ ምክንያቶች የተነሣ በጠ/ፍ/ቤቱ ይግባኝ ሰሚ ችልት ውሳኔ ላይ የተፈፀመ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለም በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የፋዳራል ጠ/ፍ/ቤት በፍ/ይ/መ/ቁ. 58732 በቀን 15/04/2003 ዓ/ም በዋለው ችልት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያልተገኘበት በመሆኑ ፀንቷል።
የዚህን ፍ/ቤት ወጪና ኪሣራ ማለትም በሰበር ደረጃ የተደረገውን ክርክር በሚመለከት አመልካችና ተጠሪ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
መዝገቡ የተዘጋ ስለሆነ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።