No summary available.
መጋቢት 6 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ሒጎስ ወልደ ዲኜ መላኩ ተሻገር ገብረ ስላሴ አልማው ወላ አሉ መሐመድ አመልካች፡- አቶ ሚኪያስ ከበደ ከጠበቃ ገ/ክርስቶስ ኪዲነ ማርያም ጋር - ቀረቡ ተጠሪ፡-
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የፍደራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤትና የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት ያቀረበው የሰበር አቤቱታ የሚጣራ ነጥብ ያለው መሆኑ ተገልፆ ለሰበር የቀረበ በመሆኑ ነው።
የክርክሩ መነሻ ተጠሪዎች አመልካች ከአቶ ከበደ ታዬ ጋር በመሆን እያንዲንዲችን አምስት አምስት ሰው በኮንደሚኒየም ቤት እንዱያገኙ እድል የተሰጣቸው መሆኑን በመግለፅ አንደኛ ተጠሪ /አንደኛ ከሣሽ/ ከዘጠኝ ዘመድቼ ሰብስቤ የሰጠሁትን ብር 185,000/አንድ መቶ ሰማኒያ አምስት ሺህ ብር/ ሁለተኛ ተጠሪ /ሁለተኛ ከሣሽ/ ከዘመድ ሰብስበው የሰጡትን ብር 210,000/ሁለት መቶ አስር ሺህ ብር/ በድምሩ ብር 395,000 /ሶስት መቶ ዘጠና አምስት ሺህ ብር / ወስደዋል። ስለሆነም በማታለልና በማጭበርበር የወሰደትን ገንዘብ እንዱመልሱ ውሣኔ ይሰጥልን በማለት አመልክተዋል። አመልካችና በሥር ሁለተኛ ተከሣሽ የነበሩት አቶ ከበደ ታዬ ተጠሪዎች / ከሣሾች/ ክስ ያቀረቡባቸው በይሆናል እና በግምት ነው ማስረጃ የላቸውም የሚል ክርክር አቅርበዋል።
የሥር ፍርድ ቤት የተጠሪዎችን ምስክሮችና በአመልካችና በአቶ ከበደ ታዬ ላይ የተጀመረውን የፕሉስ የወንጀል ምርመራ መዝገብ አስቀርቦ ከመረመረ በኋላ አመልካች ብር 395,000 /ሶስት መቶ ዘጠኛ አምስት ሺህ ብር / የወሰደ መሆኑን በማስረጃ የተረጋገጠ መሆኑን በመግልፅ አመልካች ለተጠሪዎች ብር 395,000/ሶስት መቶ ዘጠና አምስት ሺህ ብር/ እንዱመልስና አቶ ከበደ ታዬ ከዚህ ገንዘብ ውስጥ ብር 130,000 አቶ ከበደ ታዬ በአንድነትና በነጠላ እንዱከፍል በማለት ወስኗል። አመልካች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለከፍተኛው ፍርድ ቤት አቅርበዋል።፡ የከፍተኛው ፍርድ ቤት አመልካችን በተመለከተ የተሰጠው ውሣኔ የህግ ወይም የፍሬ ጉዲይ ስህተት የለበትም በማለት በፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 337 መሰረት ሰርዞታል።
አመልካች ነሐሴ 20 ቀን 2002 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ ተጠሪዎች ገንዘብ ለእኔ የሰጡ መሆኑን የሚያስረዲ የሰነድ ማስረጃ አላቀረቡም ፍርድ ቤቱ ለፕሉስ የተሰጠን ቃል አላግባብ በማስረጃነት በመጠቀምና በፕሉስ ተፅዕኖ የደረሰብኝ መሆኑን ለማስረዲት እየጠየቅሁ እያለሁ አላግባብ ብር 395,000 ለተጠሪዎች እንድመልስ የተሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት አመልክቷል። ተጠሪዎች በበኩላቸው ህዲር 27 ቀን 2003 ዓ.ም በተፃፈ መልስ አመልካች ኮንደሚኒየም ቤት አሰጣችኋለሁ በማለት የማታለል ክስ ያቀረብንበትን ገንዘብ የወሰደ መሆኑን በማስረጃ አስረድተናል። አመልካችም ለፕሉስ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 27/1/ በሰጠው የተከሣሽነት ቃል ብቻ ሣይሆን በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 35 ለፍርድ ቤት በሰጠው የእምነት ቃል አረጋግጧል። ይኸ ማስረጃ በፍታብሓር ተቀባይነት ያለው ማስረጃ ነው። ስለሆነም አመልካች በሥር ያላነሳውን አዱስ ክርክር በማቅረብ ያቀረበውን አቤቱታ ውድቅ በማድረግ እንዱያሰናብተን በማለት መልስ ሰጥተዋል።
አመልካች ታህሣሥ 20 ቀን 2003 ዓ.ም የተፃፈ የመልስ መልስ አቅርቧል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የቀረበው ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም ጉዲዩን መርምረናል። ጉዲዩን እንደመረመርነው አመልካች ተጠሪዎች ለሥር ፍርድ ቤት ባቀረቡት ክስ የጠቀሱትን ገንዘብ ለተጠሪዎች እንዱመለስ የሥር ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚው ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጡት ውሣኔ በአግባቡ ነው ወይስ አይደለም የሚለዉ ጭብጥ መታየት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ተጠሪዎች ለሥር ፍርድ ቤት ባቀረቡት ክስ አመልካች በሥር ሁለተኛ ተከሣሽ የሆኑት አቶ ከበደ ታዬ፣ ቤቱ ለልማትና ኢንቨስትመንት የፈረሰበት ሰው ዘጠኝ ዘጠኝ ሰው ኮንደሚኒየም ቤት እንዱያገኝ ማድረግ እንደሚችል በመንግስት ውሣኔ የሰጠበት በመሆኑ ገንዘብ አሰባሰባችሁ አምጡ በማለት ከአንደኛ ተጠሪ ብር 185,000 ከሁለተኛ ተጠሪ ብር 210,000 የራሳቸውን ድርሻና ከዘመድ ያሰባሰቡትን ከወሰደ በኋላ ላልችን ሰዎች በመቁጠር የተወሰነውን ገንዘብ የመለሱ መሆኑንና ብር 395,000 የሚፈለግባቸው መሆኑን የሚያስረደ የሰው ምስክሮች አቅርበዋል። አመልካች ተጠሪዎች ገንዘቡን ለእኔ የሰጡ መሆኑን የሚያስረዲ የሰነድ ማስረጃ አላቀረቡም የበታች ፍርድ ቤቶች በህግ በኩል ተቀባይነት የላለውን የሰው ምስክር በመስማት መወሰኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት ነው የሚል ክርክር አቅርቧል።
አንድ ሰው የላላውን ሰው የሥራ ድካም ወይም በልላው ሰው ሀብት በመገልገል በቂ ባልሆነ ምክንያት ጥቅም ያገኘ እንደሆነ አላግባብ ባገኘው ጥቅም መጠን ለባለሀብቱ ወይም በጉልበቱ ለደከመው ሰው የመመለስና የመካስ ግዳታ ያለበት መሆኑ በፍታብሓር ህግ ቁጥር 2162 በመሰረታዊ መርህነት ተደንግጓል። አመልካች የኮንደሚኒየም ቤት ታገኛላችሁ ለኮንደሚኒየም ቤት የሚከፈል ነው በማለት ከተጠሪዎች ገንዘብ በመውሰድ ያልመለሰና ያለበቂ ምክንያት በገንዘቡ የተጠቀመ መሆኑን ተጠሪዎች በምስክር አስረድተዋል። ከሣሽ ተከሣሹ በንብረቱ ወይም በገንዘቡ አላግባብ የበለፀገና የተጠቀመ መሆኑን የሰነድ ማስረጃ ብቻ በማቅረብ ማስረዲት ያለበት መሆኑን የሚደነግግ ግልፅ የህግ ድንጋጌ የለም። የአንድ ማስረጃ ተቀባይነት ያለው መሆን አለመሆኑ የሚወሰነው በህግ ነው። ስለሆነም አመልካች ተጠሪዎችን በማታለል ከተጠሪዎች ገንዘብ የወሰደ መሆኑን በምስክርና በልላ ማስረጃ እንዱያስረደ የበታች ፍርድ ቤቶች መፍቀዲቸው ተገቢ መሰረታዊ የህግ ስህተት የላለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ተጠሪዎች አመልካች ክስ የቀረበበትን ገንዘብ ተቀብል የወሰደ መሆኑን በማታለል ወንጀል በተደረገበት ምርመራ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 27 እና በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 35 መሰረት ለፕሉስና ለፍርድ ቤት በማመን ቃላቸውን የሰጡ መሆኑን በፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ በማስረጃነት ከቀረበው የፕሉስ የምርመራ መዝገብ ተረጋግጧል። በማለት በሥርና በሰበር ተከራክረዋል። አመልካች ለፕሉስ የሰጡት የተከሣሽነት ቃል በፕሉስ በደረሰብኝ ተፅዕኖ የተሰጠ ነው በማለት በሰበር አቤቱታቸው ከመግለፃቸው በስተቀር ከተጠሪዎች ገንዘብ ተቀብለው የወሰደ መሆኑን በማመን ለፕሉስና ለፍርድ ቤት ቃል አልሰጠሁም በማለት በግልፅ ክደው አልተከራከሩም። አመልካች በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ አንቀፅ 27 እና አንቀፅ 35 የተሰጠው የዕምነት ቃል የተጠሪዎችን ክስ ለማስረዲት የማይችልና ተገቢነት የላለው ማስረጃ ነው በማለት ለሰበር በሰጠው የመልስ መልስ ያቀረበው ክርክር በፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 235/2/ መሰረት በመሸሽ መልክ የተሰጠና እንደታመነ ሉቆጠር የሚገባው ሆኖ አግኝተነዋል።
አመልካች ገንዘቡን ከተጠሪዎች ተቀብል የወሰደ መሆኑ በፕሉስና በፍርድ ቤት ከሰጠው የዕምነት ቃል እንዲረጋገጠ በሥር ፍርድ ቤቶች ውሣኔ ተገልፆል። አንድ ሰው ባለዕዲ መሆኑን ያመነ እንደሆነ ዕዲው የታመነለት ሰው ባለዕዲው ዕዲውን ያመነበትን ምክንያት የማስረዲት/የማረጋገጥ / ግዳታ የላለበት መሆኑን በፍታብሓር ህግ ቁጥር 2019 ንዐስ አንቀፅ 1 ተደንግጓል። እንደዚሁም ተቃራኒ ማስረጃ ከላለ በስተቀር ባለዕዲው ዕዲ እንዲለበት በማመን የሰጠው የዕምነት ቃል በአእምሮ ግምት በሚገባ/ በአግባቡ / የተሰጠ ቃል ነው ተብል የሚቆጠር መሆኑ በፍታብሓር ህግ ቁጥር 2019 ንዐስ አንቀፅ 2 ተደንግጓል።
አመልካች ለፕሉስ የተከሣሽነት ቃላን ስሰጥ ከተጠሪዎች ገንዘብ ተቀብዬ ወስጃለሁ በማለት ቃላን የሰጠሁት ፕሉስ ባደረሰብኝ ተፅዕኖ ምክንያት ነው በማለት በሰበር አቤቱታው የገለፀ ቢሆንም ይህንን ክርክሩን የሚያስረዲ ማስረጃ ለሥር ፍርድ ቤት አላቀረበም። ከዚህ በተጨማሪ አመልካች የተጠሪዎች ዕዲ እንዲለበት በማመን በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 35 የሰጠው የእምነት ቃልን ለማስተባበል የሚችል ተቃራኒ ማስረጃ በፍታብሓር ህግ ቁጥር 2019 ንዐስ አንቀፅ 2 በሚደነግገው መሰረት አላቀረበም። ስለሆነም አመልካች በሰበር ደረጃ ያነሣው ክርክር በሥር ፍርድ ቤት ያልተነሣና የፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 329/1/ን የሚጥስ በመሆኑ አልተቀበልነውም።
አመልካች የበታች ፍርድ ቤቶች የፕሉስን የምርመራ መዝገብ በማስቀረብ በምርመራ መዝገቡ የሰጠሁት የተከሣሽ ቃል በማስረጃነት መጠቀሙ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው የሚል ቅሬታ አቅርቧል። ሆኖም በፍታብሓር ጉዲይ ፕሉስ ያጣራውን የምርመራ መዝገብ አስቀርቦ እንዲያይ የሚከለክል የማስረጃ ህግ ድንጋጌ የለም። ስለሆነም አመልካች በህግ ተቀባይነት የላለውን ማስረጃ መሰረት በማድረግ የበታች ፍርድ ቤቶች ወስነውብኛል በማለት ያቀረቡት ክርክር የህግ መሰረት ያለው ሆኖ አላገኘነውም።
ከላይ በዝርዝር በገለፅናቸው ምክንያቶች የበታች ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሣኔ በማስረጃ ህግ መሰረት ተቀባይነት ያላቸውን ማስረጃዎች በመቀበልና የፍታብሓር ህግ ቁጥር 2162 ፣ የፍታብሓር ህግ ቁጥር 2164 /1/ እና የፍታብሓር ህግ ቁጥር 2019 ንዐስ አንቀፅ 1 እና ንዐስ አንቀፅ 2 ድንጋጌዎችን መሰረት ያደረገና የህግ ስህተት የላለበት ነው በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የፍደራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤትና የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጡት ውሣኔ ፀንቷል።
የሰበር ችልት ታህሣሥ 13 ቀን 2003 ዓ.ም የሰጠው የዕግድ ትዕዛዝ ተነስቷል። ይፃፍ።
በዚህ ፍርድ ቤት ያወጡትን ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ ለየራሳቸው ይቻለ።
No topics extracted.