No summary available.
መጋቢት 09 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጏስ ወልደ ዲኜ መላኩ ተሻገር ገ/ስላሴ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- አቶ ለገሰ ጥቀሄር - ቀረቡ ተጠሪ፡- ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ አ/ማህበር - ነ/ፈጅ ጌታሁን ወርቁ ቀረቡ መዝገቡ የተቀጠረው ለምርመራ ሲሆን መርምረን ፍርድ ሰጥተናል።
ይህ የሰበር ጉዲይ ላቀርብ የቻለው የአሁን አመልካች የተጠሪ ባንክ አ/ማህበር ሥራ አስኪያጅ ሆኖ ከተሰጠው ሥልጣን በላይ በማለፍ በፈፀመው ተግባር ምክንያት በተጠሪ ላይ ለደረሰው ጉዲት ያለበት ኃላፉነት ምንድን ነው? የሚለውን ግራቀኙ ባለበት አከራክሮ ተገቢውን ዲኝነት ለመስጠት ሲባል የቀረበ ነው።
የአሁን አመልካች የተጠሪ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ሥራ አስኪያጅ ሆኖ እያገለገለ በነበሩበት ጊዜ ከተሰጣቸው ሥልጣን በላይ በማለፍ ስርዎት ትሬዱንግ ኃ/የተ/የግል ማህበር ለተባለ ድርጅት ብር 2,899,984.25 (ሁለት ሚሉዮን ስምንት መቶ ዘጠና ዘጠኝ ሺህ ዘጠኝ መቶ ሰማንያ አራት ከ25/100) የሆነ የብድር ገንዘብ ያለምንም ዋስትና ብድር እንዱፈቀድለት በወሰኑት መሰረት ይኸው የብድር ገንዘብ ለተበዲሪው መለቀቁንና ተበዲሪውም በገባው ግዳታ መሰረት በብድር የወሰደውን ገንዘብ ሉመልስ አለመቻለ በሥር ፍ/ቤቶች የተረጋገጠ ጉዲይ ሲሆን፤ ይህም ከሥልጣኑ በላይ በማለፈ ብድር እንዱለቀቅ የሚያደርግ ውሣኔ የመስጠት ተግባር ባንኩ በብድር የተወሰደውን ገንዘብ መልሶ ለመሰብሰብ ያላስቻለውና በዚህም ሳቢያ ጉዲት የደረሰበት ስለመሆኑም አላከራከረም።
ይህንኑ በብድር የተሰጠውን ገንዘብ በሙለም ሆነ በከፉል ተጠሪ ሰብስቧል የሚል ክርክርም አልቀረበም።
አመልካች የተጠሪ ባንክ የሥራ ኃላፉ መሆኑ፤ የሥራ ኃላፉነቱን ሲያከናውን በተሰጠው ሥልጣን ክልል ውስጥ መሆን እንደሚገባው ከባንኩ የበላይ ውሳኔ ሰጭ አካል የገንዘብ ጣሪያ ተበጅቶ ኃላፉነት መረከቡን፤ ይህንኑ የሥልጣን ወሰን በመተላለፍ ተግባር ፈፅሞ በቀጣሪው ባንክ ላይ የገንዘብ ጉዲት አድርሶ መገኘቱ የተረጋገጡ መሰረታዊ ፍሬ ነገሮች ሆነው እስከተገኙ ድረስ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 2524 እንደተመለከተው አመልካቹ በፈፀመው ተገቢ ያልሆነ ተግባር ምክንያት በአሰሪው ላይ ለደረሰው ጉዲት ኃላፉነት ያለበት መሆኑን አስረጂ ነው።
በተጠሪ ላይ ለደረሰው የገንዘብ ጉዲትም ይህ የአመልካቹ ተግባር ቀጥተኛ መንስኤ መሆኑን ከሚያመለክት በቀር ለብድሩ አለመመለስ ምክንያት የሆነ ላላ ጉዲይ ስለመኖሩ ሳይገለፅ፤ ሳይረጋገጥ በብድር የተሰጠው ገንዘብ ሳይመለስ መቅረቱ በዚህ በአመልካች ተግባር ምክንያት ነው ብል ለመደምደም የሚቻል አይደለም፤ በምክንያቱና በውጤቱ መካከል ቅርብ የሆነና በቂ ግንኙነት አለ ማለት አይቻልም በማለት የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የሰጠው ትንታኔ ከላይ በፍሬ ነገር ረገድ ላይ የተረጋገጠውንና በጉዲዩ አግባብነት ያለውን ድንጋጌ በውል ያገናዘበ ሆኖ አላገኘነውም።
በዚህም ምክንያት በተጠሪው ላይ ለደረሰው የገንዘብ ጉዲት አመልካች ኃላፉ መሆኑን ጠቅሶ ይግባኝ ሰሚው ጠቅላይ ፍ/ቤት የሰጠው ውሳኔ በአግባቡ ሆኖ አግኝተነዋል።
በተጠሪው ላይ የደረሰው የጉዲት ልክ ምን ያህል ነው የሚለውንም ነጥብ በተከታይ እንዲየነው በፍ/ብ/ሕ/ቁ 2524(2) አስቦ ወይም በቸልተኝነት ወይም ባለመጠንቀቅ በአሰሪው ላይ ለሚደርሰው ጉዲት ሰራተኛው ኃላፉ መሆኑ ከታወቀ በአሰሪው ላይ የደረሰውን ጉዲት አስልቶ እንዱከስ ለማድረግ ለጉዲዩ አግባብነት ያለውን ህግ መሰረት ልናደርግ ይገባል ይህ ለክርክሩ ምክንያት የሆነው ተገቢ ያልሆነው የአመልካች ተግባር የተፈፀመውና ጉዲቱ የደረሰው አመልካችና ተጠሪ ካደረጉት የቅጥር ውል የመነጨ ነው። በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1676(1) እንደተመለከተው የግራ ቀኙን ውል በሚገባው ልዩ የውል ደንብ ውስጥ ደረሰ የሚባለውን የጉዲት ዓይነትና መጠን የሚያመለክት ዝርዝር ህግ ካልተገኘ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1790(2) እና 2090 እና ተከታይ ድንጋጌዎች መሰረት የጉዲት ልክ የሚወሰን ይሆናል። ከዚህም አንፃር ይህንን ጉዲይ ስንመለከተው አመልካች ከሥልጣኑ በላይ በፈፀመው ተግባር ምክንያት በተጠሪ ላይ የደረሰው ጉዲት የገንዘብ ሲሆን መጠኑም የብድር ገንዘቡ በአግባቡ ተሰጥቶ ቢሆን ኖሮ ባንኩ ማስመለስ ይቻል የነበረው ነገር ግን ሳይመለስ የቀረው እንጂ ከዚህ ያነሰ ወይም የበዛ ሆኖ አይታይም በዚህ ሁለ ምክንያት የግራ ቀኙን ጉዲይ በይግባኝ ተመልክቶ የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የኃላፉነቱን እና የጉዲት መጠኑን አስመልክቶ የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ አላገኘነውም በኢትዮጵያ ኢ.ፋ.ዱ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 80(3)(ሀ) እና በአዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀጽ 10 መሰረት አንድ የመጨረሻ ፍርድ በፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ቀርቦ ሉታረም የሚችለው መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ የተገኘ እንደሆነ ብቻ መሆኑን በማየት የሚከተለውን ውሳኔ ሰጥተናል።
የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በይ/መ/ ጥር 15 ቀን 2001 ዓ.ም የሰጠው ፍርድ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348(1) መሰረት ፀንቷል።
የአመልካች የሰበር ክርክር ህጋዊ መሰረት ያለው ሆኖ ስላላገኘነው ተቀባይነት የለውም ብለናል።
ከዚህ በፉት በዚህ መዝገብ ተሰጥቶ የነበረው የዕግድ ትዕዛዝ ተነስቷል።
በዚህ ሰበር ሰሚ ችልት ለተደረገው ክርክር ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ወጭና ኪሣራ ይቻለ።
ራ/ታ
No topics extracted.