No summary available.
ግንቦት 19 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጏስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሣ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- አቶ ይልማ ደጀኔ - ጠበቃ አቶ ስሜነህ ተክለ - ቀረቡ ተጠሪ፡- ወ/ሮ መዱና ዱታም - ጠበቃ አቶ ዘካሪያስ ምንተስኖት - ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትና የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት ያቀረቡትን አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው። ክርክሩ በመጀመሪያ የታየው በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ነው በስር ፍርድ ቤት ተጠሪ ከሣሽ አመልካች ተከሣሽ በመሆን ተከራክራዋል። ተጠሪ በስር ፍርድ ቤት በከሣሽነት ቀርበው ተከሣሹ /አመልካች/ የሻንሲ ቁጥር 8991 የሆነ ተሣቢ መኪና በውል ገዝተን ነበር። ተከሣሽ የገዛውን የሻንሲ ቁጥሩ 8991 የሆነ ተሣቢ መኪና ዳክላራሲዮን ትክክለኛነት አረጋግጣለሁ በማለት የላልች ተሣቢ መኪኖች ማለትም የሻንሲ ቁጥሩ 8951 እና የሻንሲ ቁጥሩ 8793 ተሣቢ መኪና ዳክላራሲዮን ከከሣሽ ወስዶል። የሻንሲ ቁጥሩ 8991 የሆነው ተሣቢ መኪና ሽያጭ ውል ቀሪ ሆኖ ተከሣሽ በቅድሚያ ክፍያነት የከፈለውን ብር 5ዐ,ዐዐዐ /ሀምሣ ሺ ብር/ ከከሣሽ ተቀብል ወስዶል። ተከሣሽ የሶስቱን ተሣቢ መኪኖች ዱክላራሲዮን እንዱመልስ ቢጠየቅ ለመመለስ ፈቃደኛ አልሆነም። ተከሣሽ የተሣቢ መኪኖቹን ዳክላራሲዮን ባለመመለሱ ከሣሽ በተሣቢ መኪኖቹ ሰርተው የሚያገኙት ገቢና ጥቅም ቀርቶባቸዋል። መኪኖቹ ከቆሙበት ከሐምል 22 ቀን 1999 ዓ.ም ክስ እስከ ቀረበበት ጥር 6 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም የአንድ ተሣቢ የወር ገቢ ብር 1ዐ,ዐዐዐ /አስር ሺህ ብር/ የሶስቱ ተሣቢ ብር 3ዐ,ዐዐዐ /ሰላሣ ሺ ብር/ ሂሣብ የአራት ወር ከሃያሰባት ቀን ብር 147,ዐዐዐ /አንድ መቶ አርባ ሰባት ሺ ብር/ እና መኪኖቹን ለማስጠበቅ የወጣ ብር 22,5ዐዐ /ሃያ ሁለት ሺ አምስት መቶ ብር/ በድምሩ ብር 169 5ዐዐ /አንድ መቶ ስልሣ ዘጠኝ ሺ አምስት መቶ ብር/ እንዱከፍል ውሣኔ ይሰጥልኝ በማለት ክስ አቅርበዋል። የአሁን አመልካች በተከሣሽነት ቀርበው የሻንሲ ቁጥር 8991 የሆነው ተሣቢ መኪና ሽያጭ ውል ቀሪ አልሆነም። ተከሣሽ ከከሣሽ ብር 5ዐ,ዐዐዐ /ሀምሣ ሺ ብር/ የወሰድኩት የመኪናው ቅድሚያ ክፍያ ገንዘብ ተመልሶልኝ ሣይሆን ከከሣሽ ጋር ባለኝ የግል ግንኙነት የሰጡኝ ነው። እኔ የተቀበልኩት የተሣቢ መኪና ዱክላራሲዮን የለም። ለክስ ሀላፉነት የለብኝም። አንድ ተሣቢ መኪና በወር ብር 1ዐ,ዐዐዐ /አስር ሺ ብር/ ገቢ አያስገኝም በማለት ተከራክሯል። የስር ፍርድ ቤት የግራቀኙን ክርክርና ማስረጃ ከመረመረ በኋላ የሻንሲ ቁጥሩ 8991 የሆነው ተሣቢ መኪና ሽያጭ ውል አልፈረሰም በማለት ውሣኔ ሰጥቷል።
በልላ በኩል ተከሣሽ የሻንሲ ቁጥሩ 8951 እና 8993 የሆኑትን ተሣቢዎችና የገዛውን ተሣቢዎች ዳክራላሲዮን ይዞ ለመመለስ ፈቃደኛ ባለመሆኑ ከሣሽ በመኪናዎቹ ሉያገኙ ይችለት የነበረው ጥቅም ቀርቶባቸዋል። ጉምሩክና የአገር ውስጥ ገቢ ባለስልጣን በሰጠው መረጃ መሰረት የሁለቱ ተሣቢ መኪናዎች የቀረ ገቢ ብር 99,29ዐ.80 /ዘጠና ዘጠኝ ሺ ሁለት መቶ ዘጠና ብር ከሰማኒያ ሣንቲም/ ለተሣቢ መኪኖቹ ማስጠበቂያ የወጣ ብር 12,8ዐዐ /አስራ ሁለት ሺ ስምንት መቶ ብር/ በድምሩ ብር 112ዐ90.8ዐ /አንድ መቶ አስራ ሁለት ሺ ዘጠና ብር ከሰማኒያ ሣንቲም/ ከነ ወለደ ተከሣሽ ለከሣሽ ይክፈል በማለት ወስኗል።
በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ተጠሪ ይግባኝ ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበዋል።
ተጠሪ የሻንሲ ቁጥሩ 8991 የሆነውን ተሣቢ መኪና አመልካች ለመግዛት ያደረገው ውል ፈራሽ አይደለም ተብል መወሰኑ ተገቢ ባለመሆኑ በይግባኝ ይታይልኝ። የሁለቱ ተሣቢ መኪኖች የቀረ ገቢ የአንደኛው በወር ብር 1ዐ,ዐዐዐ /አስር ሺ ብር/ የሁለቱ ብር 2ዐ,ዐዐዐ /ሃያ ሺ ብር/ መሆኑን ለማስረዲት ያቀረብኩትን ማስረጃ የስር ፍርድ ቤት ውድቅ ያደረገብኝ አላግባብ ነው በማለት ነው።
አመልካች በበኩላቸው የሶስት ተሣቢ መኪና ዳክላራሲዮን ወስደሀል በዚህም ጉዲት አድርሰሀል ተብል የተሰጠው ውሣኔ ተገቢ አይደለም በሚል መስቀለኛ ይግባኝ አቅርበዋል። የከፍተኛው ፍርድ ቤት ተጠሪ ባቀረቡት ይግባኝ ላይ አመልካች የሰጡትን መልስና ክርክር ከተቀበለና አመልካች ባቀረቡት መስቀለኛ ይግባኝ ላይ ግራቀኙ ያቀረቡትን ክርክር ከሰማ በኋላ የአመልካችን መስቀለኛ ይግባኝ የህግ መሰረት የላለው መሆኑን በመግለጽ ውድቅ አድርጏታል።
የከፍተኛው ፍርድ ቤት የተጠሪን ይግባኝ ክርክር በመቀበል የሻንሲ ቁጥሩ 8991 የሆነው ሽያጭ ውል እንዲይፈጸም ችግር የፈጠረው የአሁን አመልካች መሆኑን ከዘረዘረ በኋላ ተጠሪና አመልካች የሻንሲ ቁጥሩ 8991 የሆነውን ተሣቢ በተመለከተ ያደረጉት የሽያጭ ውል ፈራሽ ነው በማለት የስር ፍርድ ቤት ውለ ፈራሽ አይደለም በማለት የሰጠውን ውሣኔ በመሻር ውሣኔ ሰጥቷል።
የሻንሲ ቁጥራቸው 8951 እና 8793 ከሆኑ ሁለት ተሣቢዎች የቀረ ገቢ የአንደ በወር ብር 1ዐ,ዐዐዐ የሁለቱ ተሣቢ ብር 2ዐ,ዐዐዐ /ሃያ ሺ ብር/ ሂሣብ መያዝ ይገባዋል በማለት አመልካች ከሐምል 22 ቀን 1999 ዓ.ም ጀምሮ ጉዲዩ በይግባኝ ውሣኔ እስከተሰጠበት ታህሣስ 22 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም ታስቦ ብር 48ዐ,ዐዐዐ /አራት መቶ ሰማኒያ ሺ ብር/ ለተጠሪ እንዱከፍል በማለት የስር ፍርድ ቤት የሰጠውን የካሣ ውሣኔ በማሻሻል ውሣኔ ሰጥቷል።
አመልካች የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት አለበት።
የሻንሲ ቁጥሩ 8991 የሆነው ተሣቢ መኪና ሽያጭ ውል እንዱፈርስ የሰጠው ውሣኔ የህግ መሰረት የለውም። አመልካች ዳክላራሲዮን ወስዶል ተብል ጥፊተኛ መባለና ካሣ እንዱከፍል መወሰኑ የተሣቢ መኪና ሽያጭ ውለ አፈጻጸም ጋር ለማቀላጠፍ አመልካች የሰራውን ስራ የሚያሣይና ሰነድ መስጠት የተጠሪ ግዳታ መሆኑን ከግንዛቤ ውስጥ የማያስገባ በመሆኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት የካቲት 3ዐ ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም በተጻፈ የሰበር አቤቱታ አቅርበዋል ተጠሪ በበኩላቸው ሰኔ 14 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም በተጻፈ መልስ የከፍተኛው ፍርድ ቤት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለበትም በማለት ተከራክረዋል።
አመልካች ሐምል 19 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም የተጻፈ የመልስ መልስ አቅርበዋል።
ከስር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የቀረበው ክርክር ከላይ የተገለጸው ሲሆን እኛም የከፍተኛው ፍርድ ቤት የተሣቢዎቹ የወር ገቢን በተመለከተ ከግል የትራንስፕርት ድርጅት የተሰጠውን መረጃ መሰረት በማድረግ መወሰኑና የገቢዎችና የጉምሩክ ባለስልጣን መረጃ ተቀባይነት የለውም በማለት መወሰኑ ተገቢ ነው ወይስ አይደለም የሚለውንና ጉዲዩ ለሰበር ችልት ሲቀርብ የተያዘውን ጭብጥ በመያዝ ጉዲዩን መርምረናል።
ተጠሪ የስር ፍርድ ቤት የሰጠውን ይህንን ውሣኔ በመቃወም ለይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ይግባኝ አቅርበዋል። ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ተጠሪና አመልካች የሻንሲ ቁጥሩን 8991 የሆነ ተሣቢ መኪናን በተመለከተ ያደረጉት የሽያጭ ውል አመልካች አፈጻጸሙን አስቸጋሪና ከባድ ያደረገው በመሆኑ ፈራሽ ነው በማለት የስር ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ በመሻር ውሣኔ ሰጥቷል። የሻንሲ ቁጥሩ 8991 የሆነውን ተሣቢ መኪና ሽያጭ ውል ሉጸናና ህጋዊ ውጤት ሉኖረው ይገባል ወይስ ፈራሽ ላሆን ይገባል የሚለውን ጭብጥ ማዕከል በማድረግ አመልካችና ተጠሪን አከራክሮ የስር ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ በይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ሙለ በሙለ ተሽሯል፡ ይኸውም በመሆኑ አመልካች የተሣቢ መኪናውን ሽያጭ ውል በተመለከተ የከፍተኛው ፍርድ ቤት በሰጠው ውሣኔ ላይ ይግባኝ ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ማቅረብ የሚገባቸው መሆኑን ከአዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 9 ድንጋጌ ለመገንዘብ ይቻላል። አመልካች ይህንን የይግባኝ ስርዓት ሣይጨርሱ የሻንሲ ቁጥሩ 8991 የሆነው ተሣቢ መኪና ሽያጭ ውል ፈራሽ ነው ብል የከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ በሰበር እንዱታይላቸው ያቀረቡት አቤቱታ ጉዲዩን አይቶ የመጨረሻ ውሣኔ የመስጠት ስልጣን ባለው የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ቀርቦ ያልታየና የመጨረሻ ውሣኔ ያልተሰጠበት በመሆኑ በህገመንግስቱ አንቀጽ 8ዐ ንኡስ አንቀጽ 3 /ሀ/ እና አዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 1ዐ የተደነገገውን መስፈርት የማያሟላ በመሆኑ በሰበር ችልት ቀርቦ ለመታየት የሚችል ባለመሆኑ አልተቀበልነውም።
አመልካች ለተጠሪ መክፈል የሚገባውን የካሣ መጠን በተመለከተ የስር ፍርድ ቤት የሰጠውን የካሣ ውሣኔ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት በማሻሻል ውሣኔ የሰጠውን የካሣ ውሣኔ በተመለከተ ይግባኝ ስለሚቀርብበትና ተቀባይነት ስለሚያገኝበት ሁኔታ የተደነገጉ ድንጋጌዎችን መሰረት በማድረግ መሆኑ ወይም አለመሆኑ መታየት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል። የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የተጠሪ ሁለት መኪናዎች ወደ ስራ ቢሰማሩ ያስገኙ የነበሩትን የገቢ መጠን ከመወሰኑ በፉት ተሣቢ መኪናዎቹ በኢትዮጵያ ውስጥ በስራ ተስማርተውና ገቢ አስገኝተው የማያውቁ በመሆኑ የካሣውን መጠን ተሣቢዎቹ ሰርተው ወይም ተከራይተው ያስገኙትን ገቢ ለመወሰን የማይቻል መሆኑ የካሣው መጠን አወሣሰን ላይ ችግር የፈጠረ መሆኑን በውሣኔው ገልጿል። የስር ፍርድ ቤት ተሣቢ መኪናዎቹ ሰርተው ወይም ተከራይተው የሚያስገኙት ገቢ በማይታወቅበት ሁኔታ የሻንሲ ቁጥራቸው 8951 እና 8793 የሆኑት ተሣቢ መኪኖች የተመረቱበትን ዘመንና የመሸከም አቅማቸው ተመሣሣይ የሆኑ ተሣቢ መኪኖች አማካኝ አመታዊ ገቢ ምን ያህል እንደሆነ የኢትዮጵያ ጉምሩክና አገር ውስጥ ገቢ መረጃ ማግኘቱ አስፈላጊ መሆኑን በመረዲት መረጃው እንዱላክለት ትዕዛዝ ሰጥቷል።
የኢትዮጵያ ጉምሩክና ገቢዎች ባለስልጣን በስር ፍርድ ቤት በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት ከተመረተ /ከተፈበረከ/ አስራ አምስት ዓመት ያልሞላው ተሣቢ አማካኝ አመታዊ ገቢ በ 36,888 /ሰላሣ ስድስት ሺ ስምንት መቶ ሰማኒያ ስምንት ብር/ እንደሆነና ከተመረተ /ከተፈበረከ/ ከአስራ አምስት ዓመት በላይ የሆነው ተሣቢ መኪና ገቢ 31,355 /ሰላሣ አንድ ሺ ሶስት መቶ ሀምሣ አምስት/ መሆኑን በጽሁፍ አረጋግጧል። የተጠሪ ተሣቢ መኪኖች ከተመረቱ አስራ ስምንት ዓመት በላይ የሆናቸው ለመሆኑ የጉምሩክና አገር ውስጥ ገቢ ባለስልጣን የሰጠውን ማረጋገጫ መሰረት በማድረግ አመልካች ለተጠሪ መክፈል ያለበትን የካሣ መጠን ወስኗል።
አመልካች በተጠሪ ላይ ለደረሰው ጉዲት ሀላፉ የሆነው ከውል ውጭ ጥፊት በሆነ ድርጊት የሁለቱን መኪናዎች ዳክላራሲዮን አላግባብ ይዞ አልመልስም በማለቱ ምክንያት ነው። ከውል ወጭ ሀላፉ የሆነ ሰው ለተጏጂው የሚከፍለው የካሣ መጠን በመርህ ደረጃ ይግባኝ የማይቀርብበት እንደሆነ በፍታብሓር ህግ ቁጥር 2152 ስለኪሣራ ጥቅም አከፊፈል በመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኞች የተወሰነ ፍርድ ላይ ለበላይ ፍርድ ቤቶች ይግባኝ ማለት አይቻልም በማለት በግልጽ ይደነግጋል።
ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ አይቶ የካሣ ውሣኔ በሰጠው ፍርድ ቤት ውሣኔ ላይ ይግባኝ የሚፈቀደው በፍታብሓር ህግ ቁጥር 2153 ልዩና የተጠበቁ ሁኔታዎች ሲኖሩ ነው። በፍታብሓር ህግ ቁጥር 2153 የተደነገጉት ልዩና የተጠበቁ ሁኔታዎች ሶስት ሲሆኑ እነርሱም፡- /ሀ/ ዳኞች ሉገምቱት የሚገባቸውን የነገሩን አጋጣሚ አላግባብ በመያዝ ውሣኔ ሰጥተው እንደሆነ ወይም ሉገምቱት የሚገባቸውን ትክክለኛውን መንገድ ትተው ያላግባብ የሆነውን አገማመት መንገድ ይዘው የተገኙ እንደሆነ /ለ/ በዳኞች የተወሰነው የኪሣራ ገንዘብ ልክ በግልጽ ከአእምሮ ግምት ውጭ የሆነና የተወሰነውም በማዲላት ወይም በዝንባላ መሆኑ እርግጥ ሆኖ የተገኘ እንደሆነ /ሐ/ በዳኞች የተወሰነው የጉዲት ካሣ በሑሣብ መሣሣት ሆኖ የተገኘ እንደሆነ መሆኑ በግልጽ ተደንግጓል።
ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የከፍተኛው ፍርድ ቤት የስር ፍርድ ቤት የጉምሩክና አገር ውስጥ ገቢ ባለስልጣን አጣርቶ የላከለትን ዓመታዊ አማካኝ ገቢ መሰረት በማድረግና ተሣቢዎቹ ወደ ስራ ተሰማርተው የማያውቁና ለካሣ ውሣኔ መነሻ የሚሆን እርግጥኛ ገቢ የላላቸው መሆኑን ከግምት ውስጥ በማስገባት የወሰነው የኪሣራ /የካሣ ውሣኔ/ በፍታብሓር ህግ ቁጥር 2152 ከተደነገገው በተለየ ሁኔታ በይግባኝ ላታይ የሚችልበት ልዩ ምክንያትና ሁኔታ ያለ መሆኑን ከፍታብሓር ህግ ቁጥር 2153 ድንጋጌዎች አንጻር የሰጠው ምክንያትና ትንታኔ የለም። ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የስር ፍርድ ቤት የወሰነው የካሣ ውሣኔ በፍታብሓር ህግ ቁጥር 2153 ከተደነገጉትና ጉዲዩን በይግባኝ ለማየት የሚያስችለ ልዩ ሁኔታዎች የትኛውን ድንጋጌ የስር ፍርድ ቤት እንደተላለፈ ሣይገጽና ሣያረጋግጥ የካሣውን መጠን በይግባኝ አይቶ ማሻሻለ የፍታብሓር ህግ ቁጥር 2152 መሰረታዊ መርህ የሚጥስና ህግ አውጭው የፍታብሓር ህግ ቁጥር 2152 በመደንገግ ሉያሣካ የሚፈልገውን መሰረታዊ ግብና ዓላማ የማያሣካ ሆኖ አግኝተነዋል።
የስር ፍርድ ቤት የተጠሪ ሁለት ተሣቢዎች ወደ ስራ ተሰማርተው ገቢ አስገኝተው የማያውቁ ከተመረቱ ከአስራ አምስት ዓመት በላይ የሆናቸው በተጠሪ ተሣቢ መኪኖች የመሸከም አቅምና እድሜ የሚገኙ ተሣቢዎች በአመት የሚያስገኙት የተጣራ ገቢ ብር 31,355 /ሰላሣ አንድ ሺ ሶስት መቶ አምሣ አምስት ብር መሆኑን የኢትዮጵያ ጉምሩክና አገር ውስጥ ገቢ ባለስልጣን አጣርቶ የሰጠውን ማስረጃ መነሻ በማድረግ በመሆኑ በጉዲዩ ሉገመቱ የሚገባቸውን የነገሩን አካባቢ ሁኔታዎች በአግባቡ በመያዝና ትክክለኛውን መንገድ በመከተል የካሣ መጠኑን ውሣኔ የሰጠ መሆኑን ያሣያል።
በልላ በኩል ከፍተኛው ፍርድ ቤት የተጣራ ሁለት ተሣቢ መኪኖች የተመረቱበትን ዘመን የመኪኖቹን ጭነት የመሸከም አቅምና መኪኖቹ በኢትዮጵያ ውስጥ ስራ ሰርተው የማያውቁ በመሆኑ መኪኖቹ ሉያስገኙት የሚችለትን እርግጠኛ ገቢ ለመወሰን ችግር እንዱፈጠር ከግንዛቤ ውስጥ ሣያስገባ የኢትዮጵያ ጉምሩክና ገቢዎች ባለስልጣን የላከውን መረጃ ያለ በቂ ምክንያት ውድቅ በማድረግ የግል የትራንስፕርት ድርጅት የጻፈውን አስተያየት ብቻ መነሻ በማድረግ አንድ ተሣቢ በወር ብር 1ዐ,ዐዐዐ /አስር ሺ ብር/ የተጣራ ገቢ ያስገኛል፤ ሁለቱ ተሣቢዎች በወር ብር 2ዐ,ዐዐዐ /ሃያ ሺ ብር/ የተጣራ ገቢ ያስገኛለ በማለት የስር ፍርድ ቤት የወሰነውን የካሣ መጠን በመሻሻል አመልካች ለተጠሪ ብር 48ዐ,ዐዐዐ/ አራት መቶ ሰማኒያ ሺህ ብር/ እንዱከፍል የሰጠው ውሣኔ የፍታብሓር ህግ ቁጥር 2153 ንኡስ አንቀጽ 1 እና ንኡስ አንቀጽ 2 ድንጋጌዎች የተደነገጉት ልዩና የተጠበቁ ጉድለቶች የሚታዩበትና መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ስለሆነም ከጅምሩ የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የስር ፍርድ ቤት የካሣ መጠን በይግባኝ ለማየትና ለማሻሻል የሚያስችለ በፍታብሓር ህግ ቁጥር 2153 የተደነገጉ ጉድለቶች ያለበት መሆኑን ሣያረጋግጥ ጉዲዩን በይግባኝ በማየትና የኢትዮጵያ ጉምሩክና አገር ውስጥ ገቢ ባለስልጣን አጣርቶ የላከውን መረጃ ወደ ጏን በመተው የግል የትራንስፕርት ድርጅት የተጻፈውን አስተያየት መሰረት በማድረግ የካሣውን መጠን መወሰን ነበረበት በማለት የስር ፍርድ ቤት ውሣኔን በማሻሻል የሰጠው የካሣ ውሣኔ የፍታብሓር ህግ ቁጥር 2152 እና በፍታብሓር ህግ ቁጥር 2153 ንኡስ አንቀጽ 1 እና ንኡስ አንቀጽ 2 የተደነገጉትን ድንጋጌዎች የሚጥስና መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
አመልካት ተጠሪ የሻንሲ ቁጥሩ 8991 የሆነው ተሣቢ መኪና በተመለከተ ያደረጉት የሽያጭ ውል ፈራሽ ነው በማለት የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ በአዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 9 መሰረት በይግባኝ በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ቀርቦ ሣይታይና ሣይወሰን በሰበር ቀርቦ መታየት የሚችል ባለመሆኑ የአመልካችን የሰበር አቤቱታ አልተቀበልነውም።
የሻንሲ ቁጥራቸው 8951 እና 8793 የሆኑ ተሣቢ መኪኖች በአመልካች ጥፊት ምክንያት ባለመስራታቸው አመልካች ለተጠሪ ሉከፍል ይገባዋል በማለት የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በይግባኝ ጉዲዩን አይቶና አሻሽል የሰጠው ውሣኔ የፍታብሓር ህግ ቁጥር 2152 እና የፍታብሓር ህግ ቁጥር 2153 ንኡስ አንቀጽ 1 እና ንኡስ አንቀጽ 2 የሚጥስ ሆኖ በመገኘቱ ሙለ በሙለ ተሽሯል።
የፋዳራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት አመልካች ለተጠሪ ብር 112ዐ90.8ዐ /አንድ መቶ አስራ ሁለት ሺ ዘጠና ስምንት ብር ከሰማኒያ ሣንቲም/ ክስ ከቀረበበት ቀን ጀምሮ ከሚታሰብ ዘጠኝ ፏርሰንት ወለድ ጋር ለተጠሪ እንዱከፍል የሰጠውን ውሣኔ ሙለ በሙለ አጽንተናል።
በዚህ ፍርድ ቤት ያወጡትን ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ በየራሣቸው ይቻለ።
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.