No summary available.
የሰ/መ/ቁ. 5892ዐ የካቲት 22 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም ዳኞች፡ ተገኔ ጌታነህ ሐጎስ ወልደ ዲኜ መላኩ ተሻገር ገ/ሥላሴ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- አለምነው አበበ አካላ - ቀረበ ተጠሪ፡- ህብረት ኢንሹራንስ አ/ማ - ቃልኪዲን ንጉሴ - ቀረበ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ በመኪና ላይ የደረሰውን ጉዲት መነሻ በማድረግ የተጠየቀውን የካሣ ክፍያ ጥያቄ የሚመለከት ነው። ክርክሩ የተጀመረው በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን፣ በወቅቱ ከሣሽ የነበረው የአሁኑ ተጠሪ አመልካችን የከሰሰው የመድን ዋስትና በገባለት የደንበኛው መኪና ላይ የደረሰውን ጉዲት ለማስተካከል ያወጣውን ወጪ እንዱተካለት ነው። አመልካችም በበኩለ ለክሱ በሰጠው መልስ ክሱ በይርጋ ቀሪ ሆኖአል የሚል የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ እና የሥረ ነገር ክርክር አቅርቦአል። ክሱን የሰማው ፍ/ቤትም የግራ ቀኝ ወገኖችን ክርክር ከሰማ በኋላ የአመልካችን ክርክር ውድቅ አድርጎአል በዚህ መሰረትም አመልካች በተጠሪ ደንበኛ መኪና ላይ ያደረሰውን ጉዲት ለማስተካከል የወጣውን ወጪ ብር 5,5ዐዐ ከእነ ሕጋዊ ወለደ ጋር እንዱከፍል ወስኖአል። በዚህ ውሣኔ ላይ ይግባኝ የቀረበለት የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤትም ውሣኔው ጉድለት የለበትም በማለት የአመልካችን ይግባኝ ሰርዞአል። የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚህ ላይ ነው።
እኛም አመልካች ሐምል 26 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም በፃፈው ማመልከቻ ያቀረበውን አቤቱታ መሰረት በማድረግ ተጠሪን አስቀርበን ክርክሩን ሰምተናል። ክርክሩ የተሰማው አመልካች ያቀረበው የይርጋ መቃወሚያ በሥር ፍ/ቤቶች ውድቅ የተደረገው በሕጉ አግባብ ነው ወይ? በሚለው ጭብጥ ላይ ነው። በመሆኑም በዚህ ረገድ ግራ ቀኝ ወገኖች ያሰሙትን ክርክር አቤቱታው ከቀረበበት ውሣኔ እና ከሕጉ ጋር አገናዝበን መርምረናል።
ቀደም ሲል እንዲመለከትነው ክርክሩ ሉነሣ የቻለው አመልካች በተጠሪ የመድን ዋስትና የተገባለትን መኪና በመግጨት ጉዲት አድርሶአል በመባለ ነው። ገጭቶ ጉዲት ያደረሰው መኪና የአመልካች ንብረት ከመሆኑም በላይ ሲሽከረከር የነበረውም በራሱ ማለትም በአመልካቹ እንደሆነ አላከራከረም። ከሥር ጀምሮ ከተደረገው ክርክር መገንዘብ እንደቻልነው አመልካች የይርጋ መቃወሚያ ያነሣው በፍ/ብ/ሕግ ቁ. 2143/1/ የተቀመጠውን ድንጋጌ መሰረት በማድረግ ነው። ክሱን የሰማው የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት መቃሚያው ሣይቀበል የቀረው ለይርጋው መቃወሚያ አወሳሰን ተገቢነት ያለው ድንጋጌ በንዐስ ቁ./1/የተመለከተው ሣይሆን፣ በንኡስ ቁ. /2/ ያለው ነው በማለት ነው። ጊዜው ከዚህ ድንጋጌ አንፃር እየታየ ሲሰላም የክስ ማቅረቢያ ጊዜው አልፍአል ልባል አይችልም እሚል መደምደሚያ ላይ ፍ/ቤቱ ደርሶአል። አመልካች ለዚህ ሰበር ችልት ባቀረበው አቤቱታ የይርጋ መቃወሚያውን በሚመለከት ያነሣው ዋነኛ የመከራከሪያ ነጥብ በወንጀል ተከስሼ አልተቀጣሁም።
ስለዚህም በንኡስ ቁ. /2/ የተመለከተው ድንጋጌ ለጉዲዩ አወሳሰን ተገቢነት የለውም የሚል ነው።
በተጠሪ ደንበኛ መኪና ላይ ጉዲት ሉደርስ የቻለው በአመልካች ጥፊት አይደለም የሚል በፍሬ ነገር ረገድ የተረጋገጠ ነገር የለም። ይልቁንም ጉዲቱ የደረሰው በአመልካች ጥፊት ነው እሚል መደምደሚያ ላይ ተደርሶአል። አመልካች ጥፊተኛ ነው ከተባለ ደግሞ ድርጊቱ በወንጀልም የሚያስከስስ /የሚያስቀጣ/ ነው ማለት ይቻላል። ድርጊቱ /ጉዲቱ/ በወንጀል የሚያስቀጣ ሆኖ በተገኘ ጊዜ የይርጋ ዘመኑ ርዝመት በወንጀል ሕጉ በተደነገገው መሰረት እንደሚሆን ከላይ በተመለከተው የፍ/ብ/ሕግ ቁ. 2143/2/ ተደንግጎአል። ከዚህ ድንጋጌ መገንዘብ እንደሚቻለው ደግሞ ድርጊቱ በወንጀል የሚያስቀጣ መሆኑ ከሚታይ በቀር የድርጊቱ ፈፃሚ ተከሶ መቀጣት እግምት ውስጥ የሚገባ አይደለም። በመሆኑም በወንጀል አልተከሰስኩም ወይም አልተቀጣሁም በማለት አመልካች ያቀረበው ክርክር የሕግ መሰረት ያለው አይደለም በመጨረሻም የሥር ፍ/ቤቶች የይርጋውን መቃወሚያ ውድቅ በማድረጋቸው የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ለማለት አልቻልንም። ስለዚህም ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ.ቁ. 158634 ግንቦት 4 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ እና የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ. 948ዐ3 ሐምል 13 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም የሰጠው ትእዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 348/1/ መሰረት ፀንተዋል።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተቀባይነት የለውም ብለናል።
ግራ ቀኝ ወገኖች በዚህ ሰበር ችልት ለተደረገው ክርክር ወጪና ኪሣራ ይቻቻለ።
No topics extracted.