No summary available.
ታህሣስ 15 ቀን 2003 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሐጏስ ወልደ ተሻገር ገ/ስላሴ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ አመልካች፡- የኢትዮጵያ ኤላክትሪክ ኃይል ኮርፕሬሽን - ነገረ ፈጅ አቶ አያላው አለማየሁ - ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ወልደ ገብረሥላሴ ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትና የከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት በማመልከቱ ነው። የጉዲዩ መነሻ የጉዲት ካሣ ጥያቄ ነው። ተጠሪ በስር ፍ/ቤት ሦስተኛው ተከሣሽ የነበሩት አቶ ሣህለ ሀብተማርያም በተቋራጭነት የሚሰሩትን በስር የሁለተኛ ተከሣሽ የነበሩትን የአቶ ታከለ ገብሬ ባለሁለት ፍቅ ህንፃ በመሥራት ላይ እያለ በሚሰሩበት ቦታ የሚያልፈው ከፍተኛ ጉልበት ያለው የኤላክትሪክ መስመር አደጋ አድርሶባቸዋል። በአደጋው ምክንያት ሁለት እጆቻቸው መቆረጡና ሁለት ጭናቸው ላይ ጉዲት መድረሱ በየካቲት 12 ሆስፑታል የሀኪሞች ቦርድ ተረጋግጧል። አመልካች በአደጋ በደረሰባቸው ጉዲት 100% /አንድ መቶ ፏርሰንት/ የመሥራት ችልታቸውን እንዲጡ በስር ፍርድ ቤቶች ተረጋግጧል።
አመልካች በደረሰባቸው ጉዲት ምክንያት ካሣ እንዱከፍሎቸው አመልካችን በአንደኛ ተከሳሽነት የቤቱን ባለሀብት አቶ ታከለ ገብሬን በሁለተኛ ተከሣሽነት አሰሪያቸውን አቶ ሣህለ ሀብተማርያምን በሦስተኛ ተከሳሽነት ከሰዋል። አመልካችና ላልቹ ተከሣሾች በኃላፉነት አንጠየቅም የሚለባቸውን ምክንያቶች በማንሣት ተከራክረዋል። የፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በደረሰው አደጋ በኃላፉነት መጠየቅ ያለበት አንደኛ ተከሣሽ/አመልካች/ ነው በማለት ተጠሪ ለዘጠኝ ዓመት /ወደፉት/ የሚያገኘው ገቢ በቀን 50 ብር /ሀምሣ ብር/ እና በዓመት ውስጥ 200 /ሁለት መቶ/ የሥራ ቀናት የሚያገኘውን የተቋረጠበትን ገቢ ብር 50 × 200 ቀናት × 9 ዓመት አስልቶ 90,000 /ዘጠና ሺህ ብር/ የሞራል ካሣ ብር 1,000 /አንድ ሺህ ብር/ በድሩ 91,000 /ዘጠና አንድ ሺህ ብር/ አመልካች ለተጠሪ ይክፈል በማለት ወስኗል። አመልካች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለከፍተኛው ፍ/ቤት አቅርቧል። ተጠሪ በበኩለ በዓመት ሁለት መቶ ቀን ብቻ ይሰራል በሚል ሑሳብ ካሣው መሰላቱ ተገቢ አይደለም በማለት ይግባኝ ለከፍተኛው ፍርድ ቤት አቅርበዋል።
የከፍተኛ ፍ/ቤት የአመልካችንና የተጠሪን ይግባኝ አጣምሮ በማየት ለአደጋው አመልካች ብቻ ኃላፉ መባለ ተገቢ አይደለም። በስር ፍርድ ቤት ሦስተኛ ተከሣሽ በይግባኝ ሦስተኛ መልስ ሰጭ የነበሩት የአመልካች አሰሪ አቶ ሣህለ ሀብተማርያም ለደረሰው ጉዲት ከአመልካች ጋር ኃላፉነት አለበት። የመጀመሪያ ፍርድ ቤት በዓመት ተጠሪ 200 ቀናት ብቻ ነው የሚሰሩት ማለቱ ተገቢ አይደለም። ተጠሪ በዓመት ውስጥ 300 ቀን መሥራት ይችላል። በማለት የ300 ቀናት በቀን 50 /ሀምሣ ብር/ ሑሣብ የዘጠኝ ዓመት ብር 112,500 /አንድ መቶ አሥራ ሁለት ሺህ አምስት መቶ ብር/ እና የሞራል ካሣ ብር 1,000 /አንድ ሺህ ብር/ በድምሩ ብር 113,500 /አንድ መቶ አሥራ ሦስት ሺህ አምስት መቶ ብር/ አመልካችና በከፍተኛው ፍ/ቤት ሦስተኛ መልስ ሰጭ የነበሩት አቶ ሣህለ ሀብተማርያም እንዱከፍለ በማለት የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የሰጠውን ውሣኔ በማሻሻል ውሣኔ ሰጥቷል።
አመልካች የኤላክትሪክ መስመሩ ጉዲት እያደረሰ የማሰራው ህንፃ ቁመት እየጨመረ ሄድ ወደ ኤላክትሪክ መስመሩ በመጠጋቱና ተጠሪ ይዘውት በነበረው ፋሮ ብረት የኤላክትሪክ መሥመሩን በመንካታቸው ነው። ተጠሪ መስመሩ ካልተነሣ ሥራውን ማቆም ይገባቸው ነበር። ስለዚህ ለደረሰው ጉዲት የህንፃው ባለቤትና የተጠሪ አሰሪ እንጂ እኛ ኃላፉ መባላችን መሰረታዊ የህግ ስህተት አለበት በማለት አመልክተዋል። ተጠሪ በበኩላቸው በማናቸውም መንገድ ወይም ህዝብ በብዛት በሚገኝበት ሥፍራ የሚዘረጋ የኤላክትሪክ መስመር የአደጋ መከላከያ ሉኖራቸው እንደሚገባ በኤላክትሪክ ደንብ ቁጥር 49/91 አንቀጽ 35 እና አንቀጽ 41 ተደንግጓል። አመልካች ይህን ኃላፉቱን በአግባቡ አልተወጣም ስለዚህ በወቅቱ ለደረሰው ጉዲት የመካስ ኃላፉነት ያለበት በመሆኑ ያቀረበው የሰበር አቤቱታ የህግ ድጋፍ የለውም በማለት መልስ ሰጥቷል። አመልካች የመልስ መልስ አቅርቧል።
ከስር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የቀረበው ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም መዝገቡን መርምረናል። መዝገቡን እንደመረመርነው አመልካች በተጠሪ ላይ ለደረሰው ጉዲት ካሣ የመክፈል ኃላፉነት አለበት በማለት የተሰጠው ውሣኔ ተገቢ ነው? ወይስ አይደለም? የሚለው ጭብጥ መታየት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ተጠሪ ይህንን ሥራ በሚሰሩበት ወቅት በአካባቢው በሚያልፈው የኤላክትሪክ መስመር በደረሰባቸው አደጋ ምክንያት ሁለት እጆቻቸው የተቆረጡ መሆኑ ተረጋግጧል። አመልካች በሰበር ደረጃ አደጋው የደረሰው ተጠሪ ከፍተኛ መስመር ይተላለፍበት የነበረውን የኤላክትሪክ መስመር በፋሮ ብረት ስለነካ ነው። ጥፊቱ የተጠሪ በመሆኑ ኃላፉ ልንሆን አይገባም በማለት በሰበር አቤቱታው ገልጿል። ሆኖም ይህ አመልካች በሰበር ያቀረበው ክርክር ለስር ፍርድ ቤት ያልቀረበ አዱስ የፍሬ ጉዲይ መከራከሪያና የፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 329/1/ የሚቃረን በመሆኑ ሥርዓቱን ጠብቆ የቀረበ መከራከሪያ ሆኖ አላገኘነውም። ከዚህ በተጨማሪ አመልካች በወቅቱ አደጋው የደረሰው በተጠሪ ጥፊት ስለመሆኑ ያቀረቡት ማስረጃ የላለ መሆኑ በመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት እና በከፍተኛ ፍ/ቤት የተረጋገጠ በመሆኑ አመልካች በስር ፍ/ቤት ማስረጃ የማቅረብና ክርክሩን የማስረዲት ግዳታውን በአግባቡ ሳይወጣ በሰበር ያቀረበው ክርክር ለሰበር ችልት በህገመንግሥቱ አንቀፅ 80 ንዐስ አንቀጽ /ሀ/ እና አዋጅ ቁጥር 25/1988 የተሰጠውን ሥልጣን ከግንዛቤ ያላስገባና ህጋዊ መሰረት የላለው ሆኖ አግኝተነዋል።
አንድ ሰው የሚፈነደ ወይም መርዝ የሚሆኑ ቅመማት ሥራ ላይ በማዋል ወይም በማከማቸት ወይም ከፍተኛ ጉልበት ያለው የኤላክትሪክ መስመር በመዘርጋት ወይም መሬትን የተፈጥሮ መልክ በመለወጥ ወይም በተለይ አደገኛ የሆነ የኢንደስትሪ ሥራ በማካሄድ ይህ ሥራው በልላው ሰው ላይ አደጋ ያደረሰ እንደሆነ ለደረሰው ጉዲት ኃላፉ እንደሚሆን የፍታብሓር ህግ ቁጥር 2069/1/ የሚደነግግ ሲሆን ከዚህ በላይ የተዘረዘሩ ተግባራትን በመፈፀም በልላው ሰው ላይ ጉዲት ያደረሰው መንግሥትም ቢሆን ወይም ሥራውን እንዱሰራ በባለሥልጣን የተፈቀደለት መሥሪያ ቤት ቢሆንም በፍታብሓር ህግ ቁጥር 2069 ንዐስ አንቀጽ 1 የተደነገገው ደንብ ተፈፃሚ የሚሆን መሆኑን የፍታብሓር ህግ ቁጥር 2069 ንዐስ አንቀጽ 2 በግልፅ ይደነግጋል። አመልካች ከላይ በተገለፁት የህግ ድንጋጌዎች መሰረት ለደረሰው ጉዲት የኤላክትሪክ መስመሩ ባለሀብት በመሆኑ ብቻ ኃላፉ ተብል መወሰኑ ተገቢ አይደለም በማለት ያቀረበው የሰበር አቤቱታ ተገቢ ሆኖ አላገኘነውም።
አመልካች በጉዲቱ ካደረሰው ጉዲት በኃላፉት የማይጠይቀው የፍታብሓር ህግ ቁጥር 2086 ንዐስ አንቀጽ 2 በሚደነግገው መሰረት ጉዲቱ የደረሰው በሙለ ወይም በከፉል በተበዲዩ ጥፊት መሆኑን በማስረጃ በማስረዲትና በማረጋገጥ ነው። አመልካች ለጉዲቱ ኃላፉ አለመሆኑን ለማስረዲትም በመጀመሪያ የኤላክትሪክ መሥመሩን የሚንስትሮች ምክር ቤት ስለ ኤላክትሪክ ሥራዎች ባወጣው ደንብ ቁጥር 49/1991 አንቀጽ 35 ስለ ኤላክትሪክ መስመሮችና መሣሪያዎች ደህንነት የደነገገውን በሚያሟላ ሁኔታ ተዘርግቶ የነበረ መሆኑንና በዚሁ ደንብ አንቀጽ 41 ንዐስ አንቀጽ 1 መሰረት በስር ሁለተኛ ተከሣሽ በነበረው ግቢ ከምድር በላይ ዘርግቶት የነበረው መስመር የአደጋ መከላከያ ፔላስቲክ ተሸፍኖ የነበረ መሆኑንና ተጠሪ ጥፊት የሆነ አደጋ የሚያስከትል ተግባር በመፈፀሙ ምክንያት አደጋው የደረሰ መሆኑን የሚያስረዲ ማስረጃ በፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 234/1/ እና የፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 223 መሰረት ከመከላከያ መልስ ጋር ዘርዝሮ በማቅረብና የሰነድ ማስረጃዎቹን በፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 339/1/ በሚደነግገው መሰረት በማቅረብ የማስረዲት ግዳታውን መወጣት አለበት።
በያዝነው ጉዲይ አመልካች ከላይ በተገለፀው መሰረት አደጋው የደረሰው በተጠሪ ጥፊት መሆኑን የሚያስረዲ ማስረጃ ያላቀረበ መሆኑን በበታች ፍርድ ቤቶች የተረጋገጠ በመሆኑና የበታች ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሣኔ የፍታብሓር ህግ ቁጥር 2069 ድንጋጌዎች መሰረት ያደረገ በመሆኑ የከፍተኛ ፍርድ ቤትና ተጠሪ ለጉዲቱ ኃላፉነት አለበት በማለት የሰጠው ውሣኔና ለጉዲቱ የወሰነው የካሣ መጠን መሰረታዊ የህግ ስህተት የለበትም በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ ፀንቷል።
ይህ ፍርድ ቤት ሐምል 8 ቀን 2002 ዓ.ም. የሰጠው የዕግድ ትዕዛዝ ተነስቷል። ይጻፍ።
በዚህ ፍርድ ቤት ያወጡትን ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ ለየራሳቸው ይቻለ።
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.