No summary available.
ታህሳስ 15 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሐጏስ ወልደ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ብሓራዊ የመረጃና ደህንነት አገልግልት ነገረ ፈጅ መና ህብስቱ ቀረቡ ተጠሪ፡-
ወ/ሮ ሻልም ተስፊዬ 2 ርግዓእት ገብረእየሱስ
ብርቱካን ገብረእየሱስ አልቀረቡም።
ራዓዋ ገብረእየሱስ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የትግራይ ክልል የማዕከላዊ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት እና የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት የሰበር አቤቱታ ስላቀረቡ ነው።
የክርክሩ መሰታዊ ጉዲይ አመልካች እንደስላሴ ከተማ ቀበላ 02 ህንፃ ሰርቶ እንዱያስረክበው በሥር ፍርድ ቤት ሁለተኛ ተከሳች ለነበሩት አቶ አዱሱ አብርሀ በህንፃ ሥራ ውል ሰጥቷል። በሥር ሁለተኛ ተከሳሽ የነበሩት አቶ አዱስ አብርሀ የአንደኛ ተጠሪን ባለቤትና ስማቸው ከሁለተኛው ተራ ቁጥር እስከ አራተኛ ተራ ቁጥር የተገለፀውን ተጠሪዎች ወላጅ አባት አቶ ገብረእየሱስ አባይን ቀጥሮ ሥራ በመሥራት ላይ እያለ አቶ ገብረእየሱስ ነሐሴ 21 ቀን 2001 ዓ.ም በግንባታ ላይ ካለው ህንፃ ላይ ወድቀው በደረሰባቸው ጉዲት ወደ ሆስፑታል ከተወሰደ በኋላ ነሐሴ 22 ቀን 2001 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩ መሆኑ ተረጋግጧል። ተጠሪዎች አመልካች በግንባታ ላይ የሚገኘው ጅምር ህንፃ ባለቤት በመሆናቸው አቶ አዱሱ አብርሀ የሟች የአቶ ገብረእየሱስ አባይ ቀጣሪ በመሆናቸው በሟች መሞት ምክንያት ለደረሰብን ጉዲት ብር 154‚200 /አንድ መቶ ሀምሣ አራት ሺ ሁለት መቶ ብር/ እንዱከፍለን በማለት ክስ አቅርበዋል። አመልካች ሟች ህንፃውን ለመሥራት የተዋዋለው ሥራ ተቋራጭ ሰራተኛ በመሆናቸውና ከህንፃው ወድቀው ጉዲት የደረሰባቸው በመሆኑ በኋላፉነት የሚጠየቀው የሟች አሰሪ እንጅ እኔ አይደለሁም የሚል ክርክር አቅርቧል። የሥር ፍርድ ቤት ይህንን የአመልካች መከራከሪያ ውድቅ በማድረግ አመልካችና የሟች አሰሪ በአንድነትና በነጠላ ለጉዲቱ ሀላፉ ናቸው በሥር ፍርድ ቤት ሁለተኛ ተከሳሽ የነበሩት አቶ አዱሱ አብርሀና አመልካች በአንድነትና በነጠላ ለተጠሪዎች /ከሳሾች/ ብር 36‚000 /ሰላሣ ስድስት ሺ ብር/ የዲኝነትና ላልች ወጭዎችን በቁርጥ ፍርድ ቤቱ ወስኖ ይክፈለ በማለት ውሣኔ ሰጥቷል። አመልካች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አቅርበዋል። የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የአመልካችን ይግባኝ በፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 337 መሰረት ሰርዞታል።
አመልካች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ባቀረበው የሰበር አቤቱታ የህንፃው ባለቤት ከውል ውጭ በሀላፉነት ሉጠይቅ የሚቻለው ህንፃው ለሚያደርሰው ጉዲት ብቻ መሆኑ በፍታብሓር ሕግ ቁጥር 2077 ተደንግጓል። ህንፃው በአሰራር ጉድለት ፈርሶ ወይም የህንፃው ክፍል የሆነ ነገር ወድቆ በልላ ሰው ላይ ጉዲት ካደረሰ ከላይ በተጠቀሰው የህግ ድንጋጌ መሰረት ካሣ የመክፈል ሀላፉነት ይኖርብናል። በያዝነው ጉዲይ ሟች የኮንትራክተሩ ሰራተኛ ናቸው። ሟች ሥራ እየሰሩ እያለ ከህንፃው ላይ ወድቀው ለደረሰባቸው ጉዲት ህንፃውን ለተቋራጭ ሰጥቶ እየሰራ ያለው አመልካች በኃላፉነት የሚጠይቅበት የህግ አግባብ ሣይኖር ለደረሰው ጉዲት ሀላፉነት አለባችሁ ተብል የተሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር እንዱታረምልን በማለት አመልክተዋል።
ተጠሪ በበኩላቸው ሟች የሞተው ከህንፃው ላይ ወድቆ ነው። ሟች የወደቀው ህንፃው የተሰራበት ቶንዱኖ ብረት በመታጠፈ ምክንያት ነው። አመልካች በውሣኔው መሰረት ድርሻውን ከፍሎል።
ስለሆነም አመልካች ለደረሰው ጉዲት ኃላፉነት የለብኝም በማለት የሚያቀርበው ክርክር የሕግ መሰረት የለውም በማለት መልስ ሰጥተዋል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የቀረበው ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም መዝገቡን መርምረናል። መዝገቡን እንደመረመርነው አመልካች በሟች አቶ ገብረእየሱስ አባይ ላይ ለደረሰው ጉዲት ካሣ የመክፈል ኃላፉነት አለበት ወይስ የለበትም? የሚለው ጭብጥ መታየት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ሟች አቶ ገብረእየሱስ አባይ ለሞት የተዲረጉት የአመልካችን ህንፃ የሥራ ተቋራጭ ሆኖ የሚሰራው የሥራ ተቋራጭ ሰራተኛ ሆነው ህንፃውን እየሰሩ እያለ ከህንፃው ላይ ወድቀው ነው።
የማዕከላዊ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አመልካች ሟች ህንፃውን ከሚሰራው ኮንትራክተር ጋር በነበራቸው ውል መሰረት ህንፃውን ሲሰሩ ወድቀው ለደረሰባቸው የሞት አደጋ አመልካች ኃላፉ የሚሆነው በየትኛው የሕግ ድንጋጌ መሰረት እንደሆነ አልጠቀሱም በአመልካችና በሟች መካከል የውል ግንኙነት የላለ በመሆኑ አመልካች ለጉዲዩ ኃላፉ የሚሆነው ከውል ውጭ በሚመጣ ኃላፉነት የሕግ ድንጋጌዎች አመልካች ለጉዲዩ ኃላፉነት ያለበት መሆኑን የሚደነግጉ ከሆነ ብቻ ነው።
አመልካች እየተሰራ ያለው ጅምር ህንፃ ባለቤት መሆኑ አልተካደም። የአንድ ህንፃ ወይም ቤት ባለቤት ከውል ውጭ ኃላፉ የሚሆንበት መሰረታዊ መርህ በፍታብሓር ህግ ቁጥር 2077 ንዐስ አንቀጽ 1 ተደንግጓል። በዚህ ድንጋጌ ይዘት ‛የአንድ ህንፃ ባለሀብት ወይም ለይዞታ ሕንፃው ሉደርስ ይችላል ተብል ያልታሰበ ድንገተኛ ነገር ቢደርስም ይኸ ህንፃ ለሚያደርሰው ጉዲት ኃላፉ ነው“ የሚል ነው። ሟች በመገንባት ያለው ህንፃ በመፍረሱ ወይም የህንፃው አንድ ክፍል በመደርመሱ ምክንያት ጉዲት ደርሶባቸው የሞት አደጋ ያጋጠማቸው ሰው አይደለም። ሟችን የሞት አደጋ ያጋጠማቸው ህንፃውን የሚሰራው ኮንትራክተር ሰራተኛ ሆነው ህንፃውን በመሥራት ላይ እያለ ከህንፃው ላይ በመውደቃቸው ነው። ይኸም በመሆኑ የፍታብሓር ህግ ቁጥር 2077 ንዐስ አንቀጽ 1 ድንጋጌ ለዚህ ጉዲይ አግባብነት ተፈፃሚነት ያለው ድንጋጌ አይደለም።
ሟች አመልካች የሚያሰራውን ህንፃ በውል የመሥራት ግዳታ ካለበት የሥራ ተቋራጭ ጋር ባላቸው የአሰሪና ሰራተኛ ግንኙነት በሥራ ላይ እያለ ወድቀው የሞት አደጋ ደርሶባቸዋል።
ይኸም በአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ ቁጥር 377/96 ሥራ ላይ ለሚደርሱ ጉዲቶች ስለሚሰጡ ክፍያዎች በሚለው በምዕራፍ ሶስት ሥር የሚሸፈንና የሚተዲደር እንጅ በፍታብሓር ህግ ቁጥር 2077 ንዐስ አንቀጽ 1 ሥር የሚወድቅ አይደለም። በመሆኑም የማዕከላዊ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አመልካች በሟች አቶ ገብረእየሱስ አባይ ላይ ለደረሰው ጉዲት ሀላፉ ስለሆነ ለተጠሪዎች ካሣ መክፈል አለበት በማለት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት አለበት በማለት ወስነናል።
የትግራይ ብሓራዊ ክልል የማዕከላዊ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰጡት ውሣኔ ተሽሯል።
አመልካች ለተጠሪዎች ካሣ የመክፈል ግዳታና ሀላፉነት የለበትም በማለት ወስነናል።
በዚህ ፍርድ ቤት ያወጡትን ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ ለየራሳቸው ይቻለ።
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.