No summary available.
ህዲር 3 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ ተሻገር ገ/ሥላሴ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- አቶ ደላ ያሲን - ከጠበቃ መላኩ ገ/ሥላሴ ጋር ቀረቡ ተጠሪ፡- ወ/ሮ አበበች እሸቴ - ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የፋዳራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤትና የከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት ስላመለከቱ ነው። ጉዲዩ በመጀመሪያ የታየው በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ነው። በሥር ፍርድ ቤት አመልካች አንደኛ ተከሳሽ አቶ አማረ ዘውዳ ሁለተኛ ተከሳሽ አዋሽ ኢንሹራንስ አክስዮን ማህበር ጣልቃ ገብ በመሆን ተከራክረዋል።
ተጠሪ ለሥር ፍርድ ቤት ንብረቴ የሆነችውና የሰላዲ ቁጥር 3-47351 የሆነ አይሱዙ የህዝብ ማመላለሻ መኪና ሀምላ 8 ቀን 2000 ዓ.ም ከሱልልታ ወደ አዱስ አበባ ተሳፊሪዎች ጭኖ ሲጓዝ በሥር ፍርድ ቤት ሁለተኛው ተከሳሽ በሆነው አቶ አማረ ዘውዳ የአንደኛ ተከሳሽ ማለትም የአመልካች ንብረት የሆነውን ኮድ 3-27054 በደረሰበት ግጭት በተሣፊሪዎችና በአሽከርካሪው ላይ ጉዲት የደረሰባቸው ሲሆን መኪናው በወቅቱ ብር 132,000(አንድ መቶ ሰላሳ ሁለት ሺህ ብር) ግምት ያለው መኪና ወድሟል። መኪናውን አስጠግኖ ሥራ እንዱጀምር ለማድረግ 28,000 (ሀያ ስምንት ሺህ ብር) ወጥቷል። ስለሆነም ለመኪና የወጣው 160,000 እንደዚሁም ከሀምላ 8 ቀን 2000 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ህዲር 8 ቀን 2001 ያለው የተቋረጠ ገቢ በቀን 250(ሁለት መቶ ሀምሣ ብር) በድምሩ 190,000 እና ወደፉት በክርክሩ ሑደት የሚደርስ ጉዲት እንዱከፍለ ይወሰንልኝ በማለት ክስ አቅርበዋል። በክርክሩ ጣልቃ የገባው አዋሽ ኢንሹራንስ የመኪናዋ ግምት ብር 132,000 ነው በማለት ያቀረቡት ግምት ተገቢነት የለውም። ስለዚህ የአገልግልት ዘመኑ ተቀንሶ በመንገድ ትራንስፕርት ይገመት ከዚህ በተረፈ በወቅቱ ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) እንዱቀበለ ጠይቀናቸው እንቢ ያለ በመሆኑ ከዚያ በኋላ ክስ ማቅረባቸው ተገቢ አይደለም በማለት ተከራክሯል። አመልካችም በጣልቃገቡ የተነሱትን የመከራከሪያ ነጥቦች አንስተው ተከራክረዋል። የሥር ፍርድ ቤት አመልካችና ጣልቃገብ ግምቱን በተመለከተ ያቀረቡትን ክርክር ውድቅ በማድረግ መኪናውን አገልግልት ላይ ለማዋል ብር 25,000 ወጭ ተደርጓል። መኪናው በደረሰበት አደጋ ውሣኔ እስከተሰጠበት ጊዜ ድረስ የተቋረጠ ገቢ ብር 81,420 የቀረ በመሆኑ መከፈል አለበት። መኪናው ለተጠበቀበት ብር 7080 ተከሳሾች ይክፈለ በአጠቃላይ 245,500 (ሁለት መቶ አርባ አምስት ሺህ አምስት መቶ ብር) አመልካችና ጣልቃ ገብ እንዱከፍለ ከዚህ ውስጥ ብር 100,000(መቶ ሺህ ብር) ጣልቃ ገቡ አዋሽ ኢንሹራንስ አክሲዮን ማህበር ቀሪውን አንደኛ ተከሳሽ (አመልካች) ይክፈል በማለት ውሣኔ ሰጥቷል።
አመልካች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበዋል።
የከፍተኛው ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ የሥር ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ አፅንቶታል። አመልካች መጋቢት 14 ቀን 2002 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ መኪናው የ1985 ዓ.ም ሞዳል በመሆኑ ግምቱ 132,000 እንደማያወጣ ያቀረብኩትን ክርክር የሥር ፍርድ ቤት አላግባብ አልፍብኛል። መኪናዋን አስነስቼ ያቆምኳት ስለልታ ፕሉስ ጣቢያ አንስቶ ወስድ ለጥበቃ ገንዘብ አውጥቻለሁ በማለት ተጠሪ ላቀረቡት ክስ እኔ ሀላፉ መባላ ተገቢነት የለውም። መኪናው ሙለ በሙለ ወድሟል ተብል ሙለ ግምቱን ክፈለ ብል የሥር ፍርድ ቤት ከወሰነ በኋላ ለመስታወት ለወንበር ለጋራዥ ኪራይ ያወጡትን ገንዘብ ክፈለ ብል መወሰኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው። መኪናው በወር ሰላሣ ቀን አይሰራም ስለዚህ ኪሣራው ወሩን ሙለ እንደሚሰራ ተደርጎ መታሰቡ ስህተት ያለበት ነው። ክስ የቀረበበት ብር 190,000 ሆኖ እያለ ፍርድ ቤቱ ተጠሪ ዲኝነት ከጠየቁት በላይ መወሰኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልን በማለት አመልክተዋል።
ተጠሪ በበኩላቸው መኪናውን ከገዛሁት በኋላ ወንበር መስታወት ስላልነበረው ይህንን በማስተካከል ብር 25,000 (ሀያ አምስት ሺህ ብር) አውጥቻለሁ። አሁን ንብረቱን በፉት ባለው ዋጋ ለመተካት የሚቻል አይደለም መኪናው ላይ ጉዲት በመድረሱ ገቢ መቋረጡ የሚካድ አይደለም።
ስለዚህ ለተቋረጠ ጥቅም አመልካች ካሣ እንዱከፍለ መወሰኑ ተገቢ ነው። ስለሆነም የበታች ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለበትም በማለት መልስ ሰጥተዋል። አመልካች የመኪናው ሙለ ዋጋ ገምተው ከጠየቁ በኋላ ለእያንዲንደ የመኪና አካል ካሣ መጠየቃቸው በአግባቡ አይደለም። ከዚህ በተጨማሪ የመኪናውን ቅሪት እንድንወስድ ፍርድ ቤቱ ያልወሰነልን ወይም የቅሪት አካል ዋጋ እንዱቀነስልን ማድረግ ሲገባው ይህንን አለማድረጉ ተገቢ ባለመሆኑ ሰበር ችልቱ እንዱወስንልን በማለት የመልስ መልስ ሰጥተዋል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር በግራ ቀኙ መካከል የቀረበው የፅሐፍ ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም የበታች ፍርድ ቤቶች የወሰኑት የካሣ መጠን ስለካሣ አወሳሰን የተደነገጉትን የህግ ድንጋጌዎች መሰረት ያደረገ ነው ወይስ አይደለም? የሚለውን ጭብጥ በመያዝ ጉዲዩን መርምረናል። በጭብጥነት የያዝነውን መሰረታዊ ጉዲይ ለመፍታት የሥር ፍርድ ቤት መኪናዋ ለአገልግልት ለመብቃት ተጠሪ አወጣሁ ያለትን ወጭ አመልካች እንዱከፍለ መወሰኑ በአግባቡ ነው ወይስ አይደለም ተጠሪ ለመኪናዋ ማስጠበቂያ አወጣሁ ያለትን ወጭ አመልካች ለተጠሪ እንዱተኩ የሰጠው ውሣኔ ተገቢ ነው ወይስ አይደለም? መኪናዋ ላይ ጉዲት በመድረሡ ተጠሪ ያቀረባቸውን ገቢና የደረሰባቸው ጉዲትና አመልካች ሉከፍለት የሚገባውን የካሣ መጠን ለማስላት የተከተለው ስልት ህጋዊ መሰረት ያለው ነው ወይስ አይደለም? የሚለትን ነጥቦች በዝርዝር ማየት አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል።
የመጀመሪያውን ነጥብ በተመለከተ የበታች ፍርድ ቤቶች ንብረትነቱ የተጠሪ የሆነ የሰላዲ ቁጥር 3-47351 ተሳፊሪዎች ጭኖ ሲጓዝ በአመልካች መኪና የግጭት አደጋ ስለደረሰበት ሉጠገን በማይችል ሁኔታ የወደመ መሆኑን በውሣኔያቸው ገልፀዋል። የህዝብ ትራንስፕርት አገልግልት ይሰጥ የነበረው የተጠሪ ንብረት የሆነው መኪና አደጋው ሲደርስበት ሙለ ዋጋውና ግምቱ 132,000 (አንድ መቶ ሰላሣ ሁለት ሺህ ብር) እንደሆነ ተጠሪ በክሳቸው የገለፁ ሲሆን አመልካች ግምቱ የተጋነነ ነው የሚል ክርክር አቅርቧል። ሆኖም የሥር ፍ/ቤትም ሆነ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት የመኪናውን ጠቅላላ ዋጋ ብር 132,000 (አንድ መቶ ሰላሳ ሁለት ሺህ ብር) በመገመት ተጠሪ ያቀረቡት ክስ የተጋነነ አይደለም በማለት አመልካችና ጣልቃገብ ተከራካሪው መኪናው አደጋ ሲደርስበት የነበረውን ግምት ብር 132,000(አንድ መቶ ሰላሣ ሁለት ሺህ ብር) እንዱከፍለ ውሣኔ ሰጥቷል። ከዚህ በኋላ የሥር ፍርድ ቤት ለመኪና ወንበር የመስታወትና የቴክኒክ ዋጋ ብር 25,000 (ሀያ አምስት ሺህ ብር) አመልካች ከመኪናው ግምት በተጨማሪ እንዱከፍለ የሰጡት ውሣኔ በፍታብሓር ህግ ቁጥር 2091 ለደረሰ ጉዲት የሚከፈለው ካሣ በተበዲዩ ከደረሰው ጉዲት ጋር እኩል ሆኖ መመዘን እንዲለበት የተደነገገውን መሰረታዊ መርህ ያልተከተለ ሆኖ አግኝተነዋል። ተጠሪ ብር 25,000 (ሀያ አምስት ሺህ ብር) መኪናዋን ከገዛኋት በኋላ የህዝብ ትራንስፕርት አገልግልት እንድትሰጥ ለማድረግ ለወንበርና ለመስታወት ያወጣሁት ነው በማለት በይግባኝና በሰበር ተከራክረዋል። ሆኖም መኪናው አደጋ የደረሰበት የህዝብ ትራንስፕርት አገልግልት እየሰጠ ባለበት ወቅት ነው። መኪናው አደጋ በደረሰበት ጊዜ የሚያወጣው ወቅታዊ ግምት ብር 132,000(አንድ መቶ ሰላሣ ሁለት ሺህ ብር) ነው በማለት ተጠሪ ያቀረቡትን ግምት አመልካች ተቃውመው ፍርድ ቤቱ የተለያዩ ማስረጃዎችን ከመረመሩ በኋላ መኪናዋ የግጭት አደጋ በደረሰበት ጊዜ ወቅታዊ ግምት ዋጋው ብር 132,000(አንድ መቶ ሰላሣ ሁለት ሺህ ብር) ስለሆነ አመልካች ይክፈል በማለት ውሣኔ ሰጥቷል። ከዚህ በኋላ መኪናው ከመገጨቱ በፉት ተጠሪ ለእያንዲንደ የመኪና አካል በተናጠል ከፍየዋለሁ የሚለትን ገንዘብ በመደመር አመልካች ብር 25,000 (ሀያ አምስት ሺህ ብር) እንዱከፍል የሰጠው ውሣኔ በተጠሪ መኪና ከደረሰው ጉዲት በላይ አመልካችን ካሣ እንዱከፍለ የሚያስገድድና በፍታብሓር ህግ ቁጥር 2091 የተደነገገውን መሰረታዊ መርህ የሚጥስ ሆኖ አግኝተነዋል።
የበታች ፍርድ ቤቶች አመልካች ተጠሪ መኪና ያስጠበቁበት ብር 7080 (ሰባት ሺህ ሰማንያ ብር) ለተጠሪ እንዱከፍለ የሰጡትን ውሣኔ በተመለከተ ተጠሪ ለመኪና መጠበቂያ ከፍያለሁ ያለትን ገንዘብ ወጭ ያደረጉት አደጋ ከመድረሱ በፉት መኪናቸውን ለማስጠበቅ ያወጡትን ገንዘብ በመደመር የጠየቁት መሆኑን ወይም ገንዘቡን የከፈለት የመኪናውን ቅሪት ለማስጠበቅ መሆኑን ሣያጣሩ ውሣኔ የሰጡ ሆኖ አግኝተነዋል። ተጠሪ መኪናቸው ከመገጨቱ በፉት የመኪናቸውን ደህንነት ለማስጠበቅ የከፈለትን ገንዘብ አመልካች እንዱተኩላቸው የመጠየቅ መብት የላቸውም።
በልላ በኩል አመልካች የመኪናዋ ቅሪት አካል ሱልልታ ፕሉስ ጣቢያ ያስቀመጡት መሆኑን በመግለፅ ያቀረቡትን ክርክርና የሰበር አቤቱታ ተጠሪ በግልፅ በመካድ መልስ አልሰጡበትም።
ጉዲቱ የደረሰ መሆኑንና በጉዲቱ የደረሰ ኪሣራ የማስረዲት ግዳታ ያለበት ካሣ እንዱከፈለው የሚጠይቀው ሰው እንደሆነ የፍታብሓር ህግ ቁጥር 2141 ይደነግጋል። ተጠሪ ለመኪናው ማስጠበቂያ አወጣሁ ያለት ወጭ መቼና በምን ሁኔታ እንዲወጡትና በተለይም ወጭውን ያወጡት በአደጋው ምክንያት መሆኑን የሚያስረዲ ማስረጃ ባላቀረቡበት ሁኔታ (Burdon of Presentation of Evidence) ባልተወጡበት ሁኔታ የበታች ፍርድ ቤቶች አመልካች ተጠሪ ለመኪና መጠበቂያ አውጥቻለሁ ያለትን ብር 7080(ሰባት ሺህ ሰማኒያ ብር) እንዱከፍለ የሰጡት ውሣኔ የፍታብሓር ህግ ቁጥር 2141 እና የፍታብሓር ህግ ቁጥር 2091 ድንጋጌን መሰረት ያላደረገና ተገቢነት የላለው ሆኖ አግኝተነዋል።
ተጠሪ ይህንን ገንዘብ በቅንነት በመቀበል ቀረብኝ የሚለትን ገንዘብ ከአመልካች መጠየቅ የሚችለበት እድል በኢንሹራንስ ድርጅቱ ተሰጥቷቸዋል። በተበዲይ ላይ ለደረሰ ጉዲት የሚከፈለው ካሣ ለቅን ልቦና ተቃራኒ በሆነ አኳኋን ሉጠየቅ የማይገባ መሆኑ የፍታብሓር ህግ ቁጥር 2097 ንዐስ አንቀፅ 1 ይደነግጋል። ተጠሪ አዋሽ ኢንሹራንስ (አ.ማ) ከአመልካች ጋር ያለውን የመድን ውልና በውለ ላይ ያለውን ጣሪያ መሰረት በማድረግ እንዱቀበለት የጠየቃቸውን ብር 100,000(አንድ መቶ ሺህ ብር) በቅንነት ቢቀበለ ገቢ በመቋረጡ ምክንያት የደረሰባቸውን ኪሣራ ሉያስቀሩት ወይም ሉቀንሱት የሚችለበት አቅም ይፈጥርላቸው ነበር። ተጠሪ ይህንን ባለማድረጋቸውና ወደ ክርክር መግባት የማይፈልገውን አዋሽ ኢንሹራንስ (አ.ማ) በጣልቃ ገብ ተከራካሪነት እንዱጠራ የሚያስገድድና ስድስት ወር የፈጀ ክርክር ከአመልካች ጋር ለማድረግ ተገደዋል። ላላ ሰው ኃላፉ በሆነበት ድርጊት ወይም አደጋ ጉዲት የደረሰበት ሰው ጉዲቱን ለማስቀረት ወይም የጉዲቱን መጠን ቀላል ለማድረግ ግዳታና ሀላፉነት እንዲለበት የፍታብሓር ህግ ቁጥር 2097 ንዐስ አንቀፅ 2 ተበዲዩ በማስተዋል ቢሰራ ኖሮ የደረሰበትን ጉዲት ሉያግደው ወይም ሉያቀለው የሚችል ሲሆን በደረሰበት ጉዲት መጠን በሙለ ካሣ ለመጠየቅ አይችልም በማለት በግልፅ ደንግጎታል። ተጠሪ በግጭቱ ጉዲት የደረሰበት መኪና ጠቅላላ ዋጋ ብር 132,000 መሆኑ ተረጋግጧል። ተጠሪ ከዚህ ውስጥ አዋሽ ኢንሹራንስ ለመክፈል ሙለ ዝግጁነቱን ያሣየበትን ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) ተቀብለው ቢሆን ኖሮ ከዚህ ገንዘብ ላላ ገቢ የሚያስገኝ ሥራ በመሥራት ወይም በዚህ ገንዘብ አነስተኛ መጠን ያለው ላላ መኪና በመግዛት ወይም ተጨማሪ ገንዘብ ተበድረው አደጋ የደረሰበትን መኪና ምትክ በመግዛት በአደጋው ምክንያት የተቋረጠባቸውን የገቢ መጠን ለመቀነስ እየቻለ ገንዘቡን ለመቀበል እንቢተኛ በመሆናቸው ምክንያት ኪሣራውን ለማስቀረት ወይም ሉያቀለት እንዲልቻለ ለመገንዘብ ችለናል።
ስለሆነም የበታች ፍርድ ቤቶች ከላይ የጠቀስነውን የህግ ድንጋጌ ግምት ውስጥ ሣያስገቡ ተጠሪ በአደጋው ምክንያት የተቋረጠባቸውን ገቢ አደጋው ከደረሰበት ቀን ጀምሮ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ውሣኔ እስከሰጠበት ጊዜ ድረስ ያለውን በሙለ አስበው የሰጡት ውሣኔ የህግ መሰረት ያለው ሆኖ አላገኘነውም። ስለሆነም ተጠሪ አዋሽ ኢንሹራንስ (አ.ማ) አደጋው እንደደረሰ እንዱቀበለ የጠየቃቸውን ብር 100,000 (መቶ ሺህ ብር) ቢቀበለ ኖሮ መኪናው በአደጋ በመውደሙ ምክንያት ሉያገኙት የነበረው ገቢ ከሶስት ወር በላይ ተቋርጦ የሚቀጥልበት ሁኔታ እንደማይኖር የነገሮችን ተራ ሁኔታዎችና ተጠሪ ተገቢውን ጥረት ያላደረጉና የቅንልቦና ጉድለት ያለባቸው መሆኑን በማገናዘብ በፍታብሓር ህግ ቁጥር 2097(2) ወስነናል። ስለሆነም አመልካች ተጠሪ ለቀረባቸው ጥቅም መክፈል የሚገባው የካሣ መጠን በቀን ብር 230(ሁለት መቶ ሰላሳ ብር) ሑሳብ የዘጠና ቀን ቀሪ ገቢ በድምሩ ብር 20,700(ሀያ ሺህ ሰባት መቶ ብር) ብቻ መሆን ይገባዋል በማለት በፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 348(1) አሻሽለን ወስነናል።
በአጠቃላይ ከላይ በተራ ቁጥር 1 እና በተራ ቁጥር 2 በተገለፁት ነጥቦች የበታች ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የካሣ አወሳሰን መርሆችን መሰረት ያላደረጉና ተገቢነት የላላቸው በቁጥር 3 የተመለከተው ነጥብ ደግሞ ተጠሪ በመኪናው መውደም ምክንያት የተቋረጠባቸውን የገቢ መጠን ለመቀነስ ወይም ለማቅለል የፍታብሓር ህግ ቁጥር 2097 ንዐስ አንቀፅ 2 በሚደነግገው መሰረት በቅን ልቦናና በአስተዋይነት ያደረጉት እንቅስቃሴ የላለ መሆኑን ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት የበታች ፍርድ ቤቶች ውሣኔ ያልሰጡና ውሣኔያቸው በከፉል መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበትና ሉሻሻል የሚገባው ነው በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትና የከፍተኛ ፍርድ ቤት የካሣውን መጠን በተመለከተ የሰጡት ውሣኔ ተሻሽሎል።
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትና የከፍተኛው ፍርድ ቤት አመልካች የተጠሪ መኪና አደጋ በደረሰበት ወቅት የነበረውን ግምት ብር 132,000(አንድ መቶ ሰላሳ ሁለት ሺህ ብር) ይክፈል ከዚህ ውስጥ በሥር ጣልቃ ገብ ተከራካሪ የሆነው አዋሽ ኢንሹራንስ (አ.ማ) ብር 100,000(አንድ መቶ ሺህ ብር) ይክፈል በማለት የሰጡት ውሣኔ ፀንቷል።
አመልካች ተጠሪ ለመኪናው ወንበር መስታወትና የማስጠገኛ ያወጡትን ብር 25,000(ሀያ አምስት ሺህ ብር) እንደዚሁም ተጠሪ መኪናውን ለማስጠበቅ ያወጡትን ብር 7080(ሰባት ሺህ ሰማኒያ ብር) እንዱከፍለ በማለት የበታች ፍርድ ቤቶች የሰጡት የውሣኔ ክፍል ሙለ በሙለ ተሽሯል። ስለሆነም አመልካች ከላይ የተገለፀውን ብር 32,080 (ሰላሣ ሁለት ሺህ ሰማኒያ ብር) ለተጠሪ የመክፈል ኃላፉነት የለባቸውም በማለት ወስነናል።
የበታች ፍርድ ቤቶች ተጠሪ መኪናቸው ከጥቅም ውጭ በመሆኑ ምክንያት ተጠሪ ለተቋረጠባቸው ገቢ ብር 81,420(ሰማኒያ አንድ ሺህ አራት መቶ ሀያ ብር) አመልካች እንዱከፍል በማለት የሰጡትን ውሣኔ አሻሽለን አመልካች በቀን ብር 230(ሁለት መቶ ሰላሳ ብር) ታስቦ የዘጠና ቀናት የተቋረጠ ገቢ ብር 20,700(ሀያ ሺህ ሰባት መቶ ብር) ብቻ የመክፈል ሀላፉነት አለበት ብለናል።
በአጠቃላይ በዚህ ውሣኔ መሰረት አመልካች ለተጠሪ የሚከፍለት በሁለተኛ ተራ ቁጥር እንዱከፍለ የተወሰነባቸውን እና በተራ ቁጥር 4 የተወሰነባቸው 20,700 በድምሩ ብር 52,700(ሀምሳ ሁለት ሺህ ሰባት መቶ ብር) ብቻ ነው ብለናል።
በዚህ ፍርድ ቤት ያወጡትን ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ ለየራሳቸው ይቻለ።
No topics extracted.