No summary available.
ሰኔ 14 ቀን 2ዐዐ3ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- ሸበል ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ጠበቃ ብናልፈው ነጋ - ቀረቡ ተጠሪ፡- የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዐቃቤ ህግ ተወዲጅ ሲማ - ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት ያቀረበውን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው። ጉዲዩ በአመልካች አቤቱታ አቅራቢነት ለግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ ቀርቦ የግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ አመልካች ያቀረባቸውን ሶስት መሰረታዊ ክርክሮች ውድቅ በማድረግ ወስኗል አመልካች የግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤው ተጠሪ የተጨማሪ እሴት ታክስ በግምት መወሰኑን ፣ ተጠሪ አመልካች ቅጣት እንዱከፍል መወሰኑና የተጨማሪ እሴት ታክስ ከመዝገቡ በፉት የሽያጭ ታክስ የተከፈለበትን አለመቀነሡን በመቃወም ያቀረብኩትን የህግ ክርክር አልፍብኛል በማለት ለፋደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ አቅርቧል። የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአመልካችን አቤቱታ በመዝገብ ከመረመረ በኋላ ተጠሪ አመልካች እንዱከፍል በግምት የወሰነውን የተጨማሪ እሴት ታክስ ውሣኔ ማስታወቂያ አዋጅ ቁጥር 285/94 አንቀፅ 12/1/ የሚጥስ ነው በማለት ሽሮታል። ተጠሪ አመልካች የተለያዩ ቅጣቶች እንዱከፈል የሰጠው ውሣኔ የህግን ድንጋጌ የተከተለ አይደለም በማለት በግልፅ ሽሮታል።
የከፍተኛው ፍርድ ቤት አመልካች በሽያጭ ታክስ መልክ ገቢ የሆነው ገንዘብ ከተጨማሪ እሴት ታክስ ሉቀነስልኝ ይገባል በማለት ያቀረበውን ክርክር በማጣራት ተገቢውን ውሣኔ እንዱሰጥበት በማለት ጉዲዩን ለግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ በፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 343/1/ መሰረት መልሶ ልኮለታል።
ለዚህ የሰበር ክርክር መነሻ የሆነው ውሣኔ የግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ታህሣሥ 17 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም በሰጠው ውሣኔ መሰረት ጉዲዩን አጣርቶ መስከረም 29 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ ነው። የግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ አግባብነት ያላቸው ሰነድችን በማስቀረብ ተገቢውን ማጣራትና ምርመራ ካደረገ በኋላ አመልካች ታህሣሥ 23 ቀን 1995 ዓ.ም የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ሆንም የተጨማሪ እሴት ታክስ ያስታወቀው ነሐሴ 13 ቀን 1995 ዓ.ም ነው። በዚህን ጊዜ በቅፅ 2ዐ2 ያስታወቀው የሰኔ ወር 1995 እንቅስቃሴን እንጅ በህጉ መሰረት ሉመለስለት የሚገባውን የሽያጭ ታክስ በመዘርዘር የሽያጭ ታክሱ እንዱመለስለት ጥያቄ አላቀረበም። ስለሆነም አመልካች በተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 285/94 እና ደንብ ቁጥር 79/95 መሰረት ማስታወቅና ጥያቄ ማቅረብ በሚገባበት የጊዜ ገደብ ውስጥ ያሳወቀ በመሆኑ በሽያጭ ታክስ የከፈልኩት ይቀነስልኝ በማለት ያቀረበው ጥያቄ የህግ መሰረት የለውም በማለት ውሣኔ ሰጥቷል።
አመልካች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፋደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርቧል።
የከፍተኛ ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክር በመዝገብ ከሰማ በኋላ የጉባኤውን ውሣኔ ጥቅምት 12 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም በሰጠው ውሣኔ አፅንቶታል። አመልካች ይግባኝ ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አቅርቧል። ይግባኝ ሰሚው ችልት የአመልካች መቶ ፏርሰንት ግብር አልከፈለም በማለት ይግባኙን በፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 337 ድንጋጌ ጠቅሶ ሰርዞታል።
አመልካች ነሐሴ 21 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ አመልካች የተጨማሪ እሴት ታክስ ሥራ ላይ ከመዋለ ከስድስት ወር በፉት ተገዝተው በነበሩ ዕቃዎች የከፈለውና በህጉ አግባብ ሉቀናነስለት የሚገባውን የሽያጭ ታክስ ተጠሪ ሲያቀናንስለት ከቆየ በኋላ እንቢተኛ ሆኗል።
የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በሽያጭ ታክስ የተከፈለውን እንዱቀናነስልን የምንከራከር ሆኖ እያለ መቶ ፏርሰንት ግብር ሣይከፍል የቀረበ ይግባኝ በመሆኑ ይግባኙ አይታይም በማለት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው ስለሆነም በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት አመልክቷል። ተጠሪ በበኩለ ህዲር 28 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም በተፃፈ መልስ አመልካች ግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ እንዱከፍላቸው የሚፈልገው ገንዘብ የግብር ገንዘብ በላለበት ሁኔታ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሥራ ላይ ከመዋለ ከስድስት ወር በፉት የከፈልኩት የሽያጭ ታክስ እንዱቀናነስልኝ ያቀረብኩትን ጥያቄ መቶ ፏርሰንት ግብር ከፍለህ አልቀረብክም ብል ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ውድቅ አደረገብኝ በማለት የሚያቀርበው ክርክር ተገቢ አይደለም አመልካች ብር 9,652,121.44 ተጨማሪ እሴት ታክስ እንዱከፍል ተጠሪ የሰጠውን የግብር ውሣኔ ማስታወቂያ ግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤው አፅንቶታል። ስለሆነም አመልካች ይህንን የግብር ገንዘብ መቶ ፏርሰንት ሣይከፍል ይግባኙ እንደማይታይለት በመግለፅ የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጠው ውሣኔ የአዋጅ ቁጥር 285/94 ድንጋጌዎችን መሰረት ያደረገና የህግ ስህተት የላለበት ነው በማለት ተከራክሯል።
አመልካች ጥያቄው የይቀናነስልኝ ጥያቄ በመሆኑ መቶ ፏርሰንት የሚከፈል ግብር የለም።
ይኸም ቢታለፍ አመልካች ግብሩን ከፍል እንዱቀርብ ላደረግ ይገባው ነበር ታህሣሥ 20 ቀን 2003 ዓ.ም የመልስ መልስ አቅርቧል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የቀረበው ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም ይግባኝ ሰሚው ችልት የሰጠው ትዕዛዝ ተገቢ ነው ወይስ አይደለም? በማለት ጭብጥ በመያዝ ጉዲዩን መርምረናል። ጉዲዩን እንደመረመርነው አመልካች የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ሥራ ላይ ከመዋለ ከስድስት ወራት በፉት በአመልካች እጅ በነበሩት ዕቃዎች ላይ ተከፍል የነበረው የሽያጭ ታክስ ሉቀናነስልኝ ይገባል በማለት የሚከራከረው ተጠሪ ወስኖ ካሣወቀው የተጨማሪ እሴት ታክስ ግብርና በግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤው ከፀደቀው የግብር ውሣኔ መሆኑን በሥርና በዚህ ፍርድ ቤት በግራ ቀኙ ከተደረገው ክርክር ለመገንዘብ ችለናል። በተጨማሪ እሴት ታክስ በግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ በተሰጠ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ለፍርድ ቤት ይግባኝ የሚቀርብበት ሥርዓት በግብር ይግባኝ አዋጅ ቁጥር 286/94 አግባብነት ያላቸው ድንጋጌዎች ተፈፃሚነት ያላቸው መሆኑን አዋጅ ቁጥር 285/94 በአንቀፅ 43 ንዐስ አንቀፅ 4 በግልፅ ይደንግጋል።
የግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ ውሣኔ የህግ ስህተት አለበት የሚል ቅሬታ ያለው ግብር ከፊይ ይግባኙን ሥልጣን ላለው ፍርድ ቤት የሚያቀርበው በግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤው የተወሰነበትን የግብር ገንዘብ ሙለ በሙለ ሲከፈል መሆኑ በአዋጅ ቁጥር 286/1994 አንቀፅ 112 ንዐስ አንቀፅ 4 ተደንግጓል። ስለሆነም አመልካች በግብር ይግባኝ ጉባኤ እንዱከፍል የተወሰነበትንና የተጨማሪ እሴት ታክስ ግብር ሙለ በሙለ የከፈለ መሆኑ ይግባኙን ለይግባኝ ሰሚው ችልት ለማቅረብ በህግ የተደነገገ ቅድመ ሁኔታ ነው። የአመልካች ጥያቄ የሽያጭ ታክስ ከተጨማሪ እሴት ታክስ እንዱቀናነስልኝ የቀረበ ነው በሚል ምክንያት በግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤው የተወሰነበትን የተጨማሪ እሴት ግብር ሙለ በሙለ መክፈለን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማያያዝ የቀረበውን ይግባኝ በተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 285/94 አንቀፅ 43 ንዐስ አንቀፅ 4 እና በገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 286/94 አንቀፅ 112 ንዐስ አንቀፅ 4 የተደነገገውን ቅድመ ሁኔታ ሣይሟላ የቀረበ ነው በማለት ይግባኝ ሰሚው ችልት መሰረዙ ከላይ የጠቀስናቸውን የህግ ድንጋጌዎች መሰረት ያደረገና ምንም አይነት የህግ ስህተት ያልተፈፀመበት ነው።
አመልካች ለይግባኝ ሰሚው ችልት ይግባኙን ከማቅረቡ በፉት በህግ የተጣለበትን ቅድመ ሁኔታ ያሟላ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ የማቅረብ ግዳታ አለበት። አመልካች በህጉ የተቀመጠውን ቅድመ ሁኔታ ሣያሟላ የይግባኝ መዝገብ አስከፍቶ ያገኘው ይግባኝ ሰሚው ችልት አመልካች ቅድመ ሁኔታውን አሟልቶ እንዱመጣ ትዕዛዝ ሰጥቶ አመልካች ቅድመ ሁኔታውን አሟልቶ የሚመጣ መሆኑን ለመጠባበቅ ቀጠሮ ሰጥቶ እንዱጠባበቅ የሚያስገድድው የህግ ድንጋጌ የለም። ይግባኝ ባይ ይግባኙን ለማቅረብ ሟሟላት የሚገባውን ቅድመ ሁኔታ ሣያሟላ ይግባኝ እንዲቀረበ ከተረዲ የህጉ የተደነገገውን ግዳታ ሣያሟላ ይግባኝ ባይ ያቀረበውን ይግባኝ በመሰረዝ መዝገቡን መዝጋት እንደሚችል ከአዋጅ ቁጥር 285/94 አንቀፅ 43 ንዐስ አንቀፅ 4 እና ከአዋጅ ቁጥር 286/94 አንቀፅ 112 ንዐስ አንቀፅ 4 ድንጋጌዎች የጣምራ ንባብ መንፈስና ዓላማ ለመገንዘብ ይቻላል። ስለሆነም ይግባኙን ለይግባኝ ሰሚው አቅርቦ ለማሰማት በህግ የተደነገገውን ቅድመ ሁኔታ ያሟላ መሆኑን የማስረዲተና የማረጋገጥ ግዳታ ያለበት አመልካች በህጉ የተቀመጠውን ቅድመ ሁኔታና ግዳታ ሣይፈፅም ያቀረበውን ይግባኝ ይግባኝ ሰሚው ተቀብል አለመሰማቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት አለበት በማለት የቀረበው የሰበር አቤቱታ የህግ መሰረትና ድጋፍ ያለው ሆኖ አላገኘነውም። ከዚህ በተጨማሪ ጉዲዩ ለሰበር ሲቀርብ በሰበር ችልት የተጠቀሱት የደንብ ቁጥር 79/95 አንቀፅ 5 ፣ አንቀፅ 8 እና አንቀፅ 9 አመልካች ከፍያዋለሁ የሚለው የሽያጭ ግብር ከተጨማሪ እሴት ታክስ ግብሩ ሉቀናነስለት ይገባል ወይስ አይገባም የሚለውን መሰረታዊ ጭብጥ በመወሰን ሑደት ግንዛቤ ውስጥ ሉገቡ የሚገቡ የህግ ድንጋጌዎች ናቸው በዚህ መዝገብ የተያዘውን ጭብጥ ማለትም የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አመልካች የተወሰነበትን የተጨማሪ እሴት ታክስ ሙለ በሙለ ሣይከፈል ያቀረበው ይግባኝ በህግ የተቀመጠውን ቅድመ ሁኔታ የሚያሟላ አይደለም ብል ይግባኙን መሰረዙ ተገቢ ነው ወይስ አይደለም የሚለውን ጭብጥ ለመወሰን አግባብነት ያላቸው የህግ ድንጋጌዎች ሆነው አላገኘናቸውም።
ስለሆነም የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጠው ትዕዛዝ አዋጅ ቁጥር 285/94 አንቀፅ 43 ንዐስ አንቀጽ 4 እና አዋጅ ቁጥር 286/94 አንቀፅ 112 ንዐስ አንቀፅ 4 ድንጋጌዎችን ይዘት፣ መንፈስና ዓላማ ያገናዘበና መሰረታዊ የህግ ስህተት የላለበት ነው በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ትዕዛዝ ፀንቷል።
በዚህ መዝገብ ያወጡትን ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ ለየራሳቸው ይቻለ ብለናል።
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.