No summary available.
ሰኔ 30 ቀን 2003 ዓ/ም ዳኞች፡- ሒጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- የኢ.ፋ.ዱ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር ተጠሪ፡-
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
የሰበር አቤቱታው የቀረበው የፋዳራለ ሲቪል ሰርቪስ ኤጄንሲ አስተዲደር ፍርድ ቤት በይ/መ/ቁጥር00944/2002 ሚያዚያ 15 ቀን 2002 ዓ/ም በሰጠው ውሳኔና የፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ጉዲዩን በይግባኝ አይቶ የሲቪል ሰርቪስ ኤጄንሲ አስተዲደር ፍርድ ቤት ውሳኔ ባግባቡ ነው ሲል በፍ/ይ/መ/ ታህሳስ 26 ቀን 2003 ዓ/ም በሰጠው ውሳኔ ላይ ነው።
ለሰበር አቤቱታው ምክንያነት የሆነው ጉዲይም አገልግልትና የእድሜ መስፈርቱን የማያሟለ ሰራተኞች ከስራ ሲሰናበቱ የመልሶ ማቋቋሚያ ድጋፍ እንዱያገኙ ሲደረግ በክፍያው ላይ የስራ ግብር ሉቀነስ ይገባል ወይስ አይገባም በሚለው ላይ የሲቪል ሰርቪስ አስተዲደር ፍርድ ቤትም ሆነ የፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የስራ ግብር ሉቀነስ አይገባም በማለት ውሳኔ በመስጠታቸው ነው።በዚህ መሰረት በቀረበው አቤቱታ መነሻነት ጉዲዩ ለሰበር ይቀርባል የተባለው ይህንኑ ነጥብ ለማጣራት ሲሆን አግባብ ካለው ሕግ ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ ተመርምሯል። ለዚህም ስለገቢ ግብር የሚደነግገውን የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 286/94 መመልከቱ ተገቢ ነው። በአዋጁ አንቀጽ 10(1) ስር በግልፅ እንደተመለከተው ማንኛውም ሰው በመቀጠር ምክንያት በሚያገኘው ማናቸውም ገቢ ላይ የገቢ ግብር ይከፍላል በማለት ተቀምጧል። ከግብር ክፍያ ነጻ የሆኑትን አስመልክቶ በአዋጁ አንቀጽ 13 ላይ በዝርዝር ሲገልጽ አሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበበትን ጉዲይ አይነት በግልፅ ከስራ ግብር ነፃ ስለመሆኑ አይጠቅስም። ይህ አንቀፅ ከግብር ክፍያ ነፃ የሆኑትን ከዘረዘራቸው ውስጥ ማናቸውንም አይነት የጡረታ ጥቅም፣ወይም በተቀባዩ ሰው ላይ በደረሰ የአካል ጉዲት ካሳ ወይም በልላ ሰው ላይ በደረሰ የሞት አደጋ የሚሰጥ የካሳ ክፍያ የሚለት ይገኙበታል።የካሣ ክፍያ ሲባልም በሕጉ ላይ በግልፅ እንደተመለከተው በደረሰ የአካል ጉዲት ወይም በደረሰ የሞት አደጋ የሚሰጥ የካሳ ክፍያ የሚመለከት እንጂ ማናቸውንም የካሳ ክፍያ ሁለ ከግብር ነጻ መሆኑን የሚጠቅስ አይደለም።በመሰረቱ የስራ ግብር የሚከፈለው ማንኛውም ሰው በመቀጠር ምክንያት በሚያገኘው ማናቸውም ገቢ ላይ ስለመሆኑ አዋጅ ቁጥር 286/94 አንቀጽ 10(1) በግልፅ ያሰፈረው ሲሆን አዋጁ ገቢን አስመልክቶ በሰጠው የትርጉም ክፍል ላይ ገቢ ማለት ማናቸውም የኢኮኖሚ ጥቅም ሲሆን በመደበኛነት የተገኘ ባይሆንም ከማናቸውም ምንጭ በጥሬ ገንዘብ ወይም በአይነት በማናቸውም መልክ ለግብር ከፊዩ የተከፈለው በስሙ የተያዘለትን ወይም የተቀበለውን ጥቅም ሁለ እንደሚጨምር እንዱሁም ግብር የሚከፈልበት ገቢ ማለት ደግሞ በአዋጁና በአዋጁ መሰረት በሚወጡት ደንቦች መሰረት ማናቸውም ወጪ እና ላልች ተቀናሽ ሂሳቦች ከተቀነሱ በኋላ የሚቀረው የገቢ መጠን መሆኑ አዋጁ በአንቀጽ 2(10) እና 1(11) አስፍሯል። በመሆኑም ለተጠሪዎች ይከፈል የተባለው የመቋቋሚያ ክፍያ ግብር የሚከፈልበት ገቢ ነው ለማለት የሚያስችል የሕግ መሰረት አላገኘንም።በዚህም መሰረት በጉዲዩ ላይ በተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈፅሟል ለማለት ስላልተቻለ ተከታዩን ወስነናል።
በጉዲዩ ላይ የተሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1)መሰረት ፀንቷል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.