No summary available.
መስከረም 27 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሐጎስ ወልደ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- የሚላ ገቢዎችና ጉምሩክ - ዓ/ህግ ግርማ መርሃ - ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ደረጀ ከፍያለው ሲማ - ከጠበቃ በላቸው ታደሰ ጋር - ቀረቡ መዝገቡን መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተጠሪ ከተከሰሰበት የኮንትሮባንድ ወንጀል በነፃ የተሰናበተ ቢሆንም በአዋጅ ቁጥር 622/2001 አንቀጽ 104/3/ሀ መሰረት ተሽከርካሪው እንዱወረስ በስር ፍ/ቤቶች አለመወሰናቸው የሕግ ስህተት ነው በሚል እንዱታረም ጠይቋል።
ለሰበር አቤቱታ መነሻ የሆነው ክስ የቀረበው በአመልካች በኩል ነው። የክሱ መነሻም ንብረትነቱ የተጠሪ የሆነ የሰላዲ ቁጥር ኮድ 3-15475 ኦሮ. ቅጥቅጥ አይሱዙ የሕዝብ ማመላለሻ መኪና ከሐረር ወደ አ/አ ሲጓዝ አዋሽ ጉምሩክ ፍተሻ ላይ የጉምሩክ ሥነ ሥርዓት ያልተፈፀመበትን የኮንትሮባንድ እቃ ጭኖ በመገኘቱ በጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 622/2001 አንቀጽ 91/1/ መሰረት ሾፋሩ፣ ረዲቱ እና 3ኛ ተከሳሽ /ባለንብረቱ/ በኮንትሮባንድ ወንጀል ተከሰዋል። የአፊር ክልል ከፍተኛ ፍ/ቤት የግራ ቀኙን ማስረጃ ከሰማ በኋላ የስር 1ኛ እና 2ኛ ተከሳሾች ጥፊተኛ ናቸው ብል የቅጣት ውሳኔ ሰጥቷል። 3ኛ ተከሳሽ /ባለንብረቱ/ የአሁኑ ተጠሪን ጥፊተኛ የሚያሰኝ ድርጊት አልፈፀመም በማለት ከክሱ በነፃ አሰናብቷል። የፋዳራለ ከፍተኛ ፍ/ቤት ይህንኑ ውሳኔ አጽንቷል።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረቱ ይኽው ሆኖ ተጠሪው ከወንጀል ተጠያቂነት ነፃ ቢባልም የኮንትሮባንድ እቃ የጫነው /ያጓጓዘው/ መኪና እንዱወርስ ሉወሰን ይገባ ነበር የሚል ነው።
የሰበር ችልቱም አቤቱታውን መርምሮ ስለንብረቱ መወረስ ወይም አለመወረስ ትዕዛዝ አለመሰጠቱ ተገቢነት ከተጠቀሰው ድንጋጌ አንፃር ለመመርመር ተጠሪ እንዱቀርብ አዝዟል።
ተጠሪው ነሐሴ 17 ቀን 2002ዓ.ም ባቀረበው የጽሐፍ መልስ በጉምሩክ ሕግ ገደብ የተደረገበት ወይም ቀረጥ ያልተከፈለበት እቃ የተጫነው በሹፋሩ እና በረዲቱ እንጂ በተጠሪ አለመሆኑን እንዱሁም የእቃ መደበቂያ /ሻግ/ ተሰራ የተባለው ለክሪክ፣ ለሸራና ለጎማ በተሰራ መያዣ መሆኑና ድርጊቱ የተፈፀመው ከተጠሪ እውቀትና ፍላጎት ውጪ መሆኑ ተረጋግጦ በነፃ መሰናበቱን ጠቅሶ መኪናውም ሉወረስ እንደማይገባ ተረጋግጦ እንዱመለስለት በስር ፍ/ቤት ትዕዛዝ መሰጠቱ በአግባቡ ነው በማለት በስር ፍ/ቤት ውሳኔ የተፈፀመ የሕግ ስህተት የለም ተብል እንዱፀና ጠይቋል።
የአመልካች ዓ/ህግ በሰጠው የመልስ መልስ መኪናው እንዱመለስ የተሰጠው ትዕዛዝ አለአግባብ ነው ሲል አቤቱታውን አጠናክሮ ተከራክሯል።
የጉዲዩ አመጣጥ እና የግራ ቀኙ ክርክር ከፍ ሲል በአጭሩ የተመለከተው ነው። እኛም ከተያዘው ጭብጥ አንፃር ከሕጉ አገናዝበን መርምረናል።
እንደመርመርነውም የተጠሪ ከቀረበበት የኮንትሮባንድ ወንጀል ክስ በነፃ የተሰናበተ ስለመሆኑ አላከራከረም። ዓ/ህግ አጥብቆ የተከራከረው ንብረትነቱ የተጠሪ የሆነው የሕዝብ ማመላለሻ መኪና የጉምሩክ ሥነ ሥርዓት ያልተፈፀመበትን እቃ ጭኖ መገኘቱ ተረጋግጦ ሹፋሩና ረዲቱ ጥፊተኞች ተብለው የተቀጡ ስለሆነ በጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 622/2001 አንቀጽ 104/3/ መሰረት መኪናው /ማጓጓዣው/ እንዱወረስ ዓ/ህግ ያቀረበውን የሰው እና የሰነድ ማስረጃ በማየት መወረስ ነበረበት የሚል ነው።
በመሰረቱ የሰበር ችልቱ ያስቀርባል ሲል የያዘው ጭብጥ ስለማጓጓዣው መወረስ ወይም አለመወረስ የስር ፍ/ቤት ትዕዛዝ ሳይሰጥበት የማለፈን አግባብነት ለማጣራት ነው። በዚህ ረገድ ተጠሪ በሰጠው መልስ መኪናው ለተጠሪ እንዱመለስ ፍ/ቤቱ ከውሳኔው አስቀድሞ ትዕዛዝ የሰጠ መሆኑን ጠቅሷል። ዓ/ህግ በመልስ መልሱ ላይ ይህንን ሳይክድ መኪናው እንዱመለስ የተሰጠው ትዕዛዝ የአዋጁን አንቀጽ 104/3/ ይቃረናል የሚል ክርክር አቅርቧል።
ከዚህ መረዲት የሚቻለው መኪናው እንዱመለስ በስር ፍ/ቤት ትዕዛዝ ስለመሰጠቱ ግራ ቀኙ የተማመኑበት መሆኑን ነው። ስለዚህም የሰበር ችልቱ ውሳኔ የሚሻ ጉዲይ መኪናው ለተጠሪ እንዱመለስ መታዘዙ በአግባቡ ነው ወይስ አይደለም? የሚለው ጭብጥ ነው።
በዚህ ረገድ ከክርክሩ መረዲት የተቻለው ተጠሪ የመኪናው ባለንብረት ቢሆንም ከወንጀል ድርጊቱ በነፃ የተሰናበተ መሆኑን ነው። ተከሳሽ በነፃ የተሰናበተ እንደሆነ ንብረቱ ሉወረስ የሚቻልበት ሁኔታ በአዋጁ አንቀጽ 104/3/ሀ/ ስር በተለየ ሁኔታ (exceptional situation) ተመልክቷል።
ይኸውም ስለድርጊቱ አፈፃፀም ሁኔታ የሚያስረዲ አጥጋቢ ማስረጃ መቅረቡንና ፍ/ቤቱ አሳማኝ ሆኖ ሲያገኘው (Where the court is satisfied) ስለመሆኑ የድንጋጌው ይዘት ያስገነዝባል። ከዚህ አንፃር በዚህ መዝገብ የቀረበውን ክርክር ስንመለከት ሹፋሩና ረዲቱ ጥፊተኛ ሆነው የተቀጡት በመኪናው ለክሪክ እና ሸራ፣ ጎማ መፍቻና ላልች መሰል እቃዎች ማስቀመጫ ተብል ከሹፋሩ ወንበር ጋር ተያይዞ በተሰራ ክፍል ውስጥ የጉምሩክ ሥነ ሥርዓት ያልተፈፀመበት እቃ ደብቀው በማጓጓዛቸው ስለመሆኑ ከመዝገቡ መረዲት ችለናል።
በስር ፍ/ቤት የቀረበው እና የተረጋገጠ ፍሬ ነገር ተጠሪ መኪናው ላይ ያሰራው የእቃ ማስቀመጫ ክፍል ከፍ ሲል ለተጠቀሰው አገልግልት እንጂ ለሕገ ወጥ ዓላማ ነው ሉያስብል የሚያስችል አይደለም ተብል በወንጀለ አፈፃፀም ውስጥ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ሐሳብ ነበረው ሉያሰኝ የሚችልበት ሁኔታ እንደላለ ተመልክቷል። ከዚህ የተነሳ በሕጉ አነጋገር የተጠሪ ንብረት የሆነው መኪና እንዱወረስ ለማድረግ ፍ/ቤቱን ሉያሳምን የሚችል ማስረጃ በአመልካች በኩል ያልቀረበ ስለመሆኑ መረዲት ችለናል። ከዚህ አንፃር የተጠሪ መኪና ሉወረስ አይገባም ሲል የስር ፍ/ቤት የሰጠው ውሳኔ በሕግ ረገድ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ለማለት አልተቻለም።
ስለሆነም ውሳኔው ባለበት ሁኔታ ሉፀና ይገባል ብለናል።
በአፊር ብ/ክ/መ/ ገብረሱ ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ በ17/05/2002ዓ.ም የሰጠው ፍርድ እና የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ በ24/09/2002ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ ፀንቷል።
በዚህ መዝገብ ሰኔ 17 ቀን 2002ዓ.ም ተሰጥቶ የነበረው የእግድ ትዕዛዝ ተነስቷል።
ይፃፍ።
No topics extracted.