No summary available.
ሐምል 26 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሒጎስ ወልደ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- የኢትዮጽያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን - ባህር ዲር ቅርንጫፍ አቶ ዮሱፍ አብሬ - ቀረቡ ተጠሪ፡- ወ/ሪት ትዕግስት ጥላሁን - አልቀረቡም መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የአማራ ብሓራዊ ክልል የሰሜን ጏንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት እና የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ስላለበት በሰበር ተጣርቶ ይወሰንልኝ በማለት ያቀረቡትን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው። የክርክሩ መነሻ ተጠሪ ለዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያቀረቡት ክስ ነው። ተጠሪ አራት መቶ ኩንታል ባቄላ ወደ ሱዲን ለመላክ የጉምሩክ ሥርዓትና ፍርማሉቲ አሟልታ ባቄላውን ወደ ሱዲን ሳጓጉዝ ተከሣሹ ተጨማሪ ሰላሣ ኩንታል ባቄላ አግኝቻለሁ በሚል ሰበብ የያዘብኝ ስለሆነ ባቄላውን ዋጋ ሱዲን በምሸጥበት ዋጋ ሉከፍለኝ ይገባል በማለት ክስ አቅርበዋል። አመልካች አራት መቶ ኩንታል ባቄላ የጉምሩክ ሥርዓት የተፈጸመበት ቢሆንም ይህንን ሽፊን በማድረግ ሰላሣ ኩንታል ባቄላ የጉምሩክ ቀረጥና ፍርማሉቲ ሣያሟለ ወደ ሱዲን ለማሻገር ሲሞክሩ ተይዘዋል። በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታ ንብረቱን መያዝና መወረስ እንደምንችል በህግ የተደነገገ በመሆኑ የከሳሽ ክስ የህግ መሰረት የለውም። የባቄላውን ዋጋ መክፈል አለባችሁ የሚባል ከሆነም ባቄላው በሀራጅ የተሸጠ በመሆኑ በሀራጅ በሸጥንበት ዋጋ እንጅ ከሣሽ በጠየቁት መሆን የለበትም በማለት ተከራክሯል። የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አመልካች ተጠሪ ወደ ሱዲን በመጓጓዝ ላይ ከነበረው ጭነት ውስጥ ሰላሣ ኩንታል ባቄላ የጉምሩክ ቀረጥና ፍርማሉቲ ሣይፈጸምበት ያገኘ ቢሆንም የጉምሩክ ፍርማሉቲ የተፈጸበትን አራት መቶ ኩንታል ባቄላ መያዝና መውረስ አልነበረበትም በማለት አመልካች ብር 362,346.23 የባቄላው ዋጋና የላልች ወጭዎች ብር 21,236.23 አመልካች ለተጠሪ ይክፈል በማለት ወስኗል። በዚህ ውሣኔ አመልካች ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት አቅርቧል። የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የስር ፍርድ ቤት ተጠሪ ያወጡትን ያተለያዩ ወጭዎች በማለት የወሰነውን ብር 21,236.23 ተገቢ አይደለም በማለት ወስኗል። በልላ በኩል አመልካች ብር 362,346.23 ለተጠሪ ይክፈል በማለት የሰጠውን ውሣኔ አጽንቶታል።
አመልካች የካቲት 12 ቀን 2003 ዓ.ም በተጻፈ የሰበር አቤቱታ ተጠሪ 4ዐዐ ኩንታል ባቄላ ሱዲን ወስደው ለመሸጥ የጉምሩክ ፍርማሉቲ ካሟለ በኋላ 43ዐ ኩንታል ወደሱዲን ሲወስደ መገኘታቸው በፍሬ ጉዲይ ደረጃ ተረጋግጧል። አመልካች የጉምሩክ ፍርማሉቲ የተሟላበትንና የጉምሩክ ፍርማሉቲ ያልተሟላበትን ባቄላ መያዝና መውረሳችን በአዋጅ ቁጥር 368/95 አንቀጽ 22 በተደነገገው መሰረት የፈጸምነው ህጋዊ ተግባር ሆኖ እያለ አላግባብ በልጽጓል ተብል በበታች ፍርድ ቤቶች የባቄላውን ዋጋ እንድንከፍል የተሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው።
አመልካች የመኪናውን ዋጋ ይመልስ ቢባል እንኳን ባቄላው በሀራጅ የተሸጠበትን ብር 141,556.95 መሆን ሲገባው በድላር ሂሣብ በማስላት እንድንከፍል መወሰኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት አለበት። የጠበቃ አበልና ወጭና ኪሣራም አላግባብ ተወስኖብናል በማለት አመልክቷል። ተጠሪ በበኩላቸው ወደ ውጭ እንዱልክ 168 ኩንታል ባቄላ ቀሪ አለኝ ይህ ከሆነ አመልካች የሰላሣ ኩንታል ታክስና ቀረጥ በማስከፈል ከተፈቀደልኝ 168 ኩንታል መቀነስ ሲገባው መውረሱ ህጋዊ መሰረት የለውም። አመልካች በስር ያላቀረበውን አዱስ ክርክር በሰበር ደረጃ ያቀረበ ስለሆነ ክርክሩ በፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 329/1/ መሰረት ውድቅ ላደረግ ይገባዋል። የበታች ፍርድ ቤቶች ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለበትም በሚል ዝርዝር ክርክር አቅርበዋል።
አመልካች ሚያዝያ 12 ቀን 2003 ዓ.ም የተጻፈ ዝርዝር የመልስ መልስ አቅርበዋል።
ከስር የቀረበው ክርክርና በሰበር ግራ ቀኙ ያቀረቡት የጽሁፍ ክርክር ከላይ የተገለጸው ሲሆን እኛም የበታች ፍርድ ቤቶች አመልካች አላግባብ በልጽጓል በማለት የፍታብሓር ህግ ቁጥር 2162 እና የፍታብሓር ህግ ቁጥር 2163 መሰረት በማድረግ አመልካች የአራት መቶ ኩንታል ባቄላ ዋጋ በድላር ምንዛሬ ለተጠሪ እንዱከፍል መወሰኑ ተገቢ ነው ወይስ አይደለም የሚለውን ጭብጥ በመያዝ ጉዲዩን መርምረናል። ጉዲዩን እንደመረመርነው ተጠሪ አራት መቶ ኩንታል ባቄላ ወደ ሱዲን ለመላክ የጉምሩክ ሥርዓትና ፍርማሉቲ አሟልተው ባቄላውን ወደ ሱዲን በሚያጓጉዙበት ጊዜ በጉምሩክ የመጨረሻ ጣቢያ ላይ ሲፈተሽ አራት መቶ ሰላሣ ኩንታል ባቄላ ተጭኖ መገኘቱን በበታች ፍርድ ቤቶች ተረጋግጧል። የስር ፍርድ ቤት የጉምሩክ ቀረጥና ፍርማሉቲ ያልተሟላበት ሰላሣ ኩንታል ባቄላ ተጠሪ የጫነች መሆኗ ስላልተረጋጠና ለዚህ ተጠያቂው ሹፋር ስለሆነ አመልካች ተጠሪ የጉምሩክ ቀረጥ የከፈለችበትንና አራት መቶ ኩንታል ባቄላ መወረሱ የህግ መሰረት የለውም በማለት ውሣኔ ሰጥቷል።
እኛም የበታች ፍርድ ቤቶች የሰጡት የህግ ትርጉም አዋጅ ቁጥር 60/89 መሰረታዊ ዓላማና አግባብነት ያላቸውን ድንጋጌዎች ይዘት ያገናዘበ መሆኑን መርምረናል።
ተጠሪ ወደ ሱዲን ለመላክ ከጫኑት ዕቃ ውስጥ አራት መቶ ኩንታል ባቄላ ተገቢው የጉምሩክ ሥርዓት ፍርማሉቲ የተሟላበት ሲሆን ከዚህ ጋር ተቀላቅል የተጫነው ሰላሣ ኩንታል ባቄላ ተገቢው የጉምሩክ ሥርዓትና ፍርማሉቲ ሣይሟላ የተጫነ መሆኑ ፍሬ ጉዲይ የማጣራትና ማስረጃ የመመዘን ስልጣን ባላቸው ፍርድ ቤቶች ተረጋግጧል። ከዚህም የምንረዲው ተጠሪ የጉምሩክ ሥርዓትና ፍርማሉቲ አሟልተው ከጫኑት አራት መቶ ኩንታል ጋር በመቀላቀል ሰላሣ ኩንታል ባቄላ በኮንትሮባንድ ከአገር ለማስወጣት ሲሞክሩ በመጨረሻው የጉምሩክ ጣቢያ በተደረገ ፍተሻ የተያዘ መሆኑን ነው። ከተጠሪ የጉምሩክ ሥርዓት አሟልተው ከጫኑት አራት ኩንታል ባቄላ ጋር ተቀላቅል የተያዘው ሰላሣ ኩንታል ባቄላ በኮንትሮባንድ ከአገር ሉወጣ ሲል የተያዘ ዕቃ መሆኑን በአዋጅ ቁጥር 60/89 አንቀጽ 2 ንኡስ አንቀጽ 28 ኮንትሮባንድ ማለት ህጏችንና በህግ መሰረት የወጡ መመሪያዎችን በመተላለፍ ወደ አገር ውስጥ ለመግባት የመጀመሪያውን ከአገር ለመውጣት የመጨረሻውን የጉምሩክ ጣቢያ በማለፊ ዕቃዎችን ወደ አገር ውስጥ ማስገባት ማስወጣት እንዱገቡ ወይም እንዱወጡ ማድረግ መሞከር ወይም መርዲት ወይም እነዚህን የንግድ መጠን ያላቸውን ዕቃዎች መያዝ መሸጥ ማስተላለፍና በእነዚህ ዓይነት ድርጊቶች መተባበርን ጨምሮ መሆኑ ትርጉም ተሰጥቶታል። ከዚህም የምንረዲው ተጠሪ ወደ ሱዲን አገር ለመላክ የጫኑት ዕቃ የጉምሩክ ቀረጥና ፍርማሉቲ ተሟልቶ የተጫነ ዕቃና በኮንትሮባንድ ከአገር ለማውጣት የተጫነ ዕቃ አቀላቅል የያዘ መሆኑን ነው።
አመልካች በኮንትሮባንድ ወደ አገር ውስጥ የሚገቡትን ወይም ከአገር የሚወጡትን ዕቃዎች እንቅስቃሴ የመቆጣጠር የመከላከልና በዚህ ሁኔታ የሚንቀሳቀሱ ዕቃዎችንና መጓጓዣዎችን የመያዝና አስፈላጊውን ህጋዊ እርምጃ የመውሰድ ስልጣን በአዋጅ ቁጥር 60/89 አንቀጽ 6 ንኡስ አንቀጽ 5 ተሰጥቶታል። አመልካች የጉምሩክ ሥርዓትና ፍርማሉቲ በማሟላት ተጠሪ የጫኑት አራት መቶ ኩንታል ባቄላ በኮንትሮባንድ ከአገር ለማስወጣት ከተጫነው ሰላሣ ኩንታል ባቄላ ጋር ተቀላቅል ሲያገኘው በህጋዊ መንገድ ከአገር እንዱወጣ የተፈቀደውን ዕቃና በኮንትሮባንድ ሉወጣ የነበረውን ዕቃ መውረሱ በአዋጅ ቁጥር 60/89 አንቀጽ 6 ንኡስ አንቀጽ 5 በተሰጠው ህጋዊ ስልጣን ሥር የሚወድቅ ተግባር ነው ወይስ አይደለም የሚለው ነጥብ መታየት ይገባዋል። ለዚህም ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት አዋጅ ቁጥር 60/89 ለማሻሻል የወጣው አዋጅ ቁጥር 368/95 አንቀጽ 22 ድንጋጌ ይዘት መንፈስና ዓላማ መመርመሩ አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል። በአዋጅ ቁጥር 368/95 አንቀጽ 22 ማንኛውም ሰው ተገቢ ያልሆነ ብልጽግና ለማግኘት ወይም ለላላ ሰው ለማስገኘት ወደ አገር የሚያስገባውን ወይም ከአገር የሚያስወጣውን ዕቃ በሚመለከት ቀረጥ እንዱቀንስ እንዲይከፈል ወይም እንዱመለስ የተከለከለ ገደብ ወይም ቁጥር የተደረገበት ዕቃ እንዱገባ እንዱወጣ ወይም እንዱተላለፍ በማሰብ ለባለስልጣን በጽሁፍ በቃል በአካል እንቅስቃሴ ወይም በኤላክትሮኒክስ ለጉምሩክ ሥነ ሥርዓት አፈጻጸም በሚያቀርበው ወይም በሚያደርገው የጉምሩክ ዱክላራላሲዮን ሀሰተኛ መግለጫ የሰጠ ዋጋቸው ዝቅተኛ ወይም ከፍተኛ የሆኑ ሰነድች ያቀረበ ሰነድችን የደለዘ የፊቀ አስመስል የሰራ ወይም ማናቸውም ተገቢ ያልሆነ ድርጊት የፈጸመ እንደሆነ የማጭበርበር ድርጊት የተፈጸመበት ዕቃና ለማጭበርበሩ በሽፊንነትና ከለላነት ያገለገለት ዕቃዎች ውርስ መሆናቸው እንደተጠበቀ ሆኖ በዕቃው ላይ ሉከፈል ከሚባው ቀረጥና ታክስ በማያንስ የገንዘብ መቀጮና ከአስራ አምስት እስከ ሀያ አምስት በሚደርስ እስራት ሁለቱንም በማጣመር ይቀጣል በሚል መንገድ የአዋጅ ቁጥር 60/89 አንቀጽ 67 በማሻሻል ደንግጓል።
የጉምሩክ ቀረጥ ሣይከፍል ዕቃ ወደ ውጭ ለማሳለፍ በማሰብ የጉምሩክ ቀረጥና ፍርማሉቲ ያልተሟላበትን የኮንትሮባንድ ዕቃ የጉምሩክ ፍርማሉቲ ከተሟላበት ዕቃ ጋር ቀላቅል ጭኖ መገኘት ከላይ በተገለጸው የህግ ድንጋጌ መሰረት የማጭበርበር ድርጊት እንደተፈጸመ ይቆጠራል ወይስ አይቆጠርም የሚለው በአዋጅ ቁጥር 368/95 አንቀጽ 22 ማናቸውንም ተገቢ ያልሆነ ድርጊት የፈጸመ እንደሆነ የሚለው የአማረኛው ቅጅ እና በእንግሉዝኛው ቋንቋ ‛do any mischievous act“ በሚል መንገድ ከተገለጸው አንጻር መታየት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል። ስለሆነም በህጋዊ መንገድ ወደ ውጭ እንዱላክ ከተዘጋጀ ዕቃ ጋር በህጉና በመመሪያው መሰረት የጉምሩክ ቀረጥ ያልተከፈለበት የኮንትሮባንድ ዕቃ ቀላቅል በመጫን የጉምሩክ የመጨረሻ ኬላ ለማለፍ መሞከር የአዋጅ ቁጥር 368/95 አንቀጽ 22 አማረኛው ቅጅ ማናቸውም ተገቢ ያልሆነ ድርጊት የፈጸመ እንደሆነ በሚል መንገድ በገለጸውና የእንግሉዝኛው ቅጅ ‛do any mischievous act“ በሚል መንገድ ከገለጻቸው የማጭበርበር ድርጊቶች ውስጥ የሚካተት ህገ ወጥ ተግባር ነው። ስለሆነም ተጠሪ በህጋዊ መንገድ ወደ ሱዲን ለመላክ የጉምሩክ ሥርዓትና ፍርማሉቲ ያሟለበትን አራት መቶ ኩንታል ባቄላ በሽፊንነትና በከለላነት በመጠቀም ሰላሣ ኩንታል ባቄላ በኮንትሮባንድ ከአገር ውጭ እንዱወጣ የማድረግ ተግባር የተፈጸመ መሆኑን ያረጋገጠው አመልካች በኮንትሮባንድ ከአገር ውጭ ሉወጣ የነበረውን ሰላሣ ኩንታል ባቄላ ብቻ ሣይሆን ይህንን ባቄላ በኮንትሮባንድ ለማስወጣት በሽፊንነትና ከለላነት ያገለገለውን አራት መቶ ኩንታል ባቄላ መውረሱ አመልካች በአዋጅ ቁጥር 60/89 አንቀጽ 6 ንኡስ አንቀጽ 5 በተሰጠው ስልጣን መሰረት የአዋጅ ቁጥር 368/95 አንቀጽ 22 ገዥነት ባለው ሁኔታ በደነገገው መሰረት የኮንትሮባንድ ወንጀል ለመፈጸም በሽፊንነትና በከለላነት ያገለገለውን አራት መቶ ኩንታል ባቄላ የወረሰ መሆኑ ተረጋግጦ እያለ የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ለጉዲዩ አግባብነት የላላቸውን የፍታብሓር ህግ ቁጥር 2162 እና የፍታብሓር ህግ ቁጥር 2163 ድንጋጌዎች በመጥቀስ አመልካች በህግ በተደነገገው መሰረት የወረሰውን ዕቃ ዋጋ በወቅቱ በነበረው የድላር ምንዛሬ ታስቦ እንዱከፍል የሰጡት ውሣኔ የአዋጅ ቁጥር 60/89 እና አዋጅ ቁጥር 368/95 መሰረታዊ አላማና ለጉዲዩ አግባብነት ያላቸውን የህግ ድንጋጌዎች ያላገናዘበና መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ተጠሪ የጉምሩክ ቀረጥና ፍርማሉቲ ያሟለት አራት መቶ ኩንታል ባቄላ ተቀላቅል የተጫነውን ሰላሣ ኩንታል ባቄላ በኮንትሮባንድ ከአገር ለማስወጣት በሽፊንነትና ከለላነት ያገለገለ መሆኑ በፍሬ ነገር ደረጃ ተረጋግጧል። አንድ ላኪ ዕቃ ወደ ውጭ ለመላኩ የጉምሩክ ቀረጥና ፍርማሉቲ ካሟላ በኋላ ዕቃውን ከመነሻው እስከ መድረሻው በመጓጓዝ ሂደት ሉከበሩ የሚገባቸው ሥርዓቶች በአዋጅ ቁጥር 60/89 ከአንቀጽ 16 እስከ አንቀጽ 18 ተደንግጓል። የዕቃው ላኪ እነዚህ ህጋዊ ሥርዓቶችና ደንቦችን ባከበረ ሁኔታ ከመነሻው እስከ መድረሻው ዕቃው የተጓጓዘ መሆኑን የማረጋገጥ ሀላፉነት እንዲለበትና ይህንን ግዳታውን በአግባቡ ሣይወጣ ቀርቶ ቀረጥ ያልተከፈላቸውና የተደበቁ ዕቃዎች ተቀላቅለው ከተጫኑ የዕቃው ባለቤት በሀላፉነት ሉጠየቅ የሚችል ስለመሆኑ ከአዋጅ ቁጥር 60/89 አንቀጽ 58 ንኡስ አንቀጽ 1/ለ/ ለመገንዘብ ይቻላል። ከዚህ አንጻር ስንመለከተው ተጠሪ ህጋዊ ቀረጥ የከፈለበት አራት መቶ ኩንታል ባቄላ በኮንትሮባንድ ዕቃ ለማስተላለፍ በሽፊንነትና በከለላነት በማያገለግልበት ሁኔታ በጥንቃቄ ከመነሻው እስከ መድረሻው እየተጓጓዘ መሆኑን የመከታተል ህጋዊ ግዳታና ሀላፉነት አለባቸው ተጠሪ ይህንን ሀላፉነታቸዉ ሣይወጡ ቀርተው ዕቃው የኮንትሮባንድ ዕቃ ለማሳለፍ በሽፊንነትና በከለላነትና ያገለገለ መሆኑን አመልካች ካረጋገጠ አመልካች በኮንትሮባንድ ከአገር ሉወጣ የነበረውን ዕቃ ብቻ ሣይሆን በኮንትሮባንድ ዕቃ ለማሳለፍ በከለላነትና ሽፊንነት ያገለገለውን ዕቃ ለመያዝና ለመውረስ እንደሚቻል በአዋጅ ቁጥር 368/95 አንቀጽ 22 የተደነገገ በመሆኑ የበታች ፍርድ ቤቶች በኮንትሮባንድ ከአገር ሉወጣ የነበረውን ሰላሣ ኩንታል ባቄላ በተጠሪ የተጫነ መሆኑ ስላልተረጋገጠ አመልካች ህጋዊ ቀረጥ የተከፈለበትን አራት መቶ ኩንታል ባቄላ ለመውረስ የሚችልበት ህጋዊ መሰረት የለውም በማለት የደረሰበት መደምደሚያ ተገቢነት የላለውና መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
በአጠቃላይ አመልካች ሰላሣ ኩንታል ባቄላ በኮንትሮባንድ ከአገር ለማስወጣት በሽፊንነትና ከለላነት ያገለገለውን የተጠሪን አራት መቶ ኩንታል ባቄላ የወረሰው በአዋጅ ቁጥር 60/89 አንቀጽ 6 ንኡስ አንቀጽ 5 እና በአዋጅ ቁጥር 368/95 አንቀጽ 22 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ሆኖ እያለ አላግባብ በተጠሪ ንብረት በልጽጓል በማለት የአራት መቶ ኩንታል ባቄላ ዋጋ በወቅቱ በነበረው የድላር ምንዛሬ ሂሣብ እንዱከፍል የሰሜን ጏንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የአማራ ብሓራዊ ክልል የሰሜን ጏንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሣኔ ተሽሯል።
አመልካች በአዋጅ ቁጥር 60/89 አንቀጽ 65 በአዋጅ ቁጥር 368/95 አንቀጽ 22 መሰረት የወረሰውን የአራት መቶ ኩንታል ባቄላ ዋጋ ለተጠሪ የመመለስና የመክፈል ኃላፉነት የለበትም በማለት ወስነናል።
በዚህ ፍርድ ቤት ያወጡትን ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ ለየራሣቸው ይቻለ።
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.