No summary available.
12/11/2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ሒጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ሞያላ ቅርንጫፍ ተወካይ አቶ ዲለ አብድ - ቀረቡ ተጠሪ፡- ኤፍታታ እና ቢ ኤም ኤም ኃ/የተወሰነ የግል ማህበር - አልቀረቡም መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
በሥር ከፍተኛ ፍ/ቤት የአሁኑ ተጠሪ ከሣሽ የነበረ ሲሆን አመልካች ደግሞ ተከሣሽ ነበር።
ክሱም ከሣሽ ባለኝ የውጪ ንግድ ፈቃድ መሰረት 400 ኩንታል ቦልቄ ግምቱ ብር 300,000 የሚሆነውን ወደ ኬኒያ ለማሻገር እንዱያስችለኝ ተከሣሽ መ/ቤት ተገቢውን የጉምሩክ ሥርዓት እንዱፈጽምልኝ በ13/04/2002 ዓ/ም ከቀኑ በግምት ከ7፡ዐዐ - 8፡00 ባለው ጊዜ ውስጥ መኪናው እንደጫነ ወደ ተከሣሽ መ/ቤት ሳቀርብ ተከሣሽም በ15/4/2002 ዓ.ም በተጻፈ ደብዲቤ ያልተሟለ ነገሮች ማለትም የባንክ ፈቃድ ፣ የግብር ከፊይ መለያ ቁጥር /TIN/ የመሳሰለትን አሟልቼ እንድቀርብ በማስታወቁ ከሣሽም ከተጠየቁት ነገሮች ውስጥ የባንክ ፈቃድ ብቻ አለመያዜን በመግለፅ መኪናው እንደጫነ በማቆም ወደ አዱስ አበባ የተመለስኩ ሲሆን ተከሣሽም በመሃለ ኮንትሮባንድ ነው በሚል ከመኪናው በማራገፍ ስለከለከለኝ በፍ/ህ/ቁ 2028 እና 2031 መሰረት የጉዲቱን ዋጋ (9%) እና የጠበቃ አበል 1ዐ% እንዱከፍል ይወሰንበት የሚል ነው።
ተከሣሽም ለክሱ በሰጠው መልስ ከሣሽ ቦልቄውን ወደ ተከሣሽ መ/ቤት ያቀረበውም የጉምሩክ ሥርዓት ለማስፈፀም ሲሆን ምርቱን ወደ ውጪ ለመላክ ፈቃድ ያለው ከመሆኑም ላላ የግብር ከፊይ መለያ ቁጥር /TIN/ በጊዜው የነበረው ቢሆንም እነዚህን ነገሮች ብቻ መያዝ በቂ ባለመሆኑና በአዋጅ ቁጥር 622/2001 አንቀጽ 12 እና 13 ሥር የተገለፁ ነገሮች ሁለ ተሟልተው መቅረብ ያለባቸው ሆኖ እያለ ከሣሽ በህጉ መሰረት ሳያሟላ ቦልቄው በጉምሩክ ጠረፍ ውስጥ ገብቶ ስለተገኘ በአዋጅ ቁጥር 622/2001 አንቀጽ 2/42/ እና 9/1/ ሥር የተጠቀሰው መሰረት ኮንትሮባንድ ነው በሚል ተከሣሽ መያዙ በአግባቡ ስለሆነ ክሱ ተቀባይነት የለውም ሲል ተከራክሯል።
ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ ተቀብል ያከራከረው የሥር ከፍተኛ ፍ/ቤትም በሰጠው ውሣኔ ተከሣሽ የያዘው ንብረት /ቦልቄ / የተከለከለ ካለመሆኑም ላላ ከሣሽ ህጋዊ በሆነ ሁኔታ የላኪነት ፈቃድ ኖሮት የንግድ ሥራውን የሚያከናውን ሆኖ እያለ የጉምሩክ ሥነ ሥርዓት ለመፈፀም ያልተሟለ ነገሮች ካለ እንዱሟለ ከማድረግ በቀር ቦልቄውን ኮንትሮባንድ ነው ብል ተከሣሽ መያዙ ያለአግባብ ነው በማለት የተያዘው 4ዐዐ ኩንታል ቦልቄ ለከሣሽ እንዱመለስ ብሎል።
የአሁኑ የሰበር አመልካችም በሥር ከፍተኛ ፍ/ቤት ውሣኔ ቅር በመሰኘት ለክልለ ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ይግባኝ ቢያቀርብም በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 337 መሰረት የይግባኙን መዝገብ በመዝጋቱ አመልካች በሥር ቤቶች ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ተፈጽሟል በማለት አቤቱታውን ለዚህ ችልት አቅርቧል።
አመልካች በዋናነት የጠቀሳቸው የቅሬታ ነጥቦችም፡- ተጠሪው በአዋጅ ቁጥር 622/2001 አንቀጽ 2/17/ ፣ 12/4/ እና 13/1/ መሰረት አስፈላጊ ከሆኑ ሰነድች አንድም ሳያመጣ የጉምሩክ ጠረፍ አቋርጦ ወጥቶ እያለ የተያዘውን ቦልቄ ኮንትሮባንድ አይደለም መባለ ህግን መሰረት ያደረገ አይደለም ፣ የጉምሩክ ሥነ ሥርዓት ያልተፈፀመበትን ዕቃ ከጉምሩክ ጠረፍ ማቋረጥ ይችላል መባለ ተገቢነት የለውም፣ የአመልካች ጽ/ቤት የጉምሩክ ጠረፍን በማቋረጥ ከጉምሩክ ክልል ውጪ ከኬኒያ ድንበር 100 ሜትር በማይደርስ ርቀት የሚገኝ ሲሆን የጉምሩክ ሥነ ሥርዐት በአንድ ዕቃ ላይ መፈፀሙንና አለመፈፀመን የሚረጋገጥበት ቦታ እንጂ የጉምሩክ ሥነ ሥርዓት የሚፈፀምበት ባለመሆኑ አመልካች መ/ቤት ተጠሪው ያልተሟለ ሰነድችን እስኪሚያመጣ ድረስ መጠበቅ ነበረበት መባለ ያለአግባብ ነው የሚለ ናቸው።
ተጠሪው ለሰበር አቤቱታ በሰጠው መልስ በማንኛውም መስፈርት በህጋዊ መንገድ ወደ ውጪ ሉላክ የነበረው ቦልቄ ኮንትሮባደ ነው ልባል የሚችልበት ሁኔታ ስለላለ በሥር ፍ/ቤቶች ውሣኔ ላይ የተፈፀመ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የለም በማለት ተከራክሯል።
የግራ ቀኙ ክርክር ከዚህ በላይ የቀረበ ሲሆን እኛም ተጠሪው ወደ ውጪ ሲልክ በአመልካች የተያዘው ቦልቄ ኮንትሮባንድ ባለመሆኑ አመልካች ይመልስ ተብል መወሰኑ በአግባቡ ነው ? ወይስ አይደለም ? የሚለውን ጭብጥ ይዘን እንደሚከተለው መርምረናል።
አመልካች ተጠሪው ወደ ውጪ ሉልክ የነበረውን ቦልቄ ኮንትሮባንድ ነው በማለት በዋናነት የሚከራከረው በአዋጅ ቁጥር 622/2001 በአንቀጽ 2/17/ ፣ 12/4/ እና 13/1/ የተመለከቱትን ሁኔታዎች ተጠሪው አሟልቶ ባለመገኘቱ ነው። እነዚህን አመልካች አልተሟለም የሚላቸውን ሁኔታዎች ከመመርመራችን በፉት በተጠቀሰው አዋጅ ስለኮንትሮባንድ ወንጀል የተደነገገውን የአንቀጽ 91/1/ ይዘት መመልከት ተገቢነት ይኖረዋል። በዚህ በተጠቀሰው አንቀጽ መሰረት ማንኛውም ሰው በአዋጅ ቁጥር 622/2001 ወይም የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የሚያስፈጽማቸውን ላልች ህጏች ወይም በእነዚሁ መሰረት የወጡ ደንቦችን ወይም መመሪያዎችን በመተላለፍ የተከለከለ፣ ገደብ የተደረገባቸው ወይም የጉምሩክ ሥርዓት ያልተፈፀመባቸውን ዕቃዎች ወደ ጉምሩክ ክልል ካስገባ ወይም ከጉምሩክ ክልል ካስወጣ ወይም በህጋዊ መንገድ የወጡ ዕቃዎችን በህገወጥ መንገድ መልሶ ካስገባ ወንጀለ የተፈፀመባቸው ዕቃዎችና መሳሪያዎች እና የወንጀለ ፍሬ መወረሱ እንደተጠበቀ ሆኖ በዕቃዎቹ ላይ ሉከፈል ከሚገባው ቀረጥና ታክስ ጋር በሚመጣጠን የገንዘብ መቀጮና ከሰባት እስከ አሥራ አምስት ዓመት በሚደርስ ጽኑ እሥራት ይቀጣል ይላል።
ከዚህ ድንጋጌ መንፈስ መገንዘብ እንደሚቻለው አንድ ዕቃ ኮንትሮባንድ ነው ለማለት ዕቃው ወደ ጉምሩክ ክልል እንዲይገባ ወይም እንዲይወጣ በህግ የተከለከለ ወይም ገደብ የተደረገበት ላሆን ይገባል። እንዱሁም ከድንጋጌው መገንዘብ እንደሚቻለው የጉምሩክ ሥርዓት ያልተፈፀመበትን ዕቃ ወደ ጉምሩክ ክልል ማስገባት ወይም ከጉምሩክ ክልል ማስወጣት ዕቃው ኮንትሮባንድ እንዱባል የሚያደርግ ከመሆኑም በላይ የኮንትሮባንድ ወንጀልን የሚያቋቁም ይሆናል። ከዚህ በተጨማሪ ድንጋጌው በህጋዊ መንገድ እንኳን የወጡ ዕቃዎችን በህገወጥ መንገድ ወደ ጉምሩክ ክልል ማስገባት እንደኮንትሮባንድ ወንጀል እንደሚቆጠር ይደነግጋል።
ይህንኑ የአንቀጽ 91/1/ መንፈስ ይዘን የአመልካችን ክርክር ስንመለከት አመልካች የተጠሪን ቦልቄ የያዘው የጉምሩክ ሥነ ሥርዓት ባለመፈፀሙ ሲሆን የያዘውም በጽ/ቤቱ ነው። ይሁን እንጂ የጉምሩክ ሥነ ሥርዓት ያልተፈፀመበት ዕቃ ወደ ጉምሩክ ጽ/ቤት በመምጣቱ ኮንትሮባንድ ነው ተብል እንደሚወሰድ አንቀጽ 91/1/ አይገልጽም። በዚህ ድንጋጌ መሰረት ዕቃው ኮንትሮባንድ ነው ልባል የሚችለው ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ወደ ጉምሩክ ክልል ሲገባ ወይም ከጉምሩክ ክልል ሲወጣ ነው። በአዋጅ አንቀጽ 2/7/ መሰረትም የጉምሩክ ክልል ማለት የኢትዮጵያ የግዛት ክልል ነው።
በመሆኑም ዕቃው ኮንትሮባንድ ነው ለማለት አመልካች ተጠሪው በህገ ወጥ መንገድ ቦለቄውን ከኢትዮጵያ ግዛት /ከጉምሩክ ክልል/ ሲያስወጣ መያዙን ማስረዲት ይጠበቅበታል። ይህን በአግባቡ ባላስረዲበትና እንዱሁም በሥር ከፍተኛ ፍ/ቤት በተደረገው ክርክር የአሁኑ አመልካች ተጠሪው የጉምሩክ ሥነ ሥርዓት ለማስፈፀም ወደ አመልካች ጽ/ቤት ቦልቄን ጭኖ እንደመጣ ፣ በጊዜው ተጠሪው የላኪነት ንግድ ፈቃድ እና የግብር ከፊይ መለያ ቁጥር / TIN/ ይዞ እንደነበር በማመን ሲከራከር ከቆየ በኋላ በሰበር ደረጃ የክርክሩን ጭብጥ በመቀየር ተጠሪው ከጉምሩክ ጠረፍ አቋርጦ ሲወጣ ተይዟል በማለት መከራከሩ እርስ በርሱ የሚጋጭ ነው።
በልላ በኩል አመልካች ጠቅሶ የተከራከረባቸው የአዋጅ ድንጋጌዎች ማለትም 2/17/ ፣ 12/4/ እና 13/1/ የተጠሪው ቦልቄ ኮንትሮባንድ ነው ብል ላቀረበው ክርክር የሚረደ አይደለም።
ምክንያቱም የአዋጅ አንቀጽ 2/17/ የጉምሩክ ሥነ ሥርዓት ትርጉም የሚደነግግ ሲሆን አንቀጽ 12/4/ እና 13/1/ ደግሞ የጉምሩክ ሥነ ሥርዓት በሚፈፀምበት ወቅት መሟላት የሚገባቸውን ሁኔታዎች ወይም ፍርማሉቲዎች የሚደነግጉ ናቸው። እነዚህን ሁኔታዎች ወይም ፍርማሉቲዎች ተጠሪው አሟልቶ ካልተገኘ ደግሞ የሥር ከፍተኛው ፍ/ቤት በውሣኔው እንዲሰፈረው እንዱያሟላ ከሚደረግ ውጪ ቦልቄውን ኮንትሮባንድ ነው ብል መውረስ ህግን የተከተለ አሰራር አይደለም።
በመሆኑም የሥር ፍ/ቤቶች አመልካች ቦልቄውን ኮንትሮባንድ ነው በማለት የያዘው ያለአግባብ ነው በማለት ለተጠሪው እንዱመልስ በሰጡት ውሣኔ ላይ የተፈፀመ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት አላገኘንም።
ው ሣ ኔ
የሥር ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ በቀን 14/12/2002 ዓ.ም በዋለው ችልት እና የሥር የክልለ ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ በቀን 02/13/2002 ዓ/ም በዋለው ችልት የሰጠው ትዕዛዝ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 348/1/ መሰረት ፀንተዋል።
አመልካች የወረሰውን 4ዐዐ ኩንታል ቀይ ቦልቄ ወይም በጨረታ የሸጠውን የቦልቄ ዋጋ ለተጠሪ እንዱመልስ መወሰኑ አግባቡ ነው ብለናል።
የዚህን ፍ/ቤት ወጪና ኪሣራ የግራ ቀኙ ተከራካሪዎች የራሳቸውን ይቻለ።
ከዚህ በፉት በዚህ ጉዲይ ለሥር ፍ/ቤት ተላልፍ የነበረው የዕግድ ትዕዛዝ ተነስቷል።
ይጻፍ።
No topics extracted.