No summary available.
ሰኔ 03 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሐጏስ ወልደ አልማው ወላ ነጋ ደፍሣ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- ወ/ሮ አልማዝ ደሴ - ከጠበቃቸው በላቸው ታደሰ ጋር - ቀረቡ ተጠሪ፡- የጉምሩክ ዐ/ሕግ ታደለ ተስፊዬ - ቀረቡ መዘገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
በሥር የመ/ደ/ፍ/ቤት ከሣሽ የነበረው የአሁኑ ተጠሪ በዚህ በተያዘው ጉዲይ በሁለት ተከሣሾች ላይ ክስ አቅርቦባቸው የነበረ ሲሆን 1ኛ ተከሣሽ ያሁኗ አመልካች ናት። የክሱ ፍሬ ቃልም ተከሣሾች የወ/ሕ/ቁ/32/1/ሀ/ እና የጉምሩክ ባለሥልጣንን እንደገና ለማቋቋም የወጣውን አዋጅ ቁጥር 6ዐ/89 እንደተሻሻለው አንቀጽ 73/1/ሀ/ለ/ በመተላለፍ 1ኛ ተከሣሽ በዱክላራሲዮን ሴሪ ቁጥር 317ዐ1 ተመዝግቦ ከቀረጥ ነፃ ያስገባችውን የሴለዲ ቁጥሩ ኮድ 2.76388 አ.አ ሱዚኪ መኪና ለ2ኛ ተከሣሸ አሳልፊ በመስጠት እንዱሁም አቶ ጥላሁን አበበ የተባለው ግለሰብ ከወጋገን ባንክ አራዲ ቅርንጫፍ ለተበዲረው ገንዘብ መኪናውን በዋስትና በማስያዝ በህግ ከተፈቀደው ውጪ ለላላ ሰው አገልግልት እንዱውል አድርጋለች፤ 2ኛ ተከሣሽ መኪናውን እያሽከረከረ የካቲት ዐ6 ቀን 2000 ዓ.ም ከቀኑ 6፡ዐዐ ብሓራዊ ትያትር አካባቢ በመገኘቱ ሁለቱም ተከሣሶች ከቀረጥ ነፃ የገባውን መኪና አለአግባብ ሲገለገለ ተገኝቷል የሚል ነው።
1ኛ ተከሣሽ ወንጀለን አለመፈፀሟንና ጥፊተኛ አለመሆኗን ክዲ በመከራከሯ የሥር የፋ/የመ/ደ/ፍ/ቤት የከሳሽንና የ1ኛ ተከሳሽን ማስረጃ ከመረመረ በኋላ ተከሳሿ ከቀረጥ ነፃ የገባውን መኪና መብቱ ከተሰጠበት ፈቃድ ውጪ ለላላ ሰው አገልግልት እንዱውል ማድረጓ በበቂ ማስረጃ ተረጋግጧል በማለት ተጠቅሶ ክስ በቀረበባት አዋጅ ቁጥር 6ዐ/89 እንደተሻሻለው አንቀጽ 73/1/ሀ/ ሥር ጥፊተኛ ናት ሲል በመወሰን በመኪናው ላይ የሚፈለገውን ቀረጥ ብር 1ዐዐ,489.37 /አንድ መቶ ሺህ አራት መቶ ሰማንያ ዘጠኝ ከሰላሣ ሰባት ሳንቲም/ መቀጮ እንድትቀጣ በሰላዲ ቁጥሩ ኮድ 2-76388 አ.አ የሆነው መኪናም ለመንግስት ገቢ እንዱደረግ እንዱሁም በ6 ወር እሥራት እንድትቀጣና የእሥራቱ ቅጣት ቢፈፀሙ በምታስተዲድራቸው ልጆች ላይ ከሚደርሰው ጉዲት አኳያ የእሥራቱ ቅጣት ተገድቦ ለተከሣሸ የፈተና ጊዜ ቢሰጥ ፍ/ቤቱ ተገቢ ሆኖ አግኝቶታል በማለት ስለመልካም ጠባይ ብር 5000 /አምስት ሺህ/ ዋስትና ስታቀርብ ቅጣቱ ሳይፈፀም ታግድ እንዱቆይ ወስኗል።
ተከሣሽዋም በሥር የፋዳራል የመ/ደ/ፍ/ቤት ውሳኔ ቅር በመሰኘት ለሥር ፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ ብታቀርብም በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ/195/2/ለ/2/ መሰረት የሥር የፋዳራል የመ/ደ/ፍ/ቤት የሰጠውን የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሳኔ አጽንቷል።
በአመልካች የቀረበው የሰበር አቤቱታም በሥር ፍ/ቤቶች ውሳኔ ላይ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል የሚል ሲሆን በዋናነት የዘረዘራቸው የቅሬታ ነጥቦች አዋጅ ቁጥር 6ዐ/89 እንደተሻሻለው አንቀጽ 73/1/ከቀረጥ የገባ ዕቃ ለላላ ሰው ያስተላለፈ ወይም ለላላ ሰው አገልግልት እንዱውል ያደረገ ሰው የሚጠየቅበት ሕግ ሲሆን ‛ማስተላለፍ“ የሚለው ቃል በአዋጁ ትርጉም አልተሰጠውም ። በመሆኑም በፍ/ሕ/ቁ 1186/1/ ንብረት የገዛ ወይም በልላ አኳኋን ያገኘው ወይም በኑዛዜ የተሰጠው ሰው ንብረቱን እጁ ባደረገ ጊዜ የተላለፈ ይሆናል በሚል ስለሚደነግግ እንደሁም ስለመያዣ በፍ/ሕ/ቁ/ 2834/1/ በመያዣ ውል ውስጥ በዕቃው ላይ ባለመብት የሚሆነውን ለይተው ካልተዋዋለ በቀር አስያዥ በመያዣነት ለሰጠው ዕቃ ባለቤት ሆኖ ይቆያል የሚል በመሆኑ አመልካች መኪናውን በተባለት መንገድች ይዞታውንም ሆነ ባለቤትነት መብት ያላስተላለፍኩ ስለሆነ በወንጀል ሕግ መከሰስ አይገባኝም ነበር፣
መኪናው ከባንክ ለተሰጠው ብድር ለብር 90,000 በዋስትና የተያዘ ቢሆንም ለመኪናው ያልተከፈለ ገንዘብ ደግሞ ብር 100,489.73 በመሆኑ በልዩነትም ብዙ የሚተርፍ ገንዘብ በመኖሩ አመልካች የጉምሩክ ቀረጥ ለማስቀረት አስቤ ያደረግኩት ነገር ባለመሆኑ ድርጊቱ በወንጀል ሕግ ቁጥር 23 መሰረት የወንጀልን ድርጊት ከሚያቋቁሙት ግዙፍ ተግባራት የሐሳብ ክፍለን አላሟላም በመሆኑም ወንጀል በላለበት ቅጣት አይኖርም።
መኪናውን ስያሽከረክር የነበረው የእህቴ ልጅ / 2ኛ ተከሣሽ የሆነው/ ሲሆን በጊዜው አይኔን አሞኝ ስለነበር እንዱይዝልኝ ያደረግኩ በመሆኑ ይኸው ድርጊት ‛ማስተላለፍን“ አያሟላም
ከቀረጥ ነፃ የገባው መኪና አለአግባብ ተገለገለ ቢባል እንኳን የጉምሩክ መ/ቤት መመሪያ ቁጥር 46/2002 አንቀጽ 7 መሰረት የቀረጥና የታክስ 25% መቀጫ በማስከፈል መኪናው ለአመልካች መመለስ ሲገባው እንዱወረስ ማድረጉ ሕግን የሚቃረን ነው የሚለ ናቸው ለሰበር ቅሬታ ተጠሪው በሰጠው መልስ የቀረጥ ነፃ መብት ያለተጠያቂነትና ያለገደብ የተሰጠ አይደለም። በመሆኑም በአዋጅ ቁጥር 6ዐ/89 እና 368/95 እንደተሻሻለ አንቀጽ 73 ከቀረጥ ነፃ የገባን መኪና መብቱ ከተሰጠበት አላማ ውጪ አገልግልት ላይ እንዱውል ማድረግ የተከለከለና የወንጀል ሀላፉነትን የሚያሰከትል ነው። በመሆኑም አመልካች ከአዋጅ ቁጥር 6ዐ/89 እና አዋጅ ቁጥር 368/95 እንደተሻሻለው አንቀጽ 73/2/ እንዱሁም በአዋጅ ቁጥር 622/2001 አንቀጽ 98/2/ የተደነገገውን በመተላለፍ መኪናውን እንዱያሽከረክር ላልተፈቀደለት ሰው አሳልፊ ሰጥታለች።
ይኸው የሥር 2ኛ ተከሣሽም መኪናውን ሲያሽከረክር መገኘቱን በሥር ፍ/ቤት ባቀረብነው ማስረጃ አረጋግጠናል። ከዚህ ላላ አመልካች ከቀረጥ ነፃ የገባውን መኪና ለባንክ መያዣነት በመስጠት የብድር አገልግልት አግኝታለች። አመልካች ይደግፈኛል በማለት የጠቀሰችው የጉምሩክ መመሪያ ቁጥር 46/2002 ሥራ ላይ የዋለው ከ
No topics extracted.