No summary available.
ሰኔ 30 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጏስ ወልደ አልማው ወላ አሉ መሀመድ ነጋ ደፍሣ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን - ዐቃቤ ህግ ገብረሚካኤል ወልዳ - ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ አንተነህ ካሣዬ - አልቀረቡም መዝገቡን ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ የወንጀል ክስ ሲሆን አመልካች በአሁኑ ተጠሪና በልላ የእቃው ባለቤት በተባለ ግለሰብ ላይ በቀረበው ክስ የወንጀል ህግ ቁ 32/1/ሀ/ እና የገቢዎችና ጉምሩክ አዋጅ ቁ 622/2001 አንቀጽ 91/2/ በመተላለፍ የጉምሩክ ስነ - ሥርዓት ያልተፈፀመባቸውን የተለያዩ አልባሣት ባጠቃላይ ለመንግስት ሉከፍል የነበረው ቀረጥ እና ታክስ 26,576 ብር ሲሆን የአሁኑ ተጠሪ የሰላዲ ቁጥሩ ኮድ 3-04051 ደሕ የሆነ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ባለቤትና ሹፋር በመሆኑ የተከሰሰ ሆኖ ፍርድ ቤቱ ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ በተከሰሰበት የህግ አንቀጽ ጥፊተኛ አድርጎታል።
ጉዲዩን በመጀመሪያ የተመለከተው የደቡብ ክልል የጋሞ አካባቢ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአሁን ተጠሪ በተከሰሰበት አንቀጽ ጥፊተኛ ካደረገው በኋላ የአሁኑ ተጠሪ በ7/ ሰባት/ ዐመት ፅኑ እሥራት እና በ5000/አምስት ሺህ / ብር እንዱቀጣ በመወሰን ከላይ የተመለከተው ተሽከርካሪ ለባለቤቱ እንዱመለስ ትዕዛዝ ሰጥቷል። የአሁኑ አመልካች በዚሁ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኙን ለደቡብ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያቀረበ ሲሆን ፍርድ ቤቱም ያስቀርባል በማለት ሲመለከተው ከቆየ በኋላ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ 195/2/ ለ/ 2/ መሰረት አፅንቶታል።
አሁን የቀረበው ቅሬታ በዚሁ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ሲሆን አመልካች በቀን 21/5/2003 ዓ.ም በ2 ገፅ በመፃፍ ያቀረበው የቅሬታ ፍሬ ሃሣብ ፡- ተጠሪ ጥፊተኛ የተባለበት አዋጅ ቁ 622/01 አንቀጽ 91/2/ ስንመለከት የእሥራትና የገንዘብ መቀጫው ሉጣል የሚችለው ወንጀለ የተፈፀመበት ዕቃና መሣሪያ እና የወንጀለ ፍሬ መወረሱ እንደተጠበቀ መሆኑን የሚደነግግ በመሆኑ ፣ ተጠሪ ደግሞ የመኪናው ባለቤትና በወቅቱ ሹፋር መሆኑን ራሱም ከማመኑ በተጨማሪ በማስረጃም የተረጋገጠ ሆኖ ሣለ ዕቃውን ሲያጓጉዝ የነበረው የተጠሪ መኪና እንዱወርስ መታዘዝ ሲገባው መታለፈ ያለአግባብ በመሆኑ፣ በዚሁ አዋጅ አንቀጽ 1ዐ4/1/ የጥፊተኛነት ውሣኔ ከተሰጠ ተጨማሪ ትዕዛዝ መስጠት ሣያስፈልግ ዕቃው ወይም ማጓጓዣው እንዱወረስ ይደረጋል በማለት የደነገገ ቢሆንም የሥር ፍርድ ቤት የጥፊተኝነት ውሣኔ የሰጡ ቢሆንም ተሽከርካሪው እንዱወርስ ባለማዘዛቸው መሰረታዊ የህግ ስህተት የፈፀሙ በመሆኑ፣ ተጠሪ በቀጥታ በወንጀለ ተሣታፉ በመሆኑ መኪናውን ከመወረሰ የሚያስቀር አግባብ ሣይኖር የሥር ፍ/ቤቶች መኪናው ለባለቤቱ ይመለስ በማለት የሰጡት ትዕዛዝ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ እንዱታረምልን የሚል ነው። ጉዲዩ ያስቀርባል በመባለ ተጠሪ መጥሪያ ደርሶት ግንቦት ዐ8 ቀን 2ዐዐ3 ዓም በ4 ገፅ ፅፍ ያቀረበው የመልስ ፍሬ ሃሣብ አመልካች የጠቀሳቸው የህግ አንቀጾች የተገለፀው ተሽከርካሪ እንዱወርስ የሚደነግግ አይደለም ፣ በተጠቀሰው አዋጅ 622/2001 አንቀጽ 91/2/ ዕቃና መሣሪያ የሚለው በእንግሉዝኛው /goods & equipment / ተብል የተተረጎመ በመሆኑ መኪናን አይጨምርም፣ የተላለፍኩት የጉምሩክ ሥነ ሥርዓት ባለመኖሩ መኪናው ሉወረስ አይገባም ፣ የቀረበው ክስ በዚሁ አዋጅ አንቀጽ 91/2/ በመሆኑ እና በአዋጅ አንቀጽ 1ዐ4/1/ መሰረት መኪናው እንዱወርስ የቀረበብኝ ክስ ሣይኖር የቀረበው ቅሬታ ተቀባይነት ስለላለው ውድቅ እንዱደረግልኝ በማለት ተከራክሯል። አመልካች የመልስ መልስ ቀርቧል።
በግራ ቀኙ መካከል የተደረገው የክርክር ሂደት ከላይ የተመለከተው ሲሆን ችልቱም የተነሱትን ክርክሮች፣ ከተያዘው ጭብጥና አግባብነት ካላቸው የህግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መርምሮታል። እንደመረመርነውም፡- በወንጀል ክሱ የተመለከተውን የኮንትሮባንድ ዕቃ ስታጓጉዝ የተገኘችው የተጠሪ መኪና ልትወርስ ይገባል? ወይስ አይገባም? የሚለው ጭብጥ ተይዞ የተያዘው ጉዲይ እልባት ማግኘት ያለበት ሆኖ አግንተነዋል። በዚሁ መሰረት እንደሚከተለው ተመርምሮአል።
ተጠሪ ስያሽከረክረው የነበረው መኪና ኮድ ቁ 3-04051 ደሕ የሆነ የህዝብ ማመላለሻ ሚኒባስ የራሱ የግል ንብረት የሆነ መሆኑ፣ ሁለተኛ ተከሣሽ በነበረና በመኪናው የተሣፈረ ሰው የተጫነ የኮንትሮባንድ ዕቃ ለመንግስት ሉከፈል የሚገባ ታክስ እና ቀረጥ ከ21,791.66 ብር ያልተከፈለበት ሲያጓጉዝ በፕሉሶች መያዝ ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ ያየው የጋሞ አካባቢ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በፍሬ ነገር ረገድ ያረጋገጠው ከመሆኑም አልፍ የጥፊተኝነት ውሣኔ እና ቅጣት በተጠሪ ላይ የተጣለ መሆኑን መገንዘብ ይቻላል።
በዚሁ ፍርድ ቤት የተሰጠው የጥፊተኝነት ፍርድ እና ቅጣት ስለመለወጡ በተጠሪ በኩል የተመለከተ ነጥብ የለም።
የዚህ ሰበር ሰሚ ችልት ሥልጣን በኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 80/3/ሀ/ እና በአዋጅ ቁ 25/88 አንቀጽ 1ዐ መሰረት መሰረታዊ የህግ ስህተት ማረም በመሆኑ ማስረጃን የመቀበል እና የመመዘን ሥልጣን የበታች ፍርድ ቤቶች ሥልጣን በመሆኑ በዚህ ረገድ /በፍሬ ነገር / በበታች ፍርድ ቤት የተደረሰበትን መደምደሚያ መቀበለ ተገቢ ሆኖ ተገኝቷል።
ይሄ ከሆነ ደግሞ በተጠሪ ላይ የተላለፈው የጥፊተኝነት ውሣኔ በተሽከርካሪው መወረስ አለመወረስ ጋር ተያይዞ የሚያስከትለው ውጤት ምን እንደሆነና የበታች ፍርድ ቤቶች መኪናው ለባለቤቱ /ለተጠሪ/ ይመለስ ማለታቸው መሰረታዊ የህግ ስህተት ነው ወይስ አይደለም የሚለውን ነጥብ ማየቱ ተገቢ ነው። ተጠሪዎች የተከሰሱበት የኮንትሮባንድ ወንጀል በአዋጅ ቁ 622/2001 አንቀጽ 91/2/ ወንጀለ የተፈፀመበት ዕቃ ፣መሣሪያ እንደዚሁም የወንጀለ ፍሬ የሚወረስ መሆኑ እና በዚሁ አዋጅ አንቀጽ 2/1/ ሥር ዕቃ ለሚለው ቃል ተንቀሣቃሽ ንብረት /መኪና/ በመጨመር ከመደንገጉም በላይ በዚሁ አዋጅ አንቀጽ 104/1/ መሰረት ደግሞ የተሽከርካሪ ባለቤትና ሹፋር ሆኖ ተጠሪ ሲያሽከረክር በተፈፀመ የኮንትሮባንድ ወንጀል ጥፊተኛ መባለ ተጨማሪ ትዕዛዝ መስጠት ሣያስፈልግ ወይም ተጠሪ እንደሚከራከረው በአመልካች ላይ ላላ ክስ ማቅረብ ሣያስፈልግ መጓጓዥው እንዱወረሰ መታዘዝ እንዲለበት ይደነግጋል። ይሄ ከሆነ ጉዲዩን በመጀመሪያ የወንጀል ክሱን የተመለከተው ፍርድ ቤት የጥፊተኝነት ውሣኔ ሲሰጥ ወንጀለ የተፈፀመበትን የተጠሪ ተሽከርካሪ ለመንግስት ገቢ እንዱሆን ማዘዝ ሲገባው ለባለቤቱ ይመለስ ማለቱ የአዋጁን ግልፅ ድንጋጌ ፣ ዓላማና መንፈስ ያላገናዘበ በመሆኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ብለናል። በመሆኑም ቀጥል የተመለከተውን ውሣኔ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ
የካቲት 24 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጡት ውሣኔ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕግ አንቀጽ 195/2/ መ/ መሰረት ተሻሽልአል።
በተጠሪ ስመንብረት ተመዝግቦ የሚገኘው የሰላዲ ቁጥሩ ኮድ 3-04051 ደሕ የሆነች ህዝብ ማመላለሻ ሚኒባስ የኮንትሮባንድ ወንጀል የተፈፀመበት ተሽከርካሪ በመሆኗ በመንግስት እንድትወርስ በማለት ታዟል።
ተጠሪ የተሰጠውን ውሣኔ እንዱያውቀው በአርባ ምንጭ ማረሚያ ቤት በኩል ይተላለፍላቸው ብለናል።
No topics extracted.