No summary available.
ግንቦት 30 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጏስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሣ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ጅማ ቅ/ጽ/ቤት ነገረ ፈጅ - ምህረቱ ቁምላቸው - ቀረቡ ተጠሪ፡-
ጉዲዩ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ካቀረበው የቀደምትነት ባለመብት ክርክር ጋር የተያያዘው ሲሆን የተጀመረው በኦሮሚያ ብሓ/ክ/መንግስት በጅማ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ነው። በዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት የአሁን 1ኛ ተጠሪ በሁለተኛ ተጠሪ ላይ ድርሻው እንዱሰጠው በመክሰስ ካስወሰነ በኋላ በአፈጻጸም መዝገብ የ2ኛ ተጠሪ ንብረት የሆነው ክሉንክ ተሸጦ የአፈጻጸም ድርሻ እንዱሰጠው በታዘዘው መሰረት ሁለት ጊዜ ጨረታ ወጥቶ ገዢ ባለመቅረቡ የፍርድ ባለመብት /1ኛ ተጠሪ/ ንብረቱን ለመረከብ ጥያቄ አቅርቦ እያለ የአሁን አመልካች ጣልቃ ይግባ። የአሁን አመልካች በዐ9-2- 2002 ዓ.ም ጽፍ ባቀረበው ማመልከቻ 508,564.67 ብር የግብር እዲ ከአፈጻጸም ተከሣሽ /ከአሁን 2ኛ ተጠሪ/ ላይ ስላለን በግብር አዋጅ ቁጥር 286/94 አንቀጽ 80/1/ መሰረት የቅድሚያ መብት ስላለን የቅድሚያ መብታችን እንዱከበር የሚል ነበር። የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጉዲዩን ከመረመረ በኋላ አመልካች /የአሁን አመልካች/ ከላይ እንደተመለከተው ያመልክቱ እንጅ በአዋጅ ቁ. 286/2002 አንቀጽ 78/1/ መሰረት የባለዕዲውን መያዝ የሚችለው ንብረት አፈጻጸም ላይ ከላለ እና በዋስትና ያልተያዘ ከሆነ በመሆኑና ከላይ የተጠቀሰው ንብረት ደግሞ በአፈጻጸም ላይ ስላለ የጉምሩክ ጽ/ቤት የቀደምትነት መብት የለውም በማለት ውሣኔ ሰጥቷል። የአሁን አመልካች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ለክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ብል ፍ/ቤቱ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 337 መሰረት አጽንቶታል።
አሁን የቀረበው ቅሬታ በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ሲሆን በቀን 08/10/2002 ዓ.ም በ2 ገጽ በተጻፈ ማመልከቻ በገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን አዋጅ ቁ. 286/94 አንቀጽ 80/1/ መሰረት አመልካች ለግብር ዕዲ ሲጠየቅ ዋስትና ከተሰጣቸው አበዲሪዎች /ባንኮች/ ተከትል የቅድሚያ መብት ያለው ስለመሆኑ እየታወቀ ከጉዲዩ ጋር አግባብነት የላለውና በሶስተኛ ወገን የሚገኙቱን ንብረቶች ለማስለቀቅ የተደነገገውን የአዋጁን አንቀጽ 78/1/ በመጥቀስ የቀረበውን አቤቱታ ውድቅ ማድረጉ የህግ ስህተት ነው የሚል ነው። ጉዲዩ ያስቀርባል በመባለ 1ኛ ተጠሪ በቀን 20-4-2003 ዓ.ም በ3 ገጽ እና 2ኛ ተጠሪ ተወካይ በቀን 20-4-2003 ዓ.ም በ2 ገጽ በመጻፍ መልስ ሰጥተዋል። የሰጡት መልስ ፍሬ ሃሣብ በአጭሩ 1ኛ ተጠሪ የአመልካች ጥያቄ የዘገዬና ንብረቱንም በጊዜያዊነት እንዱያስተዲድር ትዕዛዝ ከተሰጠ በኋላ የቀረበ ከመሆኑም በላይ የቀድምትነት መብት አይገባውም የሚል ሲሆን 2ኛ ተጠሪ በበኩለ አመልካች አቅርቦት የነበረው የቀደምትነት መብት ውድቅ ተደርጏ የተወሰነው ውሣኔ አግባብ ባለመሆኑ ተሽሮ የአመልካች የቀደምትነት መብት እንዱከበር በማለት መልሷል።
አመልካች የመልስ መልስ አቅርቧል።
በግራ ቀኝ መካከል የተደረገው የክርክር ሂደት ከላይ የተመለከተው ሲሆን ችልቱም የቀረበውን የግራ ቀኙን ክርክር ከተያዘው ጭብጥና አግባብነት ካላቸዉ የህግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መርምሮታል። እንደመረመረውም ጉዲዩ ያስቀርባል ሲባል አመልካች በአዋጅ ቁ. 286/94 አንቀጽ 80/1/ መሰረት በልላው ሰው ገንዘብ ጠያቂነት በተያዘ ንብረት ላይ የቀደምትነት መብት አለው ወይስ የለውም የሚል ጭብጥ በመሆኑ ከዚሁ አኳያ መፍትሓ ማግኘት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል። በዚሁ መሰረት የአሁን 1ኛ ተጠሪ ከሁለተኛ ተጠሪ /ፍሮምሲ ኃ/የተ/የግ/ማህበር/ በገንዘብ ጠያቂነት ወይም ድርሻውን ለማስከራል እንደሆን አላከራከረም። በልላ በኩል 1ኛ ተጠሪ በሁለተኛ ተጠሪ /ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ላይ/ ያቀረበው የአፈጻጸም ክስ በሚመለከተው ንብረት ላይ ቀድሞ በዋስትና ያልተሰጠው ስለመሆኑ አላከራከረም።
ይሄንን መሰረታዊ ሃሣብ ይዘን የአዋጅ ቁ. 286/94 አንቀጽ 80/1/ እንደሚከተለው ይነበባል።
‛ዋስትና የተሰጣቸው የላልች አበዲሪዎች የቅድሚያ መብት እንደተጠበቀ ሆኖ፤ በዚህ አዋጅ መሰረት ግብር ተከፊይ ከሚሆንበት አንስቶ ተከፍል እስካለቀበት ጊዜ ድረስ ግብር የመክፈል ግዳታ ባለበት ሰው ሃብት ላይ ባለስልጣኑ ከማናቸውም ላልች ዕዲዎች የቀደምትነት መብት ይኖረዋል።“ የሚል ነው።
ከዚህ አንቀጽ በግልጽ መረዲት እንደሚቻለው ከአመልካች ሉቀድም የሚችለው በዋስትና ቀድሞ የተያዘ ከሆነ ብቻ እንደሆነ መገንዘብ ይቻላል።
ከላይ በተመለከተው አዋጅ ቁ. 286/94 አንቀጽ 78/1/ አሁን ከተያዘው ጉዲይ ጋር አግባብነቱን ስንመረምር የግብር ከፊይ ንብረት የሆነ በልላ ሶስተኛ ወገን ሲገኝና በግብር አስገቢው ባለስልጣን እንዱያስረክበው ሲጠየቅ የማስረከብ ኃላፉነት ያለበት ስለመሆኑና የማያስረክብበት አንደ ምክንያት ላሆን የሚችለው በአፈጻጸም ላይ ስለመሆኑ በመግለጽ እንደሆነ የሚገልጽ ነው። ይሄ አንቀጽ ከተያዘው ጉዲይ ጋር በቀጥታ አግባብነት ያለው ባይሆንም አንቀፁ ሉደነግግ ያሰበው ንብረቱን ለመረከብ ሲፈልግ መከተል ያለበትን ስነ ሥርዓት ከመደንገግ አኳያ በመሆኑ የቀደምትነት መብትን ቀሪ የሚያደርግ አይደለም።
በአጠቃላይ በአዋጅ ቁ. 286/94 አንቀጽ 80/1/ መሰረት አመልካች ያቀረበው የቀድምትነት መብት በዚሁ አንቀጽ መሰረት ታይቶ መወሰን ሲገባው ከጉዲዩ ጋር ተያያዥነት የላለውን የአዋጁን ላላ አንቀጽ በመጥቀስ የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአመልካችን አቤቱታ ውድቅ ማድረጉና የይግባኝ ሰሚውም ፍርድ ቤት ይሄንን ሣያስተካክል ውሣኔውን ማጽናቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ አግኝተነዋል። በመሆኑም ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በኦሮሚያ ብሓ/ክ/መንግስት የጅማ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመዝ/ቁ. 10/86 በቀን 18-2- 2002 ዓ.ም እና የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት በመዝ/ቁ. 89407 በቀን 05-9-2002 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጠው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሮአል።
አመልካች የጠየቀው የግብር ዕዲ በአዋጅ ቁ. 286/94 አንቀጽ 80/1/ መሰረት ከአንደኛ ተጠሪ የቀደምትነት መብት አለው ብለናል።
በዚህ ችልት በግራ ቀኙ ለደረሰው ወጪና ኪሣራ የየራሣቸውን ይቻለ ብለናል።
መዝገቡን ዘግተናል። ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.