No summary available.
ግንቦት 5 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጏስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሣ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ዐ/ሕግ - አልቀረበም ተጠሪ፡- አቶ በርሄ ሐጏስ - ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
የስር ከሣሽ /ያሁን የሰበር አመልካች/ በስር ተከሣሽ /በሰበር ተጠሪ/ ያቀረበው ክስ ተከሣሹ ንብረትነቱ የራሱ በሆነው ኮድ3-29644 አይሱዙ የጭነት መኪና 56 ቦንዲ ልባሽ ጨርቅ ጭኖ ከጨርጨር ወደ መቀላ ከተማ በ26/4/2001 ዓ.ም ምሽት 3፡3ዐ ሲጓዝ እጅ ከፍንጅ በመያዙ የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 60/89 በተሻሻለው አዋጅ ቁጥር 368/95 አንቀጽ 64/1/ ተላልፍ በመገኘቱ ተከሷል የሚል ነው።
ተከሣሹም ፍ/ቤት ቀርቦ የእምነት ክህደት ቃለ ሲጠየቅ ወንጀለን አለመፈጸሙንና ጥፊተኛ አለመሆኑን ክድ በመከራከሩ የስር የትግራይ ክልል ደቡብ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ጉዲዩን ከቀረቡት የግራ ቀኙ ማስረጃዎች አንጻር ከመረመረ በኋላ ከሣሹ ጠቅሶ ክስ ያቀረበበትን የወንጀል አንቀጽ 64/1/ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 113/2/ መሰረት ለውጦ በአዋጅ ቁጥር 368/95 አንቀጽ 74 ስር ጥፊተኛ ነው በማለት ተከሣሹ በ3 ዓመት ቀላል እስራትና በ5ዐዐዐ ብር መቀጮ እንዱቀጣ ፣ የተያዘው 56 ቦንዲ ልባሽ ጨርቅ ለመንግስት ገቢ እንዱሆንና መኪናው ለተከሣሽ እንዱመለስ በማለት ወስኗል።
ጉዲዩን በይግባኝ የተመለከተው የትግራይ ክልል ጠ/ፍ/ቤት በበኩለ የይግባኝ ባዩን /የስር ከሣሽን/ ይግባኝ በመሰረዝ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 195/1/ ይግባኝ ባዩን አሰናብቷል።
በስር ፍ/ቤቶች ውሣኔ ላይ ቅር የተሰኘው የአሁኑ አመልካችም ባቀረበው የሰበር አቤቱታ የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 60/89 ያሻሻለው አዋጅ ቁጥር 365/95 አንቀጽ 64/4/ ተጠሪው በራሱ መኪና በህግ የተከለከለውን 56 ቦንዲ ጭኖ በመገኘቱ ክስ ተመስርቶበትና በማስረጃ ተረጋግጦ እያለ ተጠቅሶ ክስ ከቀረበበት የህግ አንቀጽ መንፈስ ወጪ መኪናው ለተጠሪ ይመለስ ተብል የተወሰነው መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት በመሆኑ የተፈጸመው የህግ ስህተት ታርሞ መኪናው ለመንግስት ገቢ እንዱደረግ እንዱወሰን ጠይቋል።
ለሰበር ቅሬታው ተጠሪው በሰጠው መልስ አመልካች በ24/6/2001 ዓ.ም ለስር ትግራይ ክልል ደቡብ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ያቀረበው ክስ ወንጀለ ብቻ የሚመለከት እንጂ አሁን ቅሬታ የቀረበበት መኪና ይወረስልኝ በሚል አይደለም። ስለሆነም በስር ፍ/ቤቶች ውሣኔ ላይ የተፈጸመ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የለም ሲል ተከራክሯል።
የግራ ቀኙ ክርክር ከዚህ በላይ እንደተመለከተው አጥሮ የቀረበ ሲሆን እኛም በተጠሪ አሽከርካሪነት 56 ቦንዲ ልባሽ ጨርቅ ጭኖ የተያዘው መኪና ለመንግስት ገቢ ላሆን ይገባል ወይስ አይገባም የሚለውን ጭብጥ ይዘን እንደሚከተለው መርምረናል።
የስር ከፍተኛ ፍ/ቤት የአሁኑ አመልካች ጠቅሶ ክስ ያቀረበበትን አዋጅ ቁጥር 368/95 አንቀጽ 64/4/ ከግራ ቀኙ ማስረጃዎች አንጻር ሲመረመር ከጉዲዩ ጋር አግባብነት የለውም በሚል በአዋጅ ቁጥር 368/95 አንቀጽ 74 ስር ጥፊተኛ ነው ብሎል። በዚህ አንቀጽ ጥፊተኛ የተደረገ ሰው ደግሞ የተያዘበት ዕቃ መወረሱ እንደተጠበቀ ሆኖ በዕቃው ላይ ሉከፍል ከሚገባው ጠቅላላ የቀረጥና የታክስ ሂሣብ በማያንስ የገንዘብ መቀጮና ከሶስት እስከ አምስት ዓመት በሚደርስ እስራት ይቀጣል።
በዚህ በተያዘው ጉዲይ ግን የስር ፍ/ቤት እንዲረጋገጠው ያሁኑ የሰበር ተጠሪ ንብረትነቱ የራሱ በሆነው አይሱዙ የጭነት መኪና የተጠቀሰውን የኮንትሮባንድ ዕቃ ጭኖ ሲጓዝ እጅ ከፍንጅ ተይዟል። በዚህ የወንጀል ድርጊትም በአዋጁ የማጓጓዝ ሀላፉነት የሚያስከትለውን ግዳታ በመጣሱ ከጉዲዩ ጋር አግባብነት ያለው እንደ ስር ፍ/ቤቶች አተረጓጏም አዋጅ ቁጥር 368/95 አንቀጽ 74 ሣይሆን የተጠቀሰው አዋጅ አንቀጽ 64/4/ ነው። የተጠሪው ድርጊት በአንቀጽ 64/4/ የሚሸፈን ከሆነ ደግሞ የሚወረሰው በኮንትሮባንድ የተያዘ ዕቃ ብቻ ሣይሆን የዕቃው ማጓጓዣ /መኪና/ ጭምር ነው።
በመሆኑም የስር ፍ/ቤቶች አመልካችን ጠቅሶ ክስ ያቀረበበትን የህግ ቁጥር ያለአግባብ በመለወጥ ጥፊተኛ ነው በማለት የቅጣት ውሣኔ ያስተላለፊበት የህግ ቁጥር የማጓጓዣ ሀላፉነት ግዳታ ጥሶ ለተገኘው ለመጓጓዣው ባለቤት ተፈጻሚነት የላለው በመሆኑ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ው ሣ ኔ
የስር የትግራይ ክልል ደቡብ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመዝገብ ቁጥር 10/12117 በቀን 24/10/2001 በዋለው ችልት የሰጠው ፍርድ እንዱሁም የትግራይ ክልል ጠ/ፍ/ቤት የወንጀል ችልት በመ/ በቀን 06/12/2001 ጉዲዩን በይግባኝ ተመልክቶ የሰጠው ትዕዛዝ ተሻሽለዋል።
የሰበር ተጠሪ በአዋጅ ቁጥር 368/95 አንቀጽ 64/4/ ስር ጥፊተኛ ነው ብለን ወስነናል።
ቅጣትን በሚመለከት የስር ከፍተኛ ፍ/ቤት በ3 ዓመት ቀላል እስራትና በ5ዐዐዐ /አምስት ሺህ/ መቀጮ ተጠሪው እንዱቀጣ የወሰነው በአግባቡ በመሆኑ ጸንቷል።
በዚህ ችልት ተጠሪው ጥፊተኛ የተደረገበት አዋጅ ቁጥር 368/95 አንቀጽ 64/4/ የኮንትሮባንድ ዕቃ የጫነው ማጓጓዣ ጭምር እንዱወረስ የሚደነግግ በመሆኑ በተጠሪ አሽከርካሪነት የተያዘው የተጠሪ ኮድ 3-29644 አይሱዙ የጭነት መኪና ተወርሶ ለመንግስት ገቢ እንዱሆን ወስነናል።
መዝገቡ የተዘጋ ስለሆነ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
እ.ከ የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት
No topics extracted.