No summary available.
የካቲት 11 ቀን 2003 ዓ/ም.
ዳኞች-፡- ሐጎስ ወልደ ዲኜ መላኩ ተሻገር ገ/ሥላሴ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- አቶ ዓለሙ ጋባ - ጠበቃ ወልደስላሴ - ቀረቡ ተጠሪ፡- የፋዳራል ገቢዎች ጉምሩክ ባለሥልጣን - ዐቃቤ ሕግ ሽመልስ አበበ - ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ ከተጨማሪ እሴት ታክስ ጋር ተያይዞ የተነሳን የወንጀል ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የአሁኑ ተጠሪ በአሁኑ አመልካች ላይ በመሰረተው ክስ መነሻ ነው። የክሱ ይዘትም፡- 1ኛ፡- አመልካች የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 285/94 በአዋጅ ቁጥር 609/2001 እንደተሻሻለው አንቀፅ 22(1) እና 50(ለ-1) ስር የተመለከተውን በመተላለፍ በአዱስ አበባ ከተማ አዱስ ከተማ ክፍለ ከተማ ቀበላ 13 ክልል ውስጥ በሚገኝ ቁጥሩ 081 በተሰጠውና በንግድ ፈቃድ ቁጥር 02/1/3/01096/98 የሚሰራ የዓባይ ዙሪያ ሆቴል ተብል በሚጠራው ቤት ጥር 14 ቀን 2002 ዓ/ም ከቀኑ 8፡00 አከባቢ የአንድ ለስላሳ እና ሻይ ግብይት በብር 5.25 ያለተጨማሪ እሴት ታክስ ደረሰኝ በሰራተኛቸው አማካይነት በመሸጣቸው ተከሰዋል የሚል ሲሆን ሁለተኛው ክስ የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 285/94 እንደተሻሻለው አንቀፅ በአንቀጽ 50(መ-1) ስር የተመለከተውን በመተላለፍ በድርጅቱ ውስጥ በባልሥጣኑ እውቅና የተሰጠበት የሽያጭ መመዝገቢያ መሥሪያ ከህዲር 25 ቀን 2002 ዓ/ም እስከ ታህሳስ 24 ቀን 2002 ዓ/ም ድረስ ባለው ጊዜ ገዝቶ የመጠቀም ግዳታ የተጣለበት ቢሆንም በሆቴለ ውሰጥ በባለስልጣኑ መሥሪያ ቤት እውቅና ያልተሰጠውንና "ናን ፉስካላይዝድ ማሽን" ሲጠቀሙ ተገኝተዋል የሚል ነው።
አመልካችም እንደ አቃቤ ክስ ድርጊቱን ያለመፈጸማቸውን በመግለፅ ክሱን ክደው የተከራከሩ ሲሆን ተጠሪ አለኝ ያላቸውን የሰው ምስክሮችን አስቀርቦ አሰምቷል። ከዚህም በኋላ አመልካች እንዱከላከለ ተደርጎ የመከላከያ ምስክሮችን አስቀርበው አሰምተዋል። ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍርድ ቤትም ጉዲዩን መርምሮ የአመልካች መከላከያ ምስክሮች የአቃቤ ሕጉን ማስረጃዎችን ያላስተባበለ መሆኑን በመግለፅ ቃላቸውን ውድቅ ከአደረገ በኋላ አመልካችን በአቃቤ ሕግ በኩል ተጠቅሶ በቀረበባቸው ድንጋጌ ስር ጥፊተኛ በማድረግ በ1ኛ ክስ በሁለት አመት ከስድስት ወር ጽኑ እስራትና በብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር)፣ በሁለተኛው ክስ ደግሞ በአንድ አመት እሥራት በድምሩ በሦስት አመትና በስድስት ወር እስራትና በብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) እንዱቀጡ ሲል ወስኗል። ከዚህም በኋላ አመልካች በስር ፍርድ ቤት በተላለፈባቸው የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበው ፍርድ ቤቱ ተጨማሪ ማስረጃዎችን ከተቀበለና ግራ ቀኙን ከአከራከሩ በሁዋላ በአመልካች ላይ የተሰጠውን የጥፊተኝነትን ውሳኔ ሙለ በሙለ በመቀበል የእስራት ቅጣት ውሳኔውን ግን ወደ ሁለት አመት እሥራት ዝቅ አድርጎ የገንዘብ መቀጮውን ደግሞ እንዲለ በመቀበል የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ አሻሽል ወስኗል።
የሰበር አቤቱታው የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
የአመልካች ጠበቃ ያቀረቡት የሰበር አቤቱታ ነሐሴ 27 ቀን 2002 ዓ.ም. የተፃፈ ሲሆን ይዘቱም ባጭሩ፡- የበታች ፍርድ ቤቶች አመልካችን ጥፊተኛ በማለት የወሰኑት በሕጉ አግባብ አቃቤ ሕግ ባላስረዲበትና ተጨማሪ ማስረጃዎችም ቢሆኑ አመልካች ደረሰኙን እንዱታተም ለማድረግ እንዱሁም ማሽኑን ለማስገባት ተገቢውን ጥረት ሲያደርግ የነበረ መሆኑን ባረጋገጡት ሁኔታ ስለሆነ የጥፊተኝነት ውሳኔው ሉሻር የሚገባው ነው በማለት መከራከራቸውን የሚያሳይ ነው። የሰበር አቤቱታው ተመርምሮም አመልካች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆኑ በመ/ቤቱ የተገለፀለት ደብዲቤ እጁ ከገባ ከታህሳስ 13 ቀን 2002 ዓ.ም. ጊዜ ጀምሮ መ/ቤቱ በሰጠው ጊዜ ውስጥ አስፈላጊውን ደረሰኞችንና የሂሳብ መኪና ለማስገባት ተገቢውን እንቅስቃሴ ሲያደርጉ መቆየቱ በስር ፍርድ ቤቶች ተረጋገጦ እያለ ጥፊተኛ ተብለው መቀጣታቸው በአግባቡ መሆን ያለመሆኑን ለመመርመር ተብል በመታዘዙ ተጠሪ ቀርቦ አመልካች ጥፊተኛ ተብለው ሉቀጡ ይገባል በሚል የተሰጠው ውሳኔ ሕጉን መሰረት ያደረገ መሆኑን ዘርዝሮ ውሳኔው ሙለ በሙለ ሉጸና ይገባል ሲል ተከራክሯል። የአመልካች ጠበቃም ባቀረቡት የመልስ መልስ የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር ተከራክረዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆኑት ውሳኔዎችና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩን በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመረውም የችልቱን ምላሽ የሚያስፈልገው አቢይ ነጥብ አመልካች ጥፊተኞች ተብለው መወሰኑ በአግባቡ ነው? ወይስ አይደለም? የሚለው ሲሆን ቅጣት ጋር ተያይዞ የቀረበው ክርክር በዚሁ ጭብጥ እልባት የሚያገኘ ሆኖ አግኝቶታል።
በዚህም መሰረት አመልካች የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 285/94 በአዋጅ ቁጥር 609 እንደተሻሻለ አንቀፅ 22(1) እና 50(ለ-1) ስር የተመለከተውን በመተላለፍ ያለተጨማሪ እሴት ታክስ ግብይት ማከናወናቸውን ተጠሪ በሕጉ አግባብ አስረድቷል ወይስ አላስረዲም?፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 285/94 በአዋጅ ቁጥር 609 እንደተሻሻለ 50(መ-1) ስር የተመለከተውን በመተላለፍ ከባለሥልጣኑ መሥሪያ ቤት እውቅና ውጪ የሽያጭ መኪና ይዘው ተገኝተዋል? ወይስ አልተገኙም? የሚለትን ጥያቄዎችን በማንሳት በስር ፍርድ ቤት በአቃቤ ሕጉ ማስረጃዎችና በአመልካች ማስረጃዎች ጭምር ከተረጋገጡት ፍሬ ጉዲዮች እና አግባብነት ካላው ሕግ ጋር በማገናዘብ ተመልክተናል። አመልካች የተከሰሱት 1ኛው ክስ፡- የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 285/94 አንቀጽ 55 እና በአዋጅ ቁጥር 609 እንደተሻሻለ አንቀፅ 22(1) እና 50(ለ-1) በመተላለፍ ሆቴል ድርጅቱን በወኪልነታቸው በሚያስተዲድሩበት ጊዜ ሽያጭ ያለተጨማሪ እሴት ታክስ ደረሰኝ አከናውነዋል በሚል ነው። በስር ፍርድ ቤት የቀረቡት የተጠሪ ምስክሮች በሰጡት የምስክርነት ቃል ይኸው ተረጋግጧል። አመልካችም እስከዚህ ሰበር ሰሚ ችልት በሚያቀርቡት ክርክር ግብይቱ በተጨማሪ እሴት ታክስ ደረሰኝ ተከናውኗል የሚል ክርክር ሳይኖራቸው አጥብቀው የሚከራከሩት በባለሥልጣኑ መሥሪያ ቤት በተሰጠው ጊዜ ውስጥ አስፈላጊውን ደረሰኞችንና የሂሳብ መኪና ለማስገባት ተገቢውን እንቅስቃሴ ሲያደርጉ የነበረ መሆኑን በመግለፅ ነው። ይሁን እንጂ ባለሥልጣኑ መሥሪያ ቤት አመልካች በውክልና የሚያስተዲድሩትን የሆቴል ድርጅት በተጨማሪ እሴት ታክስ ከፊይነት የመዘገበው ከጥቅምት 01 ቀን 2002 ዓ/ም ጀምሮ መሆኑና የምስክር ወረቀት መስጠቱን፣ ግብይቱ ያለተጨማሪ እሴት ታክስ ደረሰኝ የተከናወነው ደግሞ ጥር 14 ቀን 2002 ዓ/ም መሆኑ በአቃቤ ሕጉ ማስረጃዎች የተረጋገጠ ጉዲይ ነው። አንድ ግብር ከፊይ ለተጨማሪ እሴት ታክስ ግብር ከፊይነት ተመዘገበ የሚባለው ደግሞ ከተመዘገበበት ቀን ወይም ምዝገባው ከሚጸናበት ጊዜ ጀምሮ ስለመሆኑ በአዋጅ ቁጥር 285/1994 አንቀጽ 3(1) እና (2) ድንጋጌዎች ስር በግልፅ ተመልክቷል። የዚሁ አዋጅ አንቀጽ 22(1) ድንጋጌ ሲታይም ለተጨማሪ እሴት ታክስ ግብር ከፊይነት የተመዘገበ ማንኛውም ሰው ከተመዘገበበት ጊዜ ጀምሮ ለሚያድርገው ግብይት የተጨማሪ እሴት ታክስ ደረሰኝ ለተጠቃሚው ወዱያውኑ መስጠት እንደአለበት አስገዲጅነት ባለው ኃይለቃል ደንግጎ እናገኛለን። ሕጉ በተገቢው ጊዜ ደረሰኝ ሳያሳትም ግብይት ያከናወነ ግብር ከፊይ ጥረት እያደረገ ቢቆይና ግብይቱን ያለተጨማሪ እሴት ታክስ ከአከናወነ ተጠያቂነት የላለበት ስለመሆኑ የሚያሳይ ድግንጋጌ የለውም። አመልካች ተገቢውን ጥረት ሲያደርጉ የነበረ መሆኑን ተረጋግጧል የሚለት በመከላከያ ምስክሮችና በሰነድ ማስረጃዎቻቸው ነው። ይሁን እንጂ አመልካች ደረሰኙን በተሰጣቸው የጊዜ ገደብ ያላሳተሙበትን ሕጋዊ ምክንያት ያላስረደ መሆኑን ፍሬ ነገርን የማጣራትና ማስረጃን የመመዘን ሥልጣን ያላቸው የበታች ፍርድ ቤቶች ያረጋገጡት ጉዲይ መሆኑን ከውሳኔው ተገንዝበናል። እንዱህ ከሆነ ይህ ችልት በኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 80(3(ሀ)) እና አዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 10 መሰረት በተሰጠው ሥልጣን የበታች ፍርድ ቤቶች በፍሬ ነገር ደረጃ የደረሱበትን ድምዲሜ የሚያጣራበት ወይም ማስረጃውን የሚመዝንበት አግባብ የለም። በመሆኑም አመልካች ደረሰኙን እንዱዘጋጅ ሳያደርጉ ወይም ያላዘጋጁት ከራሳቸው ቁጥጥር ውጪ በሆነ ሁኔታ ስለመሆኑ ባላስረደበት ሁኔታ በ1ኛ ክስ የተሰጠው የጥፊተኝነት ውሳኔ ተገቢነት የለውም በማለት የሚያቀርቡት ክርክር ሕጋዊነት ያለው ሆኖ አላገኘነውም።
ላላው አመልካች ጥፊተኛ የተባለት በባለሥልጣኑ መሥሪያ ቤት በተሰጣቸው የጊዜ ገደብ ውስጥ ሕጋዊ የሽያጭ መኪና ሳይጠቀሙ ከሕግ ውጪ በሆነ ሁኔታ (ከባለሥልጣኑ መሥሪያ ቤት እውቅና ውጪ) ናን ፉሲካላይዝድ የሚባል የሽያጭ መኪና ይዘው መገኘታቸው በፍሬ ነገር ደረጃ በበታች ፍርድ ቤቶች የተረጋገጠ ጉዲይ ነው። በልላ አገላለፅ ተጠሪ አመልካች ከሕዲር 25 ቀን 2002 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ታህሳስ 24 ቀን 2002 ዓ.ም. ባለው ጊዜ ውስጥ እውቅና የተሰጠው የሽያጭ መመዝገቢያ ያለመጠቀማቸውን አስረድቷል። በአዋጅ ቁጥር 471/1998 አንቀጽ 5፣ በአዋጅ ቁጥር 285/1994 አንቀጽ 64፣ በአዋጅ ቁጥር 286/1994 አንቀጽ 117 መሰረት ደግሞ ለጉዲዩ ደንብ የማውጣት ሥልጣን ያለው አካል ተለይቶ የተቀመጠ ሲሆን ይህንኑ ተከትል ደንብ ቁጥር 139/1999 ወጥቷል። በዚህ ደንብ ደግሞ ለጉዲዩ አፈፃጸም መመሪያ ባለሥልጣኑ መሥሪያ ቤት መመሪያ ለማውጣት የሚችልበት አግባብ ያለ ስለመሆኑ አንቀጽ 22 የሚያስቀምጥ ሲሆን ደንቡን ተከትል ደግሞ መመሪያ ቁጥር 46/1999 ተብል የሚጠቀስ መመሪያ በሥራ ላይ ውሎል። በዚህም መሰረትም ተጠሪ መሥሪያ ቤት ግብር ከፊይ የሆነውና አመልካች በውክልና የሚያስተዲድሩት የሆቴል ድርጅት ሕጋዊውን የሽያጭ መመዝገቢያ ማሽን ገዝቶ እንዱጠቀም በሚገባ ያሳወቃቸው ስለመሆኑ ተረጋገጧል። አመልካች የተገለፀላቸው ጊዜ አልፍ ሕጋዊውን የሽያጭ መመዝገቢያ ማሽን ሳይጠቀሙ ሕጋዊ ያልሆነውን ሲጠቀሙ መገኘታቸው ከተረጋገጠ ደግሞ በአዋጅ ቁጥር 285/1994 በአዋጅ ቁጥር 609 እንደተሻሻለው በአንቀጽ 50(መ) መሰረት ተጠያቂነት ይኖርባቸዋል። አመልካች ተገቢውን ጥረት ሲያደርጉ ነበር፣ መሳሪያውን ገዝተው እንዱጠቀሙ የተሰጣቸውና የወንጀል ድርጊቱ ተፈፀመ የተባለበት የ
No topics extracted.