No summary available.
ጥር 1ዐ ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ ዲኜ መላኩ ተሻገር ገ/ሥላሴ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- የሰሜን ምስራቅ ጉምሩክ ሜላ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት - ነ/ፈጅ ተጠሪ፡- በረከት አሰፊ - በላለበት የሚታይ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ ከሕግ ውጭ የተያዘው መኪናዬ ይለቀቅልኝ፣ በመኪናው ሰርቼ ላገኝ እችል የነበረው የቀን ገቢ ብር 7ዐዐ,ዐዐ ተሰልቶ ይከፈለኝ በማለት የአሁኑ ተጠሪ በአሁኑ አመልካች ላይ የመሰረተውን ክስ መነሻ አድርጎ የተካሄደውን ክርክር የሚመለከት ነው። የአሁኑ አመልካች ለተጠሪ ክስ በሰጠው መልስም ድርጊቱ ሕጉ በሰጠው ስልጣን መሰረት የተፈፀመና ኃላፉነት የሚያስከትል መሆኑንና ተቋረጠ የተባለው ገቢም ሕጋዊ ስለመሆኑ በማስረጃ ያልተደገፈ መሆኑን በመግለጽ ክሱ ውድቅ ላሆን ይገባል ሲል ከመከራከሩም በተጨማሪ መኪናውን የያዙት የአመልካች መሥሪያ ቤት ሰራተኞች ወደ ክርክሩ እንዱገቡ ይታዘዙለት ዘንድ ዲኝነት ጠይቋል። ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በሁዋላ አመልካች መኪናውን እንዱለቅ፣ እንዱሁም መኪናው በአመልካች ተይዞ በመቆየቱ ምክንያት ተጠሪ የቀን ገቢ የተቋረጠባቸው መሆኑ ተረጋግጧል በሚል ምክንያት ብር 1ዐ5, ዐዐዐ.ዐዐ /አንድ መቶ አምስት ሺህ ብር/ ለተጠሪ አመልካች እንዱከፈል ሲል ወስኗል። በዚህ ውሣኔ አመልካች ባለመስማማትም ይግባኙን ለአማራ ብሓራዊ ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቢያቀርብም ይግባኙ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 337 መሰረት ተሰርዞበታል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሣኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
የአመልካች ነገረፈጅ የካቲት 27 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም በተፃፈ ሶስት ገጽ የሰበር አቤቱታ በበታች ፍርድ ቤቶች ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል የሚለበትን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም ባጭሩ የአመልካች አድርራት በአዋጅ ቁጥር 6ዐ/1989 መሰረት የተፈቀደ ሁኖ እያለና የተጠሪ የመኪና ገቢም በተገቢው መንገድ ግብር ሲከፈልበት የነበረ መሆኑ ሣይረጋገጥ የተቋረጠ ገቢ አመልካች ለተጠሪ ብር 1ዐ5,ዐዐዐ.ዐዐ /አንድ መቶ አምስት ሺህ ብር/ እንዱከፍል መወሰኑ ያላግባብ ስለሆነ ሉታረም ይገባል በማለት መከራከራቸውን የሚያሣይ ነው። አቤቱታው ተመርምሮም በጉምሩክ ተይዞ የቆየው መኪና የቤት መኪና መሆኑ ሣይካድ ተጠሪ ገቢ አጥቷል ተብል አመልካች ብር 1ዐ5,ዐዐዐ.ዐዐ ይክፈል ተብል የመወሰኑን አግባብነት ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ችልት እንዱቀርብ ተደርጓል። በዚህም መሰረት ለተጠሪ በዚህ ፍርድ ቤት ጥሪ በተገቢው መንገድ ተደርጎላቸው ባለመቅረባቸው ጉዲዩ በላለበት እንዱታይ ተደርጓል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም በስር ፍርድ ቤት የተደረገውን የግራ ቀኙን ክርክርና በበታች ፍርድ ቤቶች የተሰጠውን ውሣኔ ከአመልካች የሰበር አቤቱታና ከሕጉ ጋር በማገናዘብ ጉዲዩ ለሰበር ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው አመልካች የተጠሪን መኪና ይዞ በቁጥጥር ስር ሉያውል የቻለው መኪናዋ ኮንትሮባንድ እቃ የጫነውን መኪና ፉት ለፉት በመሆን አጅባ ትጓዝ ስለነበረ በኮንትሮባንድ ድርጊት ተሣትፍ አድርጋለች በሚል ጥርጣሬ ነው በማለት አመልካች የሚከራከር መሆኑና የተያዘችው የተጠሪ መኪና የቤት መኪና መሆኗ መረጋገጡን ነው።
የአመልካች መ/ቤት ስልጣንና ተግባር በአዋጅ ቁጥር 6ዐ/1989 በአንቀጽ 6 እና 58 ስር ተዘርዝሯል። እነዚህ የአዋጁ ድንጋጌዎች የሚያሣዩት የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴን ለመቆጣጠር የጉምሩክ ባለሥልጣንና ሹም የተሰጣቸው ስልጣንና ተግባራት በዝርዝር መቀመጣቸውን ነው።
የጉምሩክ ባለሥልጣንን እንደገና ለማቋቋምና አሰራሩን ለመወሰን የወጣውን አዋጅ ለማሻሻል የወጣው አዋጅ ቁጥር 368/1995 ደግሞ ኮንትሮባንድ ማለት ሕጎችንና በሕግ መሰረት የወጡ መመሪያዎችን በመተላለፍ ወደ ጉምሩክ ክልል ዕቃዎችን በማስገባት ወይም ከጉምሩክ ክልል በማስወጣት፣ በሕጋዊ መንገድ የመጡትን በሕገ ወጥ መንገድ መልሶ ማስገባት መያዝ፣ ማከማቸት፣ ማዘዋወር ማስተላለፍ እንዱገቡ ወይም እንዱወጡ ለማድረግ መሞከር እና እንደዚህ ላለ ድርጊቶች መተባበርን እንደሚጨምር በአንቀጽ 2/28/ተርጓሜ ሰጥቶበታል።
ከላይ እንደተጠቀሰው አመልካች ተግባሩን ሕጋዊ ነው ብል ሲከራከር በተለይ መሰረት ያደረጋቸው የአዋጅ ቁጥር 6ዐ/89 አንቀጽ 6/5/ እና 58/1/ለ/ ድንጋጌዎችን ነው። አንቀጽ 6/5/ ሙለ ይዘቱ ሲታይ ባለሥልጣኑ ‛በኮንትሮባንድ ወደ አገር የሚገቡትን ወይም ከአገር የሚወጡትን ዕቃዎች እንቅስቃሴ ይቆጣጠራል፣ ይከላከላል፣ በዚሁ ሁኔታ የሚንቀሣቀሱ ዕቃዎችንና ማጓጓዣዎችን ይይዛል፤ አስፈላጊውን ሕጋዊ እርምጃ ይወስዲል“ በማለት ሲደነግግ አንቀጽ 58/1/ለ/ ደግሞ ወደ አገር እንዲይገቡ ወይም ከአገር እንዲይወጡ የተከለከለ፣ ገደብ የተደረገባቸው ወይም ቀረጥ እንዲይከፈልባቸው በማሰብ የተደበቁ ዕቃዎች በፍተሻ ሲገኙ ዕቃዎችን የመያዝ እንዱሁም እንደሁኔታው ማጓጓዣውን የማጓጓዣውን ኃላፉ ወይም የዕቃውን ባለቤት ይዞ ለምርመራ በጥበቃ ሥር የማቆየት ስልጣንና ኃላፉነት የጉምሩክ ባለሥልጣን ያለው መሆኑን ይደነግጋል። ከእነዚህ ድንጋጌዎች ይዘት መገንዘብ የሚቻለው የጉምሩክ ባለሥልጣን በኮንትሮባንድ ወደ አገር የሚገቡትን ወይም ከአገር የሚወጡትን ዕቃዎች እንቅስቃሴ የመቆጣጠር፣ የሚንቀሣቀሱ ዕቃዎችንና ማጓጓዣዎችን የመያዝና አስፈላጊ እርምጃዎችን የመውሰድ፣ በሕገ ወጥ መንገድ መገልገያ የሆኑ መጓጓዣዎችን የመያዝና አስፈላጊ እርምጃዎችን የመውሰድ በሕገ ወጥ መንገድ መገልገያ የሆኑ መጓጓዣዎችን ጭምር ይዞ ለምርመራ በጥበቃ ስር የማቆየት ስልጣን በሕጉ የተሰጠው መሆኑን ነው። እነዚህን ተግባራት የሚያከናውነው ግን ኮንትሮባንድ ተብል በሕግ የተሰጠው ትርጓሜ ተሟልቶ ሲገኝ ነው ተብል ይታመናል። ማንኛውም የዕቃ እንቅስቃሴ ኮንትሮባንድ ስለመሆኑ አሣማኝ እና በቂ ምክንያት ሣይኖረው ባለሥልጣኑ መ/ቤት እንዱይዝና እንዱቆጣጠር ሕጉ ስልጣን ተሰጥቶታል ተብል አይታሰብም። እንዱሁም እቃው ኮንትሮባንድ ስለመሆኑ በቂ ጥርጣሬ ሲኖረውም ባለሥልጣኑ መሥሪያ ቤት ዕቃውን የመያዝ ስልጣን ያለው መሆኑን ከላይ የተጠቀሱት ድንጋጌዎች ይዘት ያሣያል። የኮንትሮባንድ ድርጊት ደግሞ የኮንትሮባንድ እቃ ነው የተባለውን ጭኗል በተባለ መኪና ብቻ ይፈፀማል ወደሚለው ድምዲሜ የሚያደርስ ሕጋዊ ምክንያት የለም። ድርጊቱ ወንጀል እንደመሆኑ መጠን የአድራጊዎች ተሣትፍም የተለያየ ደረጃና መልክ ሉኖረው እንደሚችል ይታመናል። በመሆኑም የባለሥልጣኑ መሥሪያ ቤት በሕጉ የተሰጠውን ኃላፉነትና ተግባር ሲወጣ ኮንትሮባንድ ስለመሆኑ የጠረጠረውን ዕቃ የጫነ መኪና ከመያዝ ባለፈ በቂና አሣማኝ ጥርጣሬ እስካለው ድረስ የኮንትሮባንድ ወንጀለ ተሣታፉ ነው የሚለውን መኪና ሁለ በመያዝ በቁጥጥር ሥር የማዋል ሥልጣን አለው። የሥር ፍርድ ቤት የኮንትሮባንድ እቃ ያልጫነ መኪናን አመልካች መያዙ ሕገወጥ ነው በማለት ሙለ በሙለ መደምደሙ ለአመልካች በሕግ ተለይቶ የተሰጠውን ስልጣንና ተግባር ከኮንትሮባንድ ወንጀል አፈፃፀምና የተሣትፍ ሁኔታ ጋር ያልተገናዘበ ሁኖ አግኝተናል።
ስለሆነም አመልካች መኪናውን መያዙ ሙለ በሙለ ሕገወጥ ተግባር ነው መባለ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ነው። ይሁን እንጂ የባለሥልጣኑ መሥሪያ ቤት በቂና አሣማኝ ጥርጣሬ ኑሮት እቃውን መያዝ ይችላል ማለት ተገቢና ምክንያታዊ ባልሆነ ጊዜ እቃውን ይዞ የመቆየት ስልጣን አለው ወደሚለው ድምዲሜ አያደርስም። በመሆኑም መሥሪያ ቤቱ ኃላፉነቱንና ተግባሩን ሲወጣ በጥርጣሬ የያዘውን እቃ ተገቢና ምክንያታዊ በሆነ የጊዜ ገደብ ውስጥ አጣርቶ ተገቢውን እርምጃ መውሰድ አለበት። በጥርጣሬ የያዘውን ንብረት ምክንያታዊ ለሆነ ጊዜ ከያዘና ስልጣን ያለው ፍርድ ቤትም ጉዲዩን አጣርቶ የተያዘው ንብረት እንዱለቀቅ ውሣኔ ከሰጠ በሁዋላ ባለሥልጣኑ መሥሪያ ቤት ወዱያውኑ ከለቀቀ ተገቢና ምክንያታዊ በሆነ ጊዜ ውስጥ ንብረቱ በመቆሙ የታጣውን ገቢ እንዱከፍል የሚገደድበት የሕግ አግባብ የለም። የጊዜው ተገቢነትና ምክንያታዊነትም እንደ ጉዲዩ ባህርይና ከባቢያዊ ሁኔታዎች እየታየ ግንዛቤ ሉወሰድበት የሚገባው ነው። በጥርጣሬ የተያዘው እቃ ከምክንያታዊ ጊዜ በላይ መያዙ ከተረጋገጠ ግን አመልካች በሕግ አግባብ ኃላፉ የማይሆንበት ምክንያት የለም።
እጃችን ወዲለው ጉዲይ ስንመለስ በአመልካች የተጠሪ መኪና የተያዘው የኮንትሮባንድ እቃ ጭኗል በሚል ጥርጣሬ ሣይሆን የኮንትሮባንድ እቃ የጫነ መኪናን አጅቦ ሲሄድ ነበር ሲሆን ጉዲዩ ሲጣራ ቆይቶ መኪናው እንዱለቀቅ በፍርድ ቤት ትእዛዝ የተሰጠ ሲሆን ፍርድ ቤቱ ትእዛዝ ከሰጠ በሁዋላ መኪናው ወዱያውኑ ተለቋል፤ እንዱሁም ጉዲዩ እስከሚጣራና በፍርድ ቤት ውሣኔ ጉዲዩ እስከሚያልቅ ድረስ መኪናው በአመልካች ተይዞ የቆየው ለአምስት ወራት መሆኑ ተረጋግጧል።
ይሁን እንጂ አመልካች የተጠሪን መኪና የያዘው የኮንትሮባንድ እቃ የጫነ መኪና አጅቦ ሲሄድ ነው በሚል ምክንያት ሲሆን ይህንኑ ምክንያት በማጣራት ተገቢውን እርምጃ ያልወሰደበትን ምክንያት በስር ፍርድ ቤት አላስረዲም። መኪናው ከተያዘበት ምክንያትና ከባቢያዊ ሁኔታዎች ስንነሣም ጉዲዩን አጣርቶ ተገቢውን እርምጃ ለመውሰድ ከሦስት ወራት ጊዜ በላይ ሉወሰድ ይችላል ብል ለመደምደም የሚያስችል ምክንያት የላለ መሆኑን ተገንዝበናል። በመሆኑም አመልካች የተጠሪን መኪና ከሶስት ወር ጊዜያት በላይ ያለበቂ ምክንያት ይዞ ለቆየባቸው ጊዜያት / ለሁለት ወር ጊዜያት/ ተግባሩ ሕገ ወጥ በመሆኑ ኃላፉ የማይሆንበት ሕጋዊ ምክንያት የለም።
አመልካች የተጠሪን መኪና ለሁለት ወራት ይዞ መቆየቱ ሕገወጥ ነው ከተባለ ቀጥል እልባት ማግኘት ያለበት ጉዲይ የካሣ መጠን ነው። ተጠሪ መኪናውን የቤት መኪና መሆኑን ጠቅሰው በኪራይ ብር 7ዐዐ.ዐዐ /ሰባት መቶ ብር/ በቀን ያገኙ እንደነበር ገልፀው የአምስት ወራት ገቢ እንዱከፈላቸው ይወሰን ዘንድ ዲኝነት ጠይቀዋል፣ አመልካች ደግሞ ገቢው ሕጋዊ መሆኑ አልተረጋገጠም በማለት ተከራክሯል። የስር ፍርድ ቤትም የተጠሪን ክርክር ሙለ በሙለ ተቀብሎል። ይሁን እንጂ የቤት መኪና በኪራይ ገቢ ሉያስገኝ እንደሚችል የሚታመን ቢሆንም የኪራይ ገቢ ግን ሕጋዊነቱ መረጋገጥ አለበት። ሕጋዊነቱ የሚረጋገጠው ደግሞ ከሚመለከተው አካል ተቀባይነት ያለው ማስረጃ፤ የንግድ ስራ ፈቃድ ሲቀርብ ወይም በዚህ ረገድ ተገቢ ማስረጃ ቀርቦ ሕጋዊነቱ ሲረጋገጥ ነው። በዚህ ጉዲይ የተጠሪ የኪራይ ገቢ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድን መሰረት አድርጎ የተገኘ ስለመሆኑ ሕጋዊ ማስረጃ አልቀረበበትም። የስር ፍርድ ቤት ይህንኑ ሣያረጋግጥ የተጠሪ መኪና በኪራይ መንገድ ገቢ ታስገኝ ነበር በማለት መደምደሙ ገቢ ተቋርጦብኛል የሚል ወገን በተገቢው መንገድ የማስረዲት ግዳታ አለበት በሚል በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2141 የተቀመጠውን የሕግ መንፈስ ያላገናዘበ ነው። በመሆኑም ተጠሪ መኪናቸውን በቀን በብር 7ዐዐ.ዐዐ /ሰባት መቶ ብር/ አከራይተው ገቢ ያስገኙ ነበር የሚለው የስር ፍርድ ቤት ድምዲሜ ሙለ በሙለ ተቀባይነት የሚያገኝበት የሕግ ምክንያት የለም። በልላ በኩል አመልካች የተጠሪ መኪና በሕጋዊ ንግድ በመሰማራት ተገቢውን ግብር ተጠሪ የከፈለባት ስለመሆኑ ስላልተረጋገጠ ገቢ ተቋርጧል ለማለት አይቻልም በማለት ያቀረበው ክርክርም ተቀባይነት የላለው ነው። ምክንያቱም የተጠሪ መኪና የቤት መኪና መሆኗ እና በአመልካች ደግሞ ለሁለት ወራት ያህል ያለ በቂ ምክንያት በቁጥጥር ስር መዋሎ እስከተረጋገጠ ድረስ ተጠሪ ላይ ሙለ በሙለ የጥቅም ማጣት አልደረሰባቸውም ለማለት የሚያስችል ምክንያት የለምና። ተጠሪ ለራሣቸውም ሆነ ለቤተሰባቸው የትራንስፕርት አገልግልት መኪናውን እንደሚጠቀሙ የሚታመን ሲሆን መኪናው በአመልካች ቁጥጥር በመዋለ ምክንያት ደግሞ ለወጪ እንደሚዲረጉ እሙን ነው። በመሆኑም ተጠሪ ሙለ በሙለ ያጡት ጥቅም የለም ለማለት የሚያስችል ምክንያት የለም። ይሁን እንጂ መኪናውን ባለመገልገላቸው የደረሰባቸው እርግጠኛ ወጪ ይህ ነው ብል ለመደምደም መነሻ የሚሆን ማስረጃ አልቀረበም። ሆኖም ስለ ጉዲቱ ምን ያህል ኪሣራ እንደሚከፍል በትክክል ለመወሰን ያልተቻለ እንደሆነ ዲኞቹ የነገሮቹን ተራ ሁኔታዎችንና ተጎጂውም ያደረገውን ጥንቃቄ አመዛዝነው በመገመት የኪሣራውን ልክ በርትዕ ሉወስኑ እንደሚችለ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 21ዐ2 ስር በግልጽ ተመልክቷል። በመሆኑም ተጠሪ ያጡት ጥቅም በርትዕ ሉወሰን የሚገባው ሁኖ በመገኘቱ ይህ ችልት ተጠሪ ለሁለት ወራት ያህል ያጡት ጥቅም ለእያንዲንደ ወር ከብር 2ዐዐ.ዐዐ /ሁለት መቶ ብር/ በላይ ላሆን እንደማይችል ገምቷል። በአጠቃላይ የበታች ፍርድ ቤቶች ኃላፉነትን በተመለከተ የሰጡት ውሣኔ አመልካች በአዋጅ ቁጥር 6ዐ/1989 መሰረት የተሰጠውን ስልጣን ከውል ውጪ ኃላፉነትን በተመለከተ ከተቀመጡት ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ ያላገናዘበ ሲሆን የካሣ መጠኑም በክርክሩ ሂደት የተረጋገጡትን ሁኔታዎችና ስለካሣ መጠን አወሳሰን የተመለከቱትን የፍትሐብሕር ድንጋጌዎችን መሰረት ያላደረገ እንዱሁም ይህ ሰበር ሰሚ ችልት በተመሣሣይ ጉዲዮች ከሰጠው አስገዲጅ የሕግ ትርጉም ጋር የማይጣጣም ሁኖ ስለአገኘነው ውሣኔው መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ሁኖ አግኝተናል። በዚህም መሰረት የሚከተለው ተወስኗል።
ው ሣ ኔ
348/1/ መሰረት ተሻሽሎል።
አመልካች የተጠሪን መኪናን የያዘው በሕጉ የተሰጠውን ስልጣን ሲያከናውን ቢሆንም መኪናውን ይዞ የቆየው ተገቢና ምክንያታዊ ነው ልባል ከሚቻለው ጊዜ በላይ በመሆኑ ከሶስት ወራት ጊዜያት በላይ መኪናውን ይዞ ለቆየባቸው ለሁለት ወራት የተቋረጠ ገቢ የማይከፈልበት የሕግ አግባብ የለም ብለናል።
አመልካች ለተጠሪ ሉከፍል የሚገባው የሁለት ወር የቀን ገቢ በብር 2ዐዐ /ሁለት መቶ ብር/ ሲታሰብ የሚመጣው ብር 12,ዐዐዐ.ዐዐ /አስራ ሁለት ሺህ ብር/ ነው ብለናል።
መዝገቡ ያለቀለት ስለሆነ ወደ መ/ቤት ይመለስ።
No topics extracted.