No summary available.
የሰ/መ/ቁ. 5ዐ375 ህዲር 13 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሐጏስ ወልደ ተሻገር ገ/ስላሴ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን፡- ሙለእመቤት ውባየሁ ቀረበች ተጠሪዎች፡-
ጉዲዩ በቀሪ ይፈለጋል የተባለውን ቀረጥና ታክስ ለማስከፈል የቀረበውን ክስ መነሻ በማድረግ የተካሄደውን ክርክር የሚመለከት ነው። ክርክሩ ሲጀመር ከሣሽ የነበረው አመልካች 1ኛ ተጠሪ ከውጪ ሃገር ላስመጣቻቸው የአገለገለ የፉያት መኪና ኢንጅኖች መክፈል የነበረባት ቀረጥና ታክስ ብር 526,654.25 ሆኖ ሳለ ብር 28,218.18 ብቻ ስለከፈለች ቀሪውን ትከፍል ዘንድ ይወሰንልኝ። 2ኛ ተጠሪም ወኪል በመሆኑ የጋራ ሃላፉነት አለበት ይባልልኝ በማለት ክሱን አቅርቦአል። ክሱ የቀረበለት የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ተጠሪዎችን አስቀርቦ ክርክሩን ካሰማ በኋላ፣ 1ኛ ተጠሪ ላስመጣቻቸው ኢንጅኖች ልትከፍል የሚገባት ቀረጥና ታክስ ብር 28,218.18 ነው በማለት የአመልካች ክስ ውድቅ አድርጓል። ጉዲዩ በይግባኝ የቀረበለት የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤትም ይግባኝ የተባለበትን ውሳኔ አፅንቶአል። የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚህ ላይ ነው።
እኛም አመልካች ህዲር 4 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም. በጻፈው ማመልከቻ ያቀረበውን አቤቱታ መሰረት በማድረግ ተጠሪዎችን አስቀርበን ክርክሩን ሰምተናል። ክርክሩ የተሰማው ስለቀረጡ እና ታክሱ አከፊፈል በተመለከተ የሥር ፍ/ቤቶች የሰጡት ውሳኔ ሕጉን መሰረት ያደረገ ነው ወይስ አይደለም? በሚለው ጭብጥ ላይ ነው። በዚህ መሰረትም በግራቀኙ ወገኖች በዚህ ረገድ ያሰሙትን ክርክር አቤቱታ ከቀረበበት ውሳኔ እና ከሕጉ ጋር አገናዝበን መርምረናል።
በአመልካች ክስ እንደተገለጸው 1ኛ ተጠሪ የከፈለችው ብር 28,218.18 ብቻ ሲሆን፣ መክፈል የነበረባት ግን ከዚህ እጅግ ከፍያለ እንደሆነ በኋላ በተደረገው የኦዱተሮች ምርመራ እንደተረጋገጠ በክርክሩ ተመልክቶአል። 1ኛ ተጠሪ ደግሞ ቀረጥና ታክሱ ኢንጅኖቹን ስትረከብ የከፈለችው ብቻ እንደሆነ እና ይህም በሕጉ የተመለከተ መሆኑን በመግለጽ ተከራክራለች። 2ኛ ተጠሪም ቀረጥና ታክስ ሉጠየቅ የሚገባው የዕቃው ባለቤት እንጂ ወኪል አይደለም የሚል የመከራከሪያ ነጥብ አንስቶአል።
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤትም የ1ኛ ተጠሪን ክርክር እንዲለ የተቀበለ ሲሆን፣ የሰጠው ምክንያትም አመልካች ለቀረጥና ታክሱ አተማመን መሰረት ያደረገው ሕግ ያገለገለ የመኪና ሞተሮችን/ኢንጅኖችን/ አያጠቃልልም የሚል እንደሆነ ከውሳኔው ለመገንዘብ ችለናል።
ከሥር ጀምሮ ከተደረገው ክርክር መገንዘብ እንደቻልነው ለጉዲዩ አወሳሰን ተገቢነት ያለው ሕግ የቅድመ ጭነት ምርመራ ሥርዓት ማቋቋሚያ አዋጅ ቁ.173/91 በአንቀድ 6(1) የተመለከተው ድንጋጌ ነው። የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የአመልካችን ጥያቄ/ክስ/ ውድቅ ያደረገው ለድንጋጌው ትርጉም በመስጠት እና ለክርክሩ መነሻ የሆኑ ያገለገለ ኢንጅኖች በድንጋጌው አይሸፈኑም በማለት ነው። ፍ/ቤቱ ድንጋጌውን ወደ መተርጎም የገባው ኢንጅኖቹ በኤስ ጂ ኤስ ኩባንያ የቅድመ ጭነት ምርመራ ተደርጎላቸው ዋጋም ወጥቶላቸው የገቡ በመሆኑ መቀረጥ ያለባቸው ኩባንያው በሰጠው ዋጋ መሰረት ነው በማለት ተከሣሽ በመከራከርዋ እና አመልካች /የሥር ከሣሽ/ ደግሞ ኢንጅኖቹ አሮጌ /ያገለገለ/ በመሆናቸው የቅድመ ጭነት ምርመራ እንዲይደረግባቸው ሕጉ ይከለክላል የሚል መከራከሪያ በማቅረቡ ነው። በእርግጥም አከራካሪው ነጥብ የሕግ ጭብጥ በመሆኑ በዚህ ረገድ አግባብነት ያለውን ድንጋጌ መሰረት በማድረግ የሚፈታ ነው የሚሆነው።
ማንኛውም ወደ ኢትዮጵያ የሚላክ ዕቃ በማጓጓዣ ላይ ከመጫኑ በፉት የቅድመ ጭነት ምርመራ እንደሚደረግበት ከላይ በተጠቀሰው አዋጅ በአንቀጽ 4(1) ተደንግጎአል። የቅድመ ጭነት ምርመራ ሽፊን የእቃውን ዋጋ እና የምንዛሬውን ተመን ትክክለኛነት፣ ጥራት፣ ብዛት፣ የአስተሻሸግ ሁኔታ እና የታሪፍ ምደባ የሚመለከት እንደሚሆንም በአንቀጽ 5 ተመልክቶአል። በልላ በኩል ደግሞ በአንቀጽ 4 መሰረት የሚደረገው የቅድመ ጭነት ምርመራ ተፈጻሚ የማይሆንባቸው ዕቃዎች እንዲለ ‹‹ልዩ ሁኔታዎች›› በሚል በተደነገገው በአንቀጽ 6 ተመልክተዋል። የቅድመ ጭነት ምርመራ አይደረግባቸውም የተባለት ዕቃዎች በአንቀጽ 6(1) በዝርዝር የተመለከቱ ሲሆኑ፣ ያገለገለ ተሽከርካሪንም አጠቃለው የያዙ ናቸው። እንግዱህ በዚህ ድንጋጌ መሰረት ወይም አነጋገር ከውጪ ሃገር ወደ ኢትዮጵያ የሚላከው የአገለገለ ተሽከርካሪ ወይም መኪና በአንቀጽ 4 እንደተደነገገው አይነት የቅድመ ጭነት ምርመራ አይደረግበትም ማለት ነው። ተሽከርካሪው ወይም መኪና ሉሽከረከር ወይም አገልግልት ላሰጥ የሚችለው ሞተር ወይም ኢንጅን ሲኖረው እንደሆነም የሚዘነጋ አይደለም። 1ኛ ተጠሪ ከውጪ ሃገር ያስገባቻቸው ኢንጂኖች የፉያት መኪና ኢንጅኖች እንደሆኑ በክርክሩ ተመልክቶአል። ይህ ማለት ደግሞ በፉያት መኪኖች ተገጥመው ሥራ ላይ የሚውለ ናቸው ማለት ነው። እውነታው ይህ ከሆነም ሕግ አውጪው በአሮጌ ወይም ያገለገለ ተሽከርካሪዎች (ፉያት መኪኖችን ጨምሮ) ላይ የቅድመ ጭነት ምርመራ አይደረግም እያለ ባገለገለ ሞተሮቻቸው/ኢንጅኖች/ ላይ ግን የቅድመ ጭነት ምርመራ ይደረግባቸዋል የሚል ተቃራኒ ሃሳብ ይዞ ሕጉን ያወጣል ብል ማሰብ ምክንያታዊ አይሆንም።
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ኢንጅኖቹ በአዋጁ አንቀጽ 6(1) አይሸፈኑም ለማለት የበቃው በዝርዝሩ ውስጥ ያገለገለ የመኪና ሞተሮች በሚል አልተመለከተም በማለት ነው።
በመሰረቱ ሕግ አውጪው ሕጉን በሚተገብረው/በሚተረጏመው/ አካል በትርጉም ሉደረስበት የሚችለውን ነጥብ በሙለ እየዘረዘረ ያወጣል ብል በጥቅለ ማሰብ ተገቢም፤ ምክንያታዊም አይሆንም። በያዝነው ጉዲይ እንደምናየው ያገለገለ ተሽከርካሪዎች ወይም መኪኖች በግልጽ እስከተመለከቱ ድረስ የመኪኖቹን/የተሽከርካሪዎቹን/ ዋነኛ አካል /አንቀሳቃሽ/ የሆነው ሞተር ተለይቶ ነው የሚታየው ወደሚለው መደምደሚያ መድረስ ትክክል አይሆንም። ሕጉም መተርጎም ያለበት ምክንያትን መሰረት በማድረግ እንደሆነ ልብ ልባል ይገባል። የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ለድንጋጌው የሰጠው ትርጉም ከዚህ አንፃር ሲታይ በምክንያት ላይ ወይም ምክንያታዊ በሆነ የሕግ አተረጓጎም ስልት ላይ በመመሥረት የተሰጠ ነው የሚባል አይደለም። በመሆኑም ውሳኔው መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው ለማለት ችለናል።
በመቀጠል የተመለከትነው አቤቱታ የቀረበበት ውሳኔ በሕጉ አተረጓጎም ረገድ መሰረታዊ ስህተት ያለበት ነው ከተባለ በምን አይነት አግባብ ሉታረም ይገባል የሚለው ነው። ከላይ በዝርዝር እንዲየነው የሥር ፍ/ቤቶች ክሱ ተቀባይነት የለውም እሚል ድምዲሜ ላይ በመድረሳቸው እና ለዚህ ድምዲሜአቸው መሰረት ያደረጉት ለሕጉ የሰጡት ትርጉም በመሆኑ ወደ ፍሬ ነገሩ ክርክር ገብተው ስለቀረጥና ታክሱ መጠን በተመለከተ ውሳኔ አልሰጡም። ከዚህ የተነሳም ፍሬ ነገሩን በሚመለከት ከመጀመሪያው ክርክር ማድረጉ አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል። በዚህ መሰረትም ተከታዩን ወስነናል።
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ. ታህሣስ 8 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም. የሰጠው ውሳኔ እና የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ. ጥቅምት 19 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም. የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ.348(1) መሰረት ተሽረዋል።
ለክርክሩ መነሻ የሆኑት ኢንጅኖች በአዋጁ አንቀጽ 6(1) የሚሸፈኑ በመሆናቸው የቅድመ ጭነት ምርመራ አይደረግባቸውም ብለናል።
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ክርክሩን በተከፈተው መዝገብ እንዱቀጥል በማድረግ ሉከፈል በሚገባው ታክስ እና ቀረጥ መጠን ከግራ ቀኝ ወገኖች የሚቀርብለትን ክርክር ከሰማ በኋላ ተገቢውን ይወስን ዘንድ ጉዲዩ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ.343(1) መሰረት ይመለስለት ብለናል።
ግራ ቀኝ ወገኖች ወጪና ኪሣራ ይቻቻለ።
No topics extracted.