No summary available.
የሰ/መ/ቁ. 542ዐ3 ኀዲር 27 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ ተሻገር ገ/ሥላሴ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- የኢት/ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን - የቀረበ የለም።
ተጠሪ፡- ወ/ሮ ሙለእመቤት ኃ/ሚካኤል - የቀረበ የለም።
**
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ይህ የሰበር አቤቱታ ላቀርብ የቻለው አመልካች የተጠሪን መኪና ያለአግባብ ይዟል ተብል መኪናውን እንዱመልስና የተቋረጠ ገቢ ብር 9944.44 እንዱከፍል የተሰጠው ውሣኔ እንዱታረም አመልካች ስላመለከተ ነው።
የጉዲዩ አጀማመር ባጭሩ ሲታይ ንብረትነቱ የተጠሪ የሆነ የሰላዲ ቁጥር 3-01ዐ17 አ.አ የሆነ መኪና አመልካች ያለአግባብ ይዞ በቁጥጥር ሥር አቆይቷል። መኪናውን እንዱለቅ እና መኪናው በመቆሙ የተቋረጠ ገቢ ብር 5ዐ,ዐዐዐ /ሃምሣ ሺህ/ እንዱከፍል ይወሰንልኝ ሲለ ተጠሪ ያቀረቡትን ክስ የሥር ፍ/ቤት ተቀብል መኪናው እንዱመለስ እና የተቋረጠ ገቢ ከፍ ሲል የተጠቀሰውን መጠን አመልካች እንዱከፍል ወስኗል። አመልካች በውሣኔው ቅር ተሰኝቶ ለፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ ያቀረበ ቢሆንም ፍ/ቤቱ ይግባኙን ሰርዟል። ለዚህ ሰበር ችልት አቤቱታ የቀረበው በዚህ ላይ ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ አመልካች በሕግ የተሰጠውን ተግባር ሲያከናውን ይዞ ያቆየውን መኪና አስረክብ መባለ እና የተቋረጠ ገቢ እንዱከፍል መወሰኑ ከአዋጅ ቁጥር 6ዐ/89 እንደተሻሻለው አዋጅ ቁጥር 368/95 አንቀጽ 73 እና 78 አኳያ ሉመረመር የሚገባ ሆኖ በመገኘቱ ተጠሪ መልስ እንዱሰጡ ተደርጓል። የተጠሪ ጠበቃ ሰኔ 24 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም. በተፃፈ መልስ አቅርበዋል። በይዘቱም ተጠሪ በመንግሥት ፈቃድ ከውጪ ሀገር ያስገቡት መኪና ስለመሆኑ ገልጸው ይህ መኪና ለንግድ ሥራ እንዱውል የፋዳራል የመንገድና ትራንስፕርት ባለሥልጣን ፈቅድላቸው እየሰሩበት ስለመሆኑና ይህም በአመልካች አውቅናና ስምምነት ለመሆኑ ዘርዝረው በመግለጽ መኪናው መያዙ ሕገ ወጥ ተግባር ነው በማለት ተከራክረዋል።
አመልካች ክርክሩን አጠናክሮ የመልስ መልስ ሰጥቷል።
የጉዲዩ አመጣጥ እና የግራ ቀኙ ክርክር ከፍ ሲል በአጭሩ የተመለከተ ሲሆን እኛም በዚህ ሰበር ችልት እንዱመረመር ከተያዘው ጭብጥ አንፃር ከሕጉ ጋር አገናዝበን መርምረናል።
ከመዝገቡ መረዲት እንደተቻለው አመልካች በሥር ፍ/ቤት አጥብቆ የተከራከረው ተጠሪ ከቀረጥ ነፃ ለግል አገልግልት ከውጪ ሀገር ያስገቡትን መኪና ተገቢው ቀረጥ ሳይከፈልበት ለንግድ ሥራ አውለውት በመገኘታቸው ድርጊቱ በሕግ የተከለከለ በመሆኑ ይህንኑ ለማጣራት በሕግ በተሰጠው ሥልጣን መሰረት መኪናውን በቁጥጥር ሥር ያዋለ ስለመሆኑ እና ይህም በሕግ የተቀበለው ሃላፉነት በመሆኑ ክሱ ተቀባይነት ሉኖረው እንደማይገባ ነው።
የጉምሩክ ባለሥልጣን ማቋቋሚያና ሥልጣንና ኃላፉነትን የተመለከተው አዋጅ ቁጥር 6ዐ/89 በአዋጅ ቁጥር 368/95 እንደተሻሻለው አንቀጽ 73/1/ እንደሚያመለክተው ከቀረጥ ነፃ የገባ እቃ ለላላ አገልግልት ማዋል ሕገወጥ ተግባር አለመሆኑ ተደንግጓል። ይህንንም ተግባር እንዲይፈጸም ለመከላከል እንዱሁም ተፈጽሞ ሲገኝ መመርመር እና ሕጋዊ ውሣኔ የማሰጠት ኃላፉነት ለጉምሩክ ባለሥልጣን የተሰጠ ስለመሆኑ የጉምሩክ አዋጅ ይዘት ያመለክታል።
ከተያዘው ጭብጥ አንፃር በጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 368/95 /እንደተሻሻለው/ አንቀጽ 78 ላይ እንደተደነገገው የጉምሩክ ሕግን በመተላለፍ የተገኙ እቃዎችን እና ማጓጓዣዎችን አግባብ ያለው የመጨረሻ ውሣኔ አስኪሰጥባቸው ድረስ መያዝና በቁጥጥር ማዋል ይቻላል በማለት ተደንግጓል።
ወደተያዘው ጉዲይ ስንመለስ አመልካች ይህንኑ በሕግ የተሰጠውን ኃላፉነት ለመወጣት የተንቀሳቀሰ መሆኑን በመግለጽ ተከራክሯል። ተጠሪም መኪናውን ከቀረጥ ነፃ ለግል አገልግልት ከውጪ ሀገር ያስገቡ ስለመሆኑ አምነው ነገር ግን መኪናው ለንግድ ሥራ እንዱውል የተደረገው በፋዳራል የመንገድ ትራንስፕርት ባለሥልጣን ፈቃድ እና በአመልካች እውቅናና ስምምነት ነው በማለት ተከራክረዋል።
እንግዱህ ከዚህ የግራ ቀኙ ክርክር አንፃር መኪናው ለተጠሪ ሉመለስ ይገባል ወይንስ አይገባም? አመልካች መኪናውን በመያዙ የተቋረጠ ገቢ ለተጠሪ የመክፈል ኃላፉነት አለበት ወይንስ የለበትም የሚለት ጭብጦች ውሣኔ ከማግኘታቸው በፉት ተጠሪ መኪናውን በምን ሕጋዊ አግባብ ለንግድ ሥራ አገልግልት እንዱውል አደረጉት? ይኸው ከቀረጥ ነፃ የገባው መኪና ለንግድ ሥራ አገልግልት ሲንቀሳቀስ በመልካች መያዙ ሕጋዊ አካሄድ ነው? ወይስ አይደለም? የሚለው መሰረታዊ ጭብጥ ምላሽ የሚያሻው መሆኑን መረዲት ተችሎል።
የሥር ፍ/ቤት እነዚህን ጭብጦች ከግራ ቀኙ ክርክር እና ማስረጃ አንፃር ከሕጉ በማገናዘብ ሳይመረምር አመልካች የተጠሪን መኪና ያለፍርድ በቁጥጥር ሥር ማድረጉና መወረሱ ተገቢ አይደለም ከሚል የተሣሣተ ድምዲሜ ደርሷል። በመሰረቱ አመልካች የተጠሪ መኪና ተወርሷል የሚል ክርክርም አላቀረቡም።
ስለሆነም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ በተደነገገው አግባብ የግራ ቀኙን ክርክር መሰረት በማድረግ ተገቢውን ጭብጥ በመያዝ በአግባቡ በማጣራት ውሣኔ መሰጠት እየተገባው አመልካች መኪናውን እንዱመልስ እና የተቋረጠ ገቢ ለተጠሪ እንዱከፍል በሥር ፍ/ቤት የተሰጠው ውሣኔ እና በከፍተኛው ፍ/ቤትም ይኸው ውሣኔ መጽናቱ ተገቢውን የክርክር አመራር ሥርዓት ያልተከተለ እና ከሕጉ ጋር በአግባቡ ያልተገናዘበ ሆኖ ስላገኘው ሉታረም የሚገባው ነው ብለናል።
በመሆኑም በክርክር አመራር ረገድ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ ተከታዩን ውሣኔ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ
የሰጠው ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
አመልካች የተጠሪ መኪና ሉመለስ ይገባል? ወይንስ አይገባም? የተቋረጠ ገቢ የመክፈል ኃላፉነት አለበት ወይንስ የለበትም? የሚለውን ጭብጥ ከመወሰኑ በፉት ተጠሪ ከቀረጥ ነፃ ያስገቡትን መኪና ለንግድ ሥራ አገልግልት ያዋለት በሕግ አግባብ ነው ወይንስ አይደለም? አመልካች የተጠሪን ድርጊት ለመመርመር ሲል መኪናውን መያዙ ተገቢ ነው ወይንስ አይደለም? የሚለትን ጭብጦች ከግራ ቀኙ ክርክር እና ማስረጃ አንፃር መርምሮ ተገቢውን ውሣኔ እንዱሰጥበት ብለን መዝገቡን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 343/1/ መሰረት ለፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት መልሰናል፤ ይፃፍ።
መዝገቡ ተዘግቷል ይመለስ።
No topics extracted.