No summary available.
ጥቅምት 18 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሐጎስ ወልደ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- የአዱስ አበባ ላጋር ጉምሩክ - ነ/ፈጅ እመቤት ባዩ - ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ አደኛ አበለ - የቀረበ የለም **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ ያላግባብ የተከፈለ ቀረጥ ይመለስልኝ ጥያቄን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ ተጠሪ በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ባሁኑ አመልካች ላይ ሐምል 04 ቀን 1998 ዓ.ም በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው። የክሱ ይዘትም ተጠሪ ከቱርክ አገር ሶስት ማሸነሪዎችን ሰኔ 09 ቀን 1995 ዓ.ም በህጋዊ መንገድ ወደ አገር ማስገባታቸውን ለማሽነሪዎች የተሳሳተ 00 የሆነ የታሪፍ ኮድ እንዱሰጣቸው ተደርጎ የዋጋቸውን 40% ብር 40,514.02 እንዱከፍለ መደረጉን ይህንኑ ገንዘብ እቃውን ለመረከብ ሲለም መክፈላቸውንና እቃዎቹ በትክክለኛ የታሪፍ መጠን ተቀርጠው በአብላጫ የከፈለት እንዱመለስላቸው አመልክተው የኢትዮጵያ ጉምሩክ ባለስልጣን መስከረም 04 ቀን 1996 ዓ.ም ለአዱስ አበባ ላጋር ጉምሩክ በጻፈው ደብዲቤ በትክክለኛ የታሪፍ መደብ እንዱስተናገደ በሚል ማሳወቁን በትክክለኛው ኮድ ሉከፍለ ይችለ የነበሩት የገንዘብ መጠንም የዋጋውን 5% ብር 12,510.42 መሆኑን ዘርዝረው በአብላጫ የተከፈለው ብር 28,003.06(ሃያ ስምንት ሺህ ሶስት ብር ከዜሮ ስድስት ሳንቲም) ከወለድ እንዱሁም ከወጪና ኪሳራ ጋር እንዱከፈላቸው ይወሰን ዘንድ ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው።
የአሁኑ አመልካችም በአዋጅ ቁጥር 60/1989 አንቀጽ 55 መሰረት በአብላጫ የተከፈለ ቀረጥና ታክስን መመለስ የሚቻለው እቃው ወደ አገር ውስጥ ከገባበት በስድስት ወር ውስጥ የታወቀ የሆነ እንደሆነ እንጂ እንደተጠሪ እቃው መስከረም 27 ቀን 1995 ዓ.ም አስገብቶ እቃውንም ህዲር 13 ቀን 1996 ዓ.ም አውጥቶ ከወሰደ በኋላ አይደለም ጥያቄው በይርጋ ቀሪ ነው በማለት ዘርዝሮ ክሱ ውድቅ ላሆን ይገባል ሲል ተከራክሯል። ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር እና ማስረጃዎችን በመመርመር ተጠሪ በአብላጫ የተከፈለ ቀረጥ ይመለስልኝ ጥያቄ ያቀረቡት በአዋጅ ቁጥር 60/89 አንቀጽ 55 ስር በተመለከተው የስድስት ወር የጊዜ ገደብ ውስጥ አይደለም በማለት ክሱን በይርጋ ውድቅ አድርጎ ወስኗል። ከዚህ በኋላ ተጠሪ ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ የስር ፍርድ ቤት የጠቀሰው ድንጋጌ ክፍያ ላይ ስህተት ሲፈጠር የሚፈፀም እንጂ ያላግባብ ለተከፈለ ክፍያ የሚሆን አይደለም በሚል ምክንያት የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ በመሻር አመልካችን ለክሱ ኃላፉ በማድረግ ለክሱ መሰረት የሆነውን የገንዘብ መጠን ክሱ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ ተከፍል እስከሚያልቅ ድረስ ከሚታሰብ ሕጋዊ ወለድ (9%) ዘጠኝ በመቶ ጋር ለተጠሪ እንዱከፍል ሲል ወስኗል። ከዚህም በኋላ አመልካች ይግባኙን ለፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቅርቦ ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሳኔ ሙለ በሙለ ፀንቷል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ ለማስቀየር ነው።
የአመልካች ነገረ ፈጅ መጋቢት 06 ቀን 2002 ዓ.ም በፃፈት ሁለት ገፅ የሰበር አቤቱታ በይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈፅሟል የሚለበትን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም ባጭሩ ይርጋውን በተመለከተ አመልካች ያቀረበው ክርክር የታለፈው ከአዋጅ ቁጥር 60/89 እንደተሻሻለ አንቀጽ 55፣ 53 ድንጋጌዎች ውጪ ስለሆነ ሉታረም የሚገባው ነው በማለት መከራከራቸውን የሚያሳይ ነው። አቤቱታው ተመርምሮም ለጉዲዩ አግባብነት ያለው ድንጋጌ የትኛው ነው የሚለውን ነጥብ ለመለየት ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ችልቱ እንዱቀርብ ተደርጎአል።
ተጠሪም በጠበቃቸው ሰኔ 28 ቀን 2002 ዓ.ም በተጻፈ አንድ ገፅ መልሳቸውን ሰጥተዋል።
በመልሳቸውም ለጉዲዩ አግባብነት ያለው ይርጋ መደበኛው ነው በማለት ተከራክረዋል። የአመልካች ነገረ ፈጅም ሐምል 12 ቀን 2002 ዓ.ም በጻፈት ማመልከቻ የመልስ መልሳቸውን ሰጥተዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመረውም የዚህን ችልት ምላሽ የሚያስፈልገው አብይ ነጥብ አመልካች አዋጅ ቁጥር 60/89 እንደተሻሻለው አንቀጽ 53 እና 55 መሰረት አድርጎ ያቀረበው የይርጋ ክርክር የመታለፈ አግባብነት ነው።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው ተጠሪ ክሱን ሉመሰርቱ የቻለት ያላግባብ የከፈልኩት የቀረጥ ገንዘብ ሉመለስልኝ ይገባል በሚል ሲሆን አመልካች በበኩለ ጥያቄው በስድስት ወር የጊዜ ገደብ ውስጥ ያልቀረበና በሕጉ አግባብ የተፈፀመ መሆኑን ገልጾ ክሱ ውድቅ ላሆን ይገባል በማለት ተከራክሯል።
የዋጋ ኢንቮይስ ውድቅ የሆነበት ቀረጥ ከፊይ ቅሬታ ካለው በአዋጅ ቁጥር 60/1989 አንቀጽ 53 መሰረት ለተጠሪ መስሪያ ቤት የበላይ ኃላፉ አቅርቦ ተገቢው ውሳኔ እንዱሰጥበት ማድረግ የሚችል ሲሆን በዚሁ የበላይ ኃላፉ ውሳኔ ቅሬታ ካለው ብቻ ወደሚመለከተው ፍርድ ቤት መሄድ የሚችል መሆኑን ተመልክቷል። በዚህ ድንጋጌ መሰረት አከራካሪ ስለሆኑ ጉዲዮች በሚለው በእቃዎች ዋጋ አተማመን፣ በታሪፍ አሰያየምና አመዲደብ እንዱሁም በታሪፍ ልክ ላይ ተቃውሞ የቀረበ እንደሆነ የተቃውሞ ነጥብ ከተመዘገበ በኋላ የጉምሩክ ሹም በሚወስነው መሰረት ቀረጡ እንደሚከፈል በተቃውሞ የተከፈለው ቀረጥ ጉዲዩ በሶስት ወር ጊዜ ውስጥ በባለስልጣኑ የበላይ ኃላፉ ውሳኔ እንደሚሰጥበት ባለጉዲዩ በውሳኔው ካልተስማማ በውሳኔው አለመስማማቱን ገልፆ በሰላሳ ቀናት ውስጥ በፍርድ ቤት ክስ ማቅረብ ያለበት መሆኑን አስገዲጅነት ባለው መልኩ አስቀምጧል። ይህ ስርዓት ሳይፈፀም በቀጥታ በፍ/ቤት ክስ የሚመሰረትበት አግባብ የላለ መሆኑን ከተጠቀሰው ድንጋጌ መንፈስ እና ይዘት መገንዘብ የምንችለው ጉዲይ ነው። ይህ በሕጉ ላይ የተመለከተው የስነ ስርዓት ጥያቄ ነው። ይኸው የስነ ስርዓት ጉዲይም በሕጉ በተዘረጋው ሥርዓት መሰረት ባግባቡ መፈፀም አለበት። ይህ ለአስተዲደራዊ ውሳኔም የራሱ የሆነ ጠቀሜታ ይኖረዋል ተብልም ይታሰባል።
በብልጫ የተከፈለ የቀረጥ ገንዘብ ለከፊዩ ሉመለስ እንደሚገባ አዋጁ በአንቀፅ 55 ስር በግልፅ ደንግጓል። ይህንኑ ያሻሻለው አዋጅ ቁጥር 368/95 አንቀጽ 15 ድንጋጌ ደግሞ ቀረጡ ተመላሽ የሚደረገው ስህተቱ መኖሩን ባለሥልጣኑ እንዲወቀ ወይም ባለቤቱ ጥያቄ እንዲቀረበ ይሆናል በሚል ካስቀመጠ በኋላ ቀረጡ ተመላሽ የሚደረገው ዕቃው የጉምሩክ ሥነ ሥርዓት አጠናቆ ወደ አገር ከገባበት ወይም ወደ ውጪ ሀገር ከተላከበት ቀን ጀምሮ ስድስት ወራት ውስጥ ስህተቱ የታወቀና ጥያቄ የቀረበ እንደሆነ ነው በማለት ፍጹም የሆነ የይርጋ ጊዜ ደንግጓል። ወደ ተያዘው ጉዲይ ስንመለስም ተጠሪ ቀሪ የቀረጥ ክፍያ መኖሩን አረጋግጠው ክፍያው እንዱፈፀምላቸው የጠየቁት እቃው ወደ አገር ከገባ ከአንድ አመት አስራ አንድ ወራት በኋላ መሆኑ ተረጋግጧል። ተጠሪ ለአመልካች መስሪያ ቤት ሹም በብልጫ የተከፈለ ቀረጥ እንዱመለስላቸው በአዋጅ ቁጥር 60/89 አንቀጽ 53 መሰረት ጥያቄ አቅርበው ተገቢ ውሳኔ ተሰጥቶ ክሱን ፍርድ ቤት የመሰረቱ ሳይሆን ቀረጡ በስህተት መከፈለን ተገንዝበው ስህተቱ ተስተካክል በብልጫ የተከፈለ ገንዘብ እንዱመለስላቸው አቤቱታ አቅርበው ተገቢው እንዱፈፀም እናት መስሪያ ቤት ለቅርንጫፍ መስሪያ ቤት የፃፈውን ደብዲቤ መሰረት አድርገው መፍትሓ ሳያገኙ ሲቀሩ በፍርድ ቤት ክስ መስርተዋል።
ይሁን እንጂ ጥያቄያቸውን በአዋጁ መሰረት እቃውን ከውጪ ከአስገቡ በኋላ በስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ አላቀረቡም። ይህም የሚያሳየው የአመልካች ጥያቄ በሕጉ የተገደበ መሆኑን ሲሆን አመልካች በአዋጁ አንቀጽ 55 መሰረት ያነሱት እና የተጠቀሙበት ተቃውሞ አለመኖሩን ነው። በመሆኑም አመልካች ክስ የመሰረቱበትን የቀሪ ቀረጥ ክፍያ ጥያቄ በተጠሪዎች በኩል በአዋጁ አንቀጽ 53(1) መሰረት ተቃውሞ ቀርቦ ተገቢው ለውጥ ባልተደረገበት ሁኔታ እንዱሁም በአዋጁ አንቀጽ 55 መሰረት በስድስት ወር ጊዜ ያልቀረበ የቀረጥ ይመለስልኝ ጥያቄ ተቀባይነት የሚያገኝበት አግባብ ባለመኖሩ በፍርድ ቤት ክስ መመስረታቸው በይርጋ ቀሪ ነው በማለት የፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ በበላይ ፍርድ ቤቶች መሻሩ ለጉዲዩ አግባብነት ያለውን የአዋጁን ቁጥር 55 ባላገናዘበ መልኩ በመሆኑ ውሳኔው መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ሁኖ አግኝተናል።
በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ መጋቢት 17 ቀን 2001 ተሰጥቶ በፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/ ታህሳስ 27 ቀን 2002 ዓ.ም የፀናው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ተሽሯል።
በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት መ/ ሐምል 25 ቀን 1999 ዓ.ም የተሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ጸንቷል።
የተጠሪ የቀረጥ ይመለስልኝ ጥያቄ በስድስት ወር ይርጋ የታገደ ነው ብለናል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.