No summary available.
ጥር 25 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ዲኜ መላኩ ተሻገር ገ/ሥላሴ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- የልደታ ክፍለ ከተማ ቀበላ 12 አስተዲደር ፅ/ቤት - ምርመራና ክስ ኤክስፏርት አቶ ሰይፈ ይፍሩ ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ተስፊዬ አሰፊ - ጠበቃ አዜብ ገ/ወልድ ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የሁከት ይወገድልኝ ጥያቄ ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ ተጠሪ ባሁኑ አመልካች ላይ በአዱስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው። የክሱ ይዘትም ባጭሩ በልደታ ክፍለ ከተማ ቀበላ 12 ክልል ውስጥ ቁጥሩ 406 በሆነው ቤት ውስጥ ከወላጅ እናታቸው ወ/ሮ አበበች ፍሰሃ ጋር ሲኖሩ እናታቸው በ28/05/1997 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት በመለየታቸው ከላልች ተወላጆች ጋር ወራሽነታቸውን አረጋግጠው የቤቱን ኪራይ በራሳቸው ስም እንዱዞር በማድረግ በቤቱ በመገልገል ላይ እያለ አመልካች ያላግባብ ከቤቱ እንዱወጡ ማስጠንቀቂያ የሰጣቸውና ይህም ተግባር ሁከት መሆኑን ገልፀው ሁከቱ እንዱወገድ ይወሰንላቸው ዘንድ ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። የአሁኑ አመልካች ለክሱ በሰጠው መከላከያ መልስም ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ለተጠሪ ሳይሆን ለወ/ሮ ቀለሟ ታየ በመሆኑ ተጠሪ ክስ ለመመስረት የሚያስችላቸው መብትና ጥቅም የላላቸው መሆኑን በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት በአማራጭ ደግሞ በልደታ ክፍለ ከተማ ቀበላ 12 ክልል ውስጥ ቁጥሩ 406 የሆነውን ቤት ለቀው እንዱያስረክቡ ማስጠንቀቂያ የተሰጠው የሟች አበበች ፍሰሀ ልጅ ለሆኑት እና በልደታ ክፍለ ከተማ ቀበላ 16/17 ክልል ውስጥ የቤት ቁጥር 967 የሆነ የቀበላ ቤት በስማቸው ላለው ለወ/ሮ ቀለሟ ታዬ ሲሆን አንድ ግለሰብ ሁለት የመንግስት ቤት ሉይዝ ስለማይችል ማስጠንቀቂያ መስጠታቸውን ተገቢ ነው፣ ተጠሪ ወራሽነት ያገኙትም ያላግባብ ነው፣ ተጠሪ የሟች ወ/ሮ አበበች ፍሰሀ ልጅ ሳይሆኑ የሟች እህት ልጅ ሁነው የሚኖሩትም በልደታ ክፍለ ከተማ ቀበላ 12 የቤት ቁጥር 779 በሆነው ቤት ውስጥ ከእናታቸው ከወ/ሮ ይመኙሻል ፍሰሀ እና ከአባታቸው ከአቶ አሰፊ አባተ ጋር ነው በማለት ክሱ የማይገባ ጥቅም ለማግኘት የቀረበ በመሆኑ ውድቅ ላሆን ይገባል ሲል ተከራክሯል። ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር መርምሮ በአመልካች በኩል የቀረቡትን የክርክር ነጥቦች ውድቅ አድርጎ በአመልካች የተሰጠው ማስጠንቀቂያ ይዘቱ ተጠሪ በቤቱ ላይ እንዲይኖሩ የሚያደርግ በመሆኑ ተግባሩ ሁከት ነው በማለት ሁከቱ እንዱወገድ፣ የተለያዩ ወጪዎች ለተጠሪ እንዱከፍል ሲል ወስኗል። በዚህ ውሳኔ አመልካች ባለመስማማት ይግባኙን ለአዱስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ቢያቀርብም ይግባኙ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 337 መሰረት ተሰርዞበታል። የሰበር አቤቱታ የቀረበለት የከተማው ሰበር ሰሚ ችልትም በጉዲዩ ላይ በተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የለም በማለት ወስኗል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም በዚሁ ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈፅሟል በማለት ነው።
የአመልካች ነገረ ፈጅ ሰኔ 08 ቀን 2002 ዓ.ም የጻፈት የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም ተጠሪ በአከራካሪው ቤት በወራሽነት የኪራይ መብት አግኝቼአለሁ የሚለት በተጭበረበረ መንገድ መሆኑ ተገልፆ ቀበላ የሚያስተዲድረውን ቤት እንዱለቁ ማስጠንቀቂያ መፃፈ የሁከት ተግባር ነው ተብል ሉወሰድ የማይገባው በመሆኑ ውሳኔው ሉታረም የሚገባው ነው በማለት መከራከራቸውን የሚያሳይ ነው። አቤቱታው ተመርምሮም የአመልካች ተግባር ሁከት ነው ተብል መወሰኑ ባግባቡ መሆን ያለመሆኑን ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ችልት እንዱቀርብ ተደርጓል። በዚህም መሰረት ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎላቸው ቀርበው የበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ሕጋዊ መሆኑን በመዘርዘር ሉፀና ይገባል ሲለ ተከራክረዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩ ለሰበር ችልት ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው በአመልካችና በተጠሪ መካከል ግንኙነቱ ተጠሪ የሚባለው በአመልካችና ተጠሪ እናቴ ናቸው የሚሎቸው ወ/ሮ አበበች ፍሰሃ ባደረጉት የቤት ኪራይ ውል መሆኑን፣ ተጠሪ ሟቿ ያላቸው የተከራይነት መብት በፍርድ ቤት ተረጋግጦ በተሰጣቸው የወራሽነት ማስረጃ ተላልፍልኛል በማለት የሚከራከሩ ቢሆንም አመልካች ይኸው የወራሽነት ማስረጃ የተገኘው በተጭበረበረ መንገድ ነው በማለት የሚከራከር መሆኑን ነው። በመሆኑም የክርክሩ ይዘት የሚያሳየው ክርክሩ መሰረት ያደረገው የኪራይ ውለን መሆኑን ነው። አመልካች ለተጠሪ ማስጠንቀቂያ ሉጽፍ የቻለውም ቤቱ ያላግባብ ተይዟል በሚል ነው።
በመሰረቱ የሁከት ይወገድልኝ ክስ ላቀርብ የሚችለው ይዞታውን በእውን በሚያዘው ሰው አጠቃቀም ላይ ችግር ወይም መሰናክል ሲፈጠር ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1140 እና 1149 ድንጋጌዎች ይዘት ያሳያል። ባለይዞታው የሁከት ይወገድልኝ ክስ ለማቅረብ ይዞታውን በግልፅ ሁኔታ የያዘው መሆኑ መረጋገጥ ያለበት ጉዲይ ነው። በባለይዞታውና ሁከቱን ፈጠረ በተባለ ሰው መካከልም የተፈጠረው ግንኙነት ካለ ግንኙነቱ የሚገዛበት የሕግ አግባብ ተለይቶ መታየት ያለበት ጉዲይ ነው። ወደተያዘው ጉዲይ ስንመለስም አመልካች የአከራካሪው ቤት ባለቤት መሆኑ የሚያከራክር ሳይሆን ተጠሪ ወራሽ ነኝ ካለ ከተጠሪ ጋር የሚኖረው ግንኙነት ደግሞ የአከራይና የተከራይ ነው። ይህ ግንኙነት በመጀመሪያ የተፈጠረው በቀጥታ በአመልካችና በተጠሪ መካከል ሳይሆን በአመልካችና ተጠሪ አውራሼ ናቸው በሚለት በሟች ወ/ሮ አበበች ፍሰሃ መካከል ነው።
አመልካች ደብዲቤውን ሉፅፍ የቻለው ተጠሪ ቤቱን በሕጉ አግባብ የተከራዩት አይደለም በማለት መሆኑን ከክርክሩ ሂደት የምንገነዘበው ጉዲይ ነው። እንዱህ ከሆነ ተጠሪ ሰፉ የሆነ የባለቤትነት መብት ካለው አመልካች ጋር ሉከራከሩ የሚችለት በሕጉ አግባብ የተደረገ የኪራይ ውል መኖሩን በማሳየት በውለ መሰረት መብታቸው እንዱጠበቅላቸው እንጂ የሁከት ይወገድልኝን ክስ በማቅረብ ላሆን አይችልም። ተጠሪ በፍርድ ቤት የተረጋገጠ የወራሽነት ማስረጃ መያዛቸውም አመልካች ማስረጃውን በቅድሚያ እንደያሰርዝ የሚያስገድደው ካለመሆኑም በላይ ማስረጃው ዋጋ የለውም የሚለውን ተቃውሞ በማናቸውም የክርክር ደረጃ ከማቅረብ የሚከለክለው አይደለም። በመሆኑም የበታች ፍርድ ቤቶች ጉዲዩ የሚገዛው የኪራይ ግንኙነትን በሚገዙት ድንጋጌዎች ሆኖ እያለ አመልካች ማስጠንቀቂያ መፃፈን በመመልከት ብቻ ተግባሩ ሁከት ነው በማለት የደረሱበት ድምዲሜ በአመልካችና በተጠሪ መካከል አለ የተባለውን ግንኙነት ስለሁከት አጠቃላይ ይዘትና በዚህ ረገድ በፍርድ ቤት ስለሚጠየቀው መፍትሓ ከባለቤትነት መብት አድማስ ጋር ያላገናዘበ በመሆኑ ውሳኔው መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሁኖ አግኝተናል። በዚህም መሰረት ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በጉዲዩ ላይ በበታች ፍርድ ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ተሽሯል።
አመልካች ለተጠሪ ማስጠንቀቂያ መጻፈ ሁከት ልባል የሚችል አይደለም ብለናል።
ተጠሪ ከአመልካች ጋር የመሰረቱት ሕጋዊ የኪራይ ውል አለ የሚለ ከሆነ ይህንኑ መሰረት በማድረግ መብታቸውን ከሚያስከብሩ በስተቀር በአመልካች ላይ የሁከት ይወገድልኝ ክስ ሉያቀርቡ አይገባም ብለናል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.