No summary available.
ኀዲር 28 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ሒጏስ ወልደ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ሡልጣን አባተማም አመልካቾች፡-
መዝገቡን ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
በዚህ መዝገብ የቀረበው ክርክር የቤት ሽያጭ ውልን አፈፃፀም የተመለከተ ነው። ክርክሩ የተጀመረው 1ኛ ተጠሪ 2ኛ ተጠሪ ላይ በመሰረተው ክስ ነው። የዲኝነት ጥያቄውም ጥር 9 ቀን 1989 ዓ.ም በተደረገ የሽያጭ ውል ከ1ኛ አመልካች የገዛውን ቤት ስመ ሐብት እንዱያዛውርለት እና ካርታ በስሙ እንዱሰራለት ማዘጋጃ ቤቱ ተጠይቆ ፈቃደኛ ስላልሆነ በፍርድ ሃይል ተገድ ይፈጽምልኝ የሚል ነበር። ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የዲኝነት ሥልጣኑ ያከራከረው የከተማ ነክ ፍ/ቤት ማዘጋጃ ቤቱ አስተዲደራዊ ተግባሩን እንዱያከናውን ውሳኔ ሰጥቷል። ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም አመልካቾች በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 358 ለፍርድ ቤቱ አቤቱታ አቅርበዋል።
ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር ሰምቶ የአመልካቾችን መቃወሚያ ባለመቀበል ቀደም ሲል የሰጠውን ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 360/2/ መሰረት አጽንቷል።
አመልካቾች በውሳኔው ቅር ተሰኝተው ለከተማው ነክ ጉዲዮች ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት ይግባኝ ያቀረቡ ቢሆንም ፍ/ቤቱ አልተቀበለም።
የአማራ ብ/ክ/መ/ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት አቤቱታ ቀርቦለት የሥር ፍ/ቤቶች ውሳኔ የሕግ ስሕተት የለውም በማለት አጽንቷል።
ለዚህ ሰበር ችልት አቤቱታ የቀረበው በዚሁ ላይ ነው። ይህ ሰበር ችልት የአመልካችን አቤቱታ ከመረመረ በኋላ የጏንደር ከተማ ፍርድ ቤት ጉዲዩን አይቶ ለመወሰን የሚያስችለው የዲኝነት ሥልጣን አለው ወይስ የለውም የሚለውንና ተጠሪ በውልና ማስረጃ ጽ/ቤት የተደረገ የሽያጭ ውል በማቅረብ ስም ይዛወርልኝ፤ ካርታ ይሰራልኝ ጥያቄ የማቅረብ መብት አለው ወይንስ የለውም?
የሚለውን ለመመርመር ተጠሪ መልስ እንዱሰጥ ተደርጓል።
1ኛ ተጠሪ ጥር 27 ቀን 2002 ዓ.ም የተፃፈ መልስ አቅርበዋል። በይዘቱ ሲታይ የ1ኛ ተጠሪ ክስ በይርጋ ያልታገደ ስለመሆኑ፣የተጠየቀው ዲኝነትም በሕግ የተመሰረተ ውል መሰረት ያደረገ ስለመሆኑና የጏንደር ከተማ ነክ ፍርድ ቤት በክልለ ሕግ መሰረት ጉዲዩን የመዲኘት ሥልጣን አለው በማለት ተከራክሯል።
የጉዲዩ አመጣጥ እና በግራ ቀኙ ክርክር ከፍ ሲል በአጭሩ የተመለከተው ሲሆን እኛም በዚህ ሰበር ችልት እንዱመረመር የተያዘውን ጭብጥ መሰረት አድርገን ከሕጉ ጋር በማገናዘብ መርምረናል።
የመጀመሪያው ጭብጥ የጏንደር ከተማ ፍ/ቤት ጉዲዩን የመዲኝት ሥልጣንን በተመለከተ ነው። በመሰረቱ የፍርድ ቤቶች የዲኝነት ሥልጣን በሕግ የሚወሰን መሆኑ እሙን ነው። በተያዘው ጉዲይ 1ኛ ተጠሪ 2ኛ ተጠሪ ላይ ክስ የመሰረተው በግዥ ውል የተላለፈለትን መብት መሰረት በማድረግ የከተማው ማዘጋጃ ቤት አገልግልት አሰጣጥን የሚመለከት ስለመሆኑ መዝገቡ ያስረዲል።
በአማራ ብ/ክ/መ/በወጣው አዋጅ ቁጥር 91/96 እና ደንብ ቁጥር 12/2000 በተደነገገው መሰረት ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግልት ጋር በተያያዘ የሚነሳ ክርክር የከተማ ነክ ፍ/ቤቶች የመዲኝት ሥልጣን እንዲላቸው ተመልክቷል በማለት ጉዲዩን የተመለከቱት የሥር ፍ/ቤቶች የወሰኑት ስለመሆኑ ከውሳኔው ይዘት ለመረዲት ችለናል።
በክልለ ሕግ መሰረት ጉዲዩን ለመዲኘት ሥልጣን እንደተሰጣቸው በሥር ፍ/ቤቶች ያረጋገጡት በመሆኑ በዚህ ረገድ የሥር ፍ/ቤቶች ውሳኔ የሥልጣን መሰረት የለውም የሚባልበት ምክንያት አልተገኘም።
በሁለተኛ ደረጃ የተያዘው ጭብጥ ተጠሪ በውልና ማስረጃ ምዝገባ ጽ/ቤት የተደረገ ውልን በመያዝ ክስ የማቅረብ መብት አለውን? የሚለውን በተመለከተ ነው።
ከመዝገቡ መረዲት እንደተቻለው 1ኛ ተጠሪ በግዥና ሽያጭ ውል ያገኘውን መብት መሰረት በማድረግ 2ኛ ተጠሪ ስም የማዛወር ግዳታ እና ካርታ የመስጠት ተግባር አልተወጡም በሚል መነሻ ክስ አቅርቧል።
ይህ ሰበር ሰሚ ችልት በሰበር መ/ቁ. 33945 በሰጠው ውሳኔ እንደተመለከተው ገዥ በሽያጭ ውለ መሰረት ስም ይዛወርልኝ ጥያቄን መሰረት በማድረግ ሻጭ ላይ የሚያቀርበው ክስ የክስ ምክንያት የለውም። ይልቁንም ይህ ተግባር የአስተዲደር አካል ተግባር ነው በሚል ትርጉም ሰጥቷል። በተያዘው ጉዲይ 1ኛ ተጠሪ 2ኛ ተጠሪን የከሰሰው የአስተዲዲር ተግባር አልተወጣልኝም በሚል ነው። ከፍ ሲል ከተጠቀሰው የሰበር መዝገብ ውሳኔ መረዲት የሚቻለውም አስተዲደሩ በሕግ የተሰጠውን ተግባር ካልተወጣ ገዥ መብቱን ለማስከበር ክስ ማቅረብ የሚገበው በአስተዲደር አካለ ላይ ስለመሆኑ ነው።
No topics extracted.
ስለሆነም 1ኛ ተጠሪ 2ኛ ተጠሪ ላይ ያቀረበው ክስ የክስ ምክንያት የለውም ልባል የሚቻል ሆኖ አላገኘውም። በመሆኑም የ1ኛ ተጠሪን የዲኝነት ጥያቄ መሰረት በማድረግ በሥር ፍ/ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ በሕግ አተገባበር ወይም አፈፃፀም ረገድ መሰረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈፀመበት ሆኖ አላገኘነውም። ለዚህም ወሳኔው ባለበት ሁኔታ ሉፀና ይገባል ብለናል።
በጏንደር ከተማ ነክ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 00449 በ01/07/2001 ዓ.ም የተሰጠው ውሳኔ፣የከተማ ነክ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 00226 የሰጠው ትእዛዝ እና የአ/ብ/ክ/መ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቁ. 01571 በ29/10/2001 ዓ.ም የሰጠው ትእዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ፀንቷል።
ይህ ውሳኔ 2ኛ ተጠሪ የሚያቀርቡትን የሽያጭ ውል መነሻ ያደረገ የመብት ጥያቄ የሚገድብ አይደለም።
መዝገቡ ተዘግቷል ይመለስ።
በዚህ መዝገብ ላይ የካቲት 3 ቀን 2002 ዓ.ም የተሰጠው የእግድ ትእዛዝ ተነስቷል።
ይፃፍ።