No summary available.
መጋቢት 23 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሐጎስ ወልደ ዲኜ መላኩ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- አቶ ሳሙኤል ታደሰ አልቀረቡም ተጠሪዎች፡- ወ/ት እጥፍ ወርቅ ኃይለማርያም አልቀረቡም መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትና የከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጡት የአፈፃፀም ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት አመልካች ያቀረቡት የሰበር አቤቱታ የሚጣራ ነጥብ ያለው መሆኑ ተገልፆ ለሰበር የቀረበ ነው። ክርክሩ የፍርድ አፈፃፀምን የሚመለከት ሲሆን ተጠሪ የፍርድ ባለመብት አመልካች የፍርድ ባለዕዲ በመሆን ተከራክረዋል። ተጠሪ የአመልካች ንብረት የሆነ የኮንደሚኒየም ቤት ያለ በመሆኑ ቤቱ ተሸጦ በፍርድ የተረጋገጠለትን ገንዘብ ቤቱ በሀራጅ ተሸጦ እንዱከፈል ውሣኔ ይሰጥልኝ በማለት አመልክተዋል።
የፋዳራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት የፍርድ አፈፃፀም መምሪያ በአራዲ ክፍለ ከተማ ቀበላ 1ዐ በሰራተኛ ሰፈር ሣይት የህንፃ ቁጥር ዐ1 የቤት ቁጥር 52-Bs-2506 የወለል ቁጥር 002 የቤቱ ስፊት 43.37 ካሬ ሜትር የሆነውን ኮንደሚኒየም ቤት በሐራጅ በመሸጥ ለፍርድ ቤት ባለመብት ብር 300,000 /ሶስት መቶ ሺ ብር/ በታህሣሥ 30 ቀን 2002 ዓ.ም ጀምሮ ገንዘቡ ተከፍል እስከ አለቀ ድረስ ከሚታሰብ ከአሥራ ሁለት በመቶ ወለድ ጋር እንዱከፈል በማለት ትዕዛዝ ሰጥቷል። አመልካች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበዋል። የከፍተኛው ፍርድ ቤት በፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 337 መሰረት ይግባኙ ፍሬ ነጥብ የላለው መሆኑን በመግለፅ ሰርዞታል።
አመልካች ግንቦት 9 ቀን 2002 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ የሥር ፍርድ ቤት በፍርድ የተወሰነብኝን ገንዘብ ለመክፈል የአንድ ወር ጊዜ እንዱሰጠኝ ያቀረብኩትን ጥያቄ አለመቀበለ የፍታብሓር ሥነሥርዓት ሕግ ቁጥር 186/2/ የሚጥስና መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው።
ከዚህ በተጨማሪ ኮንደሚኒየም ቤቱ አምስት ዓመት ሣይሞላው ለዕዲ መክፈያነት እንዱሸጥ የበታች ፍርድ ቤቶች የሰጡት ትዕዛዝ የአዱስ አበባ አስተዲደር ምክር ቤት ያወጣውን አዋጅ ቁጥር 19/97 አንቀፅ 14/2/ እና አንቀፅ 21 እንደዚሁም የፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 404/ሰ/ የተደነገገውን የሚጥስና መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት አመልክተዋል። ተጠሪ በበኩላቸው ጥቅምት 19 ቀን 2003 ዓ.ም በተፃፈ መልስ አመልካች ዕዲውን ያለመክፈል የተለያየ ሰበብ እየፈጠሩ አጉላልተውኛል። አዋጅ ቁጥር 19/97 የቤቱ የባለሀብትነት ምስክር ወረቀት የሚሰጠው ዕዲው ተከፍል ሲያልቅ መሆኑን ከሚደነግግ በስተቀር ገንዘብ የተበደረና የኮንደሚኒየም ቤት ያለው ሰው ዕዲው ቤቱ ተሸጦ እንዲይከፈል አይከለክልም።
ስለዚህ የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተገቢ ባለመሆኑ የሰበር አቤቱታውን ውድቅ በማድረግ ያሰናብተኝ በማለት መልስ ሰጥተዋል። አመልካች ታህሣሥ 22 ቀን 2003 ዓ.ም የተፃፈ የመልስ መልስ አቅርበዋል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር ግራ ቀኙ በፅሐፍ ያቀረቡት ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም መዝገቡን መርምረናል። ጉዲዩን እንደመረመርነው አመልካች የፍርድ ባለዕዲ መሆናቸው በሥር ፍርድ ቤትም ሆነ በሰበር የታመነ ጉዲይ ነው። ባለዕዲ መሆኑ በፍርድ የተረጋገጠበት ሰው በፍርድ የተወሰነበትን ገንዘብ ለፍርድ ባለመብቱ የማይከፍልበት በአፈፃፀም ወቅት ሉያነሣው የሚችለው መከራከሪያ ያለው ስለመሆኑ አፈፃፀሙን ለያዘው ፍርድ ቤት ቀርቦ እንዱያስረዲ ፍርድ ቤቱ እድል የሚሰጠው መሆኑን ከፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 378/1/ ድንጋጌ ለመረዲት ይቻላል። አመልካች በፍርደ መሰረት ፈፅሞ ከሆነ ፍርደን የፈፀመ መሆኑን በፍርደ መሰረት ያልፈፀመ ከሆነ ያልፈፀመበትን ምክንያት ሲጠየቅ አፈፃፀሙን የያዘው ፍርድ ቤት ፍርደን ለመፈፀም ተጨማሪ ጊዜ እንዱሰጠው ጥያቄ አቅርቧል። የሥር ፍርድ ቤት ይህንን የአመልካችን ተጨማሪ ጊዜ ይሰጠኝ ጥያቄ ውድቅ በማድረግ የፍርድ አፈፃፀሙ በአመልካች ንብረት ላይ የሰጠው ትዕዛዝ የህግ ስህተት ያልተፈፀመበት በመሆኑ አመልካች የሥር ፍርድ ቤት ተጨማሪ ጊዜ ሉሰጠኝ ይገባ ነበር በማለት ያቀረበውን ክርክር አልተቀበልነውም።
በሁለተኛ ደረጃ አመልካች ለፍርድ አፈፃፀምና ለአመልካቿ እዲ መክፈያ ይሆን ዘንድ የኮንደሚኒየም ቤቱ በሀራጅ እንዱሸጥ የበታች ፍርድ ቤቶች የሰጡት የአፈፃፀም ትዕዛዝ የአዱስ አበባ አስተዲደር ምክር ቤት ያወጣውን አዋጅ ቁጥር 19/97 አንቀፅ 14 ንዐስ አንቀፅ 2 እና አንቀፅ 21 የሚጥሱና መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው በማለት አመልካች ያቀረቡት አቤቱታ ስንመረምረው ከላይ የተጠቀሱት የህግ ድንጋጌዎች ይዘት መንፈስና ዓላማ ጠቅላላ ዋጋውን ከፍል ያጠናቀቀ የኮንደሚኒየም ቤት ባለሃብት የሆነው ሰው ክፍያ ያጠናቀቀበትን የኮንደሚኒየም ቤት በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ተሸጦ ለፍርድ ማስፈፀሚያ እንዲይሆን የሚከለክለ ድንጋጌዎች ሆነው አላገኘናቸውም። የአዋጅ ቁጥር 19/94 አንቀፅ 14 ንዐስ አንቀፅ 2 ድንጋጌ የመጀመሪያው ፕራግራፍ ቃል በቃል ሲነበብ ‛ገዢው ጠቅላላ ዋጋውን ከፍል ቢያጠናቅቅም ቤቱን ለሶስተኛ ወገን በሽያጭ ወይም በስጦታ ለማስተላለፍ የሚቻለው ቤቱን ከገዛ በኋላ አምስት ዓመት ሲሞላው ብቻ ይሆናል“ በማለት የሚደነግግ ሲሆን የአዋጁ አንቀፅ 21 ከአዋጁ ጋር የሚቃረን የተለመደ አሰራር ወይም ህግ በዚህ አዋጅ በተሸፈነ ጉዲዮች ተፈፃሚነት የለውም በማለት የሚደነግግ ድንጋጌ ነው።
የአዋጅ ቁጥር 19/97 አንቀፅ 14/2/ የኮንደሚኒየም ቤት ዋጋ ከፍል ያጠናቀቀ ባለሃብት ቤቱን የመሸጥ የመለወጥና ለሶስተኛ ወገን የማስተላለፍ መብቱን በተሟላ ሁኔታ ተግባር ላይ የሚያውለው ከአምስት ዓመት በኋላ መሆኑን የሚደነግግ ነው። ድንጋጌው የኮንደሚኒየም ቤት ባለሃብት የሆነው ሰው በራሱ ፈቃድና ፍላጎት ቤቱን በሽያጭ ወይም በስጦታ ስለሚያስተላለፍበት ሁኔታ የሚደነግግ ነው። ይህ ድንጋጌ የቤቱን ዋጋ አጠቃል የከፈለ የኮንደሚኒየም ቤት ባለሃብት እንዱከፍል በፍርድ የተወሰነበት የላላ ሰው ዕዲ ያለበት በሆነ ጊዜ ፍርድ ቤቶች ዕዲው ተጠቃልል የተከፈለውን የኮንደሚኒየም ቤት በሀራጅ ተሸጦ ለፍርድ ማስፈፀሚያ እንዱሆን ትዕዛዝ ከመስጠት የሚከለክል ወይም ሥልጣናቸውን የሚገድብ የህግ ድንጋጌ አይደለም። አመልካች የጠቀሱት የአዋጅ ቁጥር 19/97 አንቀፅ 21 ዋጋው ተጠናቅቆ የተከፈለውን የፍርድ ባለዕዲ የኮንደሚኒየም ቤት ፍርድ ቤቶች በሀራጅ ተሸጦ ለፍርድ ማስፈፀሚያ ከማድረግ የሚገደብ ይዘት ያለው ድንጋጌ አይደለም።
ስለሆነም አመልካች የበታች ፍርድ ቤቶች የፍርድ ማስፈፀሚያ ይሆን ዘንድ በሀራጅ እንዱሸጥ ትዕዛዝ የሰጡበት የኮንደሚኒየም ቤት በህግ ለላላ ሰው እንዲይሸጥ ክልከላ የተደረገበት ነው በማለት የአዋጅ ቁጥር 19/77 አንቀፅ 14/2/ እና አንቀፅ 21 ከፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 404/ሰ/ ጋር በማጣመር ያቀረቡት ክርክር የተጠቀሱትን የህግ ድንጋጌዎች መሰረታዊ ይዘት መንፈስና ግብ ያላገናዘበ በመሆኑ አልተቀበልነውም። ስለሆነም የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሰጠውን የአፈፃፀም ትዕዛዝ ይግባኝ ሰሚው ከፍተኛው ፍርድ ቤት በማፅናት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለበትም በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትና የፍደራል የከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ ፀንቷል።
በዚህ ፍርድ ቤት ህዲር 8 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም የተሰጠው የዕግድ ትዕዛዝ ተነስቷል።
ይፃፍ።
No topics extracted.