No summary available.
የሰ/መ/ የካቲት 22 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሐጎስ ወልደ ዲኜ መላኩ ተሻገር ገ/ሥላሴ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ወ/ት ታሪክ ጌታቸው ተጠሪዎች፡- 1ኛ ወ/ሮ አልጋነሽ ተጠምቀ 2ኛ ወ/ሮ ልዕልቲ በላይ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
በዚህ መዝገብ ለሰበር ለቀረበው ክርክር መነሻ ሆኖ የተገኘው የሟች አቶ ጌታቸው በላይ ንብረት የሆነ በመቀላ ከተማ የሚኝ 325 ካሬ ሜትር የቦታ ይዞታ ያለውን ቤት የሟች ልጅና ህጋዊ ወራሽ የሆነችው የአሁኗ አመልካች እያለች አቶ በላይ በየነ የተባለት ሰው እና የአሁኗ 1ኛ ተጠሪ ወ/ሮ አልጋሽ ተጠምቀ የሟቹ ወራሾች እኛ ነን ብለው ፍ/ቤት በመቅረብ የወራሽነት ማስረጃ እንዱሰጣቸው ጠይቀው የወራሽነት ማስረጃ በመውሰድ የሟችን ቤት ስም ባለሃብትነት በሥማቸው ካዛወሩ በኃላ ልጃቸው ለሆነችው ለአሁኗ 2ኛ ተጠሪ ወ/ሮ ልዕልቲ በላይ ብር 50,000 በመሸጥ አስተላልፈው በሥሟ እንዱመዘገብ አድርገው መገኘታቸው ነው።
የአሁኗ አመልካች ለመቀላ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ባቀረበችው ክስ የሟቹ የአቶ ጌታቸው በላይ ልጅና ህጋዊ ወራሽ መሆኗን 1ኛ፣ 2ኛ እና 3ኛ ተከሣሾች በማይመለከታቸውና ያለአግባብ የሟችን ቤትና ቦታ ተሻሽጠውና አዛውረው እንደሚገኙ በመዘርዘር እንዱያስረክቧት ጠይቃለች። አቶ ጌታቸው በላይ በ1986 ዓ.ም ከዚህ አለም በሞት የተለዩ ስለመሆናቸውና ሟች ባደረጉት ኑዛዜ ስለልጅቱ አስተዲዲሪ ለወላጆቻቸው በሰጡት መሰረት የአሁኗ አመልካች የስድስት አመት ዕድሜ ሲሞላት 2ኛዋ ተከሣሽ ወደ ደሴ ከተማ መጥታ ልጅቷን ወደ መቀላ ከተማ በመውሰድ ከእነርሱ ጋር ስትኖር ቆይታ ዕድሜዋ ለአካለመጠን ሲደርስ ሐምል 14 ቀን 2000 ዓ.ም ፍ/ቤት ቀርባ የሟቹ ህጋዊ ወራሽ ስለመሆኗ የሚያረጋግጥ ማስረጃ እንደተሰጣት በክሱ ላይ ተገልጿል። አመልካች በክሷ ቤት ብቻ ሳይሆን ላልች የጠየቀቻቸው ነገሮች ነበሩ። በዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት 1ኛ እና 2ኛ ተከሣሾች የነበሩት የይርጋ የመቃወሚያና ላልች የፍሬ ነገር ክርክሮች ያቀረቡ ሲሆን ቤቱን ገዝታለች የተባለችው 3ኛዋ ተከሣሽ የነበረችው የአሁኗ 2ኛ ተጠሪ በበኩሎ 1ኛ እና 2ኛ ተከሣሾች ቤቱን በይዞታቸው ሥር ለ10 አመት አቆይተው በብር 50,000 ሸጠውልኝ ንብረቱ በሚመለከተው የሕግ ክፍል በፍትሐብሄር ሕግ 1723 መሰረት ተመዝግቦ በቅንነት የገዛሁትን መልሺ ተብዬ ልገደድ አይገባም በማለት ተከራክራለች። የመቀላ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ክሱን፣ የግራ ቀኙን ክርክሮች እና ማስረጃዎችን መርምሮ ክሱ በ10 አመት ይርጋ ይታገዲል በሚል ለተነሣው ክርክር ከሣሽዋ የአካለመጠን ዕድሜ በመድረስ የመክሰስ ችልታ እንዲገኘች በ30/10/2000 ዓ.ም ክሱን ያቀረበች ስለሆነ ክሱ በይርጋ የሚታገድ አይደለም ብል ውድቅ ካደረገው በኋላ የክሱን ዋና ፍሬ ነገር በተመለከተም ቤቱ የሟቹ የአቶ ጌታቸው በላይ ንብረት መሆኑ በቀረበው የጽሐፍ ማስረጃ ተረጋግጧል 1ኛ እና 2ኛ ተከሣሾች ከሣሽዋን በሞግዚትነት እያሳደጓት ባለበትና የመውረስ መብት ባልነበራት ወቅት ወራሾች ሣይሆኑ ተሯሩጠው የሟች ወራሽ ስለመሆናቸው በማስወሰን ቤቱን ለልጃቸው ለ3ኛዋ ተከሣሽ ሸጠው መገኘታቸው በሕግ የሚደገፍ አሻሻጥ አይደለም፣ የራሣቸው ያልሆነውን ንብረት መሸጥ በሕጉ አይፈቀድም፣ ሸያጩ በሕጉ ውጤት የለውም ፈራሽ ነው፤ ያገኙት ወራሽነትና ያደረጉት ሽያጭ ቅንነት የጉደለው የማይገባ ብልጽግና ለማግኘት የተፈፀሙ በመሆኑ ተቀባይነት የለውም፣ 3ኛዋ ተከሣሽም ንብረቱን የገዛችው ቅንነት ከላላቸውና በቤቱ ላይ መብት ከላላቸው ወራሾች ነው፣ ራሷም ብትሆን ቤቱን በቅንነት የገዛች ባለመሆኑ ሽያጩ ተቀባይነት የለውም በማለት በክሱ ላይ አዋሳኞቹ የተጠቀሰውን በውስጡ 8 ክፍል መኖሪያ፣ ሽንት ቤትና ማዕድ ቤት የያዘ የቦታ ስፊቱ 325 ካሬ ሜትር የሆነውን ቤት 1ኛ፣ 2ኛ እና 3ኛ ተከሣሾች ለከሣሽዋ ለአሁኗ አመልካች ሉያስረክቧት ይገባል ብል ወስኗል።
የአሁኑ ተጠሪዎች በዚህ የመቀላ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በሰጠው ውሣኔ ቅር በመሰኘት ለትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኙን ያቀረቡ ቢሆንም መርምሮ የዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት የሰጠው ውሣኔ የሚተችበትና የሚጣራ ነገር የለውም በማለት በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 337 መሰረት የሚያስቀርብ አይደለም ብል መዝገቡን ዘግቶታል።
እንደገና የአሁኑ ተጠሪዎች በዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት የተሰጠው ውሣኔና የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤትም ጉዲዩ በይግባኝ ቀርቦለት አይቶት የሰጠው ትዕዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው በማለት ለክልለ ሰበር ሰሚ ችልት አቤቱታ አቅርበው ጉዲዩ ያስቀርባል ተብል ሁለቱ ተከራካሪ ወገኖች ቀርበው ክርክሩ ከተሰማ በኃላ ሰበር ሰሚው ችልት በበኩለ መርምሮ የአሁኗ 1ኛ ተጠሪ ከባለቤቷ ጋር ሆና ሟቹ ልጃችን ወራሽ የለውም፣ ወራሾቹ እኛ ነን ብለው ቤቱን ወደ ሥማቸው በማዛወር ለአሁኗ 2ኛ ተጠሪ በብር 50,000 ሸጠው ስለተገኙ በህጋዊ መንገድ የገዙትን ቤት ሉያስረክቡ አይገባም፣ ቤቱን በመሸጥ ጥቅም ያገኘችው የአሁኗ 1ኛ ተጠሪ ብር 50,000 ክሱ ከቀረበበት ጊዜ አንስቶ ተከፍል እስኪያልቅድረስ 9% ወለድ ጨምራ ለአሁኗ አመልካች ትክፈል የሚል ውሣኔ በመስጠት የዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት የሰጠውን ውሣኔና የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት የሰጠውን ትዕዛዝ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348(1) መሰረት ሽሮታል።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታም የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት የሰበር ሰሚ ችልት የሰጠው ውሣኔ መሰታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው በማለት በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 80(3) መሰረት የቀረበ ሲሆን ተመርምሮ ጉዲዩ ለሰበር ችልት ቀርቦ ይታይ ተብል በመወሰኑ ማመልከቻው ለአሁኑ ተጠሪዎች ተልኮ ቀርበው ክርክሩ እንዱሰማ ተደርጓል። በሁለቱም በኩል ቀርበው የተከራከሩት በየባለጉዲዮቹ የተወከለት ጠበቆች ናቸው። በዚህም መሰረት የአመልካች ጠበቃ ቤቱ ለ2ኛዋ ተጠሪ ተሽጧል የተባለበት ውል በተንኮል የተደረገ ስለሆነ ሉፀና አይገባም፣ ሻጮችም በቤቱ ላይ ህጋዊ መብት የላቸውም፣ በትክክል በሚታይበት ጊዜ ሁለተኛዋ ተጠሪ ቤቱን ሆነ ብላ ነው የገዛችው፣ ገንዘቧን ማግኘት አለባት ከተባለም ማግኘት ያለባት ከሸጡላት ወላጆቿ ነው። ውለ ፈርሶ ቤቱን ለአመልካች መስጠት አለባቸው፣ ይህ እንኳን ቢታለፍ በክሱ ላይ የቤቱ ግምት ብር 120,000 ተብል ስለቀረበ እነርሱ የተሻሻጡበት ብር 50,000 ይከፈላት የተባለው ያለአግባብ ነው ብለው በመዘርዘር ተከራክረዋል። የተጠሪዎች ጠበቃ በበኩላቸው 1ኛዋ ተጠሪ 10 አመት በሙለ በቤቱ ሲገብሩበት ቆይተው ይዞታቸውን መሸጣቸው ህጋዊ ነው፣ ገዢዋም ብትሆን ሕጉ በሚፈቅደው መሰረት በሥማቸው ተመዝግቦ የሚገኘውን ቤት መግዛቷ ህገ ወጥ አያሰኝም። በቦታው ላይ 5 ክፍል ቤት ሰርታበታለች፣ ይዞታው ሁለ ተለውጧል፣ ሸያጩ በአግባቡ ስለሆነ ሉፈርስ አይገባም፣ ብር 120,000 ነው የቤቱ ግምት ያለት በክሱ እንዱከፈላቸው የጠየቁት ስላልሆነ ተቀባይነት የለውም፣ የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የሰጠው ውሣኔ በአግባቡ በመሆኑ ሉፀና ይገባል የሚለትን ክርክሮች አቅርበዋል። የጉዲዩ አመጣጥና የክርክሮቹ ይዘት ከዚህ በላይ እንደተመለከተው ሲሆን ጉዲዩም ከሕጉ ጋር ተገናዝቦ እንደሚከተለው ተመርምሯል።
ለክርክሩ መነሻ ሆኖ የተገኘው ቤት የአሁኗ አመልካች አባትና አውራሽ የሆኑት የሟቹ የአቶ ጌታቸው በላይ ንብረት መሆኑና 1ኛዋ ተጠሪ የአሁኗን አመልካችን አባቷ እንደሞቱ ገና የ6 አመት ህፃን ልጅ እያለች ወስዲት አብራቸው እየኖረች ባለበት ወቅት የሟች ልጅ መሆኗን እያወቀች 1ኛ ተከሣሽ ከነበረው ከአቶ በላይ በየነ ጋር በመሆን የሟች ወራሾች እኛነን ብለው ለፍ/ቤት በማመልከት የወራሽነት ማስረጃ እንዱሰጣቸው አድርገው የሟቹን ቤት የባለሃብትነት ሥም በራሣቸው ሥም በማዛወር ልጃቸው ለሆነችው ለአሁኗ 2ኛ ተጠሪ ቤቱን በመሸጥ በሥሟ እንዱዛወር ማድረጋቸው፣ በሥር ፍ/ቤት በተደረጉ ክርክሮችና በቀረቡት ማስረጃዎች የተረጋገጡ ፍሬ ነገሮች ናቸው።
ከወላጆቿ ቤቱን ገዝታለች የምትባለው የአሁኗ 2ኛ ተጠሪም የአሁኗ አመልካች የሟች የአቶ ጌታቸው በላይ ልጅ ስለመሆኗና ቤቱም ቀደም ሲል የሟቹ ንብረት መሆኑን አላውቅም አትልም።
የአሁኗ አመልካች አብራቸው እየኖረችና እንደ ሞግዚትም ሆነው እያሳደጓት እያለ አካለመጠን ያልደረሰችውን ልጅ የአባቷን የውርስ ሀብት ጠብቀው በሥርዐት እንዱተላለፍላት ማድረግ ሲገባቸው ሆነ ብለው አካለመጠን ባልደረሰችው ልጅ ላይ ጉዲት ለማድረስና መብቷን ለማሳጣት፣ ለራሣቸው የማይገባ ጥቅም ለማግኘት የፈፀሙት ድርጊት መሆኑን ከተረጋገጡት ፍሬ ነገሮች መረዲት ይቻላል።
በእንዱህ አይነት መንገድ አካለመጠን ላልደረሰችው ልጅ በሕጉ አግባብ በውርስ ሉተላለፍለት የሚገባውን ንብረት አሳዲጊዎቿ የነበሩት ሰዎች የሟቹ ወራሾች እኛ ነን ብለው የወራሽነት ማስረጃ በመውሰድ ቤቱን ለገዛ ልጃቸው ሸጥዋል ተብል መገኘቱ በሕጉ የሚኖረው ውጤት ምንድ ነው? ቤቱ ለህጋዊ ወራሿ እንዱለቀቅ የማይደረግበት የሕግ ምክንያት አለ ወይንስ የለም የሚለውን በተመለከተም የፍትሐብሄር ሕግ ቁጥር 2884(1) ላይ የተመለከተው ድንጋጌ የተሸጠው የማይንቀሳቀስ ንብረት በሙለ ወይም በከፉል የሻጩ ሀብት ሣይሆን የቀረ እንደሆነ የመነቀልን የአላፉነት ዋስትናን የሚመለከቱ ድንጋጌዎች ተፈፃሚ እንደሚሆኑ ያስረዲል። እነዚህ የመነቀልን የአላፉነት ዋስትና የሚመለከቱት ድንጋጌዎች ደግሞ የአንድን ነገር ባለሃብትነት ማስተላለፍን ስለሚመለከቱት ውልች ከተደነገጉት ድንጋጌዎች መካከል ከፍትሐብሄር ሕግ ቁጥር 2282 - 2285 የሚገኙ ናቸው። ከእነዚህ ድንጋጌዎች መገንዘብ እንደሚቻለው የተሸጠው ነገር ላላ ሰው በነበረው መብት ምክንያት ይለቀቅልኝ በሚል ለሚቀርበው ጥያቄ ለገዢው መድን የሚሆነው ሻጩ ነው። የፍትሐብሄር ሕግ ቁጥር 2284(2) የተሸጠው ነገር ለይለቀቅልኝ ባዩ በሚለቀቅበት ጊዜ በውላቸው ላይ ተቃራኒ የውል ቃል ከላለ ሻጩ በሽያጩ የተቀበለውን ዋጋ ለገዢው የመመለሰ ግዳታ ያለበት ስለመሆኑ የሚደነግግ ነው። ድንጋጌዎቹ ለማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭም የሚያገለግለ ናቸው። ከላይ የተጠቀሰው የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2884 ድንጋጌ እና በፍትሐብሄር ሕግ ቁጥር 2884(2) እንዱሁም በፍትሐብሄር ሕግ ቁጥር 2285 ላይ የተመለከቱት ድንጋጌዎች ተያይዘው በአንድነት ሲታዩ የተሸጠው የማይንቀሳቀስ ንብረት በሙለ ወይም በከፉል የሻጩ ሀብት ሣይሆን የላላ ሰው ሀብት ሆኖ ከተገኘ ገዢው እንደሚነቀል ወይም እንዱለቅ የሚደረግ ስለመሆኑ የሚጠቅሱ ናቸው። ገዢው በሕጉ ያለው መፍትሄ ሻጩን መጠየቅ ነው።
በልላም በኩል አንድ ሰው አንድን ንብረት በሽያጭ ለላላ ሰው ሉያስተላልፍ የሚችለው በንብረቱ ላይ ትክክለኛ ህጋዊ ባለመብት ሲሆን ወይም በሕጉ አግባብ የንብረቱ ህጋዊ ባለመብት የሆነው ሰው የመሸጥና የመለወጥ ሥልጣን ሰጥቶት ሲገኝ ነው። የላላውን ሰው ንብረት ንብረቴ ነው ብል መሸጥ ከሕጉ ጋር የሚቃረን በመሆኑ ህገ ወጥ ነው። ሕገወጥ ውል ደግሞ በፍትሐብሄር ሕግ ቁጥር 1716 መሰረት ፈራሽ ነው። ገዢው ከንብረቱ የሚነቀለው ወይም ለህጋዊ ባለመብቱ እንዱለቅ የሚደረገውም በዚህ ምክንያት ነው።
በቀረበው ጉዲይም የአሁኗ 1ኛ ተጠሪ እና ክሱ ሲቀርብ 1ኛ ተከሣሽ የነበሩት አቶ በላይ በየነ የአሁኗ አመልካች የሟቹ የአቶ ጌታቸው በላይ ልጅ መሆኗን እየወቁና ወስደዋት በማሣደግ ከእነርሱ ጋር አብራቸው እየኖረች እያለ እኛ ነን የሟች ወራሾች ብለው ማስረጃ በመውሰድ በውርስ ለአመልካች ሉተላለፍ የሚገባውን ቤት በሥማቸው በማዛወር ከልጃቸው ከ2ኛዋ ተጠሪ ጋር አድርገናል የሚለት የመሻሻጥ ውል ከዚህ የተለየ ትርጉም የሚሰጠው አይደለም። በወቅቱ አካለመጠን ካልደረሰችው የሟች ልጅ ንብረቱን ለማሸሽ ወላጆችና ልጅ ያደረጉት የሟችን ቤት መሻሻጥ ውል ህጋዊ ላሆን አይችልም።
የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የአሁኗ አንዲኛ ተጠሪ እና አቶ በላይ በየነ ወራሾች ነን ብለው የቤቱን ሥመ ባለሃብትነት በሥማቸው በማዛወር ለልጃው ለአሁኗ 2ኛ ተጠሪ በብር 50,000 ከሸጡላት ቤቱን ለአሁኗ አመልካች ማስረከብ የለባትም፣ ቤቱን ሸጣ ጥቅም ያገኘችው የአሁኗ 1ኛ ተጠሪ ስለሆነች ገንዘቡን ትመልስላት ያለውም ሥመ ባለሃብትነቱን በሥማቸው ማዘወራቸው ውለን ህጋዊ ሉያደርገው ስለማይችል ተቀባይነት የለውም።
2ኛዋ ተጠሪ ለቤቱ ዋጋ ብር 50,000 ለሻጮች ከፍላ ከሆነ በሕጉ መሰረት እንዱመልሱላት መጠየቅ ይኖርባታል።
በሕጉ 2ኛዋ ተጠሪ ቤቱን ለህጋዊ ባለመብቷ ለመልቀቅ ትገደዲለች።
ሲጠቃለል ከዚህ በላይ በተዘረዘሩት ምክንያቶች የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የአሁኗ 2ኛ ተጠሪ ቤቱን በህጋዊ መንገድ የገዛችው ስለሆነ ለአሁኗ አመልካች ልታስረክብ አይገባም፣ ቤቱ ተሸጧል የተባለበትን ዋጋ ብር 50,000 የአሁኗ 1ኛ ተጠሪ ለአመልካች ትክፈል በሚል የሰጠው ፍርድ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ሆኖ ተገኝቷል።
በዚህ ጉዲይ የመቀላ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት እና የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት የሰጡት ውሣኔ አግባብነት ያለው በመሆኑ የሚሻርበት የሕግ ምክንያት የለም።
ው ሣ ኔ
የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰ/መ/ በ18/02/2002 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348(2) መሰረት ተሽሯል።
የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ በ05/09/2002 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ እና የመቀላ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ 6429 በ26/08/2001 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ ፀንቷል።
በዚህ የሰበር ክርክር ምክንያት የደረሰውን ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሣቸውን ይቻለ።
በዚህ መዝገብ የተሰጠው ፍርድ ትክክለኛ ግልባጭ ይተላለፍ።
No topics extracted.