No summary available.
ግንቦት 15 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የንብረት ግምት ይከፈለን ጥያቄ ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ 1ኛ ተጠሪ አመልካች ከቡታጅራ ሆሣዕና በሚያሰራው መንገድ ምክንያት በሆሣዕና ከተማ የሚገኙ ንብረቶቻቸው እንዱነሱ የግምት ሥራ ተሰርቶላቸው በዚሁ መጀመሪያ ግምት የከተማው አስተዲደር ንብረቶቻቸውን ያስነሳቸው መሆኑን የንብረቶቻቸው ዓይነትና ግምት ምን ያህል እንደሆነ ዘርዝረው አመልካች ካሣ እንዱከፍለን ይወሰንልን በማለት ዲኝነት ጠይቀው በአሁኑ አመልካች ላይ በሀድያ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመሰረቱት የተናጥል ክስ ሲሆን የአሁኑ አመልካችም በተከሣሽነቱ ቀርቦ ለመንገድ ሥራው የዱዛይን ለውጥ ማድረጉንና በተለወጠው ዱዛይን መሰረትም ንብረቶቹ መነሳት የማያስፈልጋቸው በመሆኑ ኃላፉነት እንደላለበት የተነሱ ወይም እንዱፈርሱ የተደረጉ ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 455 አንቀጽ 3(1) እና 4(1) ድንጋጌዎች ስር የተመለከተውን ሥርዓት ባልተከተለ መልኩ የተከናወነ በመሆኑ ሉጠየቅ የማይገባ መሆኑን እንዱሁም አዋጁን ባልተከተለ መንገድ የራሱን ሥራ ለመስራት ንብረቶችን አስነሳ የተባለው የሆሳዕና ከተማ አስተዲደር በክርክሩ ጣልቃ ገብቶ እንዱከራከር ይታዘዝለት ዘንድ በመግለፅ ተከራክሯል። የስር ፍርድ ቤትም የተጠሪዎችን ክርክር በተለያዩ መዛግብት መርምሮ የሆሳዕና ከተማ አስተዲደር ወደ ክርክሩ ይግባልኝ የሚለውን የአመልካችን አቤቱታ ውድቅ አድርጎ አመልካች ካሣ የመክፈል ኃላፉነት ያለበት መሆኑን በመግለፅ ተጠሪዎች በጠየቁት ዲኝነት መሰረት ወስኖላቸዋል። በዚህ ውሳኔ አመልካች ባለመስማማት ይግባኙን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርቦ ይኸው ፍርድ ቤትም ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ መዛግብትን በአንድ ላይ በማጣመር መርምሮ የስር ፍርድ ቤትን ውሣኔ ሙለ በሙለ አፅንቶታል። ከዚህም በኋላ አመልካች የሰበር አቤቱታውን ለዚህ ችልት አቅርቦ ይህ ችልት ግራ ቀኙን አከራክሮ የአሁኑ 2ኛ ተጠሪ (የሆሳእና ከተማ አስተዲደር) ለክርክሩ የግድ ተካፊይ ላሆን የሚገባው ወገን ሁኖ አያለ መታለፈ ያላግባብ ነው በሚል ምክንያት በጉዲዩ ላይ የተሰጠውን ውሳኔ ሙለ በሙለ በመሻር ይኸው ተጠሪ ወደ ክርክሩ እንዱገባ ተደርጎ ጉዲዩ እንደገና ታይቶ እንዱወሰን ለስር ፍርድ ቤት መልሶለት የሥር ፍርድ ቤትም የሆሳዕና ከተማ አስተዲደር ወደ ክርክሩ እንዱገባ በማድረግ የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ ከሰማ በኋላ አመልካችን ለጉዲዩ ኃላፉ በማድረግ የሆሳዕና ከተማ አስተዲደርን ግን ከኃላፉነቱ ነፃ አድርጎ ወስኗል። ከዚህ በኋላም አመልካች ይግባኙን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቢያቀርብም ተቀባይነት አላገኘም። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ በድጋሚ የቀረበውም ይህንኑ የስር ፍርድ ቤቶችን ውሣኔ በመቃወም ለማስቀየር ነው።
የአመልካች ነገረ ፈጅ ሕዲር 13 ቀን 2003 ዓ.ም በፃፈት 5(አምስት) ገፅ የሰበር አቤቱታ በስር ፍርድ ቤቶች ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈፅሟል የሚለበትን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም ባጭሩ ጉዲዩ የዲኝነት ሳይከፈልበት መታየቱ ያላግባብ መሆኑን የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤቱ ጉዲዩን ያየው ከስልጣኑ ውጪ መሆኑንና በዚህ ሰበር ሰሚ ችልት ከተላከለት ውጪ ሶስተኛ ወገንን ጨምሮ ውሳኔ መስጠቱ የስነ ሥርዓት ግድፈት ያለበት መሆኑን በመጀመሪያ መንገደ ሉሰራበት በታሰበው ስፊት መሰረት የተሰራው ግምት እጅግ የተጋነነ በመሆኑ ተቀባይነት እንደላለው ለከተማ አስተዲደሩ አመልካች ከገለጸለት በኋላ አስተዲደሩም ይህንን አውቆ የዱዛይን ክለሳ እና በዚህም መሰረት የግምት ሥራ ከተጠናቀቀ በኋላ በቀድሞው ዱዛይን መሰረት ተነስቷል የሚባል ንብረት ቦታው ለሕዝብ ጥቅም ባልዋለበትና በህጉ አግባብ ላልተነሳ ንብረት ካሣ ለመክፈል ህጋዊ ግዳታ የላለበት መሆኑን በመዘርዘር የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ሙለ በሙለ እንዱሻር ዲኝነት መጠየቁን የሚያሣይ ነው። አቤቱታው ተመርምሮም በሰበር ችልቱ ላታይ ይገባዋል በመባለ ተጠሪዎች ቀርበው የጽሁፍ መልሳቸውን ሰጥተዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሣኔና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩ ለሰበር ችልቱ ሲቀርብ ከተያዘው አንጻር በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመረውም ጉዲዩ ለሰበር ችልቱ ሲቀርብ የተያዘው ጭብጥ አመልካች ለተጠሪዎች ካሳ ይክፈል የተባለበትን አግባብ ለመመርመር ሲባል ነው። በዚህም መሰረት ጉዲዩን እንደሚከተለው አይቶታል።
ክርክሩ ሲጀመር በተራ ቁጥር አንድ የተጠቀሱት ተጠሪዎች በተናጠል ክሳቸውን አቅርበው ጉዲያቸው የታየ ሲሆን በይግባኝ ደረጃ የተጣመሩ መሆኑን ከክርክሩ ሂደት ተገንዝበናል። የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጉዲዩን ያየውም የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትን ስልጣን በመወከል መሆኑንና የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሚሰጠው ውሳኔ ቅሬታ ያለበት ወገን ሁለ ይግባኙን ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ማቅረብ ይገባ የነበረ መሆኑን ከአዋጅ ቁጥር 322/95 እና ይህ ሰበር ሰሚ ችልት በዚህ ረገድ በመ/ እና በላልች በርካታ መዛግብት ከሰጠው አስገዲጅ የሕግ ትርጉም የምንገነዘበው ጉዲይ ነው። ይሁን እንጂ በዚህ ጉዲይ ይህ ሰበር ሰሚ ችልት ጉዲዩ ለዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተመልሶ እንዱታይ ውሳኔ ሲሰጥ ይግባኙ በፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት መታየቱ ላይ ያስቀመጠው ትችት ባለመኖሩና ክርክሩ ከወሰደው ጊዜ እንዱሁም ከሥነ ስርዓት አላማ ስንነሳ በይግባኝ አቀራረብ ሥርዓቱ ላይ የተፈጸመውን ስህተት አልፈነዋል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው አመልካች በመጀመሪያ መንገደ ሉሰራበት በታሰበው ስፊት መሰረት የተሰራው የንብረቶች ግምት ባልተለመደ ሁኔታ እጅግ የተጋነነ በመሆኑ እንደማይቀበለው ለከተማ አስተዲደሩ ገልጾና አሳውቆ የዱዛይን ክለሳና የግምት ሥራ ተጠናቅቆ ከአለቀ በኋላ ንብረቶቹ እንዱነሱ ወይም እንዱፈርሱ ለተደረገው ሁኔታ አመልካች ኃላፉነት እንደላለበትና ይህንን ድርጊት የከተማው አስተዲደር ለራሱ ሥራ ሲል ስለአከናወነው ኃላፉነት ሉወስድ ስለሚገባ ወደ ክርክሩ ጣልቃ እንዱገባ ሉታዘዝ ይገባል በማለት የሥነ ሥርዓት ጥያቄ አንስቶ ይህ ችልትም በሰ/መ/ የከተማው አስተዲደር ወደ ክርክሩ እንዱገባ ተደርጎ ለጉዲዩ ኃላፉነት ያለበት ወገን እንዱለይ ውሳኔ መስጠቱን ነው። በዚህም መሰረት የስር ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ማስረጃዎችን ሰምቶ አመልካች የዱዛይን ክለሳ ከማድረጉ በፉት የ1ኛ ተጠሪዎች ንብረቶች ተገምተው በአስቸኳይ እንዱፈርሱ መደረጉን፣ ይህንኑ ስራ ሲመሩ የነበሩት የአመልካች መስሪያ ቤት ሰራተኛም የ1ኛ ተጠሪዎች ንብረቶች እንዱፈርሱ ያደረጉ መሆኑን እንዱሁም የሆሳዕና ከተማ አስተዲደር የመንገደ ዱዛይን ክለሳ ስለመኖሩ ያወቀው የ1ኛ ተጠሪዎች ንብረቶች እንዱፈርሱ ከተደረገ በኋላ ስለመሆኑና ከ1ኛ ተጠሪዎች በተመሳሳይ ሁኔታ ንብረታቸው የፈረሰባቸው ሰዎች ካሳ በአመልካች መከፈለ በአመልካች መከላከያ ምስክሮች ጭምር መረጋገጡን ምክንያት በማድረግ አመልካችን ለጉዲዩ ኃላፉ አድርጓል።
በመሰረቱ ማንኛውም ኢትዮጵያ ዜጋ የግል ንብረት ባለቤት መሆን/መሆኗ የተከበረለት/ላት መሆኑን የኢ.ፋ.ዱ.ሪፐብላክ ሕገ መንግስት በአንቀጽ 40(1) ስር በግልፅ ደንግጎ የምናገኘው ጉዲይ ነው። የሕገ መንግስቱ አንቀፅ 40(7) ድንጋጌም ማንም ኢትዮጵያዊ በጉልበቱ ወይም በገንዘቡ በመሬቱ ላይ ለሚገነባው ቋሚ ንብረት ወይም ለሚያደርገው ቋሚ መሻሻል ሙለ መብት እንዲለው ይህ መብት የመሸጥ፣ የመለወጥ፣ የማውረስ፣ የመሬቱ ተጠቃሚነቱ ሲቋረጥ ንብረቱን የማንሳት፣ ባለቤትነቱን የማዛወር ወይም የካሳ ክፍያ የመጠየቅ መብትን እንደሚያካትት የተደነገገ ሲሆን የዚሁ አንቀፅ ንኡስ አንቀጽ ስምንት ደግሞ የግል ንብረት ባለቤትነት መብት እንደተጠበቀ ሁኖ መንግስት ለሕዝብ ጥቅም አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው ተመጣጣኝ ካሳ በቅድሚያ በመክፈል የግል ንብረትን ለመውሰድ ይችላል በሚል ተቀምጧል። ይህንኑ ተከትል የወጣው አዋጅ ቁጥር 455/97 ደግሞ ለህዝብ ጥቅም ትርጉም አስቀምጧል። በዚህም መሰረት የህዝብ ጥቅም ማለት በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ መንገድ ሕዝቦች በመሬት ላይ ያላቸውን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እና የከተማ ልማትን በቀጣይነት ለማጎልበት አግባብ ያለው አካል በመሪ ፔላን ወይም በልማት እቅድ የሕዝብ ጥቅም ብል የሚወስነው ነው በሚል በአንቀፅ 2(5) ስር ይዞ እናገኛለን። በተያዘው ጉዲይ 1ኛ ተጠሪዎች ይዞታቸው አመልካች ለሚያሰራው መንገድ የተወሰደባቸው መሆኑና ንብረቱ የፈረሰውም የመንገደ ዱዛይን ክለሳ ከመደረጉ በፉት በአመልካች ባለሙያ ግፉት መሆኑ በፍሬ ነገር ደረጃ ተረጋግጧል።
አመልካች ይህ ተቀባይነት በላለው ሁኔታ የተረጋገጠ ስለሆነ ሕጋዊ አይደለም በማለት የሚያቀርበው ክርክር በግልፅ የማስረጃ ጉዲይ መሆኑን የምንገነዘበው ሲሆን ፍሬ ነገርን የማጣራትና ማስረጃን የመመዘን ስልጣን ያለው የበታች ፍርድ ቤት የአመልካችን ክርክር በማስረጃ የተደገፈ አለመሆኑን አረጋግጧል። ይህ ሰበር ሰሚ ችልት ደግሞ በኢ.ፋ.ዱ.ሪፐብላክ ሕገ መንግስት አንቀፅ 80(3/ሀ) እና 25/1988 አንቀፅ 10 የተሰጠው ስልጣን መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ሲፈፀም ማረም በመሆኑ አመልካች ያቀረበው ክርክርና ማስረጃ አሳማኝ ነው? ወይስ አይደለም? የሚለውን ጉዲይ የሚመለከተው ሁኖ አላገኘውም። እንዱህ ከሆነ የ1ኛ ተጠሪዎች ይዞታ ቦታ ለሕዝብ ጥቅም ሲባል ሲወሰድና በቦታው ላይ የነበሩት ንብረቶች በአመልካች ባለሙያ ጭምር ግፉት ተደርጎ እንዱነሱና እንዱፈርሱ ከተደረገ በኋላ የዱዛይን ክለሳ ሲደረግ ንብረቶቹ የማይነሱ መሆኑ ተረጋግጧል በሚል ምክንያት ብቻ በመመስረት አመልካች የካሳ ገንዘቡን ለመክፈል ኃላፉነት የለበትም ልባል የሚችልበት ሕጋዊ ምክንያት የላለ ስለመሆኑ አዋጅ ቁጥር 455/97 አንቀፅ 3(1 እና 2) እንዱሁም ከአንቀፅ 4(1) ድንጋጌዎች ከላይ ከተጠቀሱት የሕገ መንግስቱ ድንጋጌዎች ጋር ተደምረው ሲታዩ የአመልካች ክርክር ተቀባይነት የሚያገኝ ሁኖ አልተገኘም። በመሆኑም የስር ፍርድ ቤት በጉዲዩ ላይ የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ነው ለማለት ስላልተቻለ ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የሀድያ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ግንቦት 05 ቀን 2002 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ጸንቷል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.