No summary available.
ግንቦት 16 ቀን 2003 ዓ/ም ዳኞች፡- ሒጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- ፒዝ ፊይንደር ኢንተርናሽናል ኢትዮጰያ - ጠበቃ ኒቆዱሞስ ጌታነ-ቀረቡ ተጠሪ፡-
መዝገብ ተመርምሮ ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል።
ይህ የስበር ጉዲይ የቀረበው አንድ የማይንቀሳቀስ ንብረት በተከራይ እጅ እያለ በእዲ ምክንያት በተለላለፈ ጊዜ ገዥው በባለቤትነቱ ተከራይ ደግሞ በተከራይነቱ የሚኖራቸው መብት ምንድን ነው የሚለውን አስመለክቶ ግራቀኙ ያቀረቡትን ክርክር ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች አንፃር በማየት አስፈላጊውን ትርጉም ለመስጠት ሲባል ነው።
የጉዲዩ መነሻ የአሁን አመልካች በተጠሪዎች ላይ በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የመሰረተው የሁከት ይወገድልኝ ክሰ ነው የአመልካች የክስ ይዘትም ሐጂ ይማም ሙዙይን ከተባለ ግለሰብ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ቀበላ 04 ውስጥ የሚገኝ ቁጥሩ 1212 የሆነ ቤት ሐምል 11 ቀን 2002 ዓ/ም በተጻፈና እስከ መስከረም 20 ቀን 2005 ፀንቶ በሚቆይ የኪራይ ውል ተከራይቶ በመጠቀም ላይ እያለ አከራዩ ግለሰብ ከአሁኑ 1ኛ ተጠሪ የወሰደን የብድር ገንዘብ ለመክፈል ባለመቻላቸው ባንኩ ለአሁኑ 2ኛ ተጠሪ መሸጡን ግልጾ የኪራይ ውለ ከአከራዩ ጋር ባላበቃበት ሁኔታ ባንኩ የተከራይነት መብቱን ለአመልካች ሳይጠብቅ ለ2ኛ ተጠሪ ቤቱን በመሽጥ ተከራዩ አመልካች ቤቱን ለ2ኛ ተጠሪ እንዱያስረክብ የጻፈው ማስጠንቀቂያ የሁከት ተግባር በመሆኑ ሁከቱ ሉወገድ ይገባል በማለት ዲኝነት መጠየቁን የሚያሳይ ነው። የአሁኑ አመልካች ለክሱ በሰጠው መልስም በአዋጅ ቁጥር 97/90 በተሰጠው ስልጣን የተጠቀመው መብት በመሆኑ ሁከት ልባል አይችልም የሚል ሆኖ ክሱ ውድቅ እንዱሆን ዲኝነት የሚጠይቅ ሲሆን የአሁኑ 2ኛ ተጠሪ ተጠሪም በሕጉ አግባብ ተጫርቶ የገዛው ንብረት በመሆኑ የሁከት ተግበር ልባል እንደማይችል ገልፆ ተከራክሯል። ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የፋደራለ መጀመሪያ ደርጃ ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር መርምሮ የተጠሪዎች ተግባር ሁከት ልባል የሚችል አይደለም በማለት የአመልካችን ክስ ውድቅ አደርጎታል በዚህ ውሳኔ አመልካች ባለመስማማት ይግባኝ ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ባያቀርብም ይግባኙ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 337 መሰረት ተሰርዞል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም የበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2931 እና 2933 በአዋጅ ቁጥር 97/90 አንቀጽ 6 እና በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 449 ስር የተመለከቱትን ድንጋጌዎችን ያላገናዘበ በመሆኑ ሉታርም የሚገባው ነው በማለት መከራከሩን የሚያሳይ ነው። አቤቱታው ተመርምሮም የበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1933 ስር ከተመለከተው ድንጋጌ አንፃር ተገቢ መሆን ያለመሆኑን ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ የሰበር ችልት እንዱቀርብ የተደረገ ሲሆን በዚህ መሰረት ለተጠሪዎች ጥሪ ተደርጎላቸው ቀርበው በፁሐፍ መልሳቸውን ሰጥተዋል። 1ኛ ተጠሪ ባቀረበው የፁሐፍ መልስ የፍ/ብሕ/ቁጥር 2931 እና 2933 ድንጋጌዎች በአዋጅ ቁጥር 97/90 የተሻሩና ተፈፃሚነት የላላቸው መሆኑን በመግልፅ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ እንዱፀና ዲኝነት የጠየቀ ሲሆን 2ኛ ተጠሪም በሕጉ አግባብ የገዙት ቤት ስለሆነ ተግባሩ ሁከት ልባል የሚችልበት ሕጋዊ ምክንያት የለም በማለት ተከራክረዋል።
እንግዱህ ግራቀኙ ከሥር የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ጀምሮ እስከዚህ ሰበር ችልት ድረስ በጉዲዩ ላይ ያቀረቡት ክርክር እና ለሰበር ክርክርሩ መነሻ የሆኑት የሥር ፍ/ቤቶች ውሳኔዎች ይዘት ከላይ ባጭሩ የተገለፀው ሲሆን እኛም ይህንኑ ክርክራቸውን ከስር ፍ/ቤቶች ውሳኔ እና ለጉዲዩ ተፈፃሚነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለው መርምረናል ።
እንደመረመርነውም ለዚህ የሰበር ክርክር መነሻ በሆነውና ለፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በቀረበው ክስ ላይ የአሁኑን አመልካች የጠይቁት ዲኝነት በኪራይ ውል በያዝኩት ቤት የኪራይ ውለ ዘመን ከመራዘሙ በፉት ቤቱ በሐራጅ ለ2ኛ ተጠሪ ተሸጦ ርክክብ እንዱደረግ ማስጠንቀቂያ መውጣቱ የሁከት ተግባር በመሆኑ ሉወገድ ይግባል የሚል ነው።
አከራካሪ ሆኖ የተገኘውና የህግ ትርጉም የሚያሻው ነጥብ የአሁኑ 1ኛ ተጠሪ ህንፃውን በጨረታ መሸጡና ቤቱን አመልካች ለቆ እንዱያስረክብ ማስጠንቀቂያ መስጠቱ አመልካች በሻጭና በገዥው ላይ በመቃወሚያነት በማነሳት በፍ/ሕ/ቁ 2931 እና 2933 በተደነገገው መሰረት የኪራይ ውለ ዘመን ሳያበቃ ቤቱን የማስረከብ ግዳታ የለብኝም ድርጊቱ ሁከት ነው ሉወገድ ይገባል በማለት ለመከራክር ይችላል ወይስ አይችልም? የሚለው ነው።
ክሱን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ተከራይ ለአሁን ተጠሪዎች ቤቱን እንዱያስረከብ ማስጠንቀቅያ መስጠቱ ሁከት አይደለም የሚለውን ምክንያት ለውሳኔው መደምደሚያ መሰረት ያደረገው በፍ/ብ/ሕ/ቁ 2899 አና 2932/1/ እና አዋጅ ቁጥር 97/90 ስር የተመለከተው ዓላማ ሲሆን ከላይ የተጠቀሱት የፍትሐብሕር ሕግ ድንጋጌዎች የተፈፃሚነት ወሰን አንድ ኪራይ ውለ ይዞታን በተከራይ እጅ አፅንቶ ለማቆየት አከራዩ በእዲ ምክንያት ንብረቱ የሚሸጥበት ከሆነ ንብረቱን የሚግዛው ሶስተኛው ወገን ንብረቱን የመረከብ ሁኔታ የኪራዩ ውለ ዘመን ከማብቃቱ በፉት ሉጠቀምበት የመቻለን ሁኔታ እስከመገደብ የሚደርስ ነው? የሚለውን ለይቶ ማስቀመጡ ተገቢ መሆኑን ከክርክሩ ይዘት መገንዘብ የምንችለው ጉዲይ ነው።
ከላይ የተጠቀሱትን የፍትሐብሕር ሕግ ደንጋጌዎች በተናጠልም ሆነ እረስ በእርሳቸው አስተሳስረን ስንመለከታቸው አንድ የማይንቀሳቀስ ንብረት የገዛ ሰው በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1184 መሰረት በሽያጭ ውል አማካኝነት የባለቤትነት መብት በተላለፈለት ጊዜ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1204 በህግ በተሰጠው የባለቤትነት መብት ተጠቅሞ ከመሸጡ በፉት በተሸጠው ንብረት ላይ በተከራይነት በይዞታቸው አድርገው የሚገኙት ሰዎችን በማስለቀቅ የኪራይ ውለን ማቋረጥ የማይችል በመሆኑ በፍ/ብሕ/ቁ 1204/2/ እንደተመለከተው ገደብ የጣለበት ድንጋጌዎች መሆናቸውን የሚያሳዩ ሲሆን ይህ የሚሆነው ደግሞ ገዥው ንብረቱን ከአከራይ ገዝቶ የሆነ እንደሆነ ነው።
አንድ በማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ ከአምስት ዓመት በላይ የተደረገ እና ይህም የኪራይ ውል ተመዝግቦ ከተገኘ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2899 እና 2931 ይህ ዓይነት የኪራይ ውል በገዥው ላይ መቃወሚያ ሆኖ ሉያገለግል እንደሚችልና ውለ ባለመፈፀሙ ምክንያት በተከራዩ ላይ ጉዲት ደርሶ ከሆነ ውለ እንዱፈርስና የጉዲት ኪሳራን ለመጠየቅ የሚችል መሆኑን ከሚያሳይ በስተቀር ይህ ከአምት ዓመት በላይ የሆነው የኪራይ ውል ዘመን እስከሚያበቃ ድረስ ተከራይ አከራይ ባለበት እዲ ምክንያት የአከራዩን ንብረት በሕግ አግባብ በመሸጥ እዲን ለመሰብሰብ በሕጉ ስልጣን የተሰጣቸው አካል ጨረታ በማውጣት ንብረቱን ሲሸጡና በማስታወቂያ መሰረት ቤቱን ንብረቱን የገዛው ሰው ከቀድሞው አከራይ ሳይረከብና ማናቸውንም ጥቅም የመጠየቅ መብት የለውም ማለት እንዲልሆነ ሕጎቹ ያሳያለ።
በተመሳሳይ የኪራይ ውለ ምንም እንኳ የተመዘገበ ባይሆንም የተረጋገጠ ቀን መኖሩ ከታወቀ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 2933/1/ መሰረት ገዥው የሽያጭ ውለን ካስመዘገበበት ቀን አንስቶ ተከራዩ እስከ አምስት ዓመት ድረስ መቃወሚያ ሉያደርገው ይችላል መባለ ንብረቱን በእዲ ምክንያት በሕጉ አግባብ የሚሸጥ አካል እና በዚሁ መሰረት ንብረቱን የገዛው ገዥ በዚህ አምስት ዓመት ጊዜ ውስጥ በንብረቱ ላይ እንደ ባለመብት ንብረቱን ሳይረከብ ይቆያል ወይም ማናቸውም ጥቅም ሳያገኝ ይቆያል ማለት አይደለም።
ይልቁንም የኪራይ ውል ባልተመዘገበ ጊዜ በግዥ ባለመብት የሆነው ሰው የኪራይ ውለ ላልተወሰነ ጊዜ እንደተደረገ ይቆጥረዋል ተብል በፍ/ብሕ/ቁ 2933/1/ መደንገጉ የኪራይ ውል የመመዝገብና ያለመመዝገብ ውጤት ገዥው አስቀድሞ ንብረቱን ከመግዛቱ በፉት የተደረገውን የኪራይ ውል ለማቋረጥ እና ላለማቋረጥ ያለዉን መብት የሚያመለክት እንጂ ኪራዩን ከቀድሞው ተከራይ የግድ እንዱቀጥል ወይም ንብረቱን የመረከብ መብቶች እስካለመጠየቅ ሉያደርስ የሚችል መብት ሉያሳጡ የሚችለ ድንጋጌዎች ናቸው ለማለት የሚቻልበት የሕግ አግባብ የለም ።
ስለሆነም እንደአሁኑ ባለው ጉዲይ ተከራይ በኪራይ የያዘውን ንብረት ለአዱሱ ባለንብረት በግዥ ላገኘው ባለሀብት ለማስረከብ ይገደዲል ወይስ አይገደድም? የሚለውን አከራካሪ ነጥብ ንብረቱን ገዥው በመረከቡ የተነሳ ተግባሩ ሁከት ነው ልባል የሚችልበት አግባብ የለም ። የሁከት ተግባር መብት የላለው ሰው ላላ ሕጋዊ መብት ባለው ሰው ይዞታ ላይ የኃይል ተግባር መፈፀም ወይም መስናከል ሆኖ ሲገኝ በሕግ አግባብ እንዱወገድ የሚደረግ ወይም የሚጠይቅ እንጂ በሕግ ስልጣን የተሰጠው አካል ከአከራዩ በእዲነት የሚፍለገውን እንቅስቃሴ ሁለ የሚሸፈን አለመሆኑን ከፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1140 እና 1149 እንዱሁም ከአዋጅ ቁጥር 97/90 ዓላማ እና ይዘት የምንገነዘበው ጉዲይ ነው። አመልካች በአዋጅ ቁጥር 97/90 እንቀጽ 6 ስር የተመለከተውን ድንጋጌ በመጥቅስ የፍ/ብ/ስ/ሕ/ቁጥር 449 ድንጋጌ መሰረት አድርገው ያቀረቡት ክርክር ለጉዲዩ ተፈፃሚነት ያለው ባለመሆኑ የምንቀበለው አይደለም። በዚህ ሁለ ምክንያት የበታች ፍርድ ቤቶች በጉዲዩ ላይ የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ ስላላገኘው የሚከተለው ውሳኔ ተሰጥቷል ።
በጉዲዩ ላይ የተሰጠው ውሳኔ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348/1/ መሰረት ፀንቷል።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተቀባይነት ያለው አይደለም ብለናል።
በዚህ ሰበር ችልት ግራ ቀኙ ያደረጉት ክርክር ላስከተለው ወጭና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻለ ። መዝገቡ ተዝግቷል ወደ ። መዝገብ ቤት ይመለስ ።
No topics extracted.