No summary available.
ሐምል 13 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- የኢትዮጵያ መንገድች ባለሥልጣን አልቀረበም ተጠሪ፡- አቶ ቱላ አብድ በላለበት መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
የአሁኑ ተጠሪ ለሥር የሐረሪ ሕዝብ ክልላዊ መንግስት ከፍተኛ ፍ/ቤት በአሁኑ የሰበር አመልካች / በሥር 1ኛ ተከሣሽ / እና በሥር 2ኛ ተከሣሽ በነበረው ሁናን ሁንዳ የመንገድና የድልድይ ሥራ ድርጅት ላይ ያቀረቡት ክስ ፍሬ ቃለ 1ኛ እና 2ኛ ተከሣሽ በመካከላቸው ባደረጉት የመንገድ ሥራ ውል 2ኛ ተከሣሽ ዲከር በሚባል አካባቢ የሚገኘውንና በገማች ኮሚቴ ተገምቶ ግምት 166,115 የሆነውን የከሣሽ መጋዘን እንዱፈርስ በሰኔ ወር 2ዐዐዐ ዓ/ም ምልክት በማድረግ ግምቱ ሳይከፈል መጋዘኑን በታህሣሥ ወር 2ዐዐ1 ዓ/ም ያፈረሰ ከመሆኑም ላላ ብር 2ዐ,ዐዐዐ የሚያወጣ አንድ ቤት እና ብር 15,ዐዐዐ የሚያወጡ ዛፍች ግምት ብር 15,ዐዐዐ ፣ የአንድ ክፍል ቤት ግምት 2ዐ,ዐዐዐ እና መጋዘኑ እንዱፈርስ ምልክት ከተደረገበት ቀን ጀምሮ ለ17 ወራት ገቢ የተቋረጠ ስለሆነ በቀን ብር 35ዐ ሂሣብ 178,5ዐዐ ሆኖ በድምር ብር 379,615 ተከሣሾች በአንድነትና በነጠላ እንዱከፍለ ይወሰንልኝ የሚል ነው።
የሥር 1ኛ ተከሣሽ የነበረው የአሁኑ አመልካችም በሰጠው መልስ በገማች ኮሚቴ ግምት መሰረት ንብረቱ እንዱነሣ መደረጉን በማመን ከመንገድ ክልል ውጪ ላለት የከሣሽ ንብረቶች ግን ካሣ የመክፈል ግዳታ የለብኝም ፣ በገንዘብ ልክ ተመልክቶ የሚከፈል ካሣ ዘግይቶ በመክፈል ምክንያት ለደረሰ ጉዲት መክፈል ያለበት ህጋዊ ወለድ እንጂ የተቋረጠ ጥቅም አይደለም፣ መጋዘኑ እንዱፈርስ ምልክት ቢደረግም ከሣሽ በመጋዘኑ እንዲይጠቀሙ ስለመከልከላቸው አላስረደም፣ የዕለት ገቢን በሚመለከት ከሣሽ የመንግስት ግብር የተከፈለበትን ደረሰኝ አያይዘው አልቀረቡም፣ ቤቱ ላይ ደረሰ ለተባለውም ጉዲት መጠየቅ የሚችለት የጥገና ወጪውን እንጂ የአዱስ ቤት መሥሪያ ግምት አይደለም በማለት ተከራክሯል።
የሥር 2ኛ ተከሣሽ በበኩለ ባቀረበው መልስ ከሣሽ የካሣ ጥያቄአቸውን ህጉ በሚፈቅደው መሰረት 1ኛ ተከሣሽን ከሚጠይቁ በስተቀር 2ኛ ተከሣሽን ሉጠይቁ አይገባም በማለት ተከራክሯል።
የግራ ቀኙን ክርክር የመረመረው የሥር ከፍተኛ ፍ/ቤትም በሰጠው ፍርድ 1ኛ ተከሣሽ በገማች ኮሚቴ ተገምቶ የቀረበውን የመጋዘን ዋጋ ብር 166,115 እና የመጋዘኑ የዕለት ገቢን በሚመለከት የከሣሽ ምስክሮችን ከሰማ በኋላ መጋዘኑ ከፈረሰበት ከታህሣሥ 2ዐዐ1 ጀምሮ የ17 ወራት ብር 178,5ዐዐ ፣ እንዱሁም በተጨማሪ ክስ ከተጀመረበት እስከ ግንቦት 2ዐዐ2 ያለውን የ7 ወር ብር 73,5ዐዐ ተጨምሮ በድምሩ ብር 418,115 1ኛ ተከሣሽ ለከሣሽ እንዱከፍል ወስኗል። 2ኛ ተከሣሽ ግን የንብረት ካሣን በሚመለከት ሀላፉነት ባይኖረውም በላልች የካሣ ዓይነቶች ሀላፉነት የለብኝም ለማለት የማይችል መሆኑን በውሣኔው አስፍሯል።
ጉዲዩን የአሁኑ የሰበር አመልካች በይግባኝ ለሥር ክልለ ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ያቀረበ ሲሆን ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤትም የመጋዘኑን የዕለት ገቢ በፍ/ህ/ቁ 2102 መሰረት በርትዕ ብር 75 በመወሰን የ24 ወራት ብር 54,ዐዐዐ ይግባኝ ባይ ለመልስ ሰጪው እንዱከፍል አሻሽል በመወሰን በላልች ነጥቦች ላይ ግን የሥር ከፍተኛ ፍ/ቤት ውሣኔን አጽንቷል።
በሥር ፍ/ቤቶች ውሣኔ ላይ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ተፈጽሟል በማለት አመልካች አቤቱታውን ለዚህ ችልት ያቀረበ ሲሆን በዋናነት የጠቀሳቸው የቅሬታ ነጥቦችም የመጋዘኑ ባለቤት ስለመሆናቸው ተጠሪው የባለቤትነት ማረጋገጫ ወረቀት አላቀረቡም። የገማች ኮሚቴ ለመጋዘኑ ካቀረበው የግምት ውጤት ብር 166,155 በተጨማሪ በቀን በብር 75 ሂሣብ የ24 ወራት የተቋረጠ ገቢን ብር 54,ዐዐዐ አመልካች ለተጠሪ ሉከፍል ይገባል ተብል የተወሰነው ህግና ማስረጃን መሰረት ያላደረገ ነው የሚለ ናቸው።
ለተጠሪው መጥሪያ ተልኮላቸው ለመቀበል ፈቃደኛ አለመሆናቸውን አመልካች ለዚህ ችልት በ28/8/2003 ዓ.ም በተጻፈ አቤቱታ ከመግለጹም በላይ ተጠሪው የሚኖሩበት ቀበላ አስተዲደር ጽ/ቤት በቁጥር አ/አ/ቀ/ሰ/10328/03 በቀን 26/8/2003 ዓ.ም በተጻፈ ደብዲቤ ተጠሪው የፍ/ቤቱን መጥሪያ ለመቀበል ፈቃደኛ አለመሆኑን በማረጋገጡ ክርክሩ በላለበት እንዱቀጥል ችልቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል።
በሥር ፍ/ቤት የተደረገው ክርክርና የአመልካች አቤቱታ ከዚህ በላይ ከፍ ተብል የተገለፀ ሲሆን እኛም ለመጋዘኑ ከቀረበው የግምት ገንዘብ በተጨማሪ ከመጋዘኑ የሚገኘው ገቢ ተቋርጧል በሚል የተቋረጠውን ገቢ አመልካች እንዱከፍል መወሰኑ በአግባቡ ነው? ወይስ አይደለም? የሚለውን ጭብጥ ይዘን እንደሚከተለው መርምረናል።
አመልካች ከሥር ፍ/ቤት ጀምሮ ተጠሪው የመጋዘኑ ባለቤት ስለመሆናቸው የሚያረጋግጥ ማስረጃ የላቸውም በማለት እንዱከፍል ከተወሰነበት የተቋረጠ ገቢ ጋር አያይዞ የሚከራከር ቢሆንም የሥር ከፍተኛው ፍ/ቤት በመንገድ ሥራ ምክንያት ንብረቶቻቸው ላይ ጉዲት ከደረሰባቸው ግለሰቦች መካከል አንደ ተጠሪው ስለመሆናቸው የሶፉ ቀበላ አስተዲደር ጽ/ቤት አረጋግጧል በማለት በውሣኔው ካሰፈረው ጋር ሲገናዘብ ተጠሪው የንብረቱ ባለቤት አይደለም በማለት የቀረበው ክርክር ተቀባይነት የለውም።
ወደተያዘው ጭብጥ ስንመለስ አመልካች የመጋዘኑን ግምት ዋጋ እንጂ ተጠሪው አጥተዋል የተባለውን የተቋረጠ ጥቅም መክፈል አይገባኝም በማለት ያቀረበውን የመከራከሪያ ሀሣብ ለህዝብ ጥቅም ሲባል የመሬት ይዞታ የሚለቀቅበትና ለንብረት ካሣ የሚከፈልበትን ሁኔታ ለመወሰን ከወጣው አዋጅ ቁጥር 455/97 አንፃር መመርመር ተገቢነት የሚኖረው ነው። በአዋጅ አንቀጽ 2/1/ ለ ‛ ካሣ “ በተሰጠው ትርጉም መሰረት ካሣ ማለት የመሬት ይዞታውን እንዱለቅ ለሚወሰንበት ባለይዞታ በመሬቱ ላይ ለሰፈረው ንብረት በዓይነት ወይም በገንዘብ ወይም በሁለቱም የሚከፈል ክፍያ ሲሆን የመሬት ይዞታውንም የሚለቅ ባለይዞታም በመሬቱ ላይ ለሚገኘው ንብረት ወይም ማሻሻል ካሣ እንደሚከፈለው በአዋጅ አንቀጽ 7/1/ ተደንግጓል። በይዞታው ላይ ለሚገኘው ንብረት የሚከፈለውም ካሣ ንብረቱን ባለበት ሁኔታ ለመተካት የሚያስችል መሆን ይኖርበታል።
በዚህ በተያዘው ጉዲይ ተጠሪው በመንገድ ሥራ ምክንያት የፈረሰባቸው አንድ መጋዘን ሲሆን ይኸው የመጋዘን ዋጋም በገማች ኮሚቴ ብር 166,115 ተገምቶ ቀርቧል። ይህ የመጋዘኑ ግምትም በአዋጅ አንቀጽ 7/1/2/ በተደነገገው መሰረት የፈረሰውን መጋዘን ለመተካት በሚያስችል መልኩ የቀረበ ነው። ሆኖም ተጠሪው ምናልባት ይኸው የመጋዘኑ ግምት መጋዘኑን ለመተካት የሚያስችል አይደለም የሚለ ከሆነ በአዋጅ አንቀጽ 16 በተደነገገው መሰረት ይግባኝ ማቅረብ ከሚችለ በስተቀር መጋዘኑ ተገምቶ የግምቱን ገንዘብ እንዱወስደ ከተወሰነላቸው በኋላ መጋዘኑ እንዱፈርስ ምልክት ከተደረገበት ጊዜ ጀምሮ የአጡትን ገቢ የሚጠይቁበት የህግ መሰረት የላቸውም። በልላ አነጋገር የመጋዘኑ ግምት እንዱከፈል እስከጠየቁ ድረስ የግምቱን ገንዘብ ከሚወስደ በስቀር ገቢ አጥቻለሁ በማለት የተቋረጠውን ገቢ ሉጠይቁ የሚችለበት ሁኔታ የለም።
የሥር ፍ/ቤቶችም ቢሆኑ ለውሣኔአቸው መሰረት ባደረጉት አዋጅ ቁጥር 455/97 ሆነ አዋጁን ለማስፈፀም በወጣው ደንብ ቁጥር 135/99 የንብረቱ ካሣ ለባለንብረቱ ከሚከፈል ውጪ የተቋረጠ ገቢን ለባለንብረቱ እንዱከፈል በግልጽ ባልተደነገገበት ከተጠቀሱት ህጏች ዓላማ ውጪ ለተጠሪው የተቋረጠ ገቢ እንዱከፈል መፍቀዲቸው ወይም መወሰናቸው ተገቢነት የለውም።
በልላ በኩል የሥር ፍ/ቤቶች ክርክሩን የመሩት በአግባቡ የፍ/ሥ/ሥ/ህ/ ቁጥሮችን ሳይከተለ መሆኑን የክርክሩ መዝገብ ያመለክታል። ይኸውም ተጠሪው አመልካች እንዱከፍል የጠየቁት የካሣ መጠን ብር 379,615 ሲሆን ከፍተኛው ፍ/ቤት ግን የመጀመሪያው ክስ ባልተሻሻለበት አመልካች ለተጠሪ ብር 418,115 እንዱከፍል ወስኗል። ይህም በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 182 /2/ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ተከራካሪዎቹ ወገኖች በዝርዝር ባላቀረቡት ወይም በግልጽ ባላመለከቱት ጉዲይ ላይ ፍርድ ለመስጠት አይችልም በሚል የተደነገገውን የሚቃረን ነው።
ይግባኝ ሰሚው የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤትም ቢሆን ተጠሪው ለሥር ከፍተኛ ፍ/ቤት የ17 ወሩ የተቋረጠ ገቢ እንዱከፈላቸው እንዱወሰን ጠይቀው እያለና በሥር ከፍተኛ ፍ/ቤት ውሣኔ ቅር በመሰኘት መስቀለኛ ይግባኝ ባላቀረቡበት አመልካች ባስከፈተው የይግባኝ መዝገብ በሥር ፍ/ቤት ክርክር ያልተደረገውን የ7 ወራት የተቋረጠ ገቢን በመጨመር በድምሩ የ24 ወራት የተቋረጠ ገቢን አመልካች ለተጠሪ እንዱከፍል በሚል መወሰኑ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 329/1/ በመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ያልተነሣውን ክርክርና ያልቀረበውን አዱስ ነገር ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ለመቀበል አይችልም ተብል በግልጽ የተደነገገውን ያልተከተለ ነው። ለማጠቃለል የሥር ፍ/ቤቶች በመንገድ ሥራ ምክንያት እንዱፈርስ የተባለው የተጠሪ መጋዘን ተገምቶ ግምቱ ከቀረበ በኋላ ይኸው ገንዘብ ለተጠሪው እንዱከፍል መወሰን ሲገባቸው የመጋዘኑን የተቋረጠ ገቢ ጭምር አመልካች ለተጠሪ እንዱከፍል መወሰናቸው መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ያለበት ነው በመሆኑም የሚከተለውን ውሣኔ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ
የሥር የሐረሪ ሕዝብ ክልላዊ መንግስት ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ በቀን 17/10/2002 በዋለው ችልት የሰጠው ውሣኔ እና የክልለ ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ቁ ዐ167ዐ በቀን ዐ5/4/2003 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 348/1/ መሰረት ተሻሽለዋል።
አመልካች ለተጠሪው የመጋዘኑን የተቋረጠ ገቢ እንዱከፍል የተወሰነው የውሣኔ ክፍል ተሽሯል። ስለሆነም የተቋረጠውን መጋዘን ገቢ አመልካች ለተጠሪ አይከፍልም ብለናል።
የዚህን ፍ/ቤት ወጪና ኪሣራ አመልካች የራሱን ይቻል ብለናል። ተጠሪው በዚህ ፍ/ቤት ቀርበው ያልተከራከሩ ስለሆነ የሚታዘዝላቸው ወጪና ኪሣራ የለም።
መዝገቡ የተዘጋ ስለሆነ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.