No summary available.
የሰ/መ/ ግንቦት 1 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ሒጎስ ወልደ አልማው ወላ አሉ መሐመድ ነጋ ደፍሣ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- የመንግስት ቤቶች ኤጀንሲ ነገረ ፈጅ አቶ ደስታ ሉበን - ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ሰለሞን ነጋሽ አልቀረቡም መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ አመልካች የፍደራል የከፍተኛ ፍርድ ቤትና የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት ያቀረቡት አቤቱታ የሚጣራ የህግ ነጥብ ያለው መሆኑ ተገልፆ ለሰበር ችልት የቀረበ ነው።
አመልካች በሰበር አቤቱታ ክርክር መነሻ የሆኑት ጉዲዮች በመጀመሪያ የታዩት በፋደራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ነው። በፋደራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት በመዝገብ ተጠሪ ከሣሽ አመልካች ተከሣሽ በመሆን ተከራክረዋል። ተጠሪ በቀድሞው አጠራር ወረዲ 22 ቀበላ ዐ7 የቤት ቁጥር 117 የሆነውንና ለሆቴል አገልግልት የሚውል የድርጅት ቤት በወር ብር 27,942.95 /ሃያ ሰባት ሺ ዘጠኝ መቶ ዘጠና ሁለት ብር ከዘጠና አምስት ሣንቲም/ ለመክፈል ተስማምተው በፈረሙት የኪራይ ውል መሰረት የአስራ ሁለት ወር /የአንድ ዓመት / የቤት ኪራይ መጠባበቂያ የሁለት ወር ኪራይ ፣ በድምሩ የአስራ አራት ወር ኪራይ ብር 442,288.61 /አራት መቶ አርባ ሁለት ሺ ሁለት መቶ ሰማኒያ ስምንት ብር ከስልሣ አንድ ሣንቲም/ ለተከሣሽ /አመልካች/ ከፍያለሁ ቤቱ የእግድ ትዕዛዝ የነበረበት በመሆኑና የቀድሞው ተከራይ ሁከት ስለፈጠረብኝ ቤቱን ለተከራየሁበት ዓላማ ማዋል አልቻልኩም። ስለሆነም አከራዩ አመልካች የከፈልኩትን ገንዘብ እንዱመለስ ውሣኔ ይሰጥልኝ በማለት ክስ አቅርቧል አመልካች/ ተከሣሽ/ በተከራይነት ቀርቦ የአከራይነት ግዳታውን የተወጣ መሆኑን ገልፆ የኪራይ ውለ የሚፈርስበትና ከሣሽ/ ተጠሪ/ የከፈለውን የቤት ኪራይ የምንመልስበት ምክንያት የለም በማለት ተከራክሯል። የፍደራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ ከመዘነ በኋላ የተጠሪን ክስ ውድቅ አድርጎታል። ተጠሪ በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፋደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበዋል።
የፍደራል የከፍተኛ ፍርድ ቤት የፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ በሰጠው ውሣኔ ቅር በመሰኘት ያቀረበውን የይግባኝ ቅሬታና ክርክር በይግባኝ መዝገብ ሰምቷል።
በፋደራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት አመልካች ከሣሽ በመሆን ተጠሪ ላይ ክስ መስርቶ በመዝገብ የአመልካቾችና የተጠሪን ክርክር በመስማት የፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሚያዚያ 7 ቀን 2001 ዓ.ም ውሣኔ ሰጥቷል። በዚህ መዝገብ አመልካች ተከራዩ /ተጠሪ/ ከሀምላ 17 2000 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ታህሣሥ 30 ቀን 2001 ዓ.ም ቤቱን ይዘው ኪራይ ያልከፈለ በመሆኑ በውለ መሰረት ኪራይ መቀጫና ላልች ክፍያዎች ብር 171,487.63/አንድ መቶ ሰባ አንድ ሺ አራት መቶ ሰማኒያ ሰባት ብር ከስልሣ ሶስት ሣንቲም/ ሉከፍል ይገባል በማለት ክስ አቅርቧል።
ተጠሪ የኪራይ ውለ እንዱፈርስ ክስ አቅርቦ የሥር ፍርድ ቤት በሰጠው ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለከፍተኛው ፍርድ ቤት አቅርቤአለሁ። ተጨማሪ ኪራይ የመክፈል ሀላፉነት የለብኝም የሚል ክርክር አቅርቧል።
የፍደራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ተጠሪ/ ተከሣሽ/ አመልካች/ከሣሽ/ በክሱ የጠየቀውን ብር 171,487.63 እንዱከፍል በማለት ውሣኔ ሰጥቷል። ተጠሪ የፍደራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት በሰጠው ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኙን በይግባኝ መዝገብ ለከፍተኛው ፍርድ ቤት አቅርቧል።
የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተጠሪ በይግባኝ መዝገብ ያቀረበውን ይግባኝ ከይግባኝ መዝገብ ካቀረበው ይግባኝ ጋር በማጣመር መርምሮ አመልካች በቅድሚያ ክፍያነት ከተጠሪ የወሰደውን የቤት ኪራይ ብር 442,288.61/አራት መቶ አርባ ሁለት ሺ ሁለት መቶ ሰማኒያ ስምንት ብር ከስልሣ አንድ ሣንቲም/ ለተጠሪ የመመለስ ግዳታ አለበት። ተጠሪ የቤት ኪራይ ብር 171,487.63/አንድ መቶ ሰባ አንድ ሺ አራት መቶ ሰማኒያ ሰባት ብር ከሥልሳ ሶስት ሣንቲም/ የመክፈል ሀላፉነት የለበትም በማለት የፍደራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት በመዝገብ እና በመዝገብ የሰጣቸውን ውሣኔዎች ሙለ በሙለ በመሻር ውሣኔ ሰጥቷል።
አመልካች የፍደራል የከፍተኛ ፍርድ ቤት በሰጠው ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፋደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አቅርቧል። የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ አፅንቶታል።
አመልካች ታህሥ 6 ቀን 2003 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ ተጠሪ በጨረታ ተወዲድረው የድርጅት ቤት ተከራይተዋል። በኪራይ ውለ መሰረት ቤቱን አስረክበናቸዋል። አመልካች በኪራይ ውለ መሰረት ግዳታውን ተወጥቷል። ተጠሪ በቤቱ የንግድ ፈቃድ ለማውጣት አልቻልኩም በማለቱ ቤቱን ቀበላ በይዞታው አድርጎ ለቆየበት ጊዜ በቅድሚያ ከፍልት የነበረውን የኪራይ ገንዘብ እንድንመልስ የከፍተኛው ፍርድ ቤትና በፋደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የተሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው። ከዚህ በተጨማሪ ተከራዩ ተጠሪ ቤቱን ለአከራዩ አመልካች መልሶ ከማስረከቡ በፉት ሉከፍለው የሚገባውን የኪራይ ገንዘብ የመክፈል ግዳታ የለበትም ተብል የተሰጠው ውሣኔና በአመልካችና በተጠሪ መካከል የተደረገውን የኪራይ ውል ይዘት ያላገናዘብና መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት አመልክቷል። ተጠሪ በበኩለ ጥር 3 ቀን 2003 ዓ.ም በተፃፈ መልስ አመልካች ያከራየኝ የድርጅቱ ቤት ሶስት የእግድ ትዕዛዞች ያለበት በመሆኑ የንግድ ፈቃድ ማውጣት እንደማልችል በሚመለከተው አካል ተነግሮኛል። አመልካች የእግድ ትዕዛዙን እንዱያስነሳልኝ ሁለት ጊዜ ማስጠንቀቂያ ሰጥቸዋለሁ። አመልካች እግደን ያላስነሣ በመሆኑ የኪራይ ውለ ፈርሶ በቅድሚያ የከፈልኩትን ብር 442,288.61 እንዱመልስልኝ የተሰጠው ውሣኔ የህግ ስህተት የለበትም። ከዚህ በተጨማሪ የኪራይ ውለ ሣይታደስ አመልካች ቤቱን ይዘህ ቆይተሀል በማለት የጠየቀውን ብር 171,487.63 የከፍተኛው ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ውድቅ ማድረጋቸው ተገቢና የህግ ስህተት የላለበት በመሆኑ የአመልካችን የሰበር አቤቱታ ውድቅ ያድርግልኝ በማለት ተከራክሯል። አመልካች በፅሐፍ የመልስ መልስ አቅርቧል።
No topics extracted.
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የቀረበው ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም ጉዲዩን መርምረናል። ጉዲዩን እንደመረመርነው የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ተጠሪ በኪራይ ውለ መሰረት የከፈለውን የኪራይ ገንዘብ አመልካች እንዱመልስ መወሰኑ ተገቢ ነው ወይስ አይደለም? የከፍተኛው ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚው ችልት ተጠሪ ያልከፈለውን የቤት ኪራይ ለአመልካች የመክፈል ሀላፉነት ያለበትም በማለት የሰጡት ውሣኔ ተገቢ ነው ወይስ አይደለም የሚለት ጭብጦች መታየት ያለባቸው ሆነው አግኝተናቸዋል።
የማይንቀሣቀሥ ንብረት የኪራይ ውል ከተደረገና ንብረቱ ለተከራይ ከተላለፈ በኋላ በላልች ሶስተኛ ወገኖች የሚቀርቡ የመብት ጥያቄዎችና የሀብት ተግባራት በማስወገድ በኩል አከራዩ ብቻ ሣይሆን በተከራዩም ላይ በህግ የተጣለ ግዳታና ሀላፉነት እንዲለ የፍታብሓር ህግ ቁጥር 2913 እና በፍታብሓር ህግ ቁጥር 2914 ድንጋጌዎች ይዘት በማየት ለመገንዘብ ይቻላል። የተከራየው የማይንቀሣቀስ ንብረት የኔነው ወይም በዚሁ ንብረት ላይ መብት አለኝ የሚል ክርክር በሶስተኛ ወገኖች ለፍርድ ቤት ክርክር ያቀረቡ በሆነ ጊዜ ተከራዩ ለአከራዩ የማሣወቅ ግዳታ እንዲለበትና አከራዩም በክርክሩም ጣልቃ ገብቶ በመከራከር ሀላፉነት ያለበት መሆኑን የፍታብሓር ህግ ቁጥር 2913 ድንጋጌዎች በማገናዘብ ለመረዲት ይቻላል። ከፍታብሓር ህግ ቁጥር 2913 ንዐስ አንቀፅ 1 ድንጋጌ ይዘት መንፈስና ዓላማ ለመገንዘብ የሚቻለው አከራዩ በዋቢነት ቀርቦ ክርክር የማድረግ ሀላፉነት ያለበት የተከራየው ንብረት ባለሀብት ነኝ የሚል ሰው በሚመጣ ጊዜ ወይም በተከራየው የማይንቀሣቀሥ ንብረት ላይ ከህግ ወይም ከውል የመነጨ ህጋዊ ጥበቃ የተሰጠው መብት አለኝ የሚለ ሶስተኛ ወገኖች ክርክር ያነሡ በሚሆንበት ጊዜ መሆኑን ‛የተከራየው የማይንቀሣቀሥ ንብረት የኔ ነው ወይም በዚሁ ንብረት ላይ መብት አለኝ ብል ሶስተኛ ወገን ክርክር ያነሣ እንደሆነ ተከራዩ ለአከራዩ ማሳወቅ አለበት“ በሚል ይዘት ካለው የፍታብሓግ ህግ ቁጥር 2913 ንዐስ አንቀፅ 1 እና እንደዚህ አይነት ሁኔታ ሲያጋጥም ተከራዩ ከክርክሩ ውጭ የሚሆን ስለመሆኑ በፍታብሓር ህግ ቁጥር 2913 ንዐስ አንቀፅ 2 ከተደነገገው ለመገንዘብ እንችላለን።
በያዝነው ጉዲይ የቀድሞው የቤቱ ተከራይ ከላልች ሰዎች ጋር በነበረው ክርክር ምክንያት የፍርድ ቤት የዕግድ ትዕዛዝ ተሰጥቶ የነበረ መሆኑ ተረጋግጧል። የዕግድ ትዕዛዙ የተሰጠው በአመልካች ላይ የቀድሞው ተከራይ በፍርድ ቤት ክስ በማቅረቡ ምክንያት እንዲልሆነ ወይም ቤቱ የእኔ ንብረት ነው የሚል ክርክር በመቅረቡ ምክንያት እንዲልሆነ የፍደራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት አረጋግጧል። የዕግድ ትዕዛዝ በፍርድ ቤት የተሰጠው የቤቱ ባለንብረት ነኝ ወይም በቤቱ ላይ ከውል ወይም ከህግ በመነጨ መብት አለኝ የሚለ ሶስተኛ ወገኖች ክርክር በማቅረባቸው ሣይሆን ከቀድሞው ተከራይ ጋር ክርክር የነበራቸው ሰዎች የቀድሞውን ተከራይ የሆቴል ንግድ ድርጅት በፍርድ ቤት ትዕዛዝ እንዱከበርላቸው ባቀረቡት ማመልከቻ መነሻ መሆኑ ተረጋግጧል።
ተጠሪ በተከራየው ቤት ላይ በፍታብሓር ህግ ቁጥር 2913/1/ መሰረት ከሶስተኛ ወገኖች የቀረበ ክርክር አለመኖሩ በሥር ፍርድ ቤት ተረጋግጧል። በቤቱ ላይ ከውል ወይም ከህግ ያመነጨ መብት የላላቸው ሰዎች ባቀረቡት ማመልከቻ መነሻ የተሰጠን የዕግድ ትዕዛዝ ማስነሳት በፍታብሓር ህግ ቁጥር 2914 መሰረት ቀላል የሆነ ሀብት የማስወገድ ተግባር ነው። በፍታብሓር ህግ ቁጥር 2914 ንዐስ አንቀፅ 1 በተከራየው የማይንቀሣቀስ ንብረት ላይ የባለቤትነት መብት ወይም ላላ መብት አለን በማይለ በሶስተኛ ወገኖች አድራጎት ለሚነሳው ሁከት አከራዩ ዋስትና እንዱሰጥ የማይገደድ መሆኑን በግልፅ ይደነግጋል። ይህን የመሰለውን ሁከት ለማስወገድ ተከራዩ በራሱ ስም ለመከራከር ይቻላል በማለት የፍታብሓር ህግ ቁጥር 2914 ንዐስ አንቀፅ 2 ይደነግጋል። የዕግድ ትዕዛዙ በፍርድ ቤት የተሰጠው አመልካች ባከራየው ቤት ላይ የቀድሞው ተከራይ በነበረው የንግድ ድርጅት ላይ መሆኑ በሥር ፍርድ ቤት ተረጋግጧል።
ስለሆነም ተጠሪ ቤቱን ከአመልካች የተከራየ መሆኑንና በትዕዛዝ የተከበረው የንግድ ድርጅቱ በተከራየው ቤት ላይ የላለ መሆኑን የዕግድ ትዕዛዙን በሰጠው ፍርድ ቤት በማመልከት የዕግድ ትዕዛዙ እንዱነሳ ወይም እንዱሻሻል በፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 158 መሰረት የመጠየቅና ተጠሪ በተከራየው ንብረት ላይ የተከሰቱ ቀላል ችግሮችን የማስወገድ ሀላፉነት የተከራዩ /የተጠሪ/ መሆኑን በፍታብሓር ህግ ቁጥር 2914 ንዐስ አንቀፅ 1 የተደነገገ መሆኑን ሣያገናዝብ የፍደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት የሰጠው ትርጉምና ውሣኔ ተገቢ ሆኖ አላገኘነውም። የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የከፍተኛው ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ ማፅናቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት አለበት በማለት ወስነናል።
ሁለተኛውን ጭብጥ በተመለከተ ተጠሪ ቤቱን ከተከራየበትና ከተረከበበት ከሀምላ 17 ቀን 1999 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ታህሣሥ 30 ቀን 2001 ዓ.ም ቤቱን በይዞታቸው ሥር አድርገው የቆዩ መሆኑ ተረጋግጧል። ተጠሪ ለአመልካች የፅሐፍ ማስጠንቀቂያ ሰጥቻለሁ በማለት የሚከራከር ቢሆንም የፍታብሓር ህግ ቁጥር 2936 ንዐስ አንቀፅ 1 በሚደነግገው መሰረት የኪራይ ውለ ሲያልቅ በኪራይ የያዘውን የማይንቀሣቀስ ንብረት ለአመልካች ያስረከበ መሆኑን ተጠሪ አላስረዲም።
ተጠሪ ቤቱን ይዞ መቆየቱ በፍታብሓር ህግ ቁጥር 2968 ንዐስ አንቀፅ 1 ኪራዩን እንዲደሰ የሚያስቆጥረው ነው ስለሆነም አመልካች ከሀምላ 18 ቀን 2ዐዐዐ እስከ ታህሣሥ 3ዐ ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም ያለውን ቤት ኪራይ ተጠሪ የመክፈል ሀላፉነት አለባቸው። ስለሆነም የመጀመሪያው ጭብጥ ለመወሰን የሰጠውን የተሣሣተ የህግ ትርጉም መሰረት በማድረግ ተጠሪ ውዝፍ ቤት ኪራይ የመክፈል ሀላፉነት የለባቸውም በማለት የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጡት ውሣኔ ተሽሯል።
የፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ እና በመዝገቡ የሰጣቸው ውሣኔዎች ፀንተዋል።
ወጭና ኪሣራን ግራ ቀኙ ለየራሳቸው ይቻለ። መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።