No summary available.
ግንቦት 15 ቀን 2003 ዳኞች፡- ሒጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- ወ/ሮ ሄሪያ መሐመድ ግርግቦ - ጠበቃ አምሣለ ፀሐዬ ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ሸምሱ የሱፍ ጠበቃ በሻዲ ገመቹ - ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ ከመነሻው የስም መመሳሰልን መሰረት በማድረግ በሐሰተኛ ማስረጃ የተከናወነ የማይንቀሳቀስ ንብረት / መኖሪያ ቤት / ሽያጭ ውል ላይ የተደረገን ክርክር የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የአሁኗ አመልካች የፍርድ ባለመብት በመሆን መብታቸውን ከአስከበሩ በሁዋላ የአሁኑ ተጠሪ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 358 መሰረት ባቀረቡት አቤቱታ መነሻ መታየት የጀመረ ነው።
የተጠሪ የውሣኔ መቃወሚያ አቤቱታ ይዘትም፡- በወረዲ 25 ቀበላ ዐ4 ውስጥ የሚገኝ ቁጥር 1413 የሆነውንና አመልካች የቤቱ ባለቤት መሆናቸው በፍርድ ተረጋግጦ ውሣኔ ባገኘው መኖሪያ ቤት ሐምል 25 ቀን 1998 ዓ/ም በውልና ማስረጃ በተደረገ የሽያጭ ውል የባለሃብትነት መብት ማቋቋማቸውንና ካርታው በስማቸው ተሰርቶላቸው ቤቱን ተረክበው ይዘው እንደሚገኙ በቤቱ ላይ አመልካች የፍርድ ባለመብት መሆናቸውንም ግንቦት 03 ቀን 2001 ዓ/ም በቤቱ ላይ ከተለጠፈው ማስታወቂያ ማወቃቸውን ገልፀው ቀድሞ በቤቱ ላይ ሚያዝያ 08 ቀን 1995 ዓ.ም የተሰጠው ውሣኔ እንዱነሳላቸውና ባለሃብትነታቸው እንዱረጋገጥላቸው ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። የአሁኗ አመልካች ለተጠሪ አቤቱታ በሰጡት መልስም ተጠሪ ውሣኔውን ለመቃወም የማይችለ መሆኑን የቤቱ ሕጋዊ ባለቤት መሆናቸው በፍርድ የተረጋገጠና ተጠሪም ከሕግ ውጪ አግኝቼበታለሁ በሚለት ማስረጃ መሰረት ባለሃብት ሉሆኑ እንደማይችለ ቤቱን ከመነሻውም ባለሃብት ያልሆኑት ወ/ሮ ሄሪያ መህመድ ኢብራሂም ለአቶ ሙዱ የሱፍ በመሸጥ አቶ ሙዱ የሱፍ ለተጠሪ መሸጣቸው ተግባሩን ሕጋዊ ሉያደርግ አይችልም በማለትና ቤቱ ለተጠሪ የተላለፈበትን መንገድ ሕገ ወጥ መሆኑን ያሳያለ ያሎቸውን ፍሬ ነገሮችን በማንሳት ተከራክረዋል። የስር ፍርድ ቤትም ተጠሪ ቤቱን በውል እና ማስረጃ ፤ ከአቶ ሙዱ የሱፍ መግዛታቸውና በስማቸውም ካርታ ተሰርቶላቸው ቤቱን ይዘው የሚገኙ መሆኑ ተረጋግጧል፤ ካርታውን የሰጠው አካል እስካልሰረዘው ድረስ ተጠሪን ባለሃብት ነው ብል ለመቁጠር የሚያስችል ነው የሚለ ምክንያቶችን ይዞ ቀድሞ አመልካች የአከራካሪው ቤት ባለቤት ናቸው ሲል የሰጠውን ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥሕ/ቁጥር 360/2/ መሰረት ሰርዞታል። በዚህ ውሣኔ አመልካች ባለመስማማት ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በሁዋላ የስር ፍርድ ቤት ውሣኔ ጸንቷል። አሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሣኔ ለማስቀየር ነው።
የአመልካች ጠበቃ መስከረም 2ዐ ቀን 2003 ዓ.ም በተጻፈ አራት ገጽ የሰበር አቤቱታ በበታች ፍርድ ቤቶች ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ ሕግ ስህተት ተፈፅሟል የሚለበትን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም ባጭሩ፡- ለክርክሩ ምክንያት የሆነው ቤት የአመልካች ስለመሆኑና ለተጠሪ ሽያጭ ፈጸሙ የተባለት ሰው ምንም አይነት መብት የላላቸው መሆኑን፣ ተጠሪ የሽያጭ ውለን የፈፀሙት ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ መሆኑ በተለያዩ ጊዜአት በተሰጡት የፍርድ ቤቶች ውሣኔዎች በግልፅ ተረጋግጦ እያለ ተጠሪ ስመ ሃብቱን በአስተዲደር አካለ በተሰጠው ካርታ አስመዝግበዋል ተብል የቤቱ ሕጋዊ ባለቤት ናቸው ተብል መወሰኑ የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1195 እና 1196 ድንጋጌዎችን ያላገናዘበና ተገቢነት የላለው ስለሆነ ሉታረም ይገባል በማለት ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። አቤቱታው ተመርምሮም አቶ ሙዱ የሱፍ የንብረቱ ባለቤት አይደለም ተብል በተለያዩ መዛግብት ተወስኖ እያለ ለአሁኑ ተጠሪ በህጋዊ መንገድ እንደተሸጠ ተቆጥሮ የቤቱ ባለሃብት ተጠሪ ናቸው ተብል የመወሰኑን አግባብነት ለመመርመር ሲባል ለሰበር ችልቱ እንዱቀርብ የተደረገ ሲሆን ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎላቸው ቀርበው ግራ ቀኙ የጽሐፍ ክርክራቸውን አቅርበዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታ መነሻ ከሆነው ውሣኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩ ለሰበር ችልት ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንጻር በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው በአከራካሪው ቤት ክርክሩ የተጀመረው የአሁኗ ተጠሪ ታህሣሥ 20 ቀን 1987 ዓ/ም በመሰረቱት ክስ መሆኑን አመልካች ክስ የመሰረቱትም፡- 1ኛ/ በአቶ ሙዱ የሡፍ ፤ 2ኛ/ በመቶ አለቃ ሲሳይ መብራቱ ፤ 3ኛ / የሥጋ ሜዲ ተራራ የመኖሪያ ቤቶች የኀብረት ሥራ ማህበር ፣ 4ኛ/ በአቶ ከማል ሀምዛ እና 5ኛ/ በወ/ሮ ሄሪያ መሀመድ ኢብራሂም ላይ መሆኑን ፣ ጉዲዩ የቀረበለት የፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ማስረጃ መርምሮ አቶ ሙዱ የሱፍ ቤቱን የያዙት ቤቱን ለመሸጥ ምንም መብት ከላላቸው ሰው ስለሆነ ሽያጩ የተከናወነውም በሀሰተኛ ሰነድ በመጠቀም ስለሆነ ውለ ሉፈፀም የሚቻል አይደለምና ፈራሽ ነው በማለት ቤቱን ለአሁኗ አመልካች እንዱመልሱ ሲል ሚያዝያ 08 ቀን 1995 ዓ/ም በዋለው ችልት መወሰኑን ፣ በዚህ ውሣኔ ቅር የተሰኙት የስር ተከሣሾችም ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በተናጠል አቅርበው አቶ ሙዱ የሱፍ የተባለት ግለሰብ ያቀረቡት ይግባኝ በመ/ ሐምል ዐ2 ቀን 1995 ዓ/ም በዋለው ችልት ውድቅ የሆነ ሲሆን አቶ ከማል ሀምዛ እና ወ/ሮ ሄሪያ መሀመድ ኢብራሂም ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንድ ላይ አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በሁዋላ የስር ፍርድ ቤት ሚያዝያ ዐ8 ቀን 1995 ዓ/ም የሰጠው ውሣኔ መጋቢት 05 ቀን 1999 ዓ/ም በመ/ ቢሻርም በዚህ ውሣኔ ላይ አሁኗ አመልካች ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በሁዋላ የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሣኔ ተሽሮ ጉዲዩ እንደገና እንዱታይ ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ሰኔ 11 ቀን 2000 ዓ/ም በዋለው ችልት ተመልሶለት ጉዲዩ የተመለሰለት ፍርድ ቤትም በመ/ ጉዲዩን እንደገና አይቶ የፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቀድሞ የሰጠውን ውሣኔ መጋቢት 23 ቀን 2ዐዐ1 ዓ/ም በዋለው ችልት ማጽናቱን በዚህ ውሣኔ አቶ ከማል ሀምዛ እና ወ/ሮ ሄሪያ መሀመድ ኢብራም ቅር በመሰኘት የሰበር አቤቱታቸውን ለሰበር ሰሚ ችልት ቢያቀርቡም በጉዲዩ ላይ መሰረታዊ የሆነ ሕግ ስህተት የለበትም ተብል በመ/ ግንቦት 10 ቀን 2001 ዓ/ም በዋለው ችልት መወሰኑን ነው። ተጠሪ ቤቱ ላይ ሕጋዊ መብት አቋቋሜአለሁ የሚለት ሐምል 25 ቀን 1998 ዓ/ም ከአቶ ሙዱ የሱፍ ጋር የተደረገው የቤት ሽያጭ ውል በቅን ልቦና በውልና ማስረጃ የተደረገና ከውለ በሁዋላ በስሜ ካርታ ተሰርቶ ቤቱን ይዤው የምገኝ ነኘ በሚል ምክንያት እንጂ ቤቱን ሻጭ የሰሩት የግል ሀብታቸው መሆኑን የሚያሳይ ሕጋዊ ማስረጃ አለ አመልካችም የቤቱ ባለሃብት አይደለም በሚል ምክንያት አለመሆኑን ተንገዝበናል።
No topics extracted.
በመሰረቱ አንድ ሰው አንድን ንብረት ለላላ ሰው በሕጋዊ መንገድ ሉያስተላልፍ የሚችለው በንብረቱ ላይ መብት ሲኖረው መሆኑ የሚታወቅ ነው። በልላ አገላለፅ በሕግ ጥበቃ የማይደረግለት ወይም የላለ መብት ወደ ላላ ሰው ሉተላለፍ አይችልም። ይህ ተቀባይነት ያለው የሕግ መርሕ ነው።
የላላ ሰው ንብረት ለመሸጥ፣ ለማስተላለፍ ወይም በዋስትና ለማስያዝ ወይም የተመደበበትን አገልግልት ለመለወጥ ሕጋዊ የሆነ ስልጣን ሉኖር ይገባል።
ወደ ተያዘው ጉዲይ ስንመለስም ለተጠሪ አካራካሪውን ቤት የሸጡት አቶ ሙዱ የሱፍም ሆነ ቤቱን ከመጀመሪያውኑም ለአቶ ሙዱ የሱፍ ሸጡ የተባለት አቶ ከማል ሀምዛ እና ወ/ሮ ሄሪያ መሀመድ ኢብራሂም የአመልካችን ሕጋዊ ስምምነት ወይም ወራሽነት አግኝተው ባይሆንም የቤቱ ባለሃብት መሆናቸውን የሚያሳዩ ሐሰተኛ ሰነድችን ይዘው የነበሩ መሆኑ ፣ አቶ ሙዱ የሱፍ ቤቱን ከገዙ በሁዋላ የቤቱን ስመ- ሀብት ከተገቢው የአስተዲደር አካል ከአገኙ በኋላ ለአሁኑ ተጠሪ ውል ለማዋዋል ስልጣን ባለው አካል ፉት ቀርበው ቤቱን የሸጡላቸው የቤቱ ስመ ሃብትም በተጠሪ ስም የተመዘገበ ስለመሆኑ የተረጋገጠ ጉዲይ ነው። በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1195 ድንጋጌ መሰረት ደግሞ የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለሃብትነትን በማወቅ በአስተዲደር ክፍል የምስክር ወረቀት ሲሰጥ የምስክር ወረቀቱን ያገኘው ሰው የማንቀሳቀስውን ንብረት ባለሃብት ሁኖ ሉገመት እንደሚገባ ተመልክቷል።
ይህን ማስረጃ የያዘ ሰው ደግሞ ሃብቱን በሕጉ አግባብ ከሸጠ ተግባሩ ሕገወጥ የሚባልበት ምክንያት የለውም። አንድ ሰው በሕግ ጥበቃ የተደረገለትን መብት በሕጋዊ መንገድች ለላላ ለማስተላለፍ መብት አለውና። ይሁን እንጂ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1195 ስር የተመለከተው የሕግ ግምት ፍፁም የሆነ ወይም ደምዲሜ ላይ መድረስ የሚያስችል ማስረጃ አይደለም። ግምቱ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1196 ስር የተመለከቱት ሁኔዎች ስለመኖራቸው በማናቸውም ማስረጃ በማረጋገጥ ሉስተባብል የሚችል የሕግ ግምት ነው። በመሆኑም አንድ ሰው በአስተዲደር አካል የተሰጠ ካርታ በመያዙ ብቻ በካርታው የተጠቀሰው የማይንቀሳቀስ ንብረት ሕጋዊ ባለሃብት እንደሆነ ሕጉ ግምት ቢወስድለትም ይህ ግምት ግን ካርታው የተሰጠበትን አግባብ ከደንቡ ከአሰራሩና ከስልጣኑ ውጪ እንዱሁም በማይረጋ የምስክር ወረቀት መሰረት ማስረጃው ተሰጥቶ ከሆነ ይህንኑ በማናቸውም ማስረጃ በማረጋገጥ የሕጉን ሕሉናዊ ግምት ማፍረስ እንደሚቻል የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1196 ድንጋጌ በግልፅ ያሳያል። በስር ፍርድ ቤት 1ኛ ተከሣሽ የነበሩት አቶ ሙዱ የሱፍ ቤቱን የያዙትና ለየአሁኑ ተጠሪ ያስተላለፊት ሕጋዊ ካልሆኑ ሻጮች በመግዛት መሆኑና ለጉዲዩ የቀረቡት ሰነድች ሁለ ሕጋዊ ዋጋ የላላቸው መሆኑ ተረጋግጦ አቶ ሙዱ የሱፍ የቤቱ ባለሃብት ሉሆኑ አይችለም ተብል በተለያዩ የክርክር ደረጃዎች የተወሰነ ከሆነ አቶ ሙዱ የሱፍ ለአሁኑ ተጠሪ የሸጡት ሽያጭ ሕጋዊ የሚሆንበት ሕጋዊ ምክንያት የለም።
ተጠሪ ውለን በውልና ማስረጃ ማድረጋቸው ከመነሻው ሕገወጥ የሆነን ተግባር ሕጋዊ ሉያደርግ የሚችልበት አግባብ የለም። የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ ውል በቅን ልቦ የተደረገ ነው ተብልም በሕግ ጥበቃ የሚደረግበት አግባብ የለም። በማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ ሕጋዊ መብት የላለው ሰው በውለ ለገዥው መድህን ለመሆን ግዳታ ገብቶ ሽያጩን አከናውኖ ሲገኝም ትክክለኛው ባለሃብት ሉጠይቅ የሚችለው ተገቢውን ጥንቃቄ አድርጏ የገዛውን ገዥ ሳይሆን ሻጩን ስለመሆኑ ከፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2882 እስከ 2884 ድረስ ከተመለከቱት ድንጋጌዎች እንዱሁም ከፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 997 ድንጋጌ መንፈስ እና ይዘት የምንገነዘበው ነጥብ ነው። አቶ ሙዱ የሱፍ በቤቱ ላይ መብት የላላቸው መሆኑን ያወቁት ሐምል 02 ቀን 1995 ሲሆን ለተጠሪ ቤቱን በውልና ማስረጃ የሸጡት ግን ሐምል 25 ቀን 1998 ዓ/ም የቤቱ ባለመብት ያለመሆናቸውን እያወቁ ነው። አቶ ሙዱ ለአሁኑ ተጠሪ መድህን ለመሆን ግዳታ የገቡበት ሁኔታም የለም። ስለሆነም ተጠሪ አመልካች ለረዥም ጊዜ በክርክር ላይ በነበሩበት ሁኔታና በፍርድ መብታቸው ተረጋግጦ እያለ የክርክሩ ተሳታፉ የነበሩት ሰዎች በፍርድ መሸነፊቸውን አውቀው በአከናወኑት የሽያጭ ውል ሕጋዊ ገዥ ናቸው ሉባለ የሚችለበት ሕጋዊ ምክንያት የለም። በአጠቃላይ ተጠሪ አከራካሪውን ቤት የገዙት በሕግ ፉት ተቀባይነት ያለውን ማስረጃ ከያዙት ግለሰብ ባለመሆኑ ሽያጩ የተከናወነው ውል ለማዋዋል ስልጣን ባለው አካል ፉት በመሆኑና ካርታውም በስማቸው ተሰርቶ ተሰጥቷል በሚል ምክንያት ብቻ የሽያጭ ውለ ሕጋዊ ነው ልባል የሚችልበት ሕጋዊ ምክንያት የለም። አመልካች በኢ.ፋ.ዱ.ሪፐብላክ ሕገ መንግስት አንቀጽ 40/1/ የተከበረላቸው እና በፍትሒ ብሓር ሕጉ ስለንብረት በሚደነግጉት ድንጋጌዎች ጥበቃ የሚደረግለት የባለሃብትነት መብታቸው ከሕግ አግባብ ውጪ ስለመደረጉ በተረጋገጠዉ የሽያጭ ውል ቀሪ የሚሆንበት ምክንያት ሳይኖር የበታች ፍርድ ቤቶች የአከራካሪው ቤት ሕጋዊ ባለሃብት ተጠሪ ናቸው። በማለት የቀድሞውን ውሣኔ በመሻር የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሁኖ አግኝተናል። በዚህም መሰረት ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ ጥቅምት 10 ቀን 2002 ዓ/ም ተሰጥቶ በፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ሰኔ 29 ቀን 2ዐዐ2 ዓ/ም የጸናው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥሕ/ሕ/ቁጥር 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
በአከራካሪዉ ቤት ተጠሪ ሕጋዊ መብት የላቸውም ፣ ቤቱ የአመልካች ሕጋዊ ንብረት ነው ብለናል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ የራሳቸውን ይቻለ ብለናል።