No summary available.
ግንቦት 15 ቀን 2003 ዓ/ም ዳኞች፡- ሐጏስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- ዛፍኮ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ጠበቃ ዜና ደባሱና አቶ ታምሩ ወንድምአገኘሁ - ቀረቡ ተጠሪ፡- ብሓራዊ መሐንዱሶች ስራ ተቋራጭ ድርጅት - አልቀረቡም መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጡት ውሣኔ መሰታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት ያቀረበውን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው። ጉዲዩ በመጀመሪያ የታየው በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው።
በከፍተኛው ፍርድ ቤት ተጠሪ ከሣሽ አመልካች ተከሣሽ ሆነው የተከራከሩ ሲሆን በልላ በኩል አመልካች የተከሣሽ ከሣሽነት ክስ በማቅረቡ አመልካች የተከሣሽ ከሣሽ ተጠሪ የከሣሽ ተከሣሽ በመሆን ተከራክረዋል። በስር ፍርድ ቤት ግራ ቀኙ የሚከራከሩበት ጉዲይ የግንባታ ስራ ውል አፈጻጸምና ክፍያን የሚመለከት ነው።
አማካሪ መሐንዱስ የመጨረሻ ክፍያ የማጽደቅ ስልጣን ያላለው በመሆኑ የከሣሽ /ተጠሪ/ ክስ ተገቢነት የለውም በማለት ተከራክሯል።
ስለሆነም የከሣሽ ተከሣሽ የግንባታ ስራ ውለን ላዘገየበት 10% ቅጣት ብር 662,679.59 /ስድስት መቶ ስልሣ ሁለት ሺ ስድስት መቶ ሰባ ዘጠኝ ብር ከሀምሣ ዘጠኝ ሣንቲም/ ሉከፍል ይገባዋል። የህንጻ ስራው በመዘግየቱ ህንጻውን በማከራየት አገኘው የነበረውን ገቢ ቀርቶብኛል።
እንዱሁም ለባንክ የተከፈለው ወለድ የከሣሽ ተከሣሽ የመሸፈን ግዳታ አለበት። የከሣሽ ተከሣሽ ስራውን በሚፈለገው ጥራት ደረጃ ባለመስራቱ ጉድለቱን ለማስተካከል የወጣውን ወጭ መሸፈን ይገባዋል። ስለሆነም የከሣሽ ተከሣሽ /ተጠሪ/ ብር 5,823,704.26 /አምስት ሚልዮን ስምንት መቶ ሃያ ሶስት ሺ ሰባት መቶ አራት ብር ከሃያ ስድስት ሣንቲም/ ለተከሣሽ ከሣሽ /ለአመልካች/ እንዱከፍል ይወሰንልኝ በማለት ጠይቀዋል።
ተጠሪ የከሣሽ ተከሣሽ በመሆን የህንጻ ስራው ማጠናቀቂያ ጊዜ የተራዘመው በስምምነት በመሆኑ ከህንጻ ስራው ማጠናቀቂያ ጊዜ ጋር በማያያዝ የተከሣሽ ከሣሽ ያቀረቡት የቅጣት ክፍያና የጉዲት ካሣ ክፍያ የህግ መሰረት የለውም። የከሣሽ ተከሣሽ በሚፈለገው የጥራት ደረጃ ስራውን ሰርቶ አስረክቧል። አለ የተባለውን ጉድለት ለማስተካከል ተገቢውን ጥረት አድርጏ በተከሣሽ ከሣሽ እንቢተኛነት የቀረ በመሆኑ በሀላፉነት ልጠየቅ አይገባም። የተከሣሽ ከሣሽ ጉድለትን ለማስተካከል አወጣሁ የሚለትን ወጭ የሚያስረዲ ማስረጃ አላቀረቡም። ክሣቸው ሙለ በሙለ ውድቅ ይደረግልኝ በማለት ተከራክሯል።
ነሐሴ 29 ቀን 1984 ዓ.ም የተደረገው የግንባታ ስራ ውል ስምምነት ሀምላ 1 ቀን 1985 ዓ.ም በተደረገው ውል ተሻሽሎል። ከዚህ በኋላ የተከሣሽ ከሣሽ /አመልካች/ መስከረም 26 ቀን 1987 ዓ.ም ግንቦት 28 ቀን 1987 ዓ.ም እና ጥር 9 ቀን 1988 ዓ.ም በሰጠው የስራ ለውጥ ትዕዛዝና ተጨማሪ የግንባታ ስራ ትዕዛዝ መሰረት የስራ ውል ማጠናቀቂያ ጊዜ ግራ ቀኙ ቃለጉባኤ በመያዝ የተስማሙ በመሆኑና የከሣሽ ተከሣሽ ስራውን በተሻሻለው የጊዜ ገደብ ውስጥ ስላጠናቀቁ የከሣሽ ተከሣሽ የተከሣሽ ከሣሽ የጠየቀውን መቀጫና የጉዲት ካሣ ክፍያ የመክፈል ሀላፉነት የለበትም። ከሣሽ ለተከሣሽ ስራውን ሰርቶ ካስረከበ በኋላ የእምነበረድ ስራው የረገፈ መሆኑን የተከሣሽ ከሣሽ በተሻለ ማስረጃ አስረድቷል። ስለሆነም ጉድለት ያለበት መሆኑ በማስረጃ የተረጋገጠው የዕምነበረድ ስራ በካሬ ሜትር ብር 238 ታስቦ የ2040.64 ካሬ ሜትር እንደገና ለመስራት የሚያስፈልገው ብር 485,672.32 /አራት መቶ ሰማኒያ አምስት ሺ ስድስት መቶ ሰባ ሁለት ብር ከሰላሳ ሁለት ሣንቲም/ የከሣሽ ተከሣሽ /ተጠሪ/ ለከሣሽ ተከሣሽ /አመልካች/ የመክፈል ሀላፉነት አለበት። ስለሆነም የከሣሽ ተከሣሽ ለመልካም ስራ አፈጻጸምና መያዣ ካስያዘው ገንዘብ ውስጥ የእምነበረድ ስራውን ለማስተካከል የሚያስፈልገው ብር 485,672.32 ቀንሶ የተከሣሽ ከሣሽ ብር 28, 663.68 /ሀያ ስምንት ሺ ስድስት መቶ ስልሣ ሶስት ብር ከስልሣ ስምንት ሣንቲም/ ለከሣሽ ተከሣሽ ሉከፍል ይገባዋል በማለት ውሣኔ ሰጥቷል። አመልካች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ አቅርቧል። ይግባኝ ሰሚው ችልት የአመልካችን ይግባኝ በፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 337 መሰረት ሰርዞታል።
የስር ፍርድ ቤት አማካሪ መሀንዱስ ከስልጣኑ ወጭ ባጸደቀው የመጨረሻ ክፍያ የምስክር ወረቀት መሰረት አመልካች ለተጠሪ ክፍያ እንዱፈጽም መወሰኑ ተገቢ አይደለም። የስር ፍርድ ቤት አመልካች ያቀረበውን የልዩ አዋቂ ምስክርነት ቃል ሣይመዝነው ማለፊ ተገቢነት የለውም።
ስለሆነም ይግባኝ ሰሚው ችልት ከላይ የተዘረዘረው ጉድለት ያለበትን ውሣኔ ማጽናቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት አመልክቷል።
ተጠሪ በበኩለ አመልካች የራሱ ወኪል የሆነው አማካሪ መሀንዱስ ያዘጋጀውን የክፍያ የምስክር ወረቀት በመቃወም ለስራና ከተማ ልማት ሚኒስቴር አቤቱታ አቅርቦ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የአማካሪ መሀንዱሱ ያዘጋጀው የክፍያ የምስክር ወረቀት ጉድለት ያላለበት መሆኑን በመግለጽ ውሣኔ ሰጥቷል። ተጠሪ የስራና ከተማ ልማት ሚኒስቴር በሰጠው ውሣኔ መሰረት እንዱፈጸምለት የአፈጻጸም ክስ አቅርቦ አመልካች ጉዲዩ መወሰን ያለበት በፍርድ ቤት ነው የሚል መቃወሚያ በማቅረቡ የአፈጻጸም መዝገቡ ተዘግቷል። አመልካች ተጠሪ ክስ ሲያቀርብ ጉዲዩ በሽምግልና ላታይ ይገባል በማለት ያቀረቡት ተቃውሞ የህግ መሰረት የለውም። አመልካችና ተጠሪ ውል የተዋዋለበት መሰረታዊ ጉዲይ የማይንቀሣቀስ ህንጻ ስራ ግንባታ ውል ነው።
አመልካች ለጉዲዩ አግባብነት ያለውን ልዩ የህግ ክፍል ሣይሆን ስለ ውልች በጠቅላላው የተደነገጉ ድንጋጌዎችን በመጥቀስ ያቀረቡት የሰበር አቤቱታ ለተያዘው ጉዲይ አግባብነት ያላቸውን የህግ ድንጋጌዎች ያላገናዘበ ነው። አመልካች መጋቢት 24 ቀን 1998 ዓ.ም ጽፍ ባቀረበው መልስ የግንባታው ማጠናቀቂያ ጊዜ የተለወጠ መሆኑን አምኖ መልስ ከሰጠ በኋላ አመልካች የስራ ለውጥ ትዕዛዝና የተጨማሪ ግንባታ ስራ ትዕዛዝ ለመፈጸም የሚያስፈልገው የጊዜ መጠን ላይ በመስማማት ስራው ከተከናወነ በኋላ የግንባታ ስራ ማጠናቀቂያ ጊዜው አልተራዘመም በማለት የሚያቀርበው ክርክር የህግ መሰረት የለውም። የግንባታ ስራ የሚጠናቀቅበትን የጊዜ ገደብ ለመቀየር የሚደረግ ስምምነት በተለየ ፍርም እንዱሆን ህግ አያስገድድም። አመልካች ያቀረበው የሰበር አቤቱታ በስር ፍርድ ቤትና በይግባኝ ሰሚው ችልት አረጋግጠው የወሰኗቸው ፍሬ ጉዲዮች የሚደግፍ እንጂ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመ መሆኑን የማያመላክት በመሆኑ አቤቱታው ውድቅ እንዱሆንልኝ በማለት ሚያዝያ 8 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም በተጻፈ መልስ አቅርቧል አመልካች መስከረም 28 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም የተጻፈ የመልስ መልስ አቅርቧል።
5.1. ከላይ የተያዘውን ጭብጥ ለመወሰን በመጀመሪያ አመልካችና ተጠሪ ለሚከራከሩበት ጉዲይ ገዥነትና ተፈጻሚነት ያለው የህግ ክፍል የትኛው ነው? የሚለውን ነጥብ መወሰን አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል። አመልካች ተጠሪ የግንባታ ስራውን የሚያጠናቀቅበት ጊዜ በህግ የተደነገገውን መሰረት በማድረግ አልተሻሻለም በማለት የሚከራከረው ስለውልች የተደነገገውን የፍታብሓር ህግ ድንጋጌዎች በተለይም የፍታብሓር ህግ ቁጥር 1721፣ የፍታብሓር ህግ ቁጥር 1763 እና የፍታብሓር ህግ ቁጥር 1764 በመጥቀስ በመሆኑ ጉዲዩ ለሰበር የቀረበው የስር ፍርድ ቤትን ውሣኔ ከላይ የተጠቀሱት የህግ ድንጋጌዎችን መሰረት በማድረግ ለመመርመር ተብል ነው። ሆኖም የአመልካች ጠበቆች በስርና በሰበር ጠቅላላ የውል ህግ ድንጋጌዎችን መሰረት በማድረግ ያቀረቡት ክርክርና ጉዲዩ ለሰበር ችልት ሲቀርብ የተያዘውን ጭብጥ ህግ አውጭው የማይንቀሣቀስ ግንባታ ስራ ውልን በተመለከተ ገዥነትና ተፈጻሚነት እንዱኖራቸዉ በማሰብ ከደነገጋቸው ልዩ የህግ ማዕቀፍችና በህግ ስልጣን የተሰጣቸው አስፈጻሚ አካላት ስለማይቀሣቀስ ግንባታ ስራ ውል አውጥተው ተፈጻሚ ካደረጓቸው የአሰራር መመሪያዎች አንጻር መታየት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
የማይንቀሣቀስ ንብረት ለመስራት የሚደረግ ውል ገዥነትና ተፈጻሚነት እንዱኖራቸው በማሰብ ህግ አውጭው ከደነገጋቸው የህግ ማዕቀፍች መካከል አንደኛው በፍታብሓር ህጉ አንቀጽ 3ዐ19 እስከ አንቀጽ 3ዐ4ዐ የተደነገገው የሚገኘው ልዩ የህግ ክፍል ነው። ‛ስለማይንቀሣቀስ ንብረት ስራ ውል“ በሚል ርዕስ ስ ር የተደነገጉት እነዚህ የህግ ድንጋጌዎች የስራ ‛ተቋራጭነቱ ውል የተደረገው የህንጻን ስራ ለመስራት የተሰራውን ለማደስ ወይም አንድ የማይንቀሣቀስ ንብረት ለማደራጀት የሆነ እንደሆነ ከዚህ በታች በተነገሩት ድንጋጌዎች የሚመራ ይሆናል“ በማለት ህግ አውጭው በፍታብሓር ህግ ቁጥር 3ዐ19 ንኡስ አንቀጽ 1 በመደንገግ ለማይንቀሣቀስም ንብረት ግንባታ ስራ ውል ገዥነትና ተፈጻሚነት ያላቸዉ ልዩ የህግ ድንጋጌዎች መሆናቸዉን በግልጽ አውጇል።
ስለሆነም አመልካች ከተጠሪ ጋር ያደረገውን የስራ ውል አስመልክቶ የሚያቀርባቸው ክርክሮች ለጉዲዩ ገዥነትና ተፈጻሚነት ያላቸዉ ልዩ የህግ ድንጋጌዎችን መሰረት በማድረግ ሣይሆን ጠቅላላ የውል ህግ ድንጋጌዎችን መሰረት በማድረግ እንዱታይለትና እንዱወሰንለት የሚያቀርበው ክርክር ተገቢ ሆኖ አላገኘነውም።
የስራ ተቋራጭነት ውል ተፈጽሟል የሚባለው አሰሪውና የስራ ተቋራጩ ስለሚፈጽሙት ስራዎችና ስለ ዋጋው አከፊፈል የተስማሙ በሆነ ጊዜ እንደሆነ የፍታብሓር ህግ ቁጥር 3ዐ2ዐ ንኡስ አንቀጽ 1 የሚደነግግ ሲሆን የስራው ተቋራጭ አሰሪው እያወቀ ስራዎቹን ለመስራት ጀምሮ እንደሆነ ወይም ከዋጋው ላይ አስቀድሞ ገንዘብ ተቀብል እንደሆነ ውል ለመኖሩ በቂ ማረጋገጫ ይሆናል በማለት የፍታብሓር ህግ ቁጥር 3ዐ2ዐ ንኡስ አንቀጽ 2 ይደነግጋል። ከላይ ከተገለጹት የህግ ድንጋጌዎች የምንረዲው የግንባታ ስራ ውል በልዩ ፍርም እንዱደረግ ስለማይንቀሣቀስ ግንባታ ስራ ውል የተደነገጉት ድንጋጌዎች የሚያዙት ፣ መሆኑን ለመረዲት የሚቻል መሆኑን ነው።
ይኸው የአመልካችና ተጠሪ ክርክርና ጉዲዩ ለሰበር ችልት ሲቀርብ የተያዘው ጭበጥ የማይንቀሣቀስ ግንባታ ስራ ውል ልዩ ባህሪና ህግ አውጭው የማይንቀሣቀስ ግንባታ ስራ ውልን በተመለከተ ገዥነትና ተፈጻሚነት እንዱኖራቸዉ በማሰብ የደነገጋቸውን ልዩ የህግ ድንጋጌዎች አግባብነት ያላቸዉ የህግ ማዕቀፍች መሰረት ያደረገ ከመሆኑ አንጻር መታየት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
የማይንቀሣቀስ ንብረት ለመስራት የሚደረግ ውል አስመልክቶ ልዩ ተፈጻሚነትና ገዥነት ያላቸዉ ደንቦች ከፍታብሓር ህግ ቁጥር 3ዐ19 እስከ ፍታብሓር ህግ ቁጥር 3ዐ4ዐ የተደነገጉት ድንጋጌዎች መሆናቸውን ህግ አውጭው ‛ስለማይንቀሣቀስ ንብረት የስራ ውል“ በሚለው ክፍል ‛ የስራ ተቋራጭነቱ ውል የተደረገው የህንጻ ስራን ለመስራት ፣ የተሰራውን ለማደስ ወይም አንድ የማይንቀሣቀስ ንብረት ለማደራጀት የሆነ እንደሆነ ከዚህ በታች በተነገሩት ድንጋጌዎች የሚሰራ ይሆናል“ በማለት በፍታብሓር ህግ ቁጥር 3ዐ19 ንኡስ አንቀጽ 1 በግልጽ ደንግጓል።
ስለማይንቀሣቀስ ግንባታ ስራ ውል አስረጅነት በልዩ ሁኔታ የተደነገገው የፍታብሓር ህግ ቁጥር 3ዐ2ዐ ንኡስ አንቀጽ 1 የስራ ተቋራጭነት ውል አለ የሚባለው ሁለቱ ወገኖች /አሰሪውና የስራ ተቋራጩ /ስለሚፈጸሙት ስራዎችና ስለዋጋው የተስማሙ በሆነ ጊዜ እንደሆነ የሚደነግግ ሲሆን የስራው ተቋራጭ አሰሪው እያወቀ ስራዎቹን ለመስራት ጀምሮ እንደሆነ ወይም ከዋጋው ላይ አስቀድሞ ገንዘብ ተቀብል እንደሆነ ውል ለመኖሩ በቂ ማረጋገጫ እንደሚሆን በፍታብሓር ህግ ቁጥር 3ዐ2ዐ ንኡስ አንቀጽ 2 ይደነግጋል።
የሚሰራውን የግንባታ ስራ አይነትና መጠን እንደዚሁም ስራው ስለሚጠናቀቅበት ጊዜ መጋቢት 4 ቀን 1984 ዓ.ም በጽሁፍ ያደረጉት የስራ ውል ሐምል 1 ቀን 1985 ዓ.ም ያሻሻለት መሆኑን የስር ፍርድ ቤትና በይግባኝ ሰሚው ችልት ተረጋግጧል። አመልካች ከዚህ በኋላ የአመልካች ወኪልና አማካሪ መሀንዱስ ከተጠሪ ጋር በመስማማትና ቃለ ጉባኤ በመያዝ የሰጣቸው የስራ ትዕዛዝ ለውጦችና ተጨማሪ የግንባታ ስራዎች ስለመኖራቸውና በአሰሪው ወኪል ለውጥ የተደረገውን ስራዎችና የስራ ትዕዛዝ የተሰጠባቸው ተጨማሪ የግንባታ ስራዎች ለማከናወን የሚያስፈልገው ተጨማሪ ጊዜ የመጀመሪያው የስራ ውል በተደረገበት ፍርም መሰረት የተደረገ ባለመሆኑ ህጋዊ ውጤት የለውም በማለት የፍታብሓር ህግ ቁጥር 1721ን በመጥቀስ ያቀረቡት ክርክር ከላይ ሙለ ይዘታቸው ከተገለጸው የፍታብሓር ህግ ቁጥር 3ዐ2ዐ ድንጋጌዎች አንጻር መታየት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል። የግንባታ ስራ ውል መጠን ፣ ክፍያና የግንባታ ስራ ውል የሚጠናቀቅበትን ጊዜ ለማሻሻል አሰሪውና የስራ ተቋራጩ የተስማሙ መሆናቸውን ለማስረዲት የመጀመሪያው የስራ ውል በተደረገበት አይነት የተጻፈ ውል ማቅረብ ግዳታ እንዲልሆነ ከፍታብሓር ህግ ቁጥር 3ዐ2ዐ ንኡስ አንቀጽ 2 ድንጋጌ ይዘት ፣ መንፈስና ዓላማ ለመገንዘብ ይቻላል። ከዚህ በተጨማሪ የአሰሪው ተወካይ የሆነው አማካሪ መሀንዱስ በየዕለቱ የሚሰጣቸው የስራ ትዕዛዞች የሚጽፊቸው ማስጠንቀቂያዎችና ከስራ ተቋራጩ ጋር የተስማማባቸው ሰነድች የማይንቀሣቀስ ንብረት ግንባታ ስራ ውል ልዩና ውስብስብ ባህሪ አንጻር የስራ ተቋራጩን መብትና ወይም ግዳታ ለማስረዲት ተቀባይነት ያላቸው ማስረጃዎች እንደሆኑ የስራና ከተማ ልማት ሚኒስቴር ስለግንባታ ስራ አፈጻጸም ባወጣው መመሪያ ተመልክቷል።
ስለሆነም አመልካች በወኪለ አማካኝነት በተለያየ ጊዜ ከስራ ተቋራጭ ከሆነው ተጠሪ ጋር በማስማማትና ቃለ ጉባኤ በመያዝ የሰጣቸው የስራ ለውጥ ትዕዛዞችና ተጨማሪ የግንባታ ስራ ትዕዛዞችና የለወጣቸውን ስራዎችንና ተጨማሪ የግንባታ ስራውን ለማከናወን ተጠሪ የሚያስፈልገውን ጊዜ በሚመለከት ያደረጓቸው ስምምነቶች የመጀመሪያው የግንባታ ስራ ውል በተደረገበት ፍርም መሰረት የተከናወኑ ባለመሆኑ ህጋዊ ውጤት የላቸውም በማለት የፍታብሓር ህግ ቁጥር 1721 በመጥቀስ ያቀረበው ክርክር ተገቢ ሆኖ አላገኘነውም።
5.2. አመልካች የግንባታ ስራውን እንደ እሱ ሆኖ እንዱከታተለለት የመደበው አማካሪ መሀንዱስ በተለያየ ጊዜ ከተጠሪ ጋር በተያዘ ቃለ ጉባኤ የስራ ለውጥ ትዕዛዝ የሰጠና የተጨማሪ ግንባታ ስራ እንዱሰራ የተስማማ መሆኑ ፍሬ ጉዲይ የማጣራትና ማስረጃ የመመዘን ስልጣን ባላቸው ፍርድ ቤቶች ተረጋግጧል። አመልካች በግንባታው ሂደት ለተደረገ የስራ ለውጦችና ተጨማሪ የግንባታ ስራዎች ተጨማሪ ክፍያ ሲፈጽም የቆየ መሆኑ በማስረጃ ተረጋግጧል።
አመልካች የሰጠው የስራ ለውጥና የተጨማሪ ስራ ትዕዛዝ ተጨማሪ ስራ የሚያስከትል በሆነ ጊዜ በስራው መጠን የስራ ተቋራጩ ተጨማሪ ክፍያ የመጠየቅ መብት ያለው መሆኑ በፍታብሓር ህግ ቁጥር 3ዐ32 ንኡስ አንቀጽ 2 በግልጽ ተደንግጓል። አሰሪው የስራ ተቋራጩን ሀላፉነት የሚያከብድ የስራ ለውጥ ትዕዛዝ ወይም ተጨማሪ የግንባታ ስራ በሚያዝበት ጊዜ የተለወጠውን የግንባታ ስራ ወይም ተጨማሪ የግንባታ ስራ ለመስራት ተጨማሪ ክፍያ /ገንዘብ/ ብቻ ሣይሆን ተጨማሪ ጊዜ የማያስፈልገው በመሆኑ አመልካች ለጉዲዩ አግባብነት የላለውን የፍታብሓር ህግ ቁጥር 1763 እና የፍታብሓር ህግ ቁጥት 1764 በመጥቀስ ያቀረበው ክርክር የማይንቀሣቀስ ግንባታ ስራ በአሰሪው ትዕዛዝ ስለማለውጥበት ወይም ተጨማሪ የግንባታ ስራ ትዕዛዝ በሚሰጥበት ወቅት የስራ ተቁራጩ የተቀያየረውንና በተጨማሪነት የተሰጠውን የግንባታ ስራ ለማከናወን አስፈላጊ የሆነ ጊዜና ገንዘብ እንዱሰጠው የመጠየቅ መብት ያለው መሆኑን በፍ.ሕ፤ቁ. 3ዐ32 የተደነገገውን በግንዛቤ ውስጥ የማያስገባ በመሆኑ አልተቀበልነውም። ስለሆነም የስር ፍርድ ቤት አመልካችና ተጠሪ መጋቢት 4 ቀን 1984 ዓ.ም ያደረጉት የህንጻ ግንባታ ስራ ውል ሀምላ 1 ቀን 1985 ዓ.ም ያሻሻለት መሆኑንና ከዚህ ጊዜ በኋላ አመልካች በወኪለ አማካኝነት በሰጠው የስራ ትዕዛዝ ለውጥና የተጨማሪ ግንባታ ስራ ትዕዛዝ ምክንያት በተለያየ ጊዜ በቃለ ጉባኤ በመስማማት የግንባታው ስራ ማጠናቀቂያ ጊዜውን ያሻሻለት በመሆኑ ተጠሪ በውለ መሰረት የሚከፍለው ቅጣትም ሆነ የጉዲት ካሣ የለም በማለት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የላለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
5.3. አመልካች አማካሪ መሀንዱሱ የመጨረሻ ክፍያ የምስክር ወረቀት የማጽደቅ ስልጣን የላለው መሆኑ ግልጽ ሆኖ እያለ የስር ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚው ችልት አማካሪ መሀንዱሱ ከተሰጠው ስልጣን ውጭ ባዘጋጀው የክፍያ የምስክር ወረቀት የተመለከተውን ገንዘብ እንዱከፍል መወሰናቸው መሰረታዊ የህግ ስህተት ነው የሚል ክርክር አቅርበዋል። ጉዲዩን እንደመረመርነው የስር ፍርድ ቤት አመልካች ወኪለ በሆነው አማካሪ መሀንዱሱ ባዘጋጀው የመጨረሻ የክፍያ የምስክር ወረቀት የዘረዘረውን ክፍያ እንዱፈጽም የወሰነው ፣ የአመልካች አማካሪ መሀንዱስ የመጨረሻ ክፍያ በተናጠል የማጽደቅ ስልጣን አለው ከሚለው መደምደሚያ በመድረሱ አይደለም። የስር ፍርድ ቤት የወሰነው አመልካች ከፍያውን አልፈጽምም የሚልበት ህጋዊ ምክንያት ያለው መሆኑን የሚያስረዲ ተአማኒነት ያለው ማስረጃ ያላቀረበ መሆኑንና ተጠሪ ክፍያ የጠየቀበትንና በአመልካች አማካሪ መሀንዱስ የክፍያ የምስክር ወረቀት የተዘረዘረውን ስራ በአግባቡ ያከናወነና ክፍያውም የሚገባው መሆኑን በማስረጃ ያስረዲ መሆኑን በግልጽ በማስፈር እንደሆነ የስር ፍርድ ቤት በውሣኔው በግልጽ አስፍሯል። ከዚህ በተጨማሪ ተጠሪ የግንባታ ስራውን ሙለ በሙለ በማጠናቀቅ ለአመልካች ያስረከበ መሆኑንና ተጠሪ ለአመልካች ሰርቶ ካስረከበው ስራ ውስጥ ጉድለት የተገኘበት የእምነበረድ ስራ ብቻ መሆኑ አመልካች ባቀረበው የከሣሽ ከሣሽነት ክስ በተደረገው ክርክርና በቀረበው ማስረጃ የተረጋገጠ መሆኑን የስር ፍርድ ቤት ፍሬ ጉዲይ የማጣራትና ማስረጃ የመመዘን ስልጣኑን በመጠቀም ውሣኔ ሰጥቶበታል። ተጠሪ የእምነበረድ ስራውን በሚፈለገው የጥራት ደረጃ ባለመስራቱ አመልካች ጉድለቱን ለማስተካከል ሉያወጣ የሚችለውን ወጭ ተጠሪ ለመልካም አፈጻጸምና ለመያዣ ካስያዘው ገንዘብ ቀንሶ እንዱያስቀር የስር ፍርድ ቤት ውሣኔ ሰጥቷል።
ስለሆነም ተጠሪ አማካሪ መሀንዱሱ ባዘጋጀው የመጨረሻ የክፍያ ሰርተፉኬት የገለጸውን የስራ መጠንና ዋጋ ያለው ስራ የሰራ መሆኑን በማስረጃ እንዲስረዲ በማረጋገጥ አመልካች ተጠሪ ለሰራው ስራ ክፍያ እንዱፈጽም የስር ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚው ችልት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የላለበት በመሆኑ የአመልካችን የሰበር አቤቱታ አልተቀበልነውም። በአጠቃላይ ከላይ በዝርዝር ባስቀምጥናቸው ምክንያቶች የአመልካች ክርክር ስለማይንቀሣቀስ ንብረት ግንባታ ስራ ተፈጻሚነት ያላቸውን ልዩ የህግ ድንጋጌዎችና የአሰራር መመሪያዎች መሰረት ያላደረገ ነው። የስር ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ማጽናቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለበትም በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልትና የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጡት ውሣኔ ጸንቷል።
በዚህ ፍርድ ቤት የካቲት 1ዐ ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም የተሰጠው የዕግድ ትዕዛዝ ተነስቷል።
በዚህ ፍርድ ቤት የወጡትን ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ ለየራሣቸው ይቻለ።
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.