No summary available.
ህዲር 1 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሐጎስ ወልደ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- አቶ ጋሻው በጎሰው ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ አለበል መከተ አልቀረበም።
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው በአማራ ክልል የላይ ጋይንት ወረዲ ፍርድ ቤት የደቡብ ጎንደር ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት የሰጡት ወሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት አመልካች ስለጠየቁ ነው።
የክርክሩ መነሻ የቦታና የባህር ዛፍ አትክልት ይዞታን የሚመለከት ነው። በሥር ከሳሽ ሆኖ የቀረበው የአሁን ተጠሪ ሲሆን የከሰሰውም አቶ ሲሳይ በጎሰውንና አቶ ጋሻው በጎ ሰውን ነው። ተጠሪ ከሥር አንደኛ ተከሳሽ የነበረው አቶ ሲሳይ በጎ ሰው ብር 1900 (አንድ ሺ ዘጠኝ መቶ ብር) ተበድሮ ቆይቶ ገንዘቡን ለመክፈል ባለመቻለ ቦታውን ከእነ አትክልቱ በብር 1500 (አንድ ሺ አምስት መቶ ብር) ግምት አስረክቦኛል። ይህ ቦታ ለመንገድ ሲቀየስ ሁለተኛው ተከሳሽ (የአሁን አመልካች) ቦታውና ባህር ዛፍ የእኔ ነው በማለት 4‚400 የባህርዛፍ ግምት እንዲይከፈለኝ ቦታው የእኔ ነው በማለት በቀበላ አስተዲዲር በማመልከት ገንዘቡ እንዱያዝ አድርጓል። ስለሆነም የባህርዛፈን አላባ እንዲልቀበል ቦታውም የእኛ ነው በማለት ሁከት የፈጠሩብኝ ስለሆነ በይዞታዬ ላይ የፈጠሩት ሁከት እንዱወገድልኝ በማለት ክስ አቅርቧል። ተከሳሾች በበኩላቸው ተከሳሽ ብር 1900 ለሲሳይ በጎ ሰው ያበደረ መሆኑን በክሱ ገልጿል። ሆኖም የብድር ገንዘቡን ከሰጠኝ አስር ዓመት ያለፈ በመሆኑ ሉጠይቀኝ አይችልም የብድር ውለ በይርጋ ይታገዲል። በወቅቱ የዕዲ መክፈያ እንዱሆን የተዋዋልኩት ቦታና ባህርዛፍ አትክልት የተበዲሪው የአቶ ሲሳይ በጎ ሰው ሣይሆን የወንድሜ የጋሻው በጎ ሰው በመሆኑ ውለ ህጋዊ ውጤት የለውም በማለት በሥር አንደኛ ተከሳሽ የነበረው ሲሳይ በጎ ሰው መልስ ሰጥቷል። የአሁኑ አመልካች በበኩለ በሥር ሁለተኛ ተከሳሽ ሆኖ ቀርቦ ቦታውም ሆነ ይዞታው የእኔ እንጅ የአንደኛ ተከሳሽ የሲሳይ በጎ ሰው አይደለም። ወንድሜ በተዋዋለውና እኔ ባልተስማማሁበት ሁኔታ እኔ የይዞታ መሬቴንና የባህርዛፍ አትክልቴን ለከሳሽ የምለቅበት ምክንያት የለም። የሥር ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ማስረጃ ሰምቷል። የቀረቡት ምስክሮችም ቦታውና ባህርዛፍ አትክልቱ የጋሻው በጎሰው ነው ነገር ግን አንደኛ ተከሳሽ ሲሳይ በጎሰው ለአሁን ተጠሪ ለሥር ከሳሽ አለበል መከተ ሸጦለታል በማለት የመሰከሩ መሆናቸውን በውሣኔው ገልጿል። የወረዲው ፍርድ ቤት አመልካች በተጠሪ ላይ ሁከት ፈጥሮአል በማለት ውሣኔ ሰጥቷል። አመልካች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለከፍተኛው ፍርድ ቤት አቅረቦ የከፍተኛው ፍርድ ቤት ይግባኙን ሰርዞታል።
አመልካች የሰበር አቤቱታ ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት አቅርቦ የሰበር ችልቱ የበታች ፍርድ ቤቶች ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለበትም በማለት ትእዛዝ ሰጥቷል።
አመልካች መስከረም 13 ቀን 2001 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ የባህር ዛፍ አትክልቱና ቦታው የእኔ መሆኑ በሥር ፍርድ ቤት ካረጋገጠ በኋላ የእኔን አትክልት ግምት ወንድሜ ሲሳይ በጎሰው በተዋዋለው ውልና በተበደረው ገንዘብ መነሻ የአሁን ተጠሪ እንደወሰደ የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት አመልክቷል። ተጠሪ በበኩላቸው ይዞታው የአቶ ሲሳይ በጎ ሰው ነበር። በብር 1900 /አንድ ሺ ዘጠኝ መቶ ብር/ ተበድሮ ባለመክፈለ ቦታውንና አትክልቱን ተረክቤዋለሁ። የይዞታ የምስክር ወረቀትም አውጥቼበታለሁ ።
አሁን ግን የባህርዛፍ ግምት ለእኔ ነው የሚገባው በማለት አመልካች ሁከት የፈጠረ በመሆኑ የተፈጠረው ሁከት እንዱወገድ ክስ አቅርቤ የተወሰነው በአግባቡ ስለሆነ የበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለበትም የሚል መልስ አቅርቧል። አመልካች በበኩለ በሥር ፍርድ ቤት ተጠሪ ያቀረባቸው ምስክሮች ይዞታው የማን እንደሆነ አናውቅም ገዝቶታል ሲባል ሰምተናል በማለት የመሰከሩ ሲሆን የእኔ ምስክሮች የእኔ መሆኑን አስረድተዋል። የላይ ጋይንት ወረዲ መሬት አስተዲደር ይዞታው የእኔ መሆኑን በማረጋገጥ ጽፎል ስለሆነም ይዞታው የእኔ እንጅ የሲሳይ በጎ ሰው ባለመሆኑ ተጠሪ ቦታውን በዕዲ መክፈያነት በውል ተቀብዬ ይዥዋለሁ በማለት የሚያቀርበው ክርክር የህግ ድጋፍ ያለው ሆኖ አላኘነውም።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የቀረበው ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም መዝገቡን መርምረናል። መዝገቡን እንደመረመርነው የበታች ፍርድ ቤቶች አመልካች በተጠሪ ይዞታ ላይ ሁከት የፈጠረ ስለሆነ ሁከቱ ይወገድ በማለት የሰጡት ውሣኔ በአግባቡ ነው ወይስ አይደለም የሚለውን ጭብጥ በመያዝ ጉዲዩን መርምረናል።
ጉዲዩን እንደመረመርነው የወረዲው ፍርድ ቤት በአንድ በኩል የተጠሪ ጥያቄ የቦታ ባለቤትነት ጥያቄ ባለመሆኑ የቦታ ውለን ማጣራቱ አስፈላጊ አይደለም በማለት በውሣኔው የገለፀ ሲሆን በልላ በኩል ቦታው የጋሻው በጎሰው ነው ነገር ግን ሲሳይ በጎሰው ለተጠሪ ለመከተ ደምሴ በገንዘብ ሲሸጠው እናውቃለን በማለት የመሰከሩ መሆኑን በውሳኔው ገልፆል፡ አመልካች በተጠሪ ይዞታ ላይ ሁከት ፈጥረዋል ወይም አልፈጠሩም የሚለውን ጭብጥ ለመወሰን በመጀመያ ተጠሪ የቦታው ህጋዊ ባለይዞታ ነው ወይስ አይደለም? የሚለውን ነጥብ ማጣራት አስፈላጊ ነው።
ተጠሪ ቦታውን አገኘሁ የሚለው የአመልካች ወንድም አቶ ሲሳይ በጎሰው ብር 1900 /አንድ ሺ ዘጠኝ መቶ ብር/ ተበድሮኝ ይህንን ገንዘብ ባለመክፈለ ቦታውንና የባህርዛፍ አትክልቱን በብር 1500 /አንድ ሺ አምስት መቶ ብር/ ተገምቶ በእዲ መክፈያነት በውል አግኝቸዋለሁ በማለት የሚከራከር ሲሆን አመልካች ከሲሳይ በጎ ሰው ጋር የእዲ መክፈያ እንዱሆን የተስማማሁበት ቦታና አትክልት የእኔ ይዞታ በመሆኑ ከውል የመነጨ መብት በቦታውና በባህርዛፍ ላይ ሉኖርህ አይችልም በማለት የሚከራከር መሆኑን ነው።
ተጠሪ ቦታውን አገኘሁ የሚለው ከማን እንደሆነ በራሱ አከራካሪ ቢሆንም ተጠሪ የቦታውን ባለይዞታ ሆንኩበት የሚለው ውል በቦታው ላይ ባለይዞታ ሉያደርገው የሚችለው ነው ወይስ አይደለም? የሚለው መታየት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል። ተጠሪ ቦታውን የፍታብሓር እዲ መክፈያነት ተረክቤአለሁ የሚለው ክርክር በህገ መንግሥቱ አንቀጽ 40 ንዐስ አንቀጽ 3 መሬት የማይሸጥ የማይለወጥ የኢትዮጵያ የብሓር ብሓረሰቦችና ህዝቦች ሀብት ነው ተብል ከተደነገገው ድንጋጌ አንፃር ስናየው መሬትን ለዕዲ በመክፈያነት በውል በማስተላለፍ መሸጥና መለወጥ የማይቻልና በዚህ አይነት መንገድ ህጋዊ የመሬት ባለይዞታ መሆን የማይቻል በመሆኑ ተጠሪ የመሬቱ ባለይዞታ ሆኘበታለሁ የሚለው ውል በፍታብሓር ሕግ ቁጥር 1678 ንዐስ አንቀጽ 2 መሰረት ህጋዊ በሆነ ጉዲይ ላይ የተደረገ ባለመሆኑ ውለ ህጋዊ ውጤት የላለውና መብት የማያስገኝ ነው።
ከዚህ በተጨማሪ የሥር ፍርድ ቤት ያቀረቡት ምስክሮች ይዞታው የአመልካች መሆኑን ነገር ግን ወንድሙ ለተጠሪ አባት የሸጠ መሆኑን እናውቃለን በማለት የመሰከሩ መሆኑን በውሣኔው ገልጿል። ይዞታውና የባህርዛፍ አትክልቱ የአመልካች መሆኑ ከተረጋገጠ አመልካች ወንድሙ ሲሳይ በጎ ሰው ባደረገው ውል ሉገደድ የሚችለው አመልካች እሱን ወክል ውል እንዱዋዋል የሰጠው የውክልና ሥልጣን ካለና ወንድሙ ሲሳይ በጎ ሰው በዚህ በውክልና ሥልጣኑ መሰረት ውል የተዋዋለ መሆኑ ሲረጋገጥ ብቻ ነው። በያዝነው ጉዲይ ተጠሪ አቶ ሲሳይ በጎ ሰው ውለን የተዋዋለው ከአመልካች ባገኘው የውክልና ሥልጣን መሆኑን አላስረዲም። ስለዚህ አመልካች ባልተስማማበትና በቦታው ላይ ያለው የባህር ዛፍ አትክልት ለወንድሙ ዕዲ መክፈያ እንዱሆን ስምምነቱን ባልገለፀበት ሁኔታ ወንድሙ በተዋዋለው ውል መነሻ ቦታውንና አትክልቱን ለተጠሪ እንድለቅና በተጠሪ ላይ ሁከት እንዲይፈጥር ተብል የተሰጠው ውሳኔ ህጋዊ መሰረት ያለው ሆኖ አላገኘነውም።
በአጠቃላይ ተጠሪ በቦታዬና በንብረቴ ላይ ሁከት ተፈጥሮብኛል ብል ክስ ለማቅረብ በመጀመሪያ የቦታውና የንብረቱ ህጋዊ ባለይዞታ መሆኑን ማስረዲት ይጠበቅበታል። በሥር ፍርድ ቤት ያቀረቡት ምስክሮች ይዞታው የአመልካች መሆኑን እንደመሰከሩና ቦታውን ከነባህርዛፈ ለተጠሪ በሥር አንደኛ ተከሳሽ የነበረው ሲሳይ በጎሰው በገንዘብ ሸጦለታል የሚል የምስክረነት ቃል እንዲስመዘገቡ የወረዲው ፍርድ ቤት በውሳኔው ገልፆታል። ይኸም ተጠሪ በህገ መንግሥቱ አንቀጽ 40 ንዐስ አንቀጽ 3 የተደነገገውን የሚጥስ ተግባር በመፈፀምና የመሬቱ ህጋዊ ባለይዞታ ካልሆነው አቶ ሲሳይ በጎሰው መሬቱን በዕዲ መክፈያነት በውል ይዣለሁ በማለት የሚከራከሩ መሆኑንና የቦታው ህጋዊ ባለይዞታ የማያደርጋቸው መሆኑን የሚያረጋግጥ ሆኖ እያለ አመልካች በተጠሪ ህጋዊ ይዞታ ላይ ሁከት ፈጥሯል በማለት የተሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ወስነናል።
የአማራ ክልል የላይ ጋይንት ወረዲ ፍርድ ቤት የደቡብ ጏንደር ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት የሰጡት ውሣኔ ተሽሯል።
ተጠሪ በዚህ ክርክር ተሣታፉ ካልሆነውና በሥር አንደኛ ተከሳሽ በነበረው አቶ ሲሳይ በጎ ሰው በብድር ሰጥቸዋለሁ የሚለውን ገንዘብ እንድከፍለው ክስ አቅርቦ ከመጠየቅ ይህ ውሣኔ አያግደውም ብለናል።
አመልካች የቦታውና የአትክልቱ ሕጋዊ ባለይዞታ በመሆኑ በተጠሪ ላይ የፈጠረው ሁከት የለም በማለት ወስነናል።
በዚህ ፍርድ ቤት የወጣውን ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ ለየራሳቸው ይቻለ።
ፀ/መ
ታህሣሥ 27 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፣ ሐጏስ ወልደ ተሻገር ገ/ስላሴ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድአመልካች - የኢትዩጵያ መንገድች ባለስልጣን - መላኩ ነገሰ ቀረበ ተጠሪ- ጃዲ ብሩ ከጠበቃ ደጀኔ ፊይሳ ጋር ቀረበ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ በመንገድ ሥራ ምክንያት ለተወሰደ ንብረት ካሣ ይከፈል ዘንድ በመጠየቅ የቀረበውን ክስ የሚመለከት ነው። ክርክሩ በምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ሲጀመር ከሣሽ የነበረው ተጠሪ ነው። በአመልካች እና በሞጆ ከተማ አስተዲደር ላይ ክስ የመሰረተው በሞጆ ከተማ ቀበላ 01 ውስጥ በ400 ካ.ሜትር ቦታ ላይ ያለኝን የንግድ ቤት በሚሰራው መንገድ ምክንያት እንደሚነሳ ነግረውኝ የንብረቱን ግምት እንድወሰድ ያዘዙልኝ ቢሆንም ግምቱ ትክክል ባለመሆኑ አልወሰድኩም። በልላ በኩል ደግሞ ንብረቱን በግል ባለሙያ አስገምቼ ብር 119‚367 ዋጋ እንዲለው አረጋግጫለሁ። በመሆኑም ንብረቱ በሶስተኛ ወገን ባለሙያ እንዱገምትልኝ እና በዚሁ መሰረት ካሣው እንዱከፈል ይወሰንልኝ በማለት ነው። ከዚሁ በተጨማሪም በተወሰደው ቦታ ምትክ ላላ ቦታ ይሰጠኝ የሚል ጥያቄም አንስቶ እንደነበር ከመዝገቡ ተመልክተናል። ፍ/ቤቱ የሁለንም ወገኖች ክርክር ከሰማ በኃላ ንብረቱን እንደገና አስገምቶ ተገኘ ባለው ውጤት መሰረት ካሣ እንዱከፈል ወስኖአል። በዚህ ውሣኔ ላይ ይግባኝ የቀረበለት የኦሮሚያ ጠ/ፍ/ቤትም የከፍተኛው ፍ/ቤት የሰጠው ውሣኔ ጉድለት የለበትም በማለት ይግባኙን ሰርዞአል። የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚህ ላይ ነው።
በበኩላችንም አመልካች ሰኔ 15 ቀን 2002 ዓ.ም በጻፈው ማመልከቻ ያቀረበውን አቤቱታ መሰረት በማድረግ ተጠሪን አስቀርበን ክርክሩን ሰምተናል። ክርክሩ የተሰማው የካሣው ክፍያ ጥያቄ በቀጥታ ለመደበኛ ፍ/ቤት የሚቀርብበት አግባብ አለ ወይ? በሚለው ጭብጥ ላይ ነው። በመሆኑም ጭብጡን በማስመልከት ግራቀኝ ወገኖች ያሰሙትን ክርክር አቤቱታ ከቀረበበት ውሣኔ እና ከሕጉ ጋር አገናዝበን መርምረናል።
ከላይ ባጭሩ እንዲመለከትነው አመልካች ለተጠሪ የሚከፈለውን ካሣ በማስገመት ገንዘቡን እንዱወስድ አስቀድሞ አስታውቆታል። ተጠሪ ደግሞ የካሣው መጠን አንሶአል የሚል እምነት በመያዙ በቀጥታ ለፍ/ቤት ክሱን አቅርቦአል። አከራካሪ ሆኖ የቀረበው የሕግ ጥያቄ የተነሳውም እዚህ ላይ ነው። ተጠሪ የካሣው መጠን አንሶአል የሚል እምነት ወይም ተቃውሞ ካለው ይህን ተቃውሞውን ማቅረብ የነበረበት በምን አግባብ ነው የሚለው ጭብጥ ነው በሰበር ችልቱ ውሣኔ የሚያሻው ሆኖ የተገኘው። በዚህ ረገድ አመልካች ግልጽ የሆነ የመከራከሪያ ነጥብ አቅርቦአል።
ለጉዲዩ አወሳሰን አግባብ ያለው ሕግ ለሕዝብ ጥቅም ሲባል የመሬት ይዞታ የሚለቀቅበትንና ለንብረት ካሣ የሚከፈልበትን ሁኔታ ለመወሰን የወጣው አዋጅ ቁ 455/97 ነው። በዚህ አዋጅ አንቀጽ 11 ካሣን በሚመለከት ስለሚቀርብ አቤቱታ እና ይግባኝ ተደንግጓአል። የከተማ መሬት ይዞታውን እንዱለቅ የሚደረግ ባለይዞታ በተወሰነለት የካሣ መጠን ላይ ካልተስማማ ወይም በካሣው መጠን ላይ ቅሬታ ካለው አቤቱታውን ማቅረብ ያለበት በከተማው አስተዲደር ለተቋቋመው የመሬት ነክ አቤቱታ ሰሚ አስተዲደራዊ አካል ስለመሆኑም በዚሁ አንቀጽ 11/2/ ተመልክቶአል። የካሣውን መጠን በሚመለከት ለመደበኛ ፍ/ቤት ክርክር ወይም አቤቱታ ማቅረብ የሚቻለው በንዐስ አንቀጽ /4/ በተደነገገው መሰረት በይግባኝ ብቻ ነው።
ወደያዝነው ጉዲይ ስንመለስ ጉዲዩ የተነሳው በከተማ ክልል ውስጥ እንደመሆኑ ይህን በሚመለከት በተቀመጠው ድንጋጌ መሰረት ክርክሩ መታየት እንዲለበት የሚያከራክር አይደለም።
ክርክሩን በመጀመሪያ ደረጃ የሰማው የምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤትም ጉዲዩ መታየት ያለበት በአዋጁ መሰረት እንደሆነ መገንዘቡን ከውሣኔው ተመልክተናል። ይህን እየተገነዘበም ነው አቤቱታ የቀረበበትን ውሣኔ ላሰጥ የቻለው በመሰረቱ ፍ/ቤቶች ሉመሩ የሚገባቸው በሕጉ ስለመሆኑ የሚያከራክር አይደለም። ሕጉን መሰረት ያላደረገ ውሣኔ እንዱሰጡ አይጠበቅም። በተያዘው ጉዲይ እንደምናየው ግን ሕጉን በመተው ነው ውሣኔ የተሰጠው። በመሆኑም አቤቱታ የቀረበበት ውሣኔ በሕጉ አተገባበር ረገድ መሰረታዊ ስህተት ያለበት ነው ለማለት ችለናል።
ው ሣ ኔ
የምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ. መጋቢት 15 ቀን 2002 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ እንዱሁም የኦሮሚያ ጠ/ፍ/ቤት በመ. ሰኔ 4 ቀን 2002 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ 348/1/ መሰረት ተሽረዋል።
በካሣው መጠን ላይ በቀጥታ ለመደበኛ ፍ/ቤት ክስ ማቅረብ በሕጉ አልተፈቀደም ብለናል።
ግራቀኝ ወገኖች ወጪና ኪሣራ ይቻቻለ።
No topics extracted.