No summary available.
ህዲር 28 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጏስ ወልደ ተሻገር ገ/ስላሴ ብርሀኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ሻለቃ አሰፊ አየለ ደምሴ ጠበቃ አቶ ግርማ አይታገድ ተጠሪ፡- ፍቃደ ሙለኔታ - አልቀረበም መዝገቡ የተቀጠረው ለምርመራ ሲሆን መርምረን ፍርድ ሰጥተናል።
ይህ የሰበር ጉዲይ አንድ ተለይቶ የታወቀ ንብረት ተወስድብኛል ይመለስልኝ በሚል በሁከት ይወገድልኝ ስም ክስ በቀረበ ጊዜ ለዚህ ዓይነቱ ክስ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1149(2) የተመለከተው የይርጋ ጊዜ ተፈፃሚነት አለው ወይስ የለውም? የሚለውን አከራካሪ ነጥብ ለይቶ ለመወሰን ልንከተል የሚገባውን አተረጓጏም የሚመለከት ነው።
ለዚህ የሰበር ጉዲይ መነሻ የሆነው የአሁን አመልካች በተጠሪ ላይ በአዱስ አበባ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሰኔ 22 ቀን 1991 ዓ.ም ያቀረቡት ክስ ሲሆን ይዘቱም ባጭሩ በወረዲ 17 ቀበላ 20 ክልል ውስጥ በካርታ የተሰጠኝን ስፊቱ 250 ካ.ሜትር የሆነውን ቦታ ከእነ ጅምር ቤቱ በመያዝ አለቅም ስላለ ለቆ እንዱያስረክበኝ የሚል ነው።
የአሁን ተጠሪም በተከሳሽነቱ ክርክር ያስነሳውን ንብረት ከያዝኩበት ጊዜ ጀምሮ ከሳሽ ቦታው ተወሰደብኝ በማለት ክስ እስካቀረቡበት ድረስ ያለው ጊዜ ሲሰላ 13 ዓመት ያለፈው ስለሆነ በይርጋ ቀሪ ነው።
ቦታውን ተረክበው ግንባታ ባለማከናወናቸው በመንግስት መመሪያ ከተወሰደባቸው መንግስትን እንጂ እኔን አይጠይቁም ቦታውን በክፍለ ቀበላ አመልክቼ በ1978 ዓ.ም ተሰጥቶኝ ከዚሁ ጊዜ ጀምሮ የንግድ ፈቃድ አውጥቼ በይዞታ ሥር አድርጊያለሁ በማለት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያና የፍሬ ነገር ክርክር መልስ አቅርበዋል።
ክሱ የቀረበለት ፍ/ቤት በግራ ቀኙ መካከል የቀረበውን የሰነድና የሰው ማስረጃ ከተመለከተ በኋላ ክርክር ያስነሳውን ቦታ የአሁን ተጠሪ ከመቼ ጊዜ ጀምሮ ያዙት የሚለውን ነጥብ በሚመለከት የተጠሪ ማስረጃዎች ከአመልካቹ በተሻለ ሚዛን በሚደፊ መልኩ አረጋግጠዋል። ከዚህ በተጠሪ ይዞታ ሥር ንብረቱ ከተገኘበት ጊዜ ጀምሮ ያለው (ከ1978-1991) ዓ.ም ያለው ጊዜ ሲታሰብ ከ2 ዓመት በላይ ስለሚሆነው በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1149(2) መሰረት ክሱ በይርጋ ቀሪ ነው በማለት ወስኗል። ይህ ውሳኔ በየደረጃው ባለት ፍ/ቤቶች በመፅናቱ ይህ የሰበር ጉዲይ ላቀርብ ችሎል።
በሰበር ቅሬታቸውም ላይ ለይርጋ ጊዜ መነሻ ሆኖ የሚያዘው ጊዜ የትኛው ላሆን ይገባል የሚለውን አስመልከቶ የፍሬ ነገር ዝርዝር ክርክር ካቀረቡ በኋላ የእኔ ክስ የሥረ-ነገር ጥያቄ በሚል አገላለፅ ይጥቀሱት እንጂ የባለቤትነት ጥያቄ ነው በማለት ሁከት ይወገድ በሚለው አይወድቅም ስለሆነም በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1149 የተመለከተው ድንጋጌ ተፈፃሚነት የለውም የሚል ክርክር አቅርበዋል።
ተጠሪም በጊዜው የሁከት ይወገድልኝ አቤቱታ ለመመልከት ሥልጣን ለነበረው ፍ/ቤት ክሱን ማቅረባቸው ክሳቸው የሁከት ይወገድልኝ የሚል እንደነበረ በእራሱ አስረጂ ነው እንዱሁም ክሱ የመፊለም ሳይሆን የይዞታ ስለመሆኑ ብር 2000.00(ሁለት ሺህ) መገመታቸው ክሳቸው በሁከት ይወገድልኝ ላይ የተመሰረተ መሆኑን ያመለክታል በማለት ለተያዘው አከራካሪ ጉዲይ አግባብነት ያለውን መልስ ሰጥቷል።
የጉዲዩ አመጣጥ ባጭሩ ከላይ የተመለከተው ሲሆን፤ እኛም ጉዲዩን እንደሚከተለው መርምረናል።
የአመልካች የክስ ምክንያት ተለይቶ የታወቀ ንብረት ተወስድብኛል፤ ይመለስልኝ የሚል እንደመሆኑ የክሱ አቀራረብ ሥርዓት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 226(3) እንደተመለከተው ትክክለኛ ዋጋው ተገምቶ ነገሩን አይቶ ለመወሰን የሥረ ነገር ሥልጣን ላለው ፍ/ቤት ተገቢውን የዲኝነት ገንዘብ ተከፍልበት ላቀርብ እንደሚገባ አመላካች ነው። በዚህ መሰረት መቅረብ ሲገባው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 1149(1) ሁከት የተነሣበት ሰው ሁከት እንዱወገድለት መጠየቅ ይችላል ከሚለው የህግ አነጋገር ‛ሁከት ይወገድልኝ“ የሚለውን ለይቶ በገንዘብ ሉገመት እንደማይቻል ተደርጎ መቅረቡን ያሳያል።
ይሁን እንጂ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1149(1) ላይ ሁከት የተፈጠረበት ሰው ሁከት እንዱወገድለት፤
ይዞታው የተወሰደበት ሰው የተወሰደበት ነገር እንዱመለስለት ሁለቱንም ዓይነት ሁኔታዎች ለያይቶ የደነገገ በመሆኑ የተወሰደን ነገር ለማስመለስ በሚል ዲኝነት ለመጠየቅ በተፈለገ ጊዜ ከላይ በተመለከተው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ቁ 16፣ 226(3) መሰረት ትክክለኛ ዋጋው ተገምቶ ተገቢው ዲኝነት ተከፍልበት የሥረ ነገር ሥልጣን ላለው ፍ/ቤት የሚቀርብ እንጂ የተፈጠረ ሁከት እንዱወገድ (‛cessation of interference“) እንደሆነ ተቆጥሮ በገንዘብ የማይገመቱ አቤቱታዎች በሚቀርቡበት ሁኔታ ሉስተናገድ የሚችል እንዲልነበር ተገንዝበናል።
ይህ ዓይነቱ በክስ አቀራረብ ረገድ የሚታየው ሥነ ሥርዓታዊ ግድፈት የሥረ ነገር ሥልጣን ባለው ፍ/ቤት ቀርቦ ጉዲዩ እንዲይታይ በማድረግ ብቻ ውጤቱ የተንፀባረቀ ሳይሆን በይርጋ ደንቦች አፈፃፀም ላይ ችግርን አስከትሎል።
ከክርክሩ ዓይነት አንፃር ጉዲዩ በሁከት ይወገድልኝ አቤቱታ ሥር ሉሸፈን የሚችል ባለመሆኑ ለዚህ ለተያዘው ክርክር በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1149(2) የተቀመጠው የይርጋ ጊዜ አግባብነት የላለው መሆኑ እየታወቀ የክሱን ይዘት ሳይሆን የክሱን አርዕስት ብቻ በመመልከት የሥር ፍ/ቤቶች ለጉዲዩ ተፈፃሚነት የላለውን የይርጋ ዘመን ተፈፃሚ በማድረጋቸው የህግ ስህተት መፈፀማቸውን ተረድተናል።
በተጠሪ ክርክር ላይ እንደተገለፀው አከራካሪ የሆነው ንብረት በተጠሪ እጅ ከገባ 13 ዓመት አልፍታል የሚል ክርክር ስለቀረበ የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1149(2) ተጠቅሶ ሁለት ዓመት አልፍታል ቢባልም ከ10 ዓመት (ከአስር ዓመት) በላይ ያለፈው መሆኑ ከተረጋገጠ በይርጋ ቀሪ መሆኑ ስለማይቀር የተለየ ለውጥ አያመጣም እንዲይባል የተወሰደ ንብረት ለማስመለስ እና የመፊለም መብትን ለማስከበር የሚቀርቡ ክሶች (petitory actions) በይርጋ ዘመን ቀሪ ላሆን የማይገባበትን የህግ ትንታኔ በመስጠት ከዚህ ቀደም በዚህ የፋዳራል ሰበር ሰሚ ችልት በሰበር መ/ በሆነው ውሳኔ የተሰጠበት ስለሆነ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1677 እና 1845 መሰረት የተቀመጠው የ10 ዓመት የይርጋ ጊዜም ለዚህ ጉዲይ ተፈፃሚነት ያለው ሆኖ አይገኝም።
በልላ በኩል የክሱ አቀራረቡ ግድፈት በሥረ ነገር ሥልጣን ረገድ ያስከተለውን ሥነሥርዓታዊ ስህተት በማየት የሥረ-ነገር ሥልጣን የማይታለፍ የመርህ ጉዲይ እንደመሆኑ በሥር ፍ/ቤት ከፍርድ በፉት በማናቸውም ጊዜ በየትኛውም ደረጃ ሉታረም ይገባል የሚለውን መሰረት በማድረግም ጉዲዩን ተመልክተናል።
ለዚህ ሰበር ጉዲይ መነሻ የሆነው ክስ በቀረበበት ዘመን በ1991 ዓ.ም የአዱስ አበባ ከተማ ፍ/ቤቶች ይህንን መሰል የባለቤትነት ጉዲይ ተቀብለው ለማስተናገድ የሚያስችላቸው ስልጣን ያልነበራቸው መሆኑ ቢታወቅም፤ እንዱሁም ክርክሩ የተነሣው በሁለት ግለሰቦች መካከል እንደመሆኑ በአዋጅ ቁጥር 361/95 መሰረት ሥልጣን የላላቸው ቢሆንም በክርክር ላይ የነበሩ ጉዲዮች በምን አኳኋን መስተናገድ እንደሚኖርባቸው በሚደነግገው የተሻሻለውን የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ቻርተር ለማሻሻል በወጣው በአዋጅ ቁጥር 408/1996 አንቀጽ 2(3) በአዋጅ ቁጥር 361/95 አንቀጽ 66 ሥር የሚከተለው አንቀጽ 10 ተጨምሯል ካለ በኋላ በአንቀጽ 10 ላይ በአዱስ አበባ ከተማ ነክ ጉዲዮች ፍ/ቤት በመታየት ላይ የነበሩና በአዋጅ ቁጥር 361/95 በከተማ ፍ/ቤት ዲኝነት ሥልጣን ሥር የማይወድቁ ጉዲዮች በአዱስ አበባ ከተማ ፍ/ቤት መታየታቸው ይቀጥላል በሚል ምላሽ ስለተሰጠው ይህም ጉዲይ ከላይ በዝርዝር እንደህጉ አነጋገር ሁከት ይወገድልኝ በሚል ሥር የማይወድቅ በመሆኑ ከጅምሩም ቢሆን በአዱስ አበባ ከተማ ነክ ፍ/ቤት ሥልጣን ሥር የሚወድቅ ባይሆንም ክርክሩ ሳይቋጭ በክርክር ላይ የሚገኝ እንደመሆኑ ከላይ በተመለከተው አዋጅ መሰረት አሁንም በተጀመረበት ፍ/ቤት የሚታይ ሆኖ አግኝተነዋል። ስለሆነም የሚከተለውን ውሳኔ ሰጥተናል።
የአዱስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በፍ/ብ/መ/ በ3/2/2001 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ፣ ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት በመ/ በ15/7/2001 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ እና የከተማው ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በፍ/መ/ በ06/2/2002 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348(1) መሰረት ተሽሯል።
የአመልካች ክስ በይርጋ ዘመን ቀሪ ላሆን የሚችል ባለመሆኑ የሥር የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በቀሪው ጉዲይ ላይ ጉዲዩን ተመልክቶ ተገቢውን ዲኝነት ይስጥበት በማለት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 341 መሰረት መዝገቡን መልሰናል።
በዚህ ሰበር ደረጃ ግራ ቀኙ ባደረጉት ክርክር ወጭና ኪሣራ የየራሳቸውን ይቻለ። መዝገቡ ተዘግቷል።
ራ/ታ
No topics extracted.