No summary available.
የሰ/መ/ቁ. 48ዐ86 ህዲር 3 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ ተሻገር ገብረሥላሴ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- 1/ወ/ሮ አሰለፈች ወልደሚካኤል አልቀረበም 2/ ወ/ሮ ቀለመወርቅ ወልደሚካኤል አልቀረበም ተጠሪ፡- ቶታል ኢትዮጰያ አክሲዮን ማህበር ጠበቃ አቶ ወንድየ ግርማ ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትና የከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ስላለበት በሰበር ታይቶ ይታረምልን በማለት አመልካች ስለጠየቁ ነው። የክርክሩ መነሻ የአሁን አመልካች አባታችን ሟች አቶ ወልደሚካኤል ወልደማርያም በአዱስ አበባ ከተማ ወረዲ 1 ቀበላ ዐ7 የቤት ቁጥር 142 የሚታወቀውንና በተለመድ አርበኞች ቶታል ኩባንያ ለኮትንትራክት አስረክበዋል። የአባታችን የመጀመሪያ ደረጃ ወራሾች ስለሆንን የነዲጅ ማደያው ያልተከፊፈለ የውርስ ሀብት ስለሆነ ቢሮውንና የነዲጅ ማደያውን እንዱያስረክቡን በማለት ለፋዳራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ያቀረቡት ክስ ነው።
ተጠሪ በተከሣሽነት ቀርቦ ክሱ በይርጋ ይታገዲል፣ከሣሾች ወራሽነታቸውን አላረጋገጡም ፍርድ ቤቱ ጉዲዩን የማየት ሥልጣን የለውም የሚል የመጀመሪያ ደረጃ የክስ መቃወሚያ ያቀረቡ ሲሆን በአማራጭ አርበኞች መንገድ ተብል የሚጠራው የቶታል ቤንዚን ማደያ ቢሮ ግምት ያነሰ ነው። በተከሣሽ /ተጠሪና/ በከሣሾች አውራሽ አቶ ወልደሚካኤል ወልደማርያም መካከል ተደርጎ የነበረው ውል የነዲጅ ማደያ ኪራይ ውል አይደለም። ከሟች አቶ ወልደሚካኤል ጋር የነበረን ውል የመሬት ኪራይ ውል ነው። ከአቶ ወልደሚካኤል በተከራየው ቦታ ላይ የቤንዚን ማደያውንና ጽ/ቤቱን የሰራው ተከሣሽ /ተጠሪ/ ነው። ኪራዩ ከ1967 ዓ.ም በፉት የተደረገ በመሆኑና በአዋጅ ቁጥር 47/1967 የከተማ ቦታና ትርፍ ቤት የመንግሥት እንዱሆን የታወጀ በመሆኑ እንደዚሁም በየነዲጅ ማደያው ከመንግሥት ቦታና ቤት ተከራይተው ይሰሩባቸው የነበሩ ይዞታዎች የሚኒስትሮች ቤት መጋቢት 1ዐ ቀን 1968 ዓ.ም ቁጥር 411/68 በተፃፈ ደብዲቤ ግንኙነቱ ከመንግሥት ጋር እንጅ ከቀድሞ አከራዬች ጋር እንዲልሆነ የደነገገ በመሆኑ ክሱ ሕጋዊ መሰረት የለውም በማለት ተከራክሯል።
የሥር ፍርድ ቤት በተጠሪ በኩል የተከራይ የመጀመሪያ የክስ መቃወሚያዎችን ውድቅ በማድረግ አመልካች በነዲጅ ማደያውና በጽ/ቤቱ ላይ መብት ያላቸው መሆኑን አግባብነት ካላቸው ማስረጃዎችና የሕግ ድንጋጌዎች እንደዚሁም ከአመልካች አውራሽ ጋር ከተደረገው የመሬት ኪራይ ውል ጋር በማገናዘብ መርምሯል። የሥር ፍርድ ቤት በተጠሪና በአመልካች አውራሽ መካከል የተደረገው የመሬት ኪራይ ውል እንጅ የነዲጅ ማደያና የጽ/ቤት ኪራይ ውል አይደለም። የኪራይ ውለ የተደረገው ከአዋጅ ቁጥር 47/1967 በፉት በመሆኑና በዚህ አዋጅ የከተማ ቦታ የመንግሥት ሀብት የሆነ በመሆኑ እንደዚሁም የሚንስትሮች ምክር ቤት መጋቢት 1ዐ ቀን 1968 በቁጥር 411/68 ዱፕዎች ባለበት እንዱቀጥለ የወሰነ ስለሆነ አመልካች ተጠሪ ላይ ያቀረቡት ክስ ተገቢ አይደለም በማለት ወስኗል።
አመልካች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለከፍተኛው ፍርድ ቤት አቅርበዋል።
የከፍተኛው ፍርድ ቤት የአመልካችን ይግባኝ በፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 337 መሰረት ሰርዞታል። አመልካች ነሐሴ 5 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ ተጠሪ የተከራየው መሆኑ ብቻ አይደለም። የነዲጅ ማደያውንና ቤቱን የተከራየ መሆኑን የሚያሣይ ማስረጃ አቅርበናል።
በሚንስትሮች ምክር ቤት ተፃፈ የተባለው ደብዲቤ ታዓማኒነቱ ሣይረጋገጥ የበታች ፍርድ ቤቶች መቀበላቸው ስህተት ነው። ውለ የተደረገው 1954 ዓ.ም ሲሆን በዚህ ውል መሰረት የውለ ዘመን ሲጠናቀቅ ተጠሪ የነዲጅ መቅጃ መሣሪያዎቹን ቤቱቹን አስረክቦ ለመሄድ ተዋውሎል። ተጠሪ ቦታውን ተረክቦ ቤት ሰርቷል ስለዚህ በውለ ምዕራፍ አስር መሰረት የቤቱ ባለመብቶች እኛ ሆነን እያለ የፍታብሓር ሕግ ቁጥር 1731/11/ በመጣስ የበታች ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት አለበት በማለት አመልክተዋል። ተጠሪ የመሬት ኪራይ ውል የተፈፀመው አዋጅ ቁጥር 47/1967 ከመታወጁ በፉት ሣይሆን ውለ ከዚህ አዋጅ በኋላ ሕጋዊ አስገዲጅነት የላለው በመሆኑ የተከራየነው የነዲጅ ማደያ ቢሮ ሣይሆን መሬት በመሆኑ የበታች ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለበትም በማለት መልስ ሰጥቷል። አመልካች የመልስ መልስ ሰጥተዋል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የቀረበው ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም በአመልካwች አውራሽና በተጠሪ መካከል በተደረገው ውል መሰረት ተጠሪ እንዱፈጽም አይገደድም በማለት የበታች ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሣኔ ተገቢ ነው ወይስ አይደለም የሚለውን ጭብጥ በመያዝ መዝገቡን መርምረናል። መዝገቡን እንደመረመርነው አመልካች በአውራሻችን አቶ ወልደሚካኤልና በተጠሪ መካከል በ1954 ዓ.ም የተደረገው ውል የመሬት ኪራይ ውል ሣይሆን የነደጅ ማደያና ለጽሕፈት ቤት የሚሆን ቤት ኪራይ ውል ነው በማለት የተከራከሩ ቢሆንም ፍሬ ጉዲይ የማጣራትና ማስረጃ የመመዘን ሥልጣን ያላቸው ፍርድ ቤቶች በተጠሪና በአመልካች አውራሽ መካከል በ1954 ዓ.ም የተደረገው ውል የመሬት ኪራይ ውል መሆኑን በማረጋገጥ ወስነዋል። አመልካች የበታች ፍርድ ቤቶች የማስረጃ ተዓማኒነት እና ክብደት ሲመዝኑ ስህተት ሰርተዋል በማለት ያቀረቡት አቤቱታ የሰበር ችልት ለሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 8ዐ ንዐስ አንቀጽ 3/ሀ/ እና አዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀጽ 1ዐ የተሰጠውን ሥልጣን ከግንዛቤ ውስጥ የማያስገባና የሰበር ችልት ማስረጃ ታዓማኒነትና ክብደት እንዱመዝን የሚጠይቅ በመሆኑ አልተቀበልነውም።
በአመልካች አውራሽና አቶ ወልደሚካኤል መካከል የመሬት ኪራይ ውል የተደረገው በ1954 ዓ.ም መሆኑ ተረጋግጧል። በዚህ ጊዜ መሬት የግለሰቦች ሀብትና ርስት እንደነበር የሚታወቅ ሲሆን አቶ ወልደሚካኤል የነበረችውን ርስት መሬት ላይ ተጠሪ የነዲጅ ማደያ ድርጅትና ጽ/ቤት ገንብቶ ኪራይ እየከፈለ እንዱኖር በመጨረሻም የኪራይ ዘመኑ ሲጠናቀቅ ድርጅቱንና ግንባታውን ለቆ እንዱሄድ ተስማምተው የነበሩ መሆኑን ግራ ቀኙ በሥርና በሰበር ካደረጉት ክርክር ተገንዝበናል።
ሆኖም የኪራይ ውል ዘመኑ ከመጠናቀቁ በፉት የውለን አይነተኛ ጉዲይ በተለይም የአመልካች አውራሽ ባለመብት ሆነው የኪራዩን መሬት መንግሥት የሕዝብ ሀብት የሚያደርግ የሕግ ማዕቀፍ አዋጅ ቁጥር 47/1967 ታውጇል። በአዋጁ በባለርስትና በጭሰኛ መካከል ያለውን ግንኙነት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የተቋረጠ በመሆኑ ከነሐሴ ወር 1967 ዓ.ም ጀምሮ ተጠሪ ከአመልካች አውራሽም ሆነ በአመልካች እንዱፈጽም የሚገደድበት ሕጋዊ ውጤት የሚያስከትል ውል የለም። አንድ ውል በተዋዋዮች መካከል እንደ ሕግ ሆኖ አስገዲጅነት የሚኖረው ውለ የሚቻልና የተደረገውም ሕጋዊ በሆነ ጉዲይ ላይ የሆነ እንደሆነ መሆኑ በፍታብሓር ሕግ ቁጥር 1678 ንዐስ አንቀጽ /ለ/ ይደነግጋል። የአመልካች አውራሽና ተጠሪ በ1954 ዓ.ም ሲዋዋለ የውርስን መሬት ማከራየት፣ መሸጥና መለወጥ የሚቻል ቢሆንም ይህ ሁኔታ በአዋጅ ቁጥር 47/1967 የተቋረጠና በግለሰብ ደረጃ መሸጥ ፤መለወጥ የተከለከለ በመሆኑ የውለ መሰረታዊ ጉዲይ የማይቻልና በሕግ ያልተፈቀደ ሆኗል። ከዚህ በተጨማሪ ቀድሞ የመሬት ባለርስት ከነበሩ ሰዎች መሬት ተከራይተው የነደጅ ማደያ ያቋቋሙ ድርጅቶች ግንኙነታቸው ከመንግሥት ጋር እንደሆነና መንግሥት አይቶ ውሣኔውን የሚያሣውቃቸው መሆኑን የሚኒስትሮች ምክር ቤት መጋቢት 1ዐ ቀን 1968 በቁጥር 411/68 በፃፈው ደብዲቤ ያሣውቁ መሆኑ የበታች ፍርድ ቤቶች አረጋግጠዋል። በመንግሥት የተደረገ ክልከላ ከተዋዋይ አቅም በላይ የሆነ ምክንያት መሆኑ በፍታብሓር ሕግ ቁጥር 1793/ለ/ በግልጽ ተደንግጓል።
ስለሆነም የበታች ፍርድ ቤቶች በአመልካች አውራሽና በተጠሪ መካከል በ1954 ዓ.ም የተደረገው የመሬት ኪራይ ውል በአዋጅ ቁጥር 47/1967 ተፈፃሚነቱ የተቋረጠ በመሆኑና የሚንስትሮች ምክር ቤትም ተጠሪ የመሬቱን ኪራይ በተመለከተ ግንኙነቱ ከመንግሥት ጋር እንጅ ከቀድሞ አከራይ ጋር አለመሆኑን የሚያረጋግጥ ውሣኔ የሰጠበት መሆኑን በማጣራት ተጠሪ የነደጅ ማደያውንም ሆነ በቦታው ላይ የሰራቸውን ቤቶች ለአመልካች ለማስረከብ አይገደድም በማለት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለበትም በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትና የከፍተኛው ፍርድ ቤት የሰጡት ውሣኔ ፀንቷል።
በዚህ መዝገብ ያወጡትን ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ ለየራሣቸው ይቻለ።
ለውሣኔ አሰጣጥ እንዱጠቅም ከፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በትውስት የመጣው መዝገብ ይመለስ።
የማይነበብ የዳኞች ፊርማ አለበት
No topics extracted.