No summary available.
ኀዲር 30 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ሒጏስ ወልደ ተሻገር ገ/ስላሴ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- አቶ የሱፍ ሁሴን ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ አደን አብደላ አልቀረቡም መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የሱማላ ብሓራዊ ክልል የጅጅጋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት ሰኔ 23 ቀን 2001 ዓ.ም ስላመለከቱ ነው። የክርክሩ መነሻ ተጠሪ ለጅጅጋ ዞን ያቀረበው ክስ ነው። በዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተጠሪ ከሳሽ አመልካች ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል።
ተጠሪ ካሀ አብደላ የተባለችው እህቱ የአፈር ቤቶችና የከተማ ቦታ የነበራት መሆኑንና እህቱ ካሀ ከተጠሪ ውጭ ላላ ወራሽ የሆነ የሥጋ ዘመድ የላላት መሆኑን ገልፆ ሟች ካሀ ከዚህ ዓለም በሞት ስትለይ አክስቷ ወ/ሮ ከድጃ ሰምታ መጥታ ለተከሳሽ (አመልካች) ቤቶቹን እኔ እስክመጣ ድረስ በአደራ እየጠበቀ እንዱቆይ ለተከሳሽ (አመልካች) አባት ሁሴን አሰን ሰጥታዋለች። አቶ ሁሴን አሰን (የአመልካች አባት) በቀበላ 02 ክልል ውስጥ ያለትን የሟች ወ/ሮ ካሀ ቤትና ቦታ ይዟል። የቦታው አዋሳኝ በምስራቅ የአመኑር ቤት፣ በምእራብ መንገድ በሰሜን የአህመድ ሽፊው ቤተሰቦች በደቡብ መንገድ ሲሆን የሟች ወ/ሮ ካሃ ቤቶች ብዛት ሁለት ክፍል በአፈር ክዲን የተሰራ ቤት፣አምስት ክፍል በቆርቆሮ ክዲን የተሰራ ቤትና ስድስት መፀዲጃ ቤት ያካተተ ነው። አቶ ሁሴን አሰን ቤቶቹን እንዱያስረክበኝ ስጠይቀው ለረዥም ጊዜ ቤቶቹን ስንከባከብና ስጠብቅ ስለቆየሁ ገንዘብ ይክፈለኝ በማለቱ በሽማግላ ብር 8000 (ስምንት ሺህ ብር) ልከፈለው ከተስማማን በኋላ የቤቱ ባለሐብት ለመሆኔ ካርታና ፏላን አለኝ በማለት ቤቱን ለመሸጥ እያስማማሁ በመሆኑ ፍርድ ቤቱ ቤቱን የሰራችው ሟች ወ/ሮ ከሃ አብደላ መሆኗን፣እና ተከሳሽ የያዘው ትክክለኛ ያልሆነ የባለቤትነት ማረጋገጫ ትክክለኛ አለመሆኑ በማስረጃ ተጣርቶ እንዱወሰንልኝ በማለት ክስ አቅርቧል፣የሥር ተከሳሽ የአሁን አመልካች በበኩለ ቀደም ሲል ሟች ወ/ሮ ከሃ የግል ይዞታና ቤት የነበራት ቢሆንም በሕይወት እያለች ቤቱንና ቦታውን ለእኔ ወላጅ አባት ሁሴን ሐሰን ሰጥታዋልች ወ/ሮ ከሃ ቤቱን ለወላጅ አባቴ የሰጠች ስለመሆኑ ማስረጃ አለን። ከሳሽ (ተጠሪ) ገንዘብ እንዱከፍለኝ ያደረግሁበት ስምምነት የለም በማለት የይዞታ ማረጋገጫ የባለቤትነት የምስክር ወረቀትና ላልች ምስክሮችን ዘርዝሮ በዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት መልስ ሰጥቷል።
የዞኑ ከፍተኛው ፍርድ ቤት የተጠሪንና የአመልካችን የቃል ክርክር ሲሰማ ቤቱና ቦታው በመጀመሪያ የሟች የወ/ሮ ካሀ አብደላ መሆኑንና በአቅራቢያው ሟች ወራሽ ያልነበራት መሆኑን የተስማሙበት ፍሬ ጉዲይ እንደሆነ በውሣኔው የገለፁ ሲሆን፣ወ/ሮ ካሃ አብደላ በህይወት እያለች ቤቱን ለአመልካች አባት ሰጥታለች ወይስ አልሰጠችም የሚለው ነጥብ ግራ ቀኙ የሚከራከሩበት መሆኑን በመለየት ጭብጥ መሥርቷል። የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አመልካች ሟች ወ/ሮ ካሃ አብደላ በጽሐፍ በተደረገ የስጦታ ውል ቤቱን ለአመልካች አባት የሰጠች ስለመሆኗ የሚያስረዲ ማስረጃ እንዲላቀረበና አመልካች ያቀረበው የባለቤትነት የምስክር ወረቀት በአሁኑ ወቅት ቤቱ የአመልካች ንብረት መሆኑን የሚያስረዲ እንጅ ቤቱ የቀድሞ ባለሐብት ከሆነችውና የቤቱ ባለንብረት መሆኗ አከራካሪ ካልሆነው ሟች ወ/ሮ ካሃ አብደላ እንዳት ወደ አመልካች አባት እንደተዛወረ አያስረዲም።
በልላ በኩል ከሳሽ/ተጠሪ/ የሟች ካሃ አብደላን ቤት ከድጃ የተባለችው ሴት ለአመልካች አባት ተጠሪ የሟች ወራሽ እስኪመጣ በአደራ ይዞ እንዱቆይ የሰጠችው መሆኑንና አመልካችና ተጠሪ የተደራደሩና አመልካች ብር 8000/ስምንት ሺህ ብር/ ከተጠሪ ለመቀበል ተስማምቶ ተጠሪ ገንዘብ የላለው በመሆኑ መክፈል እንዲልቻለ አስረድቷል በማለት የአመልካች አባት ቤቱን የያዙት በአደራ በመሆኑ ለተጠሪ (ለሟች ወ/ሮ ካሃ አብደላ) ወራሽ እንዱያስረክብ በማለት ውሣኔ ሰጥቷል።
አመልካች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያቀረበ ቢሆንም የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ የዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት የሰጠውን ውሳኔ አጽንቶታል። አመልካች የሰበር አቤቱታ ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ያቀረቡ ቢሆንም የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት አቤቱታቸውን አልተቀበለውም። አመልካች ሰኔ 23 ቀን 2001 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ ወላጅ አባቴ አቶ ሁሴን አው ሐሰን 1986 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል። ወላጅ አባቴ በጅጅጋ 02 ቀበላ የቤት ቁጥር 123-01 ቤት ውስጥ ይኖሩ የነበረ ሲሆን እኔም አባቴ በሞት ከተለዩ በኋላ እየኖርኩበት እገኛለሁ። ተጠሪ ቤቱ የእህቴ ወ/ሮ ካሃ ስለሆነ ይልቀቅልኝ በማለት ክስ ለዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርቦብኝ አኔም አባቴ ለአርባ ስድስት ዓመት በቤቱ ውስጥ የኖረና በሶማሉያ ጦርነት ሰነደ /ካርታና ፏላኑ/ በመቃጠለ ወ/ሮ ካሃ በሕይወት እያለ ላላ ካርታና ፏላን አውጥተው የኖሩበት ነው በማለት ተከራክሬአለሁ። ቤቱ የአባቴ አክስት የሆነውንና የአባቴ አክስት ለአባቴ በሕይወት እያለ የሰጡት ቤት መሆኑን በህይወት ያለት የአባቴ አክስት ባል አሉ ባድል ሣይጠየቁና ሣይመሰክሩ ለተጠሪ እንዱያስረክብ የተሰጠው ውሣኔ አባቴ የቤቱ ባለሐብት መሆኑን የሚያረጋግጥ የባለሐብትነት የምስክር ወረቀት ያለው ሆኖ እያለ አላግባብ የተሰጠ ውሣኔ በመሆኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው። ስለዚህ ውሣኔው በሰበር እንዱታረምልኝ በማለት አመልክቷል።
ተጠሪ በበኩለ ቤቱ የእህቴ የሟች ወ/ሮ ካሃ አብደላ መሆኑ አከራካሪ አይደለም። አመልካች ሟች ወ/ሮ ካሃ ቤቱን ለአባቷ እንደሰጡ በመግለጽ የተከራከረ ቢሆንም ሟች ወ/ሮ ከሃ ቤቱን በስጦታ ያስተላለፈበትን ሰነድ በማቅረብ አላስረዲም። በእኔ በኩል የሟች ወ/ሮ ካሃ ወንድምና ወራሽ መሆኔን የሚያረጋግጥ ማስረጃ አቅርቤአለሁ። የአመልካች አባት ቤቱ ከቀድሞ ባለንብረቷ ከወ/ሮ ካሃ በሕጋዊ መንገድ ሣይተላለፍላት የወጣው የባለሐብትነት የምስክር ወረቀት አመልካችን የቤቱ ባለሐብት ሉያደርገው አይችልም። ስለሆነም በክልለ ፍርድ ቤቶች የተሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የላለው በመሆኑ የአመልካችን አቤቱታ ውድቅ በማድረግ እንዱያሰናብተኝ በማለት ኀዲር 10 ቀን 2002 ዓ.ም የተፃፈ መልስ አቅርቧል። አመልካች ኀዲር 15 ቀን 2002 ዓ.ም በተፃፈ የመልስ መልስ ለክርክሩ መነሻ የሆነው ቤት የአባቴ አክስት ከሆኑት ከወ/ሮ ከሃ አብደላ ለሟች አባቴ እንዱተላለፍና በሟች አባቴ ስም ካርታ ወጥቶበት እንደሚገኝ በአቤቱታዬ በሰፉው ዘርዝሬ አቅርቤያለሁ። ቤቱ በአባቴ ስም ካርታ ያለው በመሆኑ ተጠሪ ከዚህ የበለጠ የቤቱ ባለሐብት ለመሆን ማስረጃ ያላቀረቡ ስለሆነ ክርክራቸው ተገቢ አይደም የሰነድ ማስረጃ በምስክር ማቅረብ እንደማይቻል የፍታብሓር ሕግ ቁጥር 2005 ይደነግጋል የሚል ሰፉ ክርክር አቅርበዋል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የቀረበው የጽሐፍ ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም አመልካች ክርክር የተደረገበትን ቤትና ቦታ ለተጠሪ እንዱያስረክብ የተሰጠው ውሣኔ በአግባቡ ነው ወይስ አይደለም የሚለውን ጭብጥ በመመስረት ጉዲዩን መርምረናል።
ጉዲዩን እንደመረመርነው ለክርክሩ መነሻ የሆነው ቤትና ቦታ የሟች ወ/ሮ ካሃ አብደላ በህይወት እያለ ያፈሩት ንብረት መሆኑን አመልካችና ተጠሪ ያልተካካደበት ፍሬ ጉዲይ እንደሆነ የዞኑ ከፍተኛው ፍርድ ቤት በውሣኔው በግልጽ አስቀምጦታል። የክርክሩ መነሻ የሆነው ቤት በመጀመሪያ ያፈሩት ሟች ወ/ሮ ካሃ አብደላ መሆናቸውን አመልካች ለዚህ ችልት በሰጠው የመልስ መልስ ገልጿል። ስለሆነም የክርክሩ መነሻ የሆነው ቤትና ቦታ ሟች ወ/ሮ ካሃ አብደላ በህይወት እያለ ያፈሩት ሀብት መሆኑ አከራካሪ ጭብጥ አይደለም።
አከራካሪው ጭብጥ አመልካች ወ/ሮ ካሃ አብደላ ቤቱንና ቦታውን በህይወት በነበሩበት ጊዜ ለአባቴ ለአቶ ሁሴን አው ሐሰን በስጦታ አስተላልፊለት የቤቱ ባለሃብትነት ካርታና ፔላን በአባቴ ስም ሆኗል በማለት አመልካች የሚያቀርበውን ክርክር ተጠሪው በግልጽ በመካድ የአመልካች አባት አቶ ሁሴን አው ሐሰን ቤቱን ከወ/ሮ ከድጃ እኔ እስክመጣ ድረስ በአደራ እንዱጠብቅ ነው የተረከበው፣የቤቱን ባለሃብትነት ማስረጃ ያወጡት ቤቱ በስጦታ ለሺያጭ ወይም ለውርስ ከሟች ወ/ሮ ካሃ አብደላ ሣይተላለፍላቸው በተሣሣተ መንገድ ነው የሚል ክርክር አቅርቧል። ስለሆነም ቤቱ በአሁኑ ወቅት በአመልካች አባት ስም ተመዝግቦ መገኘቱና የአመልካች አባት የቤቱ ባለሐብት መሆኑን የሚያረጋግጥ የባለሐብትነት ማስረጃ ካርታና ፔላን ያለው መሆኑ ቤቱ የቀድሞ ባለንብረት ከነበሩት ወ/ሮ ከሃ አብደላ በህጋዊ መንገድ የተላለፈለት ለመሆኑ የሚያረጋግጥና ሉስተባበል የማይችል ማስረጃ ነው ወይስ አይደም? የሚለው ነጥብ መታየት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
የአንድ የማይንቀሣቀሥ ንብረት ባለቤት መሆኑን የሚያረጋግጥ የባለቤትነት ማረግገጫ የምስክር ወረቀት ወይም ማስረጃ የያዘ ሰው የማይንቀሣቀሰው ንብረት ባለቤት ነው ተብል እንደሚገመት የፍታብሓር ሕግ ቁጥር 1195/1/ የሚደነግግ ሲሆን ይኸ የሕግ ግምት ሉስተባበል የሚችል የሕግ ግምት መሆኑ የፍታብሓር ሕግ ቁጥር 1195 ንኡስ አንቀጽ 2 በግልጽ ይደነገጋል።
ከዚህ አንፃር ስንመዝነው የክርክሩ መነሻ የሆነው ቤት በአሁኑ ወቅት በአመልካች አባት ሟች አቶ ሁሴን አው ሃሰን ስም ተመዝግቦ የሚገኝ መሆኑን የአመልካች አባት የቤቱ ባለሐብት መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የባለቤትነት ማስረጃ ያላቸው መሆኑ ቤቱ የአመልካች አባት አቶ ሁሴን አው ሐሰን ሐብት ነው ብል የህሉና ግምት ለመያዝ የሚያበቃ ማስረጃ ነው። ነገር ግን ይኸ ማስረጃ ጥቅሜና መብቴ ተነክቶብኛል የሚል ላላ ሰው ቤቱ የሟች አቶ ሁሴን አው ሐሰን አለመሆኑንና የተሰጠው የባለቤትነት ማስረጃም ትክክለኛ ማስረጃ አለመሆኑን ላላ ማስረጃ በማቅረብ ሉያፈርሰውና ሉያስተባብለው የሚችል መሆኑ በፍታብሓር ሕጉ አንቀጽ 1195 ንኡስ አንቀጽ 2 የተደነገገ በመሆኑ አመልካች ንብረቱ በአባቴ ስም የተመዘገበና የአባቴ ንብረት መሆኑን የሚያረጋግጥ ካርታና ፔላን እያለ ተጠሪ ይህንን እንዱያስተባብልና በሰው ማስረጃ እንዱያፈርስ የበታች ፍርድ ቤቶች መፍቀዲቸው መሰረታዊ የህግ ስህተት አለበት በማለት ያቀረቡት አቤቱታ የሕግ መሰረት የለውም።
ተጠሪ ቤቱ በመጀመሪያ አውራሹ የሆነችው የሟች ካሃ አብደላ መሆኑን በማስረጃ ከማረጋገጡ በተጨማሪ ቤቱን በሕይወት እያለ ያፈሩት ሟች ወ/ሮ ካሃ መሆናቸውን አመልካች በሥርና በዚህ ፍርድ ቤት አምኖ ተከራክሯል። ተጠሪ ከዚህ በተጨማሪ የአመልካች አባት አቶ ሁሴን አው ሐሰን ቤቱን በአደራ ጠባቂነት ወ/ሮ ከድጃ ከተባለ የሟችና የተጠሪ ዘመድ የተረከቡ መሆኑና አመልካች ቤት በአደራ የጠበቁበትን የድካም ዋጋ ብር 8000 (ስምንት ሺ ብር) ለመቀበል ተስማምተው የነበሩ መሆኑን ጉዲዩን በሽምልና በማየት አመልካችና ተጠሪን ያስማሙ ምስክሮች እንዲረጋገጡ ፍሬ ጉዲይ የማጣራትና ማስረጃ የመመዘን ሥልጣን ባላቸው የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤትና በክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ችልት ተረጋግጧል። የአመልካች ወላጅ አባት ቤቱ ከሟች ወ/ሮ ካሃ አብደላ በሽያጭ ውል በውርስ ወይም በስጦታ ሣይተላለፍላቸው ቤቱን በአደራ ጠባቂነት ከወ/ሮ ከድጃ ከተረከቡ በኋላ የቤቱን ስመ ሐብት ማዞራቸውንና የባለቤትነት ማስረጃ የተሰጡ መሆኑን ተጠሪ በበቂ ማስረጃ ካረጋገጠ የአመልካች አባት የቤቱ ባለሐብት ናቸው የሚለውን ግምት ለማፍረስና ለማስቀረት የሚችል ምክንያት መሆኑ ከፍታብሓር ሕግ ቁጥር 1196/ሀ/ እና /ለ/ ድንጋጌዎች ለመገንዘብ የሚቻል በመሆኑ አመልካች በዚህ በኩል ያቀረቡት ቅሬታ የሕግ መሰረት ያለው ሆኖ አላገኘውም።
ቤቱ በአመልካች አባት ስም መመዝገቡና የአመልካች አባት የባለሐብትነት የምስክር ወረቀት ያላቸው መሆኑ በፍታብሓር ሕግ ቁጥር 1195/1/ መሰረት የቤቱ ባለሃብት ናቸው የሚል ግምት ሉያሣድር የሚችል ማስረጃ ቢሆንም ተጠሪ በፍታብሓር ሕግ ቁጥር 1196 /ሀ/ እና /ለ/ የተደነገጉትን ሁኔታዎች በማስረዲት የባለቤትነት ማስረጃው ትክክል አለመሆኑን በበቂ ሁኔታ እንዲስተባበለ በበታች ፍርድ ቤቶች ተረጋግጧል። በልላ በኩል አመልካች ለሟች አባቴ አቶ ሁሴን አው ሐሰን ወ/ሮ ከሃ አብደላ የቤቱን ባለሐብትነት በስጦታ አስተላልፊላቸዋለች የሚል ክርክር ከሥር ጀምሮ እስከ ሰበር ችልት ያቀረበ ቢሆንም አመልካች ሟች ወ/ሮ ካሃ አብደላ በሕይወት በነበሩበት ጊዜ ቤቱን የፍታብሓር ሕግ ቁጥር 2443 እና የፍታብሓር ሕግ ቁጥር 881 ወይም የፍታብሓር ሕግ ቁጥር 882 በሚደነግገው መሰረት በስጦታ የሰጧቸው መሆኑን የሚያስረዲ የሰነድ ማስረጃ እንዲላቀረቡ የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አረጋግጧል። አመልካች አባታቸው ቤቱን ከሟች ወ/ሮ ካሃ አብደላ ከላይ የተገለፁት የሕግ ድንጋጌዎች በሚደነግጉት መሰረት በስጦታ ያስተላለፈላቸው መሆኑን የማስረዲት ግዳትና ኃላፉነታቸውን ባልተወጡበት ሁኔታ ሟች ወ/ሮ ካሃ አብደላ ቤቱን ለአባቴ የሰጠችው መሆኑን አቶ አሉ ባድል የተባለ ሰው በሚሰጡት የምስክርነት ቃል ለማስረዲት ያቀረብኩትን ጥያቄ የበታች ፍርድ ቤቶች አላግባብ ውድቅ አድርገውብኛል በማለት ያቀረቡት ክርክር የሕግ ድጋፍና መሰረት ያለው ሆኖ አላገኘነውም።
በመሆኑም አከራካሪው ቤትና ቦታ ሟች ወ/ሮ ካሃ አብደላ በሕይወት እያለ ያፈሩት ንብረት መሆኑና ተጠሪም የሟች ወ/ሮ ካሃ ወራሽ መሆኑ የተረጋገጠ በመሆኑና ለክርክር መነሻ የሆነው ቤትና ቦታ በአመልካች አባት በአቶ ሁሴን አው ሐሰን ስም ተመዝግቦ የሚገኝና አቶ ሁሴን የቤቱ ባለሐብት መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የባለቤትነት ማስረጃ ያላቸው ቢሆንም አቶ ሁሴን የቤቱን ባለሐብትነት በስማቸው ያስመዘገቡትና የባለሐብትነት ማስረጃ የወሰደት ቤቱ በሕጋዊ መንገድ ከባለሐብቷ ሟች ወ/ሮ ካሃ አብደላ በሽያጭ፣ በውርስ ወይም በስጦታ ሣይተላለፍላቸው ይልቁንም ወ/ሮ ከድጃ የተባለ የሟች ወ/ሮ ካሃና የተጠሪ ዘመድ በአደራ እየጠበቁ እንዱቆዩ ካስረከቧቸው በኋላ ህጋዊ ባልሆነ መንገድ የቤቱን ስመ ሐብት በስማቸው ያዛወሩና የባለቤትነት ማስረጃ የወሰደ መሆኑን የፍታብሓር ሕግ ቁጥር 1196/ሀ/ ና /ለ/ በሚደነግጉት መሰረት ተጠሪ በማስረጃ ያረጋገጠና ያስረዲ መሆኑን ፍሬ ጉዲይ የማጣራትና ማስረጃ የመመዘን ሥልጣን ያላቸው የጅጅጋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ችልት የሰጡትን ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለበትም በማለት የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት ማጽደቁ ተገቢና የሕግ ስህተት ያልተፈፀመበት ነው በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የሱማላ ብሓራዊ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ችልት ሰኔ 21 ቀን 2000 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ እንዱሁም የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት የሰጠው ውሣኔ ፀንቷል።
የጅጅጋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የካቲት 1 ቀን 2000 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ ፀንቷል።
በዚህ ፍርድ ቤት ነሐሴ 13 ቀን 2001 ዓ.ም የተሰጠው የእግድ ትእዛዝ ተነስቷል።
በዚህ ፍርድ ቤት ግራ ቀኙ ያወጡት ወጭና ኪሣራ ለየራሳቸው ይቻለ።
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.