No summary available.
ጥቅምት 30 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች- ተገኔ ጌታነህ ሐጏስ ወልደ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድአመልካቾች፣
ጉዲዩ የቀረበው አመልካቾች የአዱስ አበባ አስተዲደር ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤትና የከተማው ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጡት የመጨረሻ ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልን በማለት በጠበቃቸው አማካኝነት ህዲር 16 ቀን 2002 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ ስላመለከቱ ነው። ክርክሩ በመጀመሪያ የታየው በአዱስ አበባ አስተዲደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ነው። በሥር ፍርድ ቤት ተጠሪ ከሣሽ የአሁን አመልካቾችና ላልች ሰዎች በድምሩ 151 ሰዎች ተከሣሽ በመሆን ተከራክረዋል። በሥር ፍርድ ቤት ተጠሪ በተከሣሽነት ቀርቦ አሁን ላለው የአሽከርካሪዎችና መካኒኮች የሥልጠና ማዕከል ለማስፊፊት በከተማ ልማትና ቤት ሚኒስትር 130,777 ካሬ ሜትር ቦታ የካቲት 7 ቀን 1982 ዓ.ም የተሰጠው መሆኑን ገልፀው በወቅቱ በቦታው ላይ የነበሩት ሰላሣ ዘጠኝ ሰዎች የቤታቸውን ግምት ተቀብለው በተዘጋጀላቸው ቦታ እንዱዛወሩ ተወስኗል። በዚህ መሰረት ግምት የተቀበለት ቦታውን እንዱለቁ ወይም የወሰደትን ገንዘብ እንዱመልሱ ላልቹም በህገወጥ መንገድ በቦታው የሰፈሩ በመሆኑ ቦታውን ለቅቀው እንዱያስረክቡ ይወሰንልን በማለት አመልክቷል። አመልካቾች የተጠሪ ክስ በይርጋ ይታገዲል። በቦታው ላይ የሰፈርነው መንግስት እያወቀው በህጋዊ መንገድ ነው። ከዚህ በፉት ቤታችን የተገመተው በዝቅተኛ ዋጋ ነው ስለዚህ እንደገና ተገምቶ ካሣ ሉሰጠን ይገባል የሚል ዝርዝር የመከራከሪያ ነጥቦችን አቅርበዋል።
የሥር ፍርድ ቤት አመልካቾች ያቀረቡት የይርጋ መቃወሚያ ቦታውን ተጠሪ በህዝብ አገልግልት ስም ተቋም ለማስፊፊት በህጋዊ መንገድ የያዘው በመሆኑና የፍታብሓር ህግ ቁጥር 1149/1/ ለእንደዚህ አይነት ሁኔታ የሚያገለግል ባለመሆኑ ተገቢነት የለውም በማለት ውድቅ አድርጓል። በሥር ፍርድ ቤት ስማቸውን ከአንደኛ ተራ ቁጥር እስከ ስልሣ ዘጠነኛ ተራ ቁጥር የጠቀሳቸው ተከሣሾች በወቅቱ የንብረታቸው ግምት ተገምቶ ግምቱን እንዱቀበለ በመሆኑና ምትክ ቦታ ተዘጋጅቶ የተሰጣቸው በመሆኑ የተጠሪን የይዞታ መሬት የማያስረክቡበት ህጋዊ ምክንያት የለም። ስለዚህ ቦታውን ለተጠሪ ያስረክቡ ስማቸው ከተራ ቁጥር 40 እስከ 151 የተዘረዘሩት ተከሣሾች የቤታቸው ግምት ያልወሰደ ስለሆነ ቤቱ በፉት በነበረው ግምት መጠን በቅድሚያ በመክፈል ወይም ተመሳሳይ ቤት እንዱሰጣቸው አድርጎ ይዞታውን ማስለቀቅ ይችላል በማለት ውሣኔ ሰጥቷል።
በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ስልሣ ዘጠኝ የሚሆኑ አመልካቾች ይግባኝ ለአዱስ አበባ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ያቀረቡ ሲሆን ተጠሪ በበኩለ ሰዎቹ በቦታው ላይ የሰፈሩት በህገወጥ መንገድ ሆኖ እያለ ካሣ እንድከፍል መወሰኑ ተገቢ አይደለም በማለት መስቀለኛ ይግባኝ አቅርቧል። ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት በሥር ተከሣሽ የነበሩና አሁን ይግባኝ ባይ የሆኑ ሰዎች በአስተዲደር አካላት ህጋዊ ነዋሪዎች መሆናቸውና የተለያዩ ማስረጃዎች የተሰጣቸው መሆኑን ተገንዝበናል። ስለዚህ የሥር ፍርድ ቤት ለሚፈርሰው ቤታቸው ተጠሪ ግምት እንዱከፍል የሰጠው ውሣኔ ተገቢ ነው በማለት የተጠሪን መስቀለኛ ይግባኝ ውድቅ አድርጎታል።
የካሣውን መጠን በተመለከተ ይግባኝ ባዮችም ሆኑ ላልች ግለሰቦች ቤታቸው ተጠንቶ ለተወሰኑት ካሣና ምትክ ቦታ ተሰጥቷቸዋል። በወቅቱ በቤቶቹ ግምት ላይ የቀረበ መቃወሚያ አልቀረበም ካሣው ለይግባኝ ባዩች ሣይከፈል የዘገየው ይግባኝ ባዮች በስምምነቱ መሰረት የክፍለ ማዘጋጃ ቤት ወደአዘጋጀው ቦታ ለማዛወር ፈቃደኛ ባለመሆናቸው እና አከራካሪውን ቦታ ይዘው ለመቆየት በመፈለጋቸው በመሆኑ ጥፊቱ የይግባኝ ባዩች ነው ጥፊቱ የይግባኝ ባዩች ከሆነ መልስ ሰጭ/ተጠሪ/ በወቅቱ በነበረው ግምት መሰረት እንጂ አሁን ባለው የገበያ ዋጋ ለቤቶቹ ግምት የሚከፍልበት ምክንያት የለም በማለት ውሣኔ ሰጥቷል። አቤቱታውንም ሰርዞታል። አመልካቾች ለሰበር ችልት ባቀረቡት የሰበር አቤቱታ ተጠሪ አመልካቾችና ላልች በቦታው /ስፍራው/ የሚገኙ ከሶስት መቶ በላይ የሚሆኑ ሰዎች ከሰላሣ አንድ ዓመት በላይ የያዙትን ይዞታ እንዱለቁ ክስ የቀረበው የከተማ ልማትና ቤት ሚኒስትር ፈቅድልኛል በማለት ነው።
መንግስት አንድ ንብረት የሚወሰደው ለህዝብ ጥቅም አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘውና ተመጣጣኝ ካሣ ሲከፍል ብቻ ነው። በያዝነው ጉዲይ ቦታው ለህዝብ ጥቅም የሚፈለግ ስለመሆኑ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የሰጠው ውሣኔ አልቀረበም። ቦታው በሉዝ የተወሰደ መሆኑን የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር የወሰነው ውሣኔ የለም። ስለዚህ ቦታው ለህዝብ ጥቅምና አገለግልት የሚውል መሆኑ በተገቢው የመንግስት አካል ሣይወሰን ተጠሪ ይዞታን ለማስፊፊት በማቀድ ያቀረበው ክስ ተገቢነት የለውም ተጠሪ በዚህ አይነት ሁኔታ ከንብረታችንና ከይዞታችን ለማስነሣት የሚያደርገው እንቅስቅሴ የህገመንግስቱ አንቀጽ 40/8/ ና አዋጅ ቁጥር 272/1994 ድንጋጌ ውጭ በመሆኑ ካሣውም እነዚህን የህግ ድንጋጌዎች መሰረት በማድረግ የተሰራ ባለመሆኑ የአዱስ አበባ አስተዲደር ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልን በማለት አመልክተዋል። ተጠሪ በበኩለ በይግባኝ የተከራከሩት ስልሣ ዘጠኝ ሰዎች ብቻ ሲሆኑ ሰባ ዘጠኝ ሰዎች ለችልቱ የሰበር አቤቱታ ማቅረባቸው ሥርዓቱን የተከተለ አይደለም የማሰልጠኛ ተቋሙ በአገራችን የትራፉክ አደጋን ለመቀነስና የትራፉክ ደህንነትን ለማጎልበት አስፈላጊ መሆኑ በመንግስት ታምኖበት በከፍተኛ በጀትና ወጭ የተቋቋመ ለህዝብ አገልግልት የሚሰጥ ተቋም ነው። ተቋሙን ለማስፊፊት በአቅራቢያው ያለውን ምቹ ቦታ እንዱንወሰድ ሥልጣን ባለው አካል ውሣኔ ተሰጥቶበት የቦታው ባለይዞታ የሚያደርገን ካርታና ፔላን ተሰጥቶናል ስለዚህ አመልካቾች ቦታውን ላለመልቀቅ የሚያቀርቡት ክርክር የህግ ድጋፍ የለውም በማለት በቃል ክርክር መልስ ሰጥተዋል። አመልካቾች በሚኒስትሮች ምክር ቤት ሣይወሰን ቦታውንና ንብረታችንን እንድንለቅ መደረጉ ህጋዊ አይደለም በማለት በጠበቃቸው አማካኝነት በቃል ክርክር የመልስ መልስ ሰጥተዋል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር ግራቀኙ በፅሐፍና በቃል ያቀረቡት ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም አመልካቾች ቦታውንና ንብረቱን ለተጠሪ እንዱለቁ እንደዚሁም ተጠሪ በፉት በተሰራው ግምት መሰረት ለተጠሪዎች ካሣ እንዱከፍል በአዱስ አበባ ይግባኝ ሰሚና ሰበር ችልት የተሰጠው ውሣኔ ተገቢ ነው ወይስ አይደለም የሚለውን ጭብጥ በመያዝ ጉዲዩን መርምረናል።
ጉዲዩን እንደመረመርነው ከላይ የተያዘውን ጭብጥ ከማየታችን በፉት ተጠሪ በይግባኝ ተከራካሪ የነበሩት ስልሣ ዘጠኝ ሰዎች ነበሩ አሁን ለሰበር ሰባ ዘጠኝ ሰዎች አቤቱታ ማቅረባቸው ተገቢ አይደለም በማለት ያቀረበውን ተቋውሞ መርምረናል። አመልካቾች ለዚህ ሰበር ችልት አቤቱታ ያቀረቡት የአዱስ አበባ አስተዲደር ፍርድ ቤት የሰበር ችልት የሰጠው የመጨረሻ ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት አለበት በማለት ነው። ከመዝገቡ ጋር ከተያያዘው የአዱስ አበባ አስተዲደር የሰበር ችልት የውሣኔ ግልባጭ በከተማው ሰበር ችልት አመልካች የነበሩት ስልሣ ዘጠኝ ሰዎች ሣይሆኑ ሰባ ዘጠኝ ሰዎች መሆናቸው በግልፅ ተመዝግቧል። በይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት በአንድ መዝገብ ይግባኝ አቅርበው የተከራከሩት ስልሣ ዘጠኝ ሰዎች ሲሆኑ አሰሮቹ ሰዎች በይግባኝ የብቻ መዝገብ አስከፍተው በይግባኝ ሲከራከሩ ቆይተው ወደ ከተማው ሰበር አቤቱታ ያቀረቡና መዝገባቸው ተጣምሮ የታየ መሆኑን ወይም በልላ አሳማኝ ምክንያት ፍርድ ቤቱ ለከተማ ሰበር ችልት ያቀረቡትን አቤቱታ የተቀበላቸው ስለመሆኑ ለመለየት የማይቻል ቢሆንም ተጠሪ ተቃውሞ ከማቅረብ ውጭ እንዳትና በምን ምክንያት የከተማ ሰበር ችልት ሰባ ዘጠኝ ሰዎች አመልካቾች የሆኑበትን አቤቱታ ተቀብል ትዕዛዝ ሰጠ የሚለውን ያላስረዲ በመሆኑ ያቀረበውን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ አልተቀበልነውም።
ወደ መሰረታዊ ጉዲዩ ስንመለስ ተጠሪ ያቋቋመውን የአሽከርካሪና የቴክኒክ ባለሙያዎች ማሰልጠኛ ተቋም ለማስፊፊት ክርክር ያስነሣውና ስፊቱ 137,777 ካሬ ሜትር ቦታ በወቅቱ በነበረው ከተማ ልማትና ቤት ሚኒስቴር የተሰጠ መሆኑንና ተጠሪ የይዞታ የምስክር ወረቀት፣ ካርታና ፔላን በሚመለከተው የአስተዲደር ክፍል የተሰጠው መሆኑ በሥር ፍርድ ቤትና በይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ተረጋግጧል። መንግስት ለህዝብ ጥቅም ተመጣጣኝ ካሣ በመክፈል የግለሰብ ሀብትና ንብረት መውሰድ የሚችል መሆኑ በህገመንግስቱ አንቀጽ 40 ንዐስ አንቀጽ 8 በግልፅ ተደንግጓል። መንግስት በህግ በኩል እንደአንድ ሰው የሚቆጠር መሆኑንና በመሥሪያ ቤቶቹ አማካኝነት ከተፈጥሮው ጋር የሚስማሙትን መብቶች ሁለ ሉሰራባቸውና ሉያገኝ እንደሚችል በፍታብሓር ህግ ቁጥር 394 ንዐስ አንቀጽ 1 እና ንዐስ አንቀጽ 2 ተደንግጓል። ተጠሪ የመንግስት መሥሪያ ቤት መሆኑ አከራካሪ አይደለም። ለህዝብ ጥቅምና አገልግልት ያቋቋመውን ተቋም ለማስፊፊት ጥያቄውን ለጉዲዩ ውሣኔ የመስጠት ሥልጣን ላለው የከተማው ልማትና ቤት ሚኒስቴር አቅርቦ ቦታው ተሰጥቶታል።
ስለሆነም ቦታው ለህዝብ ጥቅም የተፈለገ በመሆኑ በፍታብሓር ህግ ቁጥር 394 ንዐስ አንቀጽ 2 ተጠይቆ የፍታብሓር ህግ ቁጥር 396 አንቀጽ 2 መሰረት ታምኖበት በወቅቱ ሥልጣን ባለው ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት የተፈቀደ በመሆኑ አመልካቾች የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሣይወሰን ቦታና ንብረታችንን እንድንለቅ መደረጉ የህገ መንግስቱን አንቀጽ 40 ንዐስ አንቀጽ 8 የሚጥስ ተግባር ነው በማለት ያቀረቡት አቤቱታ የህግ ድጋፍ ያለው ሆኖ አላገኘነውም።
አመልካቾች አዋጅ ቁጥር 272/1994 በመጥቀስ ከቦታው እንድንለቅ የተሰጠው ውሣኔ የአዋጁን ድንጋጌ የሚቃረን ነው በማለት ያቀረቡትን ክርክር ስንመለከት አመልካቾች በቦታው ላይ ያለውን ንብረት በማንሣት እንዱለቁ የተወሰነው ቦታው በህዝብ ጥቅምና ግልጋልት የሚሰጥ ተቋም ማስፊፉያነት ለመጠቀም ነው። መንግስት አንድ የግል ንብረት ለህዝብ ጥቅም በሚወስድበት ጊዜ ሉከተለው የሚገባው ሥርዓት ከፍታብሓር ህግ ቁጥር 1460 እስከ ፍታብሓር ህግ ቁጥር 1488 ተደንግጓል። አመልካቾች የሚከራከሩበት ቦታና ንብረት ለህዝብ ጥቅም እንዱለቁ የተወሰነው በ1982 ዓ.ም በመሆኑ ከላይ የተጠቀሰው የህግ ድንጋጌ መሰረት በማድረግ መብታቸውን በማስከበር ከሚጠይቁ በስተቀር ለጉዲዩ አግባብነት የላለውን አዋጅ ቁጥር 272/1994 በመጥቀስ ክርክር ማቅረባቸው ተገቢ ሆኖ አላኘነውም።
አመልካቾች የህገመንግስቱ አንቀጽ 40 ንዐስ አንቀጽ 8 በሚደነግገው መሰረት ለንብረታቸው ተመጣጣኝ ካሣ ተጠሪ እንዱከፍል አልተወሰነልንም በማለት ያቀረቡትን ክርክር በተመለከተ አመልካቾች ንብረት ተጠንቶና ግምቱ ተለይቶ አመልካቾች ማዘጋጃ ቤት ወደአዘጋጀው ቦታ ተዛውረው የንብረታቸውን ግምትና ዋጋ እንዱወስደ ተጠየቀው የነበሩ መሆኑን በሥር ፍርድ ቤትና በይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ተረጋግጧል። አመልካቾች በወቅቱ ለንብረቱ የተሰጠው ግምት ከንብረቱ ዋጋ ጋር ተመጣጣኝ አይደለም ብለው የፍታብሓር ህግ ቁጥር 1477/2/ በሚደነግገው መሰረት በሶስት ወር ለፍርድ ቤት ያቀረቡት አቤቱታ እንደላለ የበታች ፍርድ ቤቶች አረጋግጠዋል።
አመልካቾች ለጉዲዩ አግባብነት ያለው የህግ ድንጋጌ በሚደነግገው የጊዜ ገደብ ውስጥ በወቅቱ ለንብረታቸው የተወሰነላቸውን የካሣ ገንዘብ በመቃወም ለፍርድ ቤት ያቀረቡት አቤቱታ የለም። በልላ በኩል አመልካቾች በቦታው ላይ ያለውን ንብረት እና ይዞታውን እንዱለቁ የሚመለከተው የመንግስት አካል ወስኖ ካሣወቃቸው በኃላ ወደ ተዘጋጀው ቦታ ላለመዛወርና ቦታውን ላለመልቀቅ የተለያየ ምክንያት እየፈጠሩ እስካሁን እንዲለቀቁ ፍሬ ጉዲይ የማጣራትና ማስረጃ የመመዘን ስልጣን ባላቸው የአዱስ አበባ አስተዲደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ተረጋግጧል።
አመልካቾች በወቅቱ ተገምቶ ተጠሪ ያሣወቃቸውን የካሣ መጠን በመቃወም በፍታብሓር ህግ ቁጥር 1477 ድንጋጌዎች መሰረት አቤቱታ ለፍርድ ቤት በማቅረብ እንዱሻሻል መከራከር ወይም ቦታውን በመልቀቅ ግምቱን መውሰድ ሲገባቸው አስካሁን በቦታው ላይ መቆየታቸው ተገቢ አለመሆኑና ጥፊቱ የተጠሪ ሣይሆን የአመልካቾች መሆኑ ተረጋግጧል። ስለሆነም አመልካቾች የህጉን ሥርዓት ተከትለው ቅሬታቸውን ማቅረብና ቦታውን በመልቀቅ ቦታውን ለተሰጠው የህዝብ ጥቅምና ግልጋልት እንዱውል ማድረግ ሲገባቸው ይህንን ሣያደርጉ በመቅረታቸውን በመዘግየታቸው ምክንያት ንብረቱ በፉት ከተገመተው ግምት በላይ የሚጠየቁበት የህግ መሰረት የለም በማለት የአዱስ አበባ አስተዲደር ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤትና የሰበር ችልት መወሰናቸው ንብረቶቹ በወቅቱ በግምታቸው ካሣ ሣይከፈል የቀረው በማን ጥፊት ነው የሚለውን ነጥብ ለማስረዲት ያቀረቡ ማስረጃዎችን በመመዘን የደረሱበት መደምደሚያ ሆኖ አግኝተነዋል።
በአጠቃላይ የአዱስ አበባ አስተዲደር ይግባኝ ሰሚ ችልትና የከተማው ሰበር ችልት የሰጡት ውሣኔ ለጉዲዩ አግባብነት ያላቸውና ከላይ የጠቀስናቸውን የህግ ድንጋጌዎች ያገናዘበና መሰረታዊ የህግ ስህተት የላለው ነው በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የአዱስ አበባ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤትና የከተማው ሰበር ችልት የሰጡት ውሣኔ ፀንቷል።
በዚህ ፍርድ ቤት የወጣውን ወጪና ኪሣራ ግራቀኙ ለየራሳቸው ይቻለ።
No topics extracted.