No summary available.
ጥቅምት 18 ቀን 2003ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሒጎስ ወልደ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ወ/ሪት ራሓራ ሥነፀሐይ - ጠበቃ አስረስ ባያው ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ መስፍን ታምራት - ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የፋዳራል የመጀመሪያ ፍ/ቤትና የከፍተኛ ፍ/ቤት የሰጡት የአፈፃፀም ትዕዛዝ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት ስላመለከቱ ነው። የክርክሩ መነሻ አመልካች የፍርድ ባለመብት የሆኑበትን እዲ ለማስከፈያ እንዱሆን የፍርድ ባለእዲው የተጠሪው ንብረት የሆነ ቤት እንዱሸጥላቸው አመልካች አመልክተዋል። ቤቱ በፍርድ ባለእዲው ልጅ ተማሪ ማራማዊት መስፍን ስም ስሙ ተዛውሮና ተመዝግቦ የተገኘ መሆኑ ተረጋግጧል። አመልካች ተጠሪ ቤቱን የእዲ መክፈያ እንዲይሆን ለማሸሽ ያደረጉት ድርጊት በመሆኑ በልጃቸው ተማሪ ማራማዊት መስፍን ስም ተመዝግቦ የሚገኘው ንብረት ተሸጦ ፍርደ እንዱፈፀምልኝ በማለት ተከራክረዋል። የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አመልካች ለፍርድ ማስፈፀሚያነት እንዱውል የጠየቁት ቤት በፍርድ ባለ እዲው ስም ሳይሆን በተማሪ ማሪማዊት መስፍን ስም የሚገኝ በመሆኑ አፈፃፀሙን በቤቱ ላይ ማስቀጠል አይቻልም በማለት ትዕዛዝ ሰጥቷል። አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለከፍተኛ ፍ/ቤት አቅርበዋል። የከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኙን በፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 337 መሰረት ሰርዞታል።
አመልካች የፍርድ ባለእዲ የሆነው ተጠሪ ቤቱን ለእዲ መክፈያ እንዲይሆን ለማሸሽ በማሰብ ምንም አይነት ሐብት ለላላት አካለ መጠን ላልደረሰች ልጁ የቤቱን ስመ ንብረት በማዛወር የፈፀመው ተግባር መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት አመልክተዋል። ተጠሪ በበኩለ ቤቱ የማራማዊት መስፍን ነው። ለዚህም ቤቱ የማራማዊት መስፍን መሆኑን የሚያረጋግጥ ውልና የቤቱ ክፍያ የተከፈለባቸው ወርሀዊ ደረሰኞች ስላለ ቤቱ የፍርድ ማስፈፀሚያ እንዱሆን ያቀረቡት ክርክር ተገቢነት የለውም በማለት መልስ ሰጥቷል። አመልካች የመልስ መልስ በጽሐፍ አቅርበዋል።
ከስር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የቀረበው ክርክር የተገለፀው ሲሆን ተጠሪ የፍርድ ባለእዲ የሆነበትን ገንዘብ ለመክፈል ጥረት በሚደረግበት ጊዜ ቤቱ የተጠሪ ልጅ በሆነችው ህፃን ማራማዊት መስፍን ስም የተዛወረ መሆኑ የስር ፍ/ቤት በሰጠው ትዕዛዝ ተረጋግጧል። የቤቱ ባለቤት ናት ቤቱም በስሟ ተመዝግቧል የምትባለው ማራማዊት መስፍን ህፃን መሆኗን የስር ፍ/ቤት በሰጠው ትዕዛዝ ተረጋግጧል።
አንድ ሰው የንብረት ባለቤት የሚሆነው በጉልበቱ በፈጠራ ችልታው ወይም በገንዘቡ ንብረቱን ያፈራው ሲሆን እንደሆነ በህገ መንግስቱ አንቀጽ 40 ንዐስ አንቀጽ 2 ተደንግጓል። በተጠሪና በተጠሪ ባለቤት በወ/ሮ አለም ዘውደ ዘርፈ ስም ተመዝግቦ የነበረው ቤት በህፃን ልጃቸው በህፃን ማራማዊት መስፍን ስም አዛውረው ቤቱን በህፃን ማራማዊት ስም አስመዝግበው መገኘታቸው ብቻውን ህፃን ማራማዊት መስፍን የቤቱ ባለሐብት ናት ከሚለው መደምደሚያ ላይ የሚያደርስ አይደለም። ይልቁንም ተጠሪ በፍርድ የተወሰነበትን እዲ መክፍያ እንዲይሆን ቤቱን በራሷ መንገድ ሰርታ ባገኘችው የገቢ ምንጭ የገዛችው ስለመሆኗ ሳያረጋግጥ የንብረቱ በህፃን ልጅ ስም በማዛወር ለፍርድ ማስፈፀሚያነት ንብረቱ እንዲይውል ለማሸሽ የሞከረ መሆኑን የሚያመለክት ተግባር ነው።
የፍርድ ባለእዲ የሆነ ሰው ንብረቱ ለፍርድ ማስፈፀሚያነት እዲይውል አካለ መጠን ባልደረሰ ህፃን ልጁ ስም እያዛወረ መልሶ ንብረቱን በሞግዚትነት የሚያስተዲድርበት የሚሸጥበትና የሚለውጥበትን ሁኔታን ህጋችን አይፈቅድም። ባለእዲው መክፈል የሚገባውን እዲ ባለመክፈል በአጭበርባሪነት የሚፈጽማቸውን ተግባራት የፍርድ ባለመብት ወይም ገንዘብ ጠያቂው የመቃወምና እዲውን ላለመክፈል ያደርገው ተግባር መሆኑን ለማሳየት በማጭበርበር የተሰራው ስራ ዋጋ እንዲይኖረውና ባለእዲው እዲውን እንዱከፍል ማድረግ የሚቻል ስለመሆኑ በፍታብሓር ህግ ቁጥር 1895 እና ከፍታብሓር ህግ ቁጥር 1896 ድንጋጌዎች ለመረዲት ይቻላል። በዚህ መዝገብ በተጠሪና በአመልካች ስም የነበረውን ቤት ተጠሪ በህፃን ልጁ ለማራማዊት መስፍን ስም ማዛወሩ ንብረቱ የፍርድ ማስፈፀሚያ እንዲይሆን ለማድረግ የተፈፀመ የማጭበርበር ተግባር ነው በማለት አመልካች ያቀረቡትን አቤቱታ ውድቅ በማድረግ የበታች ፍ/ቤቶች የሰጡት ትዕዛዝ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ወስነናል።
የፋዳራል መጀመሪያ ፍ/ቤትና የከፍተኛ ፍ/ቤት ትዕዛዝ ተሽሯል።
በመጀመሪያ በተጠሪና በባለቤታቸው ወ/ሮ ዓለም ዘውድ ዘርፈ በአሁኑ ጊዜ በህፃን ማሪማዊት መስፍን ስም ተመዝግቦ የሚገኘው ቤት አመልካች በፍርድ ያስወሰኑትን ገንዘብ ማስፈፀሚያ እንዱሆንና የሥነ ሥርዓት ሕጉ በሚፈቅደው መሰረት በሐራጅ በማሸጥ እንዱያስፈጽም ጉዲዩን ለፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 343/1/ መሰረት መልሰን ልከንለታል።
በዚህ ፍ/ቤት ያወጡትን ወጭና ኪሳራ ግራ ቀኙ ለየራሳቸው ይቻለ።
No topics extracted.