No summary available.
ጥቅምት 16 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሐጎስ ወልደ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- የኢትዮጵያ መንገድች ባለሥለጣን የቀረበ የለም ተጠሪ፡- እነ አቶ ከድር ኃላጅንሶ /አስራ ሁለት ሰዎች/- ጠበቃ አማን ቡልቡላ ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የመሬት ይዞታ ካሣ ጥያቄን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ ተጠሪዎች በአሁኑ አመልካች ላይ በአርሲ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ታህሣሥ 13 ቀን 1998 ዓ.ም በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው። በክሱ ተጠሪዎች እያንዲንዲቸው 6666 ካሬ ሜትር የሆነው የእርሻ መሬት ይዞታ የነበራቸው መሆኑን፣ አመልካች በዚሁ የእርሻ መሬት ላይ ጥቅምት ዐ5 ቀን 1997 ዓ.ም ካምፔ ያሰፈረበት መሆኑን፣ እያንዲንዲቸው በመሬቱ ላይ በሄክታር ሰላሣ ኩንታል ስንዳ የሚያገኙ መሆኑን፣ በወቅቱ የአንድ ኩንታል ስንዳ ብር 2ዐዐ.ዐዐ /ሁለት መቶ ብር/ መሆኑን ገልፀው የአምስት ዓመት ምርት በጠቅላላው ብር 24ዐ,ዐዐዐ.ዐዐ /ሁለት መቶ አርባ ሺህ ብር/ እንደሚያወጣ ጠቅሰው አመልካች በአዋጅ ቁጥር 455/97 አንቀጽ 7 እና 8 መሰረት ካሣውን እንዱከፍላቸው ይወሰን ዘንድ ዲኝነት ጠይቀዋል። የአሁኑ አመልካችም ተጠሪዎች የመሬቱን ባለይዞታ መሆናቸውን የሚያሣይ ማስረጃ ስላላቀረቡ ለመክሰስ የማይችለ መሆኑን በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት ያቀረበ ሲሆን በፍሬ ነገር ደረጃ ደግሞ ካምፐ የሰፈረበትን መሬት የሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት የተረከበ መሆኑን፣ ካምፐ ከሰፈረሰበት መሬት ውስጥም 2ዐ794.5 ካ.ሜትር ላይ ብቻ መኖሩን የሚመለከተው አካል አረጋግጦ በአዋጅ ቁጥር 8ዐ/89 እና 4ዐ1/96 መሰረት ተገቢው ካሣ መከፈለን፣ በቀሪው 79,2ዐ5.5 ካ.ሜትር ላይ ግን መሬቱ ባድ ስለሆነ የወረዲ አስተዲደርም ሆነ የቀበላ አስተዲደር ያነሱት የካሣ ጥያቄ ሣይኖር መሬቱን የተረከቡ መሆኑንና በዚሁ ይዞታ ላይ የቀረበው ክስ በተጨባጭ ማስረጃ ተደግፍ ያልቀረበ መሆኑን ዘርዝሮ ክሱ ውድቅ ላሆን ይገባል ሲል ተከራክሯል። የስር ፍርድ ቤትም የተጠሪዎችን ምስክሮችን ከሰማ እና መሬቱ እህል የሚያበቅል መሆን ያለመሆኑን ከሚመለከተው አካል ማጣራት ከአደረገ በኋላ የአመልካችን ክርክር ውድቅ አድርጎ ለካሣው በአዋጅ ቁጥር 4ዐ1/96 መሰረት ኃላፉነት አለበት የሚል ምክንያት በመስጠት ለክሱ መሰረት የሆነውን የገንዘብ መጠን አመልካች እንዱከፍል ሲል ወስኗል። በዚህ ውሣኔ አመልካች ባለመስማማት ይግባኙን ለኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቅርቦ ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ የስር ፍርድ ቤት ውሣኔ ፀንቷል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሣኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
የአመልካች ነገረፈጅ የካቲት ዐ3 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም በፃፈት ሦስት ገጽ የሰበር አቤቱታ በበታች ፍርድ ቤቶች ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል የሚለበትን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም ባጭሩ ተጠሪዎች በአከራካሪው የመሬት ይዞታ መብት ያላቸው ስለመሆኑ ሣያረጋግጡ እና መሬቱ በተወሰደበት ሰዓትም በይዞታው ላይ ምንም ሰብል በላለበት ሁኔታ የአምስት ዓመት ካሣ ይከፈላቸው ተብል የተወሰነው ከሕጉ ውጭ ስለሆነ ሉታረም የሚገባው ነው በማለት መከራከራቸውን የሚያሣይ ነው። የሰበር አቤቱታው ተመርምሮም ተጠሪዎች በይዞታው ላይ መብት ወይም ጥቅም የነበራቸው ስለመሆኑ የተረጋገጠ መሆን አለመሆኑ እና ከአዋጅ ቁጥር 4ዐ1/96 አኳያ ካሣ ይከፈል የመባለን አግባብነት ለመመርመር ሲባል ለሰበር ችልቱ እንዱቀርብ ተደርጓል።በዚህም መሰረት ተጠሪዎች በወኪልቻቸው አማካኝነት ሐምል 14 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም በተፃፈ ማመልከቻ የጽሐፍ መልስ የሰጡ ሲሆን የአመልካች ነገረፈጅ በበኩላቸው ሐምል 3ዐ ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም በተፃፈ ማመልከቻ የመልስ መልሣቸውን ሰጥተዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሣኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩ ለሰበር ችልት ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው ተጠሪዎች ክሱን የመሰረቱት የእርሻ መሬት ይዞታችን በአመልካች ለሕዝብ ጥቅም ሲባል ተወስድ ካሣ ስላልተከፈለን ሉከፈለን ይገባል በሚል መሆኑን፣ አመልካችም ተጠሪዎች ክስ ለመመሥረት የሚያስችላቸው መብት ወይም ጥቅም የላላቸው መሆኑንና ለክሱም በአጠቃላይ ሕጋዊ ኃላፉነት የላለበት መሆኑን በመጥቀስ የተከራከሩ መሆኑን ነው።
አመልካች ተጠሪዎች ክስ ለመመሥረት መብት ወይም ጥቅም የላቸውም በሚል ያቀረበው ክርክር የበታች ፍርድ ቤቶች ውድቅ ያደረጉበትን አግባብ ይህ ችልት ለመመርመር የሚችል መሆን ያለመሆኑን ስንመለከተው ፍሬ ነገር የማጣራትና ማስረጃን የመመዘን ሥልጣን ያላቸው የስር ፍርድ ቤቶች ተጠሪዎች በይዞታው ላይ መብት የነበራቸው መሆኑን በማስረጃ ማረጋገጣቸውን መሰረት በማድረግ የአመልካችን ክርክር ውድቅ ያደረጉ መሆኑን ተመልክተናል። አመልካች የማስተባበያ ማስረጃም ከሚመለከተው አካል አላቀረበም። አመልካች አጥብቆ የሚከራከረው ይዞታውን ተጠሪዎች ቀበላ አስተዲደሩ በፃፈው አንድ ደብዲቤ እና የግብር ካርኒዎች ብቻ ሉያረጋግጡ አይገባም የሚል እንድምታ ያለውን ክርክር በማቅረብ ነው። ይሁን እንጂ የቀበላ አስተዲደሩ የፃፈው ደብዲቤና የግብር ካርኒ ይዞታን ለማረጋገጥ አግባብነት የላለው ማስረጃ ነው ለማለት የሚያስችል የሕግ መሰረት የለም። በአጠቃላይ ተጠሪዎች በይዞታው ላይ መብት ወይም ጥቅም ያላቸው መሆኑን ፍሬ ነገርን የማጣራትና ማስረጃን የመመዘን ሥልጣን ያላቸው የበታች ፍርድ ቤት ያረጋገጡት ጉዲይ በመሆኑ ይህ ችልት በኢ.ፋ.ዱ.ሪፐብላክ ሕግ መንግሥት አንቀጽ 8ዐ/3/ሀ/ እና አዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 1ዐ ድንጋጌዎች የተሰጠው ስልጣን መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ማረም በመሆኑ ፍሬ ጉዲዩን ለማጣራት አልተቻለም። በመሆኑም በዚህ ረገድ የቀረበውን የአመልካችን ክርክር አልፈነዋል።
አመልካች አጥብቆ የሚከራከረው ላላውና ዋናው ነጥብ ተጠሪዎች ካሣ እንዱከፈላቸው መወሰኑ ከአዋጅ ቁጥር 4ዐ1/96 መንፈስና ይዘት ውጪ ነው የሚለው ሲሆን ይህ ችልት ይህንኑ የክርክር ነጥብ ከሕጉ ጋር አዛምድ ተመልክቷል። አመልካች የተጠሪዎች የእርሻ መሬት ይዞታ ወሰደ ተብል የተረጋገጠው ጥቅምት ዐ5 ቀን 1997 ዓ.ም ሲሆን ተጠሪዎች ክሱን የመሰረቱት ታህሣሥ 13 ቀን 1998 ዓ.ም ነው። እንዱሁም አመልካች ወሰደ የተባለው መሬት በወቅቱ እህል ማብቀል የሚችል መሆን ያለመሆኑ በሚመለከተው አካል ከመረጋገጡ ውጪ በአመልካች ሲወሰድ የስንዳ አዝመራ የነበረበት አለመሆኑ በበታች ፍርድ ቤቶች ተረጋግጧል። አመልካች በባድ የእርሻ ይዞታ መሬት ካሣ የመክፈል ኃላፉነት አለበት የተባለው መሬቱ ወደፉት ሉዘራበትና ሉመረትበት የሚችል ነው በሚል ምክንያት መሆኑን የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ውሣኔ እና ከአጠቃላይ የክርክሩ ሂደት ተገንዝበናል። እንግዱህ ጉዲዩ እንዱህ ከሆነ አግባብነት ያለው ሕግ የትኛው ነው? በዚሁ ሕግ መሰረትስ አመልካች ካሣ የመክፈል ግዳታ አለበት? ወይንስ የለበትም?
የሚለው ጥያቄ መታየት ያለበት ነው።
አመልካች የተጠሪዎችን የእርሻ ይዞታ መሬት መወሰደ በተረጋገጠበት ጥቅምት ዐ5 ቀን 1997 ዓ.ም ስራ ላይ የነበረውና ለጉዲዩ አግባብነት ያለው አዋጅ ቁጥር 4ዐ1/96 ነው። ተጠሪዎች ክስ የመሰረቱት ታህሣሥ 13 ቀን 1997 ዓ.ም ሲሆን በዚህ ወቅት ስራ ላይ ያለው ለሕዝብ ጥቅም ሲባል የመሬት ይዞታ ስለሚለቀቅበትና ለንብረት ካሣ የሚከፈልበትን ሁኔታ ለመወሰን የወጣው አዋጅ ቁጥር 455/97 መሰረት ነው። ተጠሪዎች ከጉዲዩ አግባብነት አለው በማለት የሚከራከሩትም ክስ በመሰረቱበት ወቅት ተፈፃሚ የሆነውን ይህንኑ ሕግ ነው። ይሁን እንጂ ይህ አዋጅ ተፈፃሚነት እንዱኖረው የተደረገው ከሐምል ዐ8 ቀን 1997 ዓ.ም ጀምሮ ሲሆን በመሸጋገሪያ ድንጋጌም አዋጅ ቁጥር 4ዐ1/96 ተፈፃሚነት በነበረበት ወቅት የተወሰደ የመሬት ይዞታ ጉዲዮች በአዋጅ ቁጥር 455/97 መሰረት የሚታዩበት አግባብ ስለመኖሩ አላስቀመጠም። ስለሆነም ጉዲዩ መታየት ያለበት መሬቱ ተወሰደ በተባለበት ወቅት ስራ ላይ በነበረው አዋጅ ቁጥር 4ዐ1/96 መሰረት ሁኖ ተገኝቷል።
በዚህ አዋጅ አንቀጽ 9/1/ መሰረት መሬት የሚወሰድበት ባለይዞታ በገንዘቡ፣በጉልበቱ፣ ወይም በፈጠራ ችልታው ላፈራውና በመሬቱ ላይ ለሚገኘው ንብረት እንዱሁም ላደረገው ቋሚ ማሻሻል ካሣ ይከፈለዋል በሚል የተደነገገ ሲሆን የዚሁ አንቀጽ ንዐስ ቁጥር ሁለት ድንጋጌ ደግሞ ከባለይዘታው በሚወሰደው መሬት ላይ ለሚገኝ ንብረት የሚከፈል ካሣ ንብረቱን ለመተካት ከሚያስፈልገው ወጪ ጋር ተመጣጣኝ ይሆናል ሲል ደንግጓል። ከዚህ ድንጋጌ የምንገነዘበው አቢይ ነጥብ የካሣ መሰረትና መጠን የሚወሰነው በይዞታው ላይ ንብረት ያለ መሆኑ ሲረጋገጥ መሆኑን ነው። ሆኖም መሬቱ ሲወሰድ ንብረት ያልነበረ ከሆነ ካሣ ሉከፈል ይገባል ወይስ አይገባም የሚለው ጥያቄ ምላሽ የሚያገኘው በአዋጁ አንቀጽ 1ዐ መሰረት ነው። ይህ ድንጋጌ የመሬት ይዞታው በቋሚነት የሚወሰድበት ሰው በመሬቱ ላይ ሰብል ወይም ተክል ቢኖርም ባይኖርም ተመሣሣይ መሬት ያለው ሰው የሚያገኘው አማካይ ገቢ በአዋጁ አንቀጽ 9 ከሚከፈለው ካሣ በተጨማሪ የሚከፈለው ስለመሆኑ በመርህ ደረጃ በንዐስ ቁጥር አንድ ስር ያስቀመጠ ሲሆን ዝርዝሩም በደንብ እንደሚወሰን ያሣያል።
የተጠቀሰው አንቀጽ ንዐስ ቁጥር ሁለት ድንጋጌም የመሬቱ ይዞታው ለተወሰነ ጊዜ ለሚወሰድበት ሰው ወይም ለወል መሬት ባለይዞታዎች በመሬቱ ላይ ሰብል ወይም ተክል ቢኖርም ባይኖርም መሬቱ ባይለቀቅ ኖሮ ከመሬቱ ሉገኝ ይችል የነበረው ገቢ መሬቱ እስከሚመለስ ድረስ ላለው ጊዜ ታስቦ በአዋጁ አንቀጽ ዘጠኝ መሰረት ከሚከፈለው ካሣ በተጨማሪ እንደሚከፈል፣ በአንቀጽ አስር ንዐስ ቁጥር አንድ ድንጋጌ ከሚከፈለው ክፍያ መብለጥ እንደላለበትና ዝርዝሩም በደንብ እንደሚወሰን ደንግጓል። በአዋጁ አንቀጽ አስር ንዐስ ቁጥር አንድ እና ሁለት የተቀመጡት ድንጋጌዎች ተፈፃሚ የሚሆኑት የመሬት ባለይዞታው ለተወሰደበት ሰው ተተኪ መሬት ያልተገኘለት መሆኑን አግባብ ያለው የመስተዲድር አካል ሲያረጋግጥ ብቻ እንደሆነ ተጠቃሹ ድንጋጌ በንዐስ ቁጥር ሦስት ስር በግልጽ አስቀምጧል። ለተጠሪዎች ካሣ እንዱከፈል የስር ፍርድ ቤቶች የወሰኑት ደንቡን መሰረት በማድረግ ባይሆንም ይዞታው ምን አይነት ሰብል እና ምን ያህል መጠን ሉያስምርት እንደሚችል ከሚመለከተው የክፍለ አካል የስር ፍርድ ቤት ማረጋገጫ እንዱቀርብለት አድርጎ ባጣራው መሰረት ነው። ተጠሪዎች ለተወሰደባቸው መሬት ይዞታ ተተኪ መሬት የተገኘላቸው ወይም የተሰጣቸው ስለመሆኑ አልተረጋገጠም፣ አመልካችም በዚህ ረገድ ያቀረበው ክርክር የለም፣ በስር ፍርድ ቤትም የሚመለከተው አካል ለተጠሪዎች ተተኪ መሬት የተገኘላቸው ስለመሆኑ የገለፀው ነገር የለም።
በመሆኑም ተጠሪዎች በአዋጁ አንቀጽ አስር ንዐስ አንቀጽ አንድ፣ ሁለት እና ሶስት ድንጋጌዎች ጣምራ ንባብ መሰረት የመፈናቀያ ካሣ የማያገኙበት ሕጋዊ ምክንያት የለም። በመጨረሻ የተወሰነው የመፈናቂያ ካሣ መጠን ሲታይም የተጋነነ ወይም ከክፍለ አካል ከቀረበው ማረጋገጫ ይዘት ውጪ ነው ለማለት የሚያስችልም አይደለም። በመሆኑም ተጠሪዎች ባለይዞታ ስለመሆናቸው ተረጋግጧል እስከተባለ ድረስ በቦታው ላይ ሰብል ሣይኖር ቦታውን አመልካች መውሰደ የመፈናቂያ ካሣ ለተጠሪዎች እንዱከፈል የሚያደርግ ስለመሆኑ የአዋጅ ቁጥር 4ዐ1/96 አንቀጽ 9 እና 1ዐ ድንጋጌዎች ጣምራ ንባብ እና የኢ.ፋ.ዱ.ሪፐብላክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 4ዐ/7/ ድንጋጌ ይዘትና መንፈስ የሚያስገነዝቡን ጉዲይ ሆኖ ስለአገኘን በጉዲዩ ላይ በተሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል ለማለት አልተቻለም። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በጉዲዩ ላይ በበታች ፍርድ ቤቶች የተሰጠው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348/1/ መሰረት ፀንቷል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሣቸውን ይቻለ ብለናል።
በዚህ ችልት የካቲት ዐ5 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም ተሰጥቶ የነበረው እግድ ተነስቷል።
No topics extracted.