No summary available.
ጥቅምት 03 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች- ተገኔ ጌታነህ ሐጏስ ወልደ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድአመልካች፣ ወ/ሮ አባዱት ለምለም የቀረበ የለምተጠሪዎች፣ 1. የዛለአንበሳ ከተማ አስተዲደር ጽ/ቤት ወኪል አለምፀሐይ ግርማይ ቀረቡ 2. አቶ ብርሃን ዘረፈ በላለበት **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ ቤትና ቦታን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በምስራቅ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአሁኑ አመልካች በአሁኑ ተጠሪዎች ላይ በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው። የክሱ ይዘትም ባጭሩ፡በአግባቡ በዛላንበሳ አስተዲደር የታደልኩትን በራሴ ተጨማሪ ገንዘብ ደግሞ የሰራሁትን በስሜ በርዕስተ መዝገብ የተመዘገበውን ቤትና ቦታ አስተዲደሩ ነጥቆ ለአሁኑ 2ኛ ተጠሪ የሰጣቸው መሆኑን ገልፀው ገንዘቡና ቤቱ እንዱመለስላቸው ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። የአሁኑ 1ኛ ተጠሪ ለክሱ በሰጠው መከላከያ መልስ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያና የፍሬ ነገር ክርክር አቅርቧል።
በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት ያቀረበውም አመልካች ቦታና ገንዘብ የተሰጣቸው በጦርነት ምክንያት ቤት ስለወደመባቸው መንግስት ምትክ ቦታና ገንዘብ እንዱሰጥ በአስተላለፈው አስተዲደራዊ ውሣኔ በመሆኑና ይህም ውሣኔ ፕለቲካዊ በመሆኑ በፍርድ ቤት ላታይ እንደማይችል በመግለፅ አመልካች ክስ ለመመስርት የሚያስችላቸው ሕጋዊ ምክንያት የላለ መሆኑን ያሳያል በማለት ያቀረበው ክርክር ሲሆን በፍሬ ነገር ደረጃም የአመልካች ጥያቄ በአስተዲደሩ ተጣርቶ ቤትና ገንዘብ ከመንግስት ሉያገኙ የማይችለበት ምክንያት በመገኘቱ ውድቅ የሆነ መሆኑን ጠቅሶ ተከራክሯል።
የአሁኑ 2ኛ ተጠሪም ቤትና ገንዘቡን የመንግስት አስተዲደር አካላት በሰጡት ውሣኔ መሰረት የተሰጣቸውና የተረከቡት በመሆኑ ሉከሰሱ እንደማይገባ ገልፀው ክሱ ውድቅ ላሆን ይገባል ሲለ ተከራክረዋል። ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍርድ ቤትም የግራቀኙን ክርክርና ማስረጃ ሰምቶና መርምሮ ለክሱ ምክንያት የሆነው ቤትና ገንዘብ ለአመልካች ሉመለስላቸው እንደሚገባ ገልፆ ውሣኔ ሰጥቶበታል። በዚህ ውሣኔ የአሁኑ 2ኛ ተጠሪ ባለመስማማት ይግባኛቸውን ለትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቅርበው ግራቀኙ ከተከራከሩ በሁዋላ ጉዲዩ ተመርምሮ በአስተዲደራዊ ውሣኔ የሚያልቅ እንጂ በፍርድ ቤት የሚታይ አይደለም በሚል ምክንያት የስር ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ ተሽሯል። ከዚህም በኋላ አመልካች የሰበር አቤቱታቸውን ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ቢያቀርቡም ተቀባይነት አላገኙም። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሣኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
የአመልካች ጠበቃ መጋቢት 30 ቀን 2001 ዓ.ም በጻፈት ሁለት ገጽ የሰበር አቤቱታ በጉዲዩ ላይ በተሰጠው ውሣኔ መሰታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈፅሟል የሚለበትን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም ባጭሩ፡- የአመልካች ጥያቄ ቤትና ገንዘብ ያላግባብ ተነጠቅሁ የሚል ሁኖ እያለ በፍርድ ሉያልቅ የሚችል አይደለም በሚል ምክንያት የስር ፍርድ ቤት ውሣኔ መሻሩ ያላግባብ ስለሆነ ሉታረም የሚገባው ነው በማለት መከራከራቸውን የሚያሳይ ነው። አቤቱታው ተመርምሮም በይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤትና በሰበር ሰሚ ችልት ክርክሩ አስተዲደራዊ ስለሆነ በፍርድ ቤት መዲኘት የለበትም በማለት የስር ፍርድ ቤት ውሣኔ መሻሩ ባግባቡ መሆን ያለመሆኑን ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ችልት እንዱቀርብ ተደርጏአል። በዚህም መሰረት ለተጠሪዎች መጥሪያ ተልኮላቸውና መድረሱም ተረጋግጦ ሉቀርቡ ስላልቻለ ጉዲዩ ተጠሪዎች በላለበት እንዱታይ ተደርጓል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም በበታች ፍርድ ቤቶች ግራቀኙ ያደረጉትን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሣኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩ ለሰበር ችልቱ ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንጻር በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው በዛላንበሳ አካባቢ በጦርነት ምክንያት ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው ለነበሩት ዜጎች ማቋቋሚያ የሚሆን መሬትና የብር 25,000.00 /ሃያ አምስት ሺህ/ ቤት መስሪያ እርዲታ ለመስጠት የተለያዩ አካላት ተወካዮች ያለበት ኮሚቴ ማቋቋሙን መንግስት ባወጣው የችግረኛ ተረጂዎች መለያ መስፈርት መሰረት በጦርነቱ ተፈናቅለው በፔላስቲክ ዲስ የሚኖሩ 969 ተፈናቃዮች በዕዲ መሬት ተሰጥቷቸው ገንዘቡም በየደረጃው በሶስት ጊዜ እንዱሰጥ ተወስኖ ብር 7,500.00 በማቋቋሚያ ኮሚሽን መስጠቱን አመልካችም በጦርነቱ ምክንያት ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው በፔላስቲክ ዲስ የሚኖሩና ለተረጂነት የሚያሟለ መሆኑ ተረጋግጦ መሬት ተሰጥቷቸው በስማቸው በማዘጋጃ ቤት ተመዝግቦ የመሬት ኪራይ ካርታ የፅዲት የቤት ስራ ፈቃድ የቴክኒክ አገልግልት የችካል የይዞታ ማረጋገጫ ክፍያዎችን በሙለ ከፍለው ከመንግስት በእርዲታ የተሰጣቸውን ብር 7,500.00 እና ከራሳቸው ብር 7000.00 ጨምረው በብር 14,500.00 የቆርቆሮ ክዲን እስኪቀረው ቤቱን ሰርተው ከጨረሱ በኃላ ኤርትራዊ ነሽ በሚል ምክንያት 1ኛ ተጠሪ ከአመልካች ነጥቆ ለሁለተኛ ተጠሪ እንዱሰጥ ማድረጉን ገልፀው የሚከራከሩ መሆኑን ነው። ከዚህ ሁለ መገንዘብ የተቻለው አመልካች የሚከራከሩት በመንግስት በተሰጣቸው ቦታና ገንዘብ የራሳቸውን ገንዘብ ጨምረው የገነቡት ቤትና ቦታ ያላግባብ የተነጠቁ በመሆኑ በፍርድ ኃይል እንዱመለስላቸው ይወሰንላቸው ዘንድ ዲኝነት መጠየቃቸውን ነው።
በመሰረቱ በፋዳራልም ሆነ በክልል የዲኝነት ስልጣን የፍ/ቤቶች ብቻ ስለመሆኑ በኢ.ፋ.ዱ.ሪፐብላክ ሕገ መንግስት አንቀጽ 79/ለ/ ተደንግጓል። የሕገመንግስቱ አንቀጽ 37 ድንጋጌ ሲታይ ደግሞ ፍ/ቤቶች በማናቸውም ጉዲይ ገደብ የለሽ ስልጣን የላላቸው መሆኑም ተመልክቷል።
በዚህም መሰረት የሕገመንግስቱ አንቀጽ 79/ለ/ እና 37 አንድ ላይ ሲታዩ ፍ/ቤቶች አንድን ጉዲይ ተቀብለው ለማየትና ለመወሰን ሥልጣን የሚኖራቸው ጉዲዩ በፍርድ ሉወሰን የሚገባው /Justiciable matter/ ሆኖ ከተገኘ ብቻ መሆኑን ያስገነዝባለ። የሕገ መንግስቱ አንቀጽ 37 ድንጋጌ ንዐስ ቁጥር 1 ‛ማንኛውም ሰው በፍርድ ሉወሰን የሚገባውን ጉዲይ ለፍርድ ቤት ወይም ለላላ በህግ የዲኝነት ሥልጣን ለተሰጠው አካል የማቅረብና ውሣኔ ወይም ፍርድ የማግኘት መብት አለው።“ በሚል ከተደነገገው ‛…. ወይም ለላላ በህግ የዲኝነት ሥልጣን ለተሰጠው አካል…..“ የሚለው እንዱሁም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 4 በልላ እኳኋን እንዱፈፀም በህግ ካልተገለፀ ክሱን ተቀብል ለማከራከር ሥልጣን ያለው ፍ/ቤት ብቻ ነው በሚል መደንገጉ በፍርድ ሉወሰን በሚችለው ጉዲይ ፍ/ቤቶች ብቸኛ ስልጣን ያላቸው መሆኑን የሚያስገነዝብ ነው። በመሆኑም ፍ/ቤቶች አንድን ጉዲይ ተቀብለው ማየት የሚችለት ጉዲዩ በፍርድ የሚያልቅ ሲሆንና በልላ አኳኋን እንዱታይ በሕግ እስካልተወሰነ ድረስ ነው።
ወደተያዘው ጉዲይ ስንመለስም የአመልካች ጥያቄ ቤትና ቦታዬን ያላግባብ ተነጠቅሁ የሚልና በፍርድ ኃይል የንብረት መብቻው እንዱከበርላቸው የሚጠይቅ ነው። እንዱህ አይነት ጉዲይ በፍርድ እንዲያልቅ የሚከለክል ሕግ የላለ ሲሆን ጉዲዩ አስተዲደራዊ ነው ልባል የሚችልበት ሕጋዊ ምክንያትም የለም። ጉዲዩን እንዱዲኝ በሕግ ተለይቶ ስልጣን የተሰጠው አካልም የለም። በመሆኑም ጉዲዩ በፍርድ ሉወሰን የሚገባው /Justiciable matter/ ጉዲይ እንጂ በአስተዲደር የሚያልቅ ጉዲይ አይደለም። በመሆኑም ጉዲዩ በአስተዲደር የሚያልቅ ነው በሚል ምክንያት የስር ፍርድ ቤት ውሣኔ በይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት መሻሩና የክልለ ሰበር ሰሚ ችልትም ይህንኑ ውሣኔ ማጽደቁ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ሆኖ አግኝተናል። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
No topics extracted.