No summary available.
ሰኔ 30 ቀን 1998 ዓ.ም ዳኞች፡- ከማል በድሪ ዓብደልቃድር መሐመድ ጌታቸው ምህረቴ መስፍን ዕቁበዮናስ ሂሩት መለሰ አመልካች፡- አቶ ፊንታሁን አባተ - ቀረቡ ተጠሪ፡- አቢሲኒያ ባንክ አ/ማ - ቀረቡ (ነ/ፈጅ እስክንድር)
ለሰበር አቤቱታ መነሻ የሆነውን ውሣኔ የሰጠው የፋ/መ/ደረጃ ፍርድ ቤት ነው።
አመልካች በተጠሪ ላይ ባቀረቡት ክስ በስራ ላይ ለነበሩበት ጊዜ የተከፈለው የሁለት ወራት ቦነስ እንዱከፈላቸው ጠይቀዋል። ፍ/ቤቱም የቦነስ ክፍያ ዋና አላማው ሰራተኛ በስራ ላይ በነበረበት ወቅት የሰራው ስራ ለአሰሪው ጥሩ ውጤት አስገኝቶ ከሆነ በስራ ላይ ያለው ሰራተኛ ለወደፉት ውጤታማ እንዱሆን ለማበረታታት እንጂ ስራውን የለቀቀ ሰራተኛ እንደመብት የሚጠይቀው አይደለም በማለት ጥያቄውን ውድቅ አድርጏታል። ይግባኝ የቀረበለት የፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤትም የቀረበውን ይግባኝ ሳይቀበለው ቀርቷል።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም በዚህ ውሣኔ ላይ ነው። ይህ ችልትም አመልካች በስራ ላይ ለነበሩበት ጊዜ የተከፈለውን የቦነስ ክፍያ ለአመልካቹ ስራ በመልቀቃቸው ሉከፈላቸው አይገባም የተባለበትን ህጋዊ ምክንያት በመመርመር አቤቱታው ለሰበር እንዱቀርብ አድርጓል። በዚሁ መሰረት ተጠሪ ተጠርቶ ቀርቦ ግራ ቀኙ የጽሐፍ ክርክራቸውን አቅርበዋል። ይህ ችልትም አቤቱታ የቀረበበትን ውሣኔ አግባብነት ካለው ህግ ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለው መርምሯል።
ከፍ ሲል እንደተገለፀው በዚህ መዝገብ አከራካሪ የሆነው አመልካች ስራ ላይ በነበሩበት ወራት ለተሰራ ስራ የተከፈለው ቦነስ አመልካች ከሥራ ከተሰናበቱ በኋላ ሉከፈላቸው የሚገባ መሆን አለመሆኑ ነው።
አመልካች የተጠሪ መ/ቤት ሰራተኛ የነበሩና በገዛ ፈቃዲቸው ሥራቸውን ከለቀቁ በኋላ አመልካቹ በሥራ ላይ በነበሩበት ጊዜ ለተሰራ ሥራ የቦነስ ክፍያ ለተጠሪ መ/ቤት ሰራተኞቹ መክፈለ ግራ ቀኙ አልተካካደም። ፍ/ቤቶቹ የአመልካችን ጥያቄ ውድቅ ያደረጉት የአመልካች የሥራ ውል በተቋረጠበት ጊዜ የተፈቀደ የቦነስ መብት ካለመኖሩም በላይ የቦነስ አላማው ሰራተኛው በሥራ ላይ በነበረበት ወቅት የሰራው ሥራ ለአሰሪው ጥሩ ውጤት አስገኝቶ ከሆነ ለወደፉትም በተመሳሳይ መልኩ በርትቶ ውጤታማ እንዱሆን ለማበረታታት እንጂ ስራውን የለቀቀ ሰራተኛ እንደመብት የሚጠይቀው አይደለም በማለት ነው።
እኛም ጉዲዩን እንደተመለከትነው ቦነስ የሚከፈለው በስራ ላይ ያለ ሰራተኛ ወደፉት በርትቶ እንዱሰራ ለማበረታታት ብቻ ሳይሆን ሰራተኛው በስራ ላይ በነበረበት ወቅት የሰራው ሥራ ለአሰሪው ትርፊማ ውጤት በማስገኘቱ የትርፈ ተጠቃሚ እንዱሆንም ጭምር የሚሰጥ የጥቅም ክፍያ ነው። በመሆኑም የቦነስ መብት ተጠቃሚ ለመሆን ለቦነስ ክፍያ ምክንያት ለሆነው ትርፍ ሰራተኛው አስተዋጽኦ ማድረግ አለማድረጉ ላታይ ይገባል። በእርግጥ የሰራተኛው ሥራ ትርፊማ መሆን አለመሆኑ የሚታወቀው የበጀት አመቱ ሂሳብ ከተሰራ በኋላ በመሆኑ የቦነስ መብት የሚፈቀደው ይኸው ውጤት ከታወቀ በኋላ ነው። የሂሳቡ ውጤት የአሰሪውን ትርፊማነት ካረጋገጠ ግን ለትርፊማነቱ አስተዋጽኦ ያደረገው ሰራተኛ የቦነስ ጥቅም ተካፊይ ላሆን ይገባል። በተያዘው ጉዲይ አመልካቹ በስራ ላይ በነበሩበት ጊዜ የተሰራው ሥራ ለመ/ቤቱ ትርፊማነት ምክንያት ሆኗል።
በመሆኑም ምንም እንኳን የቦነሰ መብት የተፈቀደው አመልካቹ ከሥራ ከለቀቁ በኋላ ቢሆንም የቦነስ መብቱ የተፈቀደው የአመልካች በስራ ላይ በነበሩበት ወቅት ለተሰራ ሥራ በመሆኑ አመልካች የጥቅሙ ተካፊይ የማይሆኑበት ምክንያት የለም። በመሆኑም ቦነስ በስራ ላይ ያለን ሰራተኛ ለማበረታታት ብቻ የሚሰጥ ነው በማለት የአመልካች የቦነስ ክፍያ ጥያቄ ውድቅ መደረጉ ሥህተት ሆኖ አግኝተነዋል።
ው ሣ ኔ
የፋ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 16632 በ29/6/97 የሰጠው ውሣኔ እና የፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 37603 በ25/09/97 የሰጠው ትዕዛዝ ተሽረዋል።
አመልካች በስራ ላይ ለነበሩበት ከሰኔ 24 ቀን 1995 እስከ ሰኔ 23/1996 ላለው ጊዜ ለላልች ሰራተኞች የተሰጠው ቦነስ እንዱከፈላቸው ተወስኗል።
ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ ይቻቻለ።
No topics extracted.