No summary available.
መጋቢት 18/99 ዓ.ም.
ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ አሰግድ ጋሻው መስፍን ዕቁበዮናስ ሑሩት መለሰ ተሻገር ገ/ሥላሴ አመልካች፡- የኢት/መንገድች ባለሥልጣን - ነ/ፈጅ አስመላሽ ገሰሰ ተጠሪ፡- ወ/ሮ አሚናት ገበየሁ - በላለችበት የሚታይ
አቤቱታው የቀረበው የደቡብ ወል መስተዲድር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በይ/መ/ቁ. 6ዐ83 ኀዲር 7/1997 በዋለው ችልት የኮምቦልቻ ወረዲ ፍ/ቤት በቁ. 633/96 ጥቅምት 22/97 ዓ.ም. የሰጠውን ውሣኔ በማጽናት በሰጠው ውሣኔ ላይ ነው።
የአሁን ተጠሪ ክሱን ያቀረቡት ሟች ሀሰን ዓሉ የተባለው ልጄ በተከሣሽ መ/ቤት ከ1978 ዓ.ም. ጀምሮ በወር ብር 285 እየተከፈለው በሰራተኛነት ሲያገለግል ቆይቶ በአደረበት ሕመም በ2ዐ/8/96 ከዚህ ዓለም በሞት በመለየቱ የሟች ወራሽ በመሆኔ የልጄን የ18 ዓመት የአገልግልት ካሣና ላልች ጥቅማ ጥቅሞች ይክፈለኝ የሚል ነው።
ክሱ የቀረበለት ፍ/ቤትም ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 39/2/3/ እና አንቀጽ 11ዐ/2/ሐ/፣ 3/ሐ/ መሰረት የሰራተኛው የዓመት ደመወዝ በአምስት ተባዝቶ ተከሣሽ ለከሳሽ ይክፈል ሲል ወስኗል። የዞን ከፍተኛው ፍ/ቤት ይህንኑ አጽንቶታል።
አቤቱታው የቀረበውም በዚህ ውሣኔ ላይ ሲሆን ጉዲዩ ለሰበር ይቀርባል የተባለበት ምክንያትም በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 39 መሰረት የአገልግልት ካሣ እንዱከፈል የተሰጠው ውሣኔ በአግባቡ መሆን አለመሆኑን ለማጣራት ነው።
ከሥር ክርክሩ መረዲት እንደሚቻለው ለሥራ ውለ መቋረጥ ምክንያት የሆነው የአመልካች ሰራተኛ የነበረው ሟች በአደረበት ሕመም ከዚህ ዓለም በሞት በመለየቱ ነው።
በአዋጅ ቁጥር 377/96 መሰረት ከአሰሪው የሥራ ስንብት ክፍያ የማግኘት መብት የሚኖረው በአዋጁ አንቀጽ 39/1/ ሥር ከ/ሀ/ እስከ/ረ/ በተዘረዘሩት ምክንያቶች ብቻ ነው።
በዚህ የሕግ ድንጋጌ መሰረት ሰራተኛው በሞት ምክንያት የሥራ ውለ ቢቋረጥ የሥራ ስንብት ክፍያ የሚጠየቅበት አይደለም። ሕጉ መብት አይሰጥም።
የሥር ፍ/ቤቱ ክፍያው ይፈፀም ያለው በአዋጁ አንቀጽ 39/1/ መሰረት በቅድሚያ የሥራ ስንብት ክፍያ የማግኘት መብት ስለመኖር አለመኖሩ ሳያረጋግጥ በአንቀጽ /2/ መሰረት የሥራ ስንብት ክፍያው በአንቀጽ 11ዐ/2/ ለተመለከቱት ጥገኞች ይከፈላቸዋል የሚለውን በማየት ብቻ ነው። የአዋጁ አንቀጽ 39/2/ ድንጋጌ ተፈፃሚ ላሆን የሚገባው ግን በአንቀጽ 39/1/ መሰረት የስንብት ክፍያ የማግኘት መብት መኖሩ የተረጋገጠ ሆኖ ሲገኝ ነው።
ስለዚህ የሥር ፍ/ቤቱ የሥራ ስንብት ክፍያው እንዱከፈል የወሰነው የአዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 39/1/ እና /2/ ድንጋጌን በአግባቡ ባለማገናዘብ ስለሆነ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ፈጽሟል።
ው ሣ ኔ
የኮምቦልቻ ወረዲ ፍ/ቤት በቁ. 633/96 ጥቅምት 22/97 ዓ.ም. የሰጠው ውሣኔ እና ይህንኑ በማጽናት የደቡብ ወል መስተዲድር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በይ/መ/ቁ. 6ዐ83 ኀዲር 7/97 ዓ.ም. የሰጠው ውሣኔ ተሽሯል።
የሥር ፍ/ቤት ውሣኔ የተሻረ መሆኑንም እንዱያውቁት የዚህ ውሣኔ ቅጂ ይተላለፍላቸው።
No topics extracted.