No summary available.
የካቲት 09 ቀን 2003 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሐጏስ ወልደ ዲኜ መላኩ ተሻገር ገ/ስላሴ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- የኢትዮጵያ ምርጥ ዘር ድርጅት - ነገረ ፈጅ አቶ ፈለቀ እንግዲሸት ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ኃ/ማርያም ሻረው - ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
በዚህ መዝገብ የቀረበው የሰበር ክርክር የአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይን የሚመለከት ነው።
የሰበር አቤቱታውም የአሁን ተጠሪ የሥራ ውለ ተቋርጦ እንዱሰናበት የተደረገው ከሕግ ውጭ ስለሆነ አሰሪው ድርጅት ወደ ሥራው እንዱመልሰው ይገባል፣ የሥራ ውለ ከሕግ ውጭ ከተቋረጠበት ጊዜ ጀምሮ ደመወዝና ልዩ ልዩ ጥቅሞች ሉከፈለት ይገባል በሚል የተሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው በማለት በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 80/3/ መሰረት የቀረበ ነው።
ክርክሩ የተጀመረው በገደብ አሳሳ ወረዲ ፍ/ቤት ሲሆን ከሣሹ ሰራተኛው የአሁኑ ተጠሪ ሆኖ ክሱ አሰሪው ድርጅት የሆነው የአሁኑ አመልካች ከሕግ ውጭ እኔን በወንጀል በመጠርጠር አግድኝ እንዲልሰራ ስላደረገ ወደ ሥራ እንዱመለስ ይወስንልኝ በሚል የቀረበ ነው። የአሁኑ አመልካች ሰራተኛው ከሥራው እንዱታገድ የተደረገው የመንግሥት ቼክ በሀሰት ፈርሞ ከባንክ ገንዘብ ስላወጣ ነው፣ ከሥራ የሚያሰናብተው ከፍተኛ የዱሲፔሉን ጥፊት ስለፈፀመ የተወሰደው እርምጃ ትክክል ነው የሚል ክርክር ቢያቀርብም የወረዲው ፍ/ቤት ሰራተኛው በተጠረጠረበት ወንጀል ጥፊተኛ ተብል በሕግ የተሰጠ ውሣኔ የለም፣ በመጠርጠሩ ብቻ ከሥራ ታግዶል የሚለው በሕጉ ተቀባይነት የለውም በማለት የአሁኑ አመልካች ሰራተኛውን ወደ ሥራው እንዱመልሰው፣ ደመወዝና ልዩ ልዩ ጥቅሞች ከተቋረጠበት ጊዜ ጀምሮ ሉከፍለው ይገባል በሚል ወስኗል።
የአሁኑ አመልካች በዚህ የወረዲው ፍ/ቤት ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኙን በየደረጃው ላለ የኦሮሚያ ፍ/ቤቶች ቢያቀርብም ተቀባይነት ሣያገኝ ቀርቷል።
የአሁኑ አመልካች በሥር ፍ/ቤቶች የተሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው የሚልባቸውን ምክንያቶች በ28/12/2002 በነገረ ፈጁ አማካኝነት በተጻፈ ማመልከቻ ዘርዝሮ አቅርቧል።
አቤቱታው ተመርምሮ ጉዲዩ ለሰበር ችልት ቀርቦ እንዱታይ በመባለ ማመልከቻው ለአሁኑ ተጠሪ ተልኮ ቀርቦ መልስ እንዱሰጥበት ተደርጓል።
በዚህም መሰረት ተጠሪው በ23/03/2003 የተጻፈ መልስ ሲያቅርብ የአመልካች ነገረ ፈጅም የመልስ መልስ ሰጥቶበት ተከራክሯል።
ጉዲዩም ተመርምሯል።
አሰሪው ድርጅት የአሁኑ አመልካች ሰራተኛው የአሁኑ ተጠሪ ከሥራ የተሰናበተው የድርጅቱን ቼክ በሀሰት በመፈረም ከባንክ ገንዘብ አውጥቶ በመውሰድ ከፍተኛ ጥፊት በመፈፀሙ ነው በማለት አጥብቆ የሚከራከር ሲሆን የአሁኑ ተጠሪ ደግሞ ከጥርጣሬ በቀር ወንጀለን ስለመፈፀሜ የሚያረጋግጥ ማስረጃ ስላልቀረበ የአመልካች ክርክር በሕግ ተቀባይነት የለውም ባይ ነው።
በመጀመሪያ ከሥራ ዕገዲ ሆኖ በመጨረሻ ከሥራ ስንብት ሆኗል የተባለው የአሁኑ አመልካች እርምጃ ከሕግ ውጭ ነው ወይንስ አይደለም? የሚለውን ዋናውን የክርክር ጭብጥ በተመለከተ ወረዲው ፍ/ቤት ሰራተኛው በወንጀል ተጠርጥሯል ከመባል በቀር በሕግ ጥፊተኛ ስለመሆኑ ተወስኖበት የቀረበ ማስረጃ የለም በማለት ማስረጃው የፍርድ ቤት የወንጀል ውሣኔ ብቻ እንደሆነ አድርጏ በመውሰድ አሰሪው ሰራተኛው ፈጽሟል ስለሚለው ጥፊት በማስረጃ አላስረዲም ወደሚል ድምዲሜ ያመራ ሆኖ ይገኝ እንጂ አሰሪው ድርጅት ሰራተኛው ፈጽሟል ስለሚለው ጥፊት በፍርድ ቤት የተሰጠ የወንጀል ውሣኔ በማስረጃነት ማቅረብ ሣያስፈልግ የሰው ወይም ላላ የጽሐፍ ማስረጃ በማቅረብ ማስረዲት ይችላል። በዱሲፔሉን ኮሚቴ ጉዲዩ ተጣርቶ ከሥራ የሚያስወጣው ጥፊት ፈጽሟል የተባለበት የዱሲፔሉን ውሣኔ መኖሩ ከታወቀ በጽሐፍ ማስረጃነት የማይቀርብበት ምክንያት የለም። በወንጀል ምርመራ የተጣራበት ማስረጃም ካለ በማስረጃነት ቀርቦ ላታይና ሉመዘን የሚችል ነው። የወረዲው ፍ/ቤት የአሁኑ አመልካች እነዚህን ሁለ ማስረጃዎች እንዱያቅርብ አድርጏ አጣርቶ መወሰን ሲገባው ሰራተኛው በወንጀል ተከሶ ጥፊተኛ የተባለበት የፍርድ ቤት ውሣኔ በማስረጃነት ካልቀረበ ከሥራ የሚያሰናብተው ጥፊት ስለመፈፀሙ ማስረዲት እንደማይችል አድርጏ የወሰነው ትክክል አይደለም።
ላልች ማስረጃዎች እንዱቀርቡ ተደርጏ ሣይጣራ የተሰጠው ውሣኔም መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ሆኖ ተገኝቷል።
ውሣኔ
የገደብ አሳሳ ወረዲ ፍ/ቤት በፊይል በ23/09/2002 የሰጠው ብይን፣ የምዕራብ አርሲ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 09309 በ30/10/2002 የሰጠው ትዕዛዝ እና የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችልት በመ/ቁ. 109450 በ13/12/2002 ዓ.ም. የሰጠው ትዕዛዝ፣ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽረው የገደብ አሳሳ ወረዲ ፍ/ቤት የአሁኑ አመልካች ሰራተኛው የአሁኑ ተጠሪ ፈጽሟል ስለሚለው ጥፊት በፍርድ ላይ በተዘረዘረው መሰረት አለኝ የሚላቸውን ላልች ማስረጃዎች እንዱያቀርብ አድርጏ በተገቢው መንገድ በማጣራት ከሥራ እገዲው ወይም ማሰናበቱ በሕጉ አግባብ ነው ወይንስ አይደለም በሚለው ላይ ውሣኔ እንዱሰጥበት በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 343/1/ መሰረት ጉዲዩ ተመልሷል።
የገደብ አሰሳ ወረዲ ፍ/ቤት በዚህ ውሣኔ መሰረት እንዱፈጽም ታዟል።
በዚህ መዝገበ በተደረገው ክርክር ምክንያት የደረሰውን ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሣቸውን ይቻለ።
በዚህ መዝገብ የተጠሰው ፍርድ ትክክለኛ ግልባጭ ለሥር ፍ/ቤቶች ይተላለፍ።
No topics extracted.